ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

Открыть в Telegram

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

Больше
2 794
Подписчики
+124 часа
+87 дней
+2030 дней
Архив постов
በዕለተ እሑዱ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም በወርሐዊው የቅዱስ ሚካኤል በዓል በርካታ ምዕመናን በተገኙበት አዲስ ለተመደቡት የደብራችን አስተዳዳሪ በሰበካ ጉባኤ አባላት፣ በአስተዳደር ጽ/ቤት፣ በማኅበረ ካ
+9
በዕለተ እሑዱ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም በወርሐዊው የቅዱስ ሚካኤል በዓል በርካታ ምዕመናን በተገኙበት አዲስ ለተመደቡት የደብራችን አስተዳዳሪ በሰበካ ጉባኤ አባላት፣ በአስተዳደር ጽ/ቤት፣ በማኅበረ ካሕናት እና በሰንበት ት/ቤት አባላት በተገኙበት የእንኳን ደህና መጡ መርሐግብር ተከናወነ።

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለገዳማት እና አድባራት የሰንበት ት/ቤቶች ለተመረጡ ለአዲስ የሥራ አመራር አባላት ስልጠና መስጠት ጀመረ። በ11/11/2018ዓ.ም በአዲሱ ተቋማዊ አደረጃጀት መሠረት አዲስ ለተመረጡ የሥራ አመራር አባላት ስልጠና መስጠት ጀመረ። ለስልጠናው ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ የነበረ ሲሆን በአሥራ አራት የሥልጠና ማእከላት በአራት የስልጠና አይነቶች ስልጠናው መሰጠት መጀመሩ ታውቋል። 1-በኦርቶዶክሳዊ አመራር ፣ 2- በስልታዊ አስተሳሰብ እና ስልታዊ እቅድ 3-የአዲሱ መዋቅር ትግበራ 4-በተግባቦት እና ግጭት አፈታት ሥነ ዘዴ ላይ በአራት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠናው መሰጠት ጀምሯል። ስልጠና ሲሰጥበት የነበሩ ማዕከላት በሳእሊተ ምህረት፣ በገርጂ ቅድስት ማርያም፣ በቦሌ መድኃኔዓለም፣ በጎሮ ቅዱስ ገብርኤል፣ በሰሚት ቅድስት ኪዳነ ምህረት፣በገመናዬማርያም፣ በታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም፣ በወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ፣በመካኒሳ አቦ፣ በሳሪስ አቦ፣ በቃሊቲ ገብርኤል፣ በልደታ ማርያም፣ በደብረ አሚን ተክለ ሀይማኖት እንዲሁም በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መሥካየ ህዙናን የሥልጠና ማዕከል በቀጨኔ መዳኃኔዓለም አስተባባሪነት ሲሆን በነገው እለት የቃሊቲ ገብርኤል ሰልጣኞች የስልጠና ማዕከላቸው ወደ ጃቲ ኪዳነ ምህረት እንደሚሆን የታወቀ ሲሆን በ14የስልጠና ማእከላት ከ220በላይ ሰንበት ት/ቤት አመራሮች ስልጠና ሲሰጥ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል። ስልጠናው ውጤታማ እና አሰልጣኞች ከፍተኛ ለአገልግሎት ስንቅ የሚሆን እና በተግባር የሚተረጎም እውቀት ማግኘታቸውን ከሰልጣኞች ከተሰበሰበ አስተያየት ለመረዳት ተችሏል። ለሥልጠናው መሳካት በአሰልጣኝነት በአስተባባሪነት የተሳተፋ አባላት፣ የክፍለከተማ አንድነት አመራሮች ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው ሲሆን በ አዳራሽ ከማዘጋጀት ጀምሮ የእረፍት ሻይቡና በማዘጋጀት አመራሮችን በኦርቶዶክሳዊ እንግዳ ተቀባይነት ያስተናገዱ ከላይ የተጠቀሱ ገዳማት እና አድባራት ሰንበት ት/ቤቶች ለስኬታማነቱ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እና ለሌሎች አርአያ ሆኖ የሚጠቀስ እና ምስጋና የሚገባው መልካም ተግባር በመሆኑ ልንገልጽ እንወዳለን። በስተመጨረሻ ስለጠናው ነገም የሚቀጥል ሲሆን በቀጣይ ሁለት ቅዳሜዎች እሰከ ሐምሌ25/2018ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል ። የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዛሬው ውጤታማ እንዲሆን ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ እያመሠገነ በቀጣይ ቀናት የሚደረጉ ስልጠናዎች ከዛሬው ልምድ ተወስዶ እና ከድክመቶች ትምህርት ተወስዶ ጠንካራ ጎኑን አሳግደን እና አስቀጥለን በከፍተኛ መተባበር ወጤታማነቱ እንደጅማሬው እንዲቀጥል የበኩላችንን እንወጣ ሲል መንፈሳዊ ጥሪውን ያቀርባል። ሰልጣኞች በቀጣይ በሰዓት በምልአት በመገኘት የተዘጋጀላችሁን ስልጠና በንቃት በመሳተፍ በቀጣይ በተባበረ እና በተናበበ አመራር አገልግሎታችን ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን የተዘጋጀልንን የስልጠና ማዕድ በመሳተፍ የበኩላችንን እንድንወጣ ጥሪውን ያስተላልፋል። የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

"እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።" ሐዋ 1፥14
"እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።" ሐዋ 1፥14

"ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥"
+6
"ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥" የይሁዳ መልእክት 1፥21 ዛሬ ዕለተ አርብ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ ም  በመምህር ቢትወደድ ወርቁ የዕቅበተ እምነት ክፍል-1 ትምህርት ተሰጠ። በትምህርቱ ላይ ሃይማኖትን ማድናት  ከእያንዳንዱ ክርስቲያን የሚጠበቅ መንፈሳዊ ተግባር  እንደሆነ ተብራርቷል::  ይህንንም ለመፈጸም በእምነትና በእውቀት በየእለቱ ማደግ እንደሚገባ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስተምረዋል። ለመምህራችን ቢትወደድ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እንላለን። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" መጽ. ምሳ 1፥33 ለወጣቶች በክረምት ወቅት ከተዘጋጀው የሕይወት ትምህርቶች መካከል የጋብቻ ሕይወት ክፍል-1 ትምህርት በቀሲስ ዮሴፍ ይ
+1
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" መጽ. ምሳ 1፥33 ለወጣቶች በክረምት ወቅት ከተዘጋጀው የሕይወት ትምህርቶች መካከል የጋብቻ ሕይወት ክፍል-1 ትምህርት በቀሲስ ዮሴፍ ይኩኖአምላክ በትላንትናው ዕለት የተሰጠ ሲሆን፤ ነገ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም የሚቀጥለው የእቅበተ እምነት ትምህርት በመምህር ቢትወደድ ወርቁ የሚሰጥ ይሆናል። ወጣቶች የእረፍት ጊዜያችሁን እውነተኛ እረፍት የሚሰጠውን ቃለ እግዚአብሔርን በመማር እንድታሳልፉ ሰንበት ት/ቤታችን ጥሪ ታስተላልፋለች። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

በዛሬው ዕለት ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤታችን ትምህርት ክፍል ለክረምት ወራት ያዘጋጀውን ኮርስ በሁሉም የእድሜ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የጀመረ ሲሆን፤ ትምህርቱ በቀጣይ ረቡዕ የሚቀጥል እ
+6
በዛሬው ዕለት ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤታችን ትምህርት ክፍል ለክረምት ወራት ያዘጋጀውን ኮርስ በሁሉም የእድሜ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የጀመረ ሲሆን፤ ትምህርቱ በቀጣይ ረቡዕ የሚቀጥል እንደሆነ በአስተባባሪዎች ተገልጿል። በትምህርቱ መሳተፍ የሚችሉ ሕጻናት፣ ማዕከላውያን እና ወጣቶች በትምህርቱ ላይ በመሳተፍ የእረፍት ጊዜያቸውን በቤተክርስቲያን ቃለ እግዚአብሔር በመማር እንዲያሳልፉ የተገኙ ተማሪዎች ሌሎች መማር የሚችሉ ወገኖቻቸውን ይዘው እንዲመጡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

"ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።" መዝ 41፥1 የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በጎ አድራጎት ክፍል፤ በጎዳና
"ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።" መዝ 41፥1 የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በጎ አድራጎት ክፍል፤ በጎዳና ላይ ለሚገኙ ነዳያን ወገኖቻችን የክረምቱን ዝናብ የሚከላከሉበት የዝናብ መከላከያ ልብስ ለማልበስ የእርሶን ድጋፍ ይጠይቃል። አንድ ችግረኛን በማልበስ ከችግረኞች አምላክ በረከት እንቀበል። "ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤" ማቴ 6፥20

እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ። ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነትን አክሊል የተቀበሉበትን ዓመታዊ በዓል ሐምሌ ፭ ቅድስት
+2
እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ። ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነትን አክሊል የተቀበሉበትን ዓመታዊ በዓል ሐምሌ ፭ ቅድስት ቤተክርስቲያን በታላቅ ክብር ታከብረዋለች። "ውስተ ኩሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ ወውስተ ጸሐይ ሤመ ጽላሎቶ" መዝ ፲፰፥፬ ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ዕለታዊ የሰንበት ት/ቤታችን መረጃ! በዛሬው ዕለት ለሦስት ቀናት ከተያዘው የጸሎት መርሐግብር የሦስተኛው ቀን የጸሎት መርሐግብር የደብራችን አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ብርሃናት አእምሮ ምስጋናው በተገኙበት ተከናውኗል። በዕለቱም ላለፉት አራት ዓመታት ሰንበት ት/ቤታችንን በአመራርነት ያገለገሉ ወንድሞችና እሕቶችን የምስጋና የማስታወሻ ስጦታ በክቡር አባታችን የተሰጠ ሲሆን፤ አዲስ ለተመረጡ አመራሮችና አስፈጻሚዎች አባታዊ ምክርና መመሪያ ሰጥተው በጉባኤው ፊት ቀርበው ጸሎተ ማርያም አድርሰውላቸዋል። ካሳለፋችሁት ጉዞ ይልቅ ወደ ፊት የሚጠብቃችሁ አገልግሎት ሰፊ በመሆኑ ራሳችሁን አዘጋጁ ብለው ማሳሰቢያ ሰጥተው ጉባኤውን በጸሎት አሳርገውልናል። እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር