ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر603
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-87 روز
-1630 روز
آرشیو پست ها
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፱ (9) ቀን።
✝ እንኳን ለከበሩ አባት ጌታችን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ በቤታቸው ጣራ ለገባላቸው #ለአባ_አብርሃም_ግብፃዊ ዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ አባቶች #ከአባ_ጊዮርጊስ_ከአባ_ኖስሞስና ከሮሜ ሰው #ዲዮስቅርስ ዕረፍት፣ #ከአባ_ኪናፎርያ_ከበጥሪቃና_ከጥምያኒ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_አብርሃም፦ የዚህም ቅዱስ ሰው አባቱ ድኆችን የሚወዳቸውና የሚራራላቸው ነው። በዘመኑም በግብጽ አገር ታላቅ ረሀብ ሆነ እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከደግነቱና ከታማኝነቱ ብዛት የተነሣ እርሱ በአለበት አገር ዙሪያ ያሉ አገሮች ሁሉም የምድራቸው ፍሬ በእርሱ ዘንድ አደራ ያስቀምጡ ነበር ረሀቡም በጸና ጊዜ በእርሱ ዘንድ በአደራ የተቀመጠውን እህል ሁሉንም ለድኆች ሰጠ እግዚአብሔርም ስለ ምድራቸው ፍሬ ሁሉንም ክፉ ቃልን እንዳይናገሩት አደረጋቸው። በእርሱ ዘንድ ያኖሩትን የምድራቸውን ፍሬ ሽተው ወደርሱ በሚልኩ ጊዜ ተነሥቶ ወደርሳቸው ይሔዳል እነርሱም በየራሳቸው ለያንዳንዱ የምድራቸው ፍሬ እንደደረሳቸው አድርገው ይጽፉለታል እንጂ ምንም ምን አይናገሩትም።
✝ የዚህም ቅዱስ እናት እግዚአብሔርን የምትፈራ ምእመን ናት ሰይጣንም ቀናባት በአንድ ክፉ ሰው ልቡና አድሮ በፋርስ ሰዎች ዘንድ ነገር ሠራባት እነርሱም ማርከው ወደ አገራቸው ወሰድዋት በአንዲት ሌሊትም ራዕይን አየች ያ ነገር የሠራባት ሰው በሲኦል ውስጥ በእሳት ሰንሰለት ታሥሮ "እግዚአብሔር ያደረገልሽን ተመለከትሽን ነገር የሠራብሽን ያንን ሰው ተበቅሎታልና" ይላታል እርሷ ግን "ጌታዬ ሆይ መከራና ሥቃይ በርሱ ላይ እንዲደርስ አልሻም" ትላለች ያ የሚያሳያትም "አንቺ ግን ወደ አገርሽ ተመልሰሽ በቤትሽ ትኖሪ ዘንድ አለሽ" ይላታል እንዲሁም ሆነ።
✝ ባሏም በሞተ ጊዜ አብርሃም ድኃ አደግ ሆነ እርሷም እናቱ ሚስት ልታጋባው አሰበች እርሱ ግን ይህን አልወደደም እናቱም እጅግ ደስ ተሰኘችበት። ወደ ገዳም ሒዶ ሊመነኵስ በፈለገ ጊዜ እናቱ ልትሸኘው ወጣች እጆቿንም ወደ ሰማይ አንሥታ በመጸለይ ልጇን ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠበቀች። "አቤቱ ጌታዬ ይህን ቊርባንን አድርገህ ተቀበለኝ" አለች።
✝ በዚያንም ጊዜ አባ አብርሃም ሔደ በአስቄጥስ በረሀ ውስጥ ተጒዞ በአባ ዮሐንስ አበ ምኔትነት ዘመን ወደ አባ መቃርስ ገዳም ደረሰ ወደርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ገባ ተወዳጅ ልጅንም ሆነለት። በጎ ተጋድሎንም ጀመረ በአንዲት ሌሊትም ራዕይን አየ የበዓቱ ጣሪያ ተሰነጠቀ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ ወደርሱ ሲወርድ አየው ኪሩቤልም ያመሰግኑት ነበር እርሱም ፈርቶ ተንቀጠቀጠ ፈጥኖም ሰገደ ጌታችንም ባረከውና በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ። ጌታችንም የወረደባት በቤቱ ጣሪያ የተሠነጠቀችው ምልክት ሁና እስከ ዛሬ በመታሰቢያነት አለች እርሷም ለመንፈሳዊ አባቱ ለአበ ምኔቱ አባ ዮሐንስ መኖሪያ ቅርብ ናት እርሷም በግቢግ ትባላለች። የእግዚአብሔርም መልአክ ሁል ጊዜ ይጐበኘዋል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥለታል ያስገነዝበዋልም።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፰ (8) ቀን።
✝ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ሚክያስ ለመታሰቢያ በዓል፣ #የአባ_መቃርስ_ቤተ_ክርስቲያን በከበረና በተመሰገነ በእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት #በአባ_ብንያሚን እጅ ለከበረችበትና ለእስክድርያ ሠላሳ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ብንያሚን_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ ፦ከእስክንድርያ ሠላሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_እንድራኒቆስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ነቢዩ_ቅዱስ_ሚክያስ፦ የዚህም ነቢይ ከታናሽነቱ ጀምሮ አካሔዱ መልካም ሆነ ስለ ሥራው ማማርና ስለ ጽድቁ ሕዝቡ ሁሉ ያደንቁታል ያከበሩታል ሚክያስም ይሉታል ትርጓሜውም መልአክ ነው ማለት መልኩ እጅግ ያማረ ነውና የሚናገረውም ትንቢት እንደተናገረው ይሆናል የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጾለት ያነጋገረው ነበር ሕዝቡ ግን ያንን መልአክ እያዩትም ድምፁን ግን ይሰማሉ ከእርሳቸውም ያደላቸው የሚያዩት አሉ በመሳፍንት መጽሐፍ እንደተጻፈ። በጎልማሳነቱም አርፎ በአባቶቹ ቦታ ተቀበረ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና እኛን በነቢዩ ቅዱስ ሚክያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ይሁን አሜን።
✝ ✝ ✝
✝ #የአባ_መቃርስ_ቤተ_ክርስቲያን_በአባ_ብንያሚን_እጅ_መክበር፦ ከዚህም በኋላ መቆቅዝ ከሚባል ዐላዊ መለካዊ በአባ ብንያሚን ላይ መከራ ደረሰበት አባ ቢንያሚንም ሸሽቶ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ ዐሥር ዓመትም እስኪፈጸም በዚያ ኖረ ከዚህም በኋላ ያን ዓላዊ መቆቅዝን እግዚአብሔር አጠፋው ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ ጸጥታ ሰላም ሁኖ አባ ቢንያሚንም ወደ መንበረ ሢመቱ ተመለሰ የአስቆጥስ ገዳም ሽማግሎችና መምህራን ወደርሱ መጡ ወደርሳቸውም ሒዶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን እንዲአከብርላቸው ለመኑት እርሷም የከበረ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ናት። በታላቅ ደስታም ተነሥቶ ከእርሳቸው ጋር ሔደ የቤተ ክርስቲያኒቱንም መባረኪያ ጸሎት ጀመረ።
✝ መሠዊያውንም በሜሮን ሊቀባ በጀመረ ጊዜ የክብር ባለቤት የጌታችን እጅ ከእርሱ ጋር ስትቀባ አየ ከታላቅ ፍርሀት የተነሣ በግምባሩ ፍግም ብሎ ወደቀ። ከኪሩቤልም አንዱ አነሣው እንዲህም አለው "ተነሣ አትፍራ ልዩ የሆነውን ሥርዓት ለዚህ ቦታ ጻፍ ይህ የእግዚአብሔር ምሥጢር የሚፈጸምበት ነውና ማንም በትዕቢት ወይም መማለጃ በመስጠት እንዳይገባ በውስጡ በሚገባ ከሚሾም በቀር የሚደፍርና በውስጡ ከንቱ ነገርን የሚናገር አይኑር የእግዚአብሔር መመስገኛ ቤቱ ነውና ይህም ሥርዓት በዚህ ቦታ እስከ ዘላለሙ የተሠራ ይሆናል። እነሆ ዘመን ይመጣል የአባቶችንም ትእዛዝና ሥርዓት ያፈርሳሉ ይህም የከበረ ቦታ እንደ መሣለቂያ ቦታ ይሆናል"።
✝ አባ ብንያሚንም "ይህች የእግዚአብሔር ቤት የሰማይ ደጅ ናት" አለ ይህንንም ከኪሩብ ጋር ሲነናገር ከቤተ ክርስቲያኒቱ በስተምሥራቅ ተመለከተ አንድ መልኩ የሚያምር ጽሕሙ የረዘመ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት የሚያበራ ሽማግሌ አየ። ለአባ ብንያሚንም ደስ አሰኘውና በልቡ እንዲህ አለ "ከኤጲሰሰቆጶሳት አንዱ ቢሞት በርሱ ፈንታ ይህን ሽማግሌ እሾመዋለሁ"። ኪሩብም እንዲህ አለው "ብንያሚን ሆይ ይህን አባት መቃርዮስን ኤጲስቆጵስን ታደርገዋለህ?"። እርሱ "የሊቃነ ጳጳሳት አባታቸው ነውና ዛሬ ከልጆቹ ጋር ደስ ይለው ዘንድ መጥቷልና ከልጆቹም መንፈሳዊ ሹመት የሚሾም ወይም አለቃ የሚሆን አይታጣም ከገዳማቱም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ አይታጣም"።
✝ አባ ብንያሚንም "ልጆቹ ብፁዓን ናቸው" አለ ኪሩብም እንዲህ አለ "ብፁዓንስ የሚባሉ ትእዛዞቹን ጠብቀው ፍለጋውን ቢከተሉ እነርሱ ከእርሱ ጋር አሁን በአለበት ክብር ውስጥ ይሆናሉ ትእዛዞቹን ቢተላለፋ ግን ከእርሱ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖራቸውም"። አባ ብንያሚንም ኪሩብን እንዲህ አለው "ጌታዬ ሆይ በዚህ ነገር በልጆቼ ላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አትናገር ነገር ግን በሰብል ውስጥ አንዲት ቅንጣት የተረፈች እንደሆነ እግዚአብሔር በውስጥዋ በረከቱን ያደርጋል። እንዲሁም የፍቅር ቅንጣት በውስጣቸው የተገኘ እንደሆነ እግዚአብሔር ከመንግሥቱ እንደማያርቃቸው እኔ አምናለሁ"።
✝ ከአረጋዊው አባ መቃርስ ርኅራኄ የተነሣ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን አደነቀ መልአኩ ኪሩብ እንዳዘዘውም ያንን ሥርዓት ጽፎ ለዘወትር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረው። ዕድሜው በደረሰ ጊዜ ዕረፍቱ በዚች ቀን ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው እንዲሁም ሆነለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቢንያሚን በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_እንድራኒቆስ፡- ይኽም አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሰባተኛ የሆነ ነው። ይህ አባት የሚራራ አዋቂ ሆነ እርሱ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ተምሮአልና እርሱም ለእስክንድር ገዥ የአጎቱ ልጅ ነውና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሊቃነጳጳሳት እንደሚያደርጉት በገዳም አልኖረም፤ ይልቁንም ስለቤቱና ስለክብሩ ታላቅነት በእስክንድርያ ባለው ቤቱ የሚኖር ሆነ፡፡ እርሱም የተሾመው ሕርቃል በነገሠ በ10 ዓመት ከእስክንድር ዘመነ መንግሥት በ933 ዓመት ነው፡፡ በሹመቱም ወራት ፀሐይን የሚያመልክ የፋርስ ንጉሥ ክስራ ተነሣና የሶርያንና የፍልስጤምን ከተሞች ወርሮ ዘረፋቸው፡፡ ወደ ግብጽም መጥቶ እስክንድድርያ ከተማ ደረሰ፡፡ በዙሪዋ በመነኮሳት የተሞሉ ሰባት መቶ ገዳማት ነበሩ፡፡ እነርሱም ገንዘብ ያላቸው በተድላ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ ስለዚህም በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ሥልጣንን ሰጥቶት ገዳማቱን አፈረሰ፡፡ እነርሱንም ሸሽተው ካመለጡት በቀር ሁሉንም ገደላቸው፡፡ ገንዘባቸውንም ሁሉ ማረከ፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፯ (7) ቀን።
✝ እንኳን #ለአጋዕዝተ_ዓለም_ለቅድስት_ሥላሴ የሰናዖር (የባቢሎንን) ቋንቋቸው ለደባለቁበትና የሠሩት ግንብ ላፈረሱበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዘፍ11፥1-9)፣ ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀት ላጠመቀው ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳስ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ሶል_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት #ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ ለመታሰቢያው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰሎሞን፣ #ከጎርጎርዮስ_ከማርቆስ_ከአትያኖስ_ከሉያ፣ #ከመልይን_ከሱስዮስና_ከማርትይ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #የሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳስ_አባ_ሶል_ጴጥሮስ፦ ይህንንም አባት ስለ ተጋድሎው ገናናነት ስለ አገልግሎቱም ስለ ትሩፋቱ ስለ አዋቂነቱና ስለ ደግነቱ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ መልጥያኖስ ከዐረፈ በኋላ መርጠው ሊቀ ጵጵስና በሮሜ አገር ላይ ሾሙት። በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የዕሊኒ ልጅ የሆነ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ከከሀድያን ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ምክንያት ገና አልተጠመቀም ነበርና የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ሠራላቸው።
✝ የዚህም አባት ሶል ጴጥሮስ ገድሉ እጅግ ብሩህ የሆነ ነው እርሱ ሁል ጊዜ ሕዝቡን ያስተምራቸዋልና ከልቡናቸውም ከሰይጣን የሆነ ጥርጥርንና ክፉ ሐሳብን ያርቃል። ከእነርሳቸው ሥውር የሆነውንም የመጻሕፍት ምሥጢር ተርጒሞ ያስገነዘባቸው። አይሁድንና ዮናናውያንን ሁል ጊዜ ይከራከራቸው ነበር ከእርሳቸውም ብዙዎችን መልሶ ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ስሙም በምእመናን ዘንድ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሆነ። እግዚአብሔርን ስለ ማወቅና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ብዙ ድርሳናትን ደረሰ።
✝ በተሾመ በሰባተኛውም ዓመት ስለ አርዮስ በኒቅያ ከተማ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የከበሩ አባቶች የአንድነት ስብሰባ ሆነ ይህም አባት ሶል ጴጥሮስ ከእርሳቸው አንዱ ነበር አርዮስንም ከተከታዮቹ ጋር ረገመው አውግዞም ለየው። በሹመቱም ዐሥራ አንድ ዓመት ኖረ መልካም ተጋድሎን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥር7 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሶል ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር7 ስንክሳር።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፮ (6) ቀን።
✝ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለንዑስ_በዓል ለአንዱ #ለግዝረት_ለኢየሱስ ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ በዚች ቀን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #በሥጋው_ወደ_ቤተ_ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ ልሳነ ዕረፍት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ" ብሎ እንደተናገረ። ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር ጌታችን ግን ግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን።
✝ የከበረ ወንጌል "ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት" እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን "እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ" አለችው። ዮሴፍም ሔዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው "እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቆ ያዙት" አላቸው። ሕፃን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልሶ እንዲህ አለው "ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆች መድኃኒት ይሆናል"።
✝ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችን ማርያም "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው" አላት።
✝ ሕፃኑም ለዚያ ባለሙያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው "እኔ ነኝ ትገዝረኛለህ ወይስ ተውክ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ" ያም ባለሙያ "የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?" አለው ሕፃን ጌታችንም "አብርሃም፣ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው" ባለሙያውም "እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና" አለው። በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ "አባት ሆይ ለአብርሃም፣ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ" አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ብቸኛ በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።
ጥር 4/ 2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፭ (5) ቀን።
✝ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ልደታቸው አስመልክቶ (ሳሪስ አቦ፣ፈረሳይ አቦ) የለውጥ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #ስለ_አባታች_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ልደት፦ ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡ አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡
✝ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከ ጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ" አሏት። ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ። ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"። እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፬ (4) ቀን።
✝ እንኳን #ለከበረና_ለተመሰገነ ለታላቁ #ለወንጌላዊው_ለአቡቀለምሲስ_ለቦኤኔርጌስ፣ #ለታኦሎጎስ_ለድንግላዊው_ለቊጹረ_ገጽ፣ #ለፍቊረ_እግዚእ_ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_ለፍልሰቱ (ከሞት ለተሰወረበት) ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦# ከከበረ_ከጊዮርጊስ ከሊቀ ጳጳሳት #ከማርቴና_ከሰማዕት_ታኦድራ_ከአባ_ሊቃኖስና #ቀውስጦስ_ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ፦ ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ አገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀስ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ። ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፪ (2) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጽያዊ_ጻድቅ በዓለም ላይ በንግሥና መኖርን ንቀው ለመነኑትና ብዙ ተአምራትን በማድረግ ለሚታወቁት #ለንጉሥ_ዐፄ_ይኩኖ_አምላክ ልጅ ለሆኑት #ለአቡነ_ገብረ_ክርስቶስ_ዘዳግና ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለሊቀ ሰማዕታት #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ_ለልደት በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #ፀሐይና_የአጥቢያ_ኮከብ የተባለ ታላቁና ክቡር የሆነ ሰማዕቱ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ መስፍን ነው ስሙም አንስጣስዮስ ይባላል ከቀጰዶቅያ አገር ነው የእናቱም ስም ቴዎብስታ ይባላል ከፍስጥዓዔም አገር ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ ዐረፈ። ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሔደ። ንጉሡም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው። ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #የተባረከ_የጥር_ወር_የመዓልቱ_ሰዓት_ዐሥር ነው ከእንግዲህ ይጨመርለታል።
✝ #ጥር ፩ (1) ቀን።
✝ እንኳን #ለሊቀ_ዲያቆናት_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለልደቱና_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ከሶርያ_አገር_ለሆነ በከሀዲው መክስምኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነት ለተበቀበለ #ለቅዱስ_ለውንድዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስልሳ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_መቃርስ ዕረፍት፣ #ከከበሩ_ከአክሚም_ሰማዕታት የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ከፈጸሙ ስማቸው #ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ ዕረፍት፣ በዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ቊጥራቸው #ከካህናት_ስምትት_መቶ፣ #ከዲያቆናት_መቶ_ሠላሳ_ከመምህራን_ኃምሳ፣ #ከሦስት_ከቤተ_ክርስቲያን_ሹማምንት_ከሰማንያ_መሳፍንት_ከሠላሳ_ሁለት_ንፍቅ_ዲያቆናትና_ከመቶ_ኃምሳ_ሕዝባውያን ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ታኅሣሥ ፴ (30) ቀን።
✝ እንኳን #ለታላቁ_አባት ለተመሰገኑ አባት አርባ ዓመት ሙሉ የሴቶች ፊት ሳያይ ለኖረ #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ለሆነ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመኰንኑ ከአርያኖስ የጥፍሮቹ ታላላቆች #ለቅዱሳን_ለኮርዮንና_ፊልሞና ከእናርሳቸው ጋር ካሉ #ከአርባ_ወታደሮች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋድይ ለሆነ #ለአባ_ዘካርያስ ዕረፍትና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ኄሮድስ ከገደላቸው #ከከበሩና_ከነጹ_ሕፃናት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህም ተጋዳይ የምንኵስና ልብስን ከለበሰ ጀምሮ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው ዜናውም በአገሩ ሁሉ ተሰማ። ይህም አባ ዮሐንስ ሁል ጊዜ የሚጐበኘው አንድ መኰንን ነበረ የመኰንኑም ሚስት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ እንዲወስዳት ባሏን ታምለውና ታስገድደው ነበር እርሱም "የከበረ አባ ዮሐንስ ከአርባ ዓመት ጀምሮ የሴቶችን ፊት አላየም" አላት። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሒዶ ሚስቱ ያለችውን ለአባ ዮሐንስ ነገረው አባ ዮሐንስም "በእግዚአብሔር ፈቃድ የፈለገችውን እፈጽምለሠታለሁ" አለው።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ታኅሣሥ ፳፱ (29) ቀን።
✝ እንኳን #ለተባረከና_ለተመሰገነ በሰማያት ያለ ምሥጢርን ለአየ፤ #ዐሥር_አስደናቂ_ቤተ_መቅደስን ከዐለት ደንጋይ ላይ ላነፀ፤ ክብሩ ልክ እንደ ሐዋርያት ለሆነ #ለኢትዮጵያዊው_ለጻድቁ_ለካህኑ_ንጉሥ_ለቅዱስ_ላሊበላ_ለልደት በዓል፣ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ለልደት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ልደታቸው ከጌታችን ጋር አንድ ከሆኑ ከቅዱሳን፦ #ከቅዱስ_ነአኲቶ_ለአብ_ፍቅርተ_ክርስቶስ ቅዱሳን ነገሥታት #አብርሐ_ወአጽብሓ፣ አቡነ አካለ ክርስቶስ፣ አቡነ መዝራእተ ክርስቶስ፣ መስፍኑ ኢያሱ፣ የገርአልታው አቡነ ዳንኤል፣ አቡነ አብሳዲ፣ አቡነ ፄዋ ለጽድቅ፣ ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
መልአኩም እንዲህ አላቸው እንሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለኹና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።ሉቃስ2፡10-11)እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ ፡፡
ርዕስ የግርግም ባለቤት ወግ
አቅራቢ እየሩሳሌም ታምራት
ከኪነ ጥበብ ክፍል
የ2016 ዓ.ም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደትን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቀዳሚ በሆነው እና በ1905 ዓ.ም በንጉሥ ኢያሱ ዘመን በተሰራው በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ።
++++++++++++++++++++++++++++++++++
በበዓሉ ላይ ከዋዜማ ጀምሮ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሥፍራው በመገኘት ቀድስው ሕዝበ ክርስቲያኑን በማቁረብ አባታዊ ቡራኬን ሰጥተዋል።
የጠቅላይ ቤተ ክህነት እና የሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች።
የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ዘማርያን እና ዘማርያት ከአራቱም አቅጣጫ በዓሉን ለማክበር በሥፍራው የተገኙ ምእመናን እና ምእመናት በተገኙበት በዓሉ በድምቀት ተከብራሯል።
በዕለቱ በካቴድራሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማ ቀርቧል። በማስከተልም በካቴድራሉ እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት አባላት በአባቶችሽ እግር ልጆች ተኩልሽ አንደተባለው በካቴድራሉ የሰንበት ቤት አባላት ያሬዳዊ መዝሙር ቀርቧል
በማስከተልም በካቴድራሉ መስማት የተሳናቸው አባላት ያሬዳዊ ዜማ ቀርቧል።
በበዓሉ ላይ በካቴድራሉ አስተዳዳሪ በሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ኪሮስ ፀጋዬ የዕለቱ ቃለ ወንጌል ተሰጥቷል።
በመጨረሻም በአባቶች ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ተሰጥቶ ታቦታቱ ሕዝቡን እየባረኩ በክብር ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።
መምህርት ኑኀሚን ዋቅጅራ
ከደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ !
ታኅሣሥ 28 ቀን 2016 ዓ.ም
💫የጌታችን ልደት በትንቢተ ነቢያት ፦
ከዓበይት ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፡፡
"እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ( ኢሳ.7፥14፣ ሕዝ.44፥1) ፡፡ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወልደው አማኑኤል ጌታ ነው፡፡ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ነቢዩ በጎላና በተረዳ ነገር “ሕፃን ተወልዶልናል ወልድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“ በማለት የሚወለደው ሕፃን የባሕርይ አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ እንደሆነ እና ለሥልጣኑም ወሰን ድንበር እንደሌለው ተናግሯል፡፡
💫ከደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ ሚልክያስም በቤተልሔም ስለመወለዱ፡-
"የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና" (ሚክ.5፥2፣ ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡
💫• ነቢየ እግዚብሔር ቅዱስ ዳዊትም "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ዛፍ በበዛበትም ቦታ አገኘነው እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ማደሪዎች እንገባለን ብሎ የወመለዱን ምሥጢር ተናግሯል" (መዝ.131፥6)
💫• ነቢዩ ዕንባቆምም "አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ" ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት (ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡
ከዚህ በኋላ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ድንግል ማርያም በመላክ አብሥሯታል፡፡ “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል" በማለት፡፡ ሉቃ. 1፡32
እመቤታችንም በብዙ ኅብረ አምሳል ትንቢት ሲነገርለት፤ ምሳሌ ሲመሰልለት፤ ሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቤተልሔም ግርግም ወለደችው፡፡
ይህንንም ብስራት በቤተልሔም ዋሻ መንጋቸውን ነቅተውና ተግተው ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መጋቤ ሐዲስ አብሣሬ ትስብዕት ቅዱስ ገብርኤል ፤ እነሆ ዛሬ መድኀኒት በዳዊት ከተማ ተወልዶላችኋል ይኸውም ቡሩክ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል ከዓለም በፊት ንጉሥ የነበረ ዛሬም ከዳዊት ባሕርይ /ዘር/ በቤተልሔም ዋሻ ዓለምን ለማዳን የተወለደ የዳዊት ልጅ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ሲል አበሰራቸው፡፡ (መዝ.73፥12)
💥 የጌታችንን ልደት ስናነሣ ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምናለን፡፡ እኒሁም ልደታት /ልደት ቀደማዊና/ /ልደት ደኃራዊ/ ናቸው፡፡
💫 ልደት ቀዳማዊ ፦ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት የተወለደው ልደት ሲሆን /ነቢዩ ዳዊት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ "ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽ ባህ መዝ.109፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ወለድኩህ ፤አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ" (መዝ.2፥7)
💫ልደት ደኃራዊ ፦ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈፀም በዕለት ሐሙስ ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ እንዲል ቃሉ፡፡ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን እንበለ ዘርዓ ብዕሲ ያለ አባት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም የተወለደው ልደት ነው፡፡
ቀዳማዊ ልደቱ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው የማይመረመር ስለሆነ ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለፅ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ እንደ ተወለደ ድኅረ ዓለምም ከእመቤታችን /እንበለ ዘርዓ ብዕሲ/ ያለ አባት ተወለደ፡፡ እሱም እመቤታችን ያለ አባት የወለደችው ፤ እግዚአብሔርም ያለ እናት የወለደው ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰባቱ መስተጻርራን /ተቃራኒ ነገሮች አንድ ሆነዋል ሕዝብና አሕዛብ ፤ በጠብና በክርክር ይፈላለጉ የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ በጌታችን ልደት ታርቀዋል።
✨መልካም በዓል✨
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊
✨ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ✨
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት ፤ በነቢያት ሲነገር ፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማዕከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
ታኅሣሥ ፳፰ እና ፳፱ (28 እና 29) ቀን።
✝ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለአምላካችን_ለጌታችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም_በሥጋ_ለተወለደበት የበዓላት ሁሉ ራስ ለሆነች #ለብርሃነ_ልደቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በእነዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእንዴናው_አገር_ሰዎች ከሆኑ በሰማዕትነት ካዐረፉ #ከመቶ_ሃምሳ_ወንዶችና_ከሃያ_አራት_ሴቶች፣ #ከአባቶቻች_ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ፣ #ከኤፍሬም_ወገን ከመስፋኑ #ከቅዱስ_ኢያሱ_ልደት፣ ከከበሩ #ከያዕቆብ_ከፈሊስ ከሌላው ሰማዕት፣ #ከቴዎድሮስ ከመታሰቢያቸው፣ #ከሮሀ_ንጉሥ_ከአቃርዮስ ዕረፍት፣ ሰምኑድ ከሚባል አገር ከሆነ ከገመላዊው #ከቅዱስ_ቆሪል ዕረፍትና #ከአክሚም_ሰማዕታት_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ ታላቅ #የልደት_በዓል_ሆነ_የጌታችንና_የመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን_ከከበረች_ድንግል_ማርያም_የተወለደባት_ዕለት_ከበዓላት ሁሉ ተለይታ ከፍ ከፍ ያለች ናት።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊✨
💫እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11 💫
🕊 እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ 🕊
✨ " ጌና" ✨
ጌና እና ልደት {ዋዜማና ክብረ በዓል }
/የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን ፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡
#ጌና ፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና ፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል ፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል ፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡
ይቀጥላል.............
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊እንኳን_አደረሳችሁ 🕊✨🕊✨✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊
« በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ እንገናኝ » (ነህ .6 ፥ 10 )
አሕዛብ ሁሉ የእርሱን መምጣት ተስፋ የሚያደርጉት ሕያው ቃል ወደዚህ ዓለም መጥቶ ያለ ዘርዐ ብእሲ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ የእግዚአብሔር መልአክም መንጋቸውን በትጋት ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች ተገልጦ ‹‹ እነሆ ለእናንተና ለሕዝብ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ። ›› በማለት ደስታ ርቆት ለነበረው ዓለም ሰውን ሁሉ ደስ የሚያሰኝ የምሥራች ተናገረ ። ( ሉቃ 2 ፥ 10 )
የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ምድረ ኤፍራታ ቤተ ልሔም ለተወለደው ንጉሥ መካነ ልደት በመሆኗ የምድራውያንና የሰማያውያን መገናኛ ፣ የእርቅ መጀመሪያ የጌትነቱ እጅ መንሻ ማቅረቢያ ሆነች ። ( ሚክ 5 ፥ 2 )
#መልካም_በዓል
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ታኅሣሥ ፳፯ (27) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አስቀድሞ ሽፍታ ለነበሩና በኋላም በንስሓ ተመልሰው #ለሰባት_ዓመት_ምንም_ውሃ_ሳይቀምስ እስከመኖሩ ድረስ በታላቅ ተጋድሎ ለኖሩ #ለአቡነ_በግዑ_ዘሐይቅ ለዕረፍት ዓመታዊ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_በግዑ_ዘሐይቅ፦ በመጀመሪያ ሽፍታ የነበረ ሲሆን በመንገድ ላይ ንብረት የያዘን ሰው ማንንም የማያሳልፍ ቀማኛ ሰው ነበር፡፡ ከኃይለኛነቱ የተነሳ ሕዝቡም ሁሉ ይፈራው ነበር፡፡ በእጁ ሰይፍና ጦር ይዞ ሊዘርፍ ወደ ወደደው አገር ይገባል፡፡ እየዘረፈ በሚያገኘው ገንዘብም ራሱን በተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ያስደስት ነበር፡፡ ባማሩ ልብሶችም ይዋብ ነበር፡፡ ገንዘቡ የተወሰደበት ሰውም እርሱ እንደወሰደበት ባወቀ ጊዜ ዳግመኛ መጥቶ የተረፈውን ቀምቶ እንዳይወስድበት ምንም አይከሰውም ነበር፡፡ በጉልምስናው ኃይለኛና ብርቱ ስለነበር ወደ እርሱ ማንም አይቀርብ ነበር፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
