የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Открыть в Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Больше2 617
Подписчики
+724 часа
+207 дней
+3530 день
Архив постов
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የሕጻናትና የማዕከላውያን ጉዞ ነሐሴ 25 /2017ዓ.ም እንደሚከናወን ይታወቃል ለዚህም ጉዞ የተመደበው ክፍያ 150 እስከ እሑድ ነሐሴ 11 ድረስ ብቻ ለከፈለ ሲሆን ከሰኞ ነሐሴ 12 ቀን ጀምሮ የሚከፍሉ 250 የሚደረግ ስለሆነ ያልከፈላችሁ አስቀድማችሁ ክፍያውን እንድትከፍሉ ይሁን።
የጉዞ ኮሚቴ
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
''ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው'' ሐዋ.20፥35
የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት በጎ አድራጎት ክፍል በየዓመቱ በምዕመናን እገዛ ለተቸገሩ ሕጻናት የትምህርት መሣሪያ ድጋፍ ያደርጋል። እርስዎም የቻሉትን የአቅምዎትን በመለገስ እንዲሳተፉ በትህትና እንጠይቃለን። ዝርዝራቸውም
- 1 ደርዘን ደብተር--------800
- 1 ደርዘን እስክርቢቶ -----300
- 1 ደርዘን እርሳስ ---------150
- 1 ቦርሳ -------------------900
- 1 ኮምፓስ ----------------120
ጠቅላላ ፓኬጅ ---------2270 ብር
በተናጠል መለገስ ይቻላል።
100065853292 ተስፋዬ፣ሙሉጌታ እና ሸዋንግዛው
ለበለጠ መረጃ:- 09 13 00 60 86
- 09 12 41 97 72
- 09 31 14 44 44
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
''ነገረ ክርስቶስ ''
ክፍል ሁለት
በዲ/ን ሞገስ አብርሃም
የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር
የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ጽንሰታ_ለማርያም
ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው።
ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ።
የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች።
በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት።
ንዒ ኅቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ
ድንግል ሆይ ከተወዳጅ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ እኔ ነይ ትባርኪን ዘንድ
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷ ከኛ አይለየን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን።
''ነገረ ክርስቶስ ''
ክፍል አንድ
በዲ/ን ሞገስ አብርሃም
የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር
የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
