ru
Feedback
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Открыть в Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Больше
9 019
Подписчики
-724 часа
-497 дней
-7230 день
Архив постов
«ﺃﺣﺒﺐ ﻣﻦ ﺷﺌﺖ ﻓﺈﻧﻚ ﻣﻔﺎﺭﻗﻪ» 👉መለያየት በእርግጥ የሕይወት አንድ አካል ነው። የሆነ ቀን ወደድንም ጠላን እንለያያለን። በእርግጥ አሁን ጊዜው አልደረሰም ይሆናል። t.me/https_Ass
«ﺃﺣﺒﺐ ﻣﻦ ﺷﺌﺖ ﻓﺈﻧﻚ ﻣﻔﺎﺭﻗﻪ» 👉መለያየት በእርግጥ የሕይወት አንድ አካል ነው። የሆነ ቀን ወደድንም ጠላን እንለያያለን። በእርግጥ አሁን ጊዜው አልደረሰም ይሆናል። t.me/https_Asselfya

በትዳር ውስጥ ፍቅርን የሚያጠፉ ነገሮች እውነት ነው፤ በትዳር ውስጥ ፍቅርን ሊያቀዘቅዙ አልፎ ተርፎም ሊገድሉ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን እነሆ፦ 1. መግባባት ማጣት •  በቂ አለመነጋገር: ስሜትን፣ ሐሳብን፣ ችግሮችን በግልጽ አለመነጋገር የትዳርን መሰረት ያናጋል። •  አለመስማማት: የሌላውን ሐሳብ ለማዳመጥ ፈቃደኛ አለመሆንና ሁልጊዜ የራስን ሐሳብ ብቻ ማራመድ። •  የቃላት አጠቃቀም: ስድብ፣ መሳደብ፣ ማዋረድና በንቀት መናገር ፍቅርን ያቀዘቅዛል። 2. መተሳሰብና መከባበር ማጣት •  ግዴለሽነት: ለትዳር አጋር ስሜት፣ ፍላጎትና ለችግሮቹ ደንታ ቢስ መሆን። •  አለመተሳሰብ: በትዳር አጋር ላይ ጫና መፍጠር፣ በኃላፊነት አለመተባበርና እሱን/እሷን አለማገዝ። • አክብሮት ማጣት: በሰዎች ፊት ማዋረድ፣ ማንቋሸሽና በትንሹም በትልቁም አለማክበር። 3. ክህደት •  መዋሸት: በትንንሽም ይሁን በትልልቅ ነገሮች መዋሸት የትዳርን እምነት ያሳጣል። •  ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት መፍጠር: አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ክህደት በትዳር ውስጥ ያለውን ፍቅር ይገድላል። •  እውነቱን አለመናገር: አንድ ነገር ተደብቆ ሲቆይና እውነቱ ሲጋለጥ የትዳርን ፍቅር ያቀዘቅዛል። 4. የዕለት ተዕለት ኑሮ ጫና •  ገንዘብ ነክ ችግሮች: የገንዘብ እጥረትና የገንዘብ አጠቃቀምን በተመለከተ አለመግባባት። •  የቤት ውስጥ ሥራ ጫና: የቤት ውስጥ ሥራን በእኩል አለመካፈልና አንዱ ላይ ብቻ መጫን። •  የልጆች ኃላፊነት: ልጆችን በማሳደግ ረገድ ያለመግባባትና ጫና መፍጠር። 5. የፍቅር መገለጫ ማጣት •  ስሜትን አለመግለጽ: "እወድሻለሁ/እወድሃለሁ" አለማለት፣ ማቀፍ፣ መሳም፣ ስጦታ አለመስጠት። •  አብሮ ጊዜ አለማሳለፍ: አብሮ አለመጫወት፣ ወሬ አለማውራትና የፍቅር ጊዜን አለማሳለፍ። •  የፍቅር ቃላትን አለመጠቀም: አፍቃሪና አነቃቂ ቃላትን አለመናገር። 6. ለራስ ትኩረት አለመስጠት •  የአካል ጤናን አለመጠበቅ: ራስን መንከባከብን ማቆም፣ ጤናማ አለመሆን። • ስሜታዊ ጤናን አለመንከባከብ: ጭንቀትንና ቁጣን መቆጣጠር አለመቻል፣ ስሜትን መደበቅ። • የግል ጊዜን አለመውሰድ: ለራስ ጊዜ አለመስጠትና በግል ጉዳዮች ላይ አለማተኮር። እነዚህና የመሳሰሉት ነገሮች በትዳር ውስጥ ያለውን ፍቅር ሊያቀዘቅዙ አልፎ ተርፎም ሊገድሉ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግና ችግሮች ሲፈጠሩ በውይይት መፍታት የፍቅርን ግንኙነት ለማጠናከር ይረዳል። ይቀጥላል... ✍ወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

🔖اللَّهُمَّ إنّا نسألُكَ علمًا نافعًا ورزقًا طيبًا وعملًا مُتقبَّلًا #صباح_الخير
🔖اللَّهُمَّ إنّا نسألُكَ علمًا نافعًا ورزقًا طيبًا وعملًا مُتقبَّلًا #صباح_الخير

- القارئ مًعاذ بن حامد.

~አላዋቂ ጃሂል ከሆንክ ብትኖርም ተረስተሃል ። ~አዋቂና የዒልም ባለቤት ከሆንክ  ብትሞትም ብትጠፍም አንተ የተገኘህ ህያው ነህ! 📕 تائية الإلبيري

➤አንዳንድ ሴቶች....⁉️ ባንድ ምላስ መንታ ወሬ ---------------------- አንድ ሰሞን ማሬ ውዴ አይነት ጨዋታ  ከሆነ አዳም ጋር ፎንቃ ቢጤ ጀምራ ሂወቴ  መኖሬ ያለሱ ባዶ ነው...ንገሩት ናፍቆኛል ምናምን በሚሉ ፖስቶች ፌስቡኩን፣ ቴሌግራሙን፣ ቲክቶኩን፣ ኢሞውን የሚዲያውን  መንደር እንዳለ... የሮማንስ ቀበሌ ካላደረኩ በሚል ቀውጢ ስትል ቆይታ ወር እንኳ ሳይሞላው በውል በማይታወቅ ተልካሻ ምክንያት ጥርግ በል፣ አንተ ብትሄድ ሌላ ይመጣል፣ ቀረሁብህ እንጂ  አልቀረህብኝም,,,  ንገሩት አስጠልቶኛል" ምናምን እያለች ፕሮፋይል በመቀያየር በቻይንኛ ድጋሜ በሚዲያ መንደር ከወንድ ነፃ ነኝ አይነት ማስታወቂያ የምታሸሙር ባንድ ምላስ መንታ ወሬ የምትቀምር ሴት ሳይ ሆዴን ያዞረኛል። እግሬን ያጥወለውለኛል። እህቴ ተረጋጊ በቃ ይህ አይነት ሙድ ከተበላበት ቆዬ ተነቅቶበታል ይልቅ ቆም ብለሽ አስቢና ለባልሽ ሚስት ሁኝ ሚስትነትን አምነሽ ኑሪበት ገና ስታገቢ ቢፈታኝ በሚዲያ ስሙን አጠፋዋለሁ በሚል የበቀል ስሜት ገብተሽ የራስሽን ህይወት አትመርዥ ፀፀቱ ለራስሽ ነው። አሏህ ካዘነላቸው ውጭ የዚህች አይነት ሴቶች ናቸው በንፁህ ወንድ ህይወት ውስጥ ገብተው ህይወቱን ያመሰቃቅሉና በደለኝ ፣ጨቆነኝ እያሉ በውሸት ሌሎች እህቶች  ትዳር እንድጠሉ የሚያደርጉት የዚህን ፀባይ ባለቤት የሆኑ ሴቶችን ተጠንቀቋቸው። ....ኑረዲን t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

በረካ ባልትና እቤት ውስጥ የተዘጋጁ ከባቲ የመጡ የባልትና ውጤቶች በርበሬ ሹሮ በሶ ሚጥሚጣ ሳዑድ ከተሞች ለምትኖሩ እንዲሁም ሐገር ከፈለጋችሁ ከኛ ዘንድ ያገኛሉ ! ለማዘዝ ሳዑድ፦ @Abuoumer12
በረካ ባልትና  እቤት ውስጥ የተዘጋጁ ከባቲ የመጡ የባልትና ውጤቶች በርበሬ ሹሮ በሶ ሚጥሚጣ ሳዑድ ከተሞች ለምትኖሩ እንዲሁም ሐገር ከፈለጋችሁ ከኛ ዘንድ ያገኛሉ ! ለማዘዝ  ሳዑድ፦  @Abuoumer12345 ለማዘዝ ኢትዮ ፦ @Umu_Umer_Bint_Ebrahim ወደ ግሩፕ  ለመቀላለቀል 👇👇 https://t.me/Bereka_Baltna https://t.me/Bereka_Baltna

የመጀመሪያው ፕሮግራም 🎙 በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ حفظه الله ተ ጀ መ ረ "ገባ ገባ በሉ https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy?livestream

አንዳንዴ…የትም ይሁን የት ብቻ ህመም ምናምን ወደሌለበት እርቆ መሄድን እንመኛለን! ~

• የመጀመሪያው ምክር ራስን መምከርና ማስተካከል ነው። ራሱን በአግባቡ ያልመከረ  ሌሎችን መምከር አይችልም። ቢመክርም ውጤታማ አይሆንም። راغب اصفهانى

ወንድሜ የልጆችህን እናት ስትመርጥ በሞቅታና በጊዜያዊ ስሜት አይሁን።በጥበብና በስሌት ምረጥ።ለአይንህ ደስታ ብለህ የዘላለም ስህተት አትስራ።ለአንድ ቀን ኑሮህን የማይኖሩልህ ሰዎች አግባ ስላሉህ ብቻ ተደናብረህ በማይሆን ነገር አትግባ። منقل t.me/Darutewhide/2061

ወንድሜ የልጆችህን እናት ስትመርጥ በሞቅታና በጊዜያዊ ስሜት አይሁን።በጥበብና በስሌት ምረጥ።ለአይንህ ደስታ ብለህ የዘላለም ስህተት አትስራ።ለአንድ ቀን ኑሮህን የማይኖሩልህ ሰዎች አግባ ስላሉህ ብቻ ተደናብረህ በማይሆን ነገር አትግባ። منقل

👉ዋጅብ ሶላቶች በጓደሉ ግዜ የሚሟሉት በሱና ሰላት ነዉ የሱና ሠላቶችን በችልተኝነት ልናየዉ አይገባም። አንድ የአላህ ባሪያ ወደ አላህ ሱብሀነሁ ተአላ ሊቃረብ አይችልም አላህ በሱ ላይ ግድ ዋጂብ ባደረገበት ነገር እንጅ ስለዚህ በሱና ነገሮች ወደ አላህ ይበልጥ የሚቃረብ ይሆናል።በዚህ ግዜ ከአላህ ወልዮች ዉስጥ ይሆናል።#በዚህ ግዜ አላህ የሱን ዱአ ይሠመዋል የፈለገዉን ነገር ይሠጠዋል ።ሱናን ባበዛ ግዜ ማለት ነዉ።ስለዚህ ~ የሱና ሰላት...... ~የሱና ጺያም ...ኢባዳዎችን በችልተኝነት ልንመለከታቸዉ አይገባም። ረዋቲብ የሆኑት 12 ረከዓዎች 👉እነዚህኞቹ በጣም የጠነከሩትና በየቀኑ እንዳንተዋቸው የታዘዝናቸው ሱና ሰላቶች ናቸው 🔹እነሱም፦ ~ ከዙህር በፊት 4 ረከዓ ~ ከዙህር በሗላ 2 ረከዓ ~ከመግሪብ በሗላ 2 ረከዓ ~ከኢሻ በሗላ 2 ረከዓ ~ ከሱብሒ በፊት 2 ረከዓ , ለዚህም መረጃው፦ ~ኢማም ትርሚዚ በዘገቡት ሀዲስ ላይ የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም  "እነዚህ አስራ ሁለት ረከአዎች በየቀኑ የሰገደ ሰው አላህ ጀነት ውስጥ ቤትን ይገነባለታል" ብለዋል። = t.me/https_Asselfya

ተናፋቂው ወር የአንድ ወር እድሜ ብቻ ቀርቶታል:: በሰላም በአፍያ ያድርሰን:: የምንጠቀምበትም ያድርገን:: ቀዷ ያለባችሁ ቀዷችሁን ማውጣትን አስታውሱ:: በተረፈ እንደ ረመዷን ተወዳጅ ተናፋቂ ጠቃሚ ያድርገን ••• አሚንንን አቦ!

🔖እናታችን አኢሻ (رضي الله عنها) እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል። «እናንተ ሰዎች ሆይ! (ከመልካም) ስራ የምትችሉትን ያክል ብቻ ያዙ። እናንተ እስካልተሰላቻችሁ አላህ አይሰለችም። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ ትንሽ እንኳ ብትሆን ዘውታሪነት ያለውን ነው።» [ 📖 صحيح البخاري (٥٨٦١) ] t.me/https_Asselfya

- 🔘 التفصيل في مسألة تأخير قضاء رمضان إلى رمضان التالي... 🎙فضيلة الشيخ أ.د/ سليمان الرحيلي-وفقه الله تعالى. •••🌴

اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ አስቸኳች የእርዳታ ጥሪ እህታችን ሀያት በላይ ትባላለች የትውልድ ሀገሯ ወለጋ ሰዬ ነው ተወልዳ ያደገችው አሁን ላይ
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎       አስቸኳች የእርዳታ ጥሪ እህታችን ሀያት በላይ ትባላለች የትውልድ ሀገሯ ወለጋ  ሰዬ ነው ተወልዳ ያደገችው አሁን ላይ ያለችው በደብረ ብርሀን መጠለያ ነው እህታችን ያለችበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው ባደረባት የልብ ህመም የልብ ጥበት ስላጋጠማት ሀኪሞች  በቅርብ የጠጎ ጥገና  ካልተደረግሽ ህይወትሽ ያሰጋሻል አሏት እህታችን ከአላህ በታች ስበቡን በማድረስ ህይወቴን ታደጉኝ እያለች በአላህ ስም ትማፀናለች
እህታችንን ለማገዝ የተዘጋጀ የዳዕዋ እና የንያ ፕሮግረም
    ተጋባዥ እንግዶቻችን 🎙ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ  حفظه الله 🎙ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ حفظه الله 🎙ኡስታዝ አቡ ፈውዛን حفظه الله        🎙ወንድም አቡ ኡሰይሚን حفظه الله          🎙ወንድም አቡ ሂበቲላህ حفظه الله          🎙ወንድም አቡ ፋሩቅ حفظه الله ፕሮግራም መሪ ወንድም አቡ አይመን እና ወንድ አቡ ማሂ በቻልነው አቅም ከአላህ በታች ስበብ በመሆን የእህታችንን ህይወት እንታደጋት ሊኩን ሸር በማድረግ የቻልን በገዘብ ያልቻልን በዱዓ ፕሮግራሙ ሀሙስ ከምሽቱ በኢትዩ 3:00 ይጠብቁን ፕሮግራሙ የሚካሀድበት ሊንክ ➴➴➴➴ https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy