Falcon Grade 6 2019E.C(2026/2027GC)
Открыть в Telegram
267
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
+330 дней
Архив постов
ጤና ይስጥልን ወላጆች
👉 የመጀመሪያው የሙከራ ፈተና ( 1st Test ) ከማክሰኞ ጥቅምት 10 /2019ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 13/2019ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን Communication Book መልዕክት የላክን መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም ተማሪዎች ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆችም አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
👉 ቴስቱ የሚሰጠው ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እየተማሩ ይሆናል። ፈተና ከተጠናቀቀ ከ 4:45 በኋላ መደበኛው ትምህርት የማጠናከሪያ የጥናት ትምህርትን ጨምሮ የሚቀጥል ይሆናል።
👉 ለቅድመ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ የቴስቱን ፕሮግራም ከዚህ በታች አቅርበናል
በዛሬው እለት መስከረም 28/2019ዓ.ም ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ት/ቤት አጠቃላይ ወርሃዊ ስብሰባ ከ9:30 - 11:30 ድረስ አካሂደናል። በስብሰባችን በሚከተሉት አጀንዳ ላይ ተወያይተናል
👉 በመስከረም ወር በጥናካሬ የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም ውስንነት የተስተዋለባቸው በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች
👉 በእቅዳችን መሰረት በጥቅምት ወር ትኩረት ሰጥተን በምናከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ ተወያይተናል
👉 ዋና እና ረዳት መምህራን ተቀናጅተው ተማሪዎችን በእውቀት እና በስነ ምግባር የማነፅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል ግንዛቤ ፈጥረናል
👉 ሰኞ ጥቅምት 2/ 2019ዓ.ም በሚጀምረው የማጠናከሪያ ጥናት ትምህርት ጥራቱን በጠበቀ እና ተማሪዎችን ውጤታማ በሚያደርግ መንገድ እንዲሰጥ ተወያይተናል።
👉 በአጠቃላይ የትምህርት ቤቱ አመራሮችና መምህራን በጣም ጥሩ በሆነ እና በጠንካራ ተነሳሽነት ቀጣይ ስራዎችን ለማከናወን ከስምምነት ላይ በመድረስ ስብሰባው በተሳካ ሁኔታ 11: 30 ላይ ተጠናቋል።
ቴዎድሮስ ነጋ
ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ት/ቤት
ርዕሰ መምህር
ለወላጆች በሙሉ
በቅድሚያ ለክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ነገ ሰኞ 18/1/2019ዓ.ም ትምህርት ሙሉ ቀን የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም ተማሪዎች የተሟላ የት/ት ቤት ዩኒፎርም ለብሰውና የትምህርት መሳሪያቸውን አሟልተው እንዲገኙ በጥብቅ እናሳስባለን::
ት/ት ቤቱ
