ru
Feedback
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

Открыть в Telegram

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

Больше
2 621
Подписчики
+124 часа
+227 дней
+3830 день
Архив постов
እንኳን ለዐቢይ ጾመ ጾመ ኢየሱስ አራተኛው ሰንበት ደብረ ዘይት(ለእኩለ ጾም) አደረሰን አደረሳችሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንደቀጠለ ነው አሁን ደግሞ በቀን ሁለት ምዕራፍ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት የሮ
+1
እንኳን ለዐቢይ ጾመ ጾመ ኢየሱስ አራተኛው ሰንበት ደብረ ዘይት(ለእኩለ ጾም) አደረሰን አደረሳችሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንደቀጠለ ነው አሁን ደግሞ በቀን ሁለት ምዕራፍ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት የሮሜ  መልእክትን መጀመራችን ይታወቃል አሁንም በቀን ሁለት ምዕራፍ ከ2ኛ ቆሮንጦስ ምዕራፍ 11እስከ ኤፊሶን መልእክት ምዕራፍ 5 ድረሰ ንባባችንን እንቀጥል     መልካም የንባብ ጊዜ ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

እጸ መስቀል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ሊያወጣ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ በቀራንዮ አደባባይ በመካነ ጎልጎታ በፈቃዱ ተሰቀለ። ሞተ ጥልንም በመስቀሉ ገደለ። ከፍተኛ ወንጀል የሠሩ ሰዎች ብቻ ይሰቀሉበት የነበረው መስቀል ከጌታችን ስቅለት በኋላ የድኅነት ምልክት ሆነ:: ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ተአምር በማድረጉ የተመቀኙ  አይሁድ መስቀሉን ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሩት መስቀሉ የተቀበረበትን ስፍራ የቆሻሻ መጣያ አደረጉት። ንግሥት እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳነፅ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ልጇ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ337 ዓ.ም ተጠመቀ፡፡ ንግስት እሌኒም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች የጌታችንን መስቀል መፈለግ ብትጀምርም ያለበት ስፍራ የሚነግራት ሰው ልታገኝ አልቻለችም፡፡ አይሁድ የተቀበረበትን ቦታ ለማሳየት ፍላጎት ባይኖራቸውም  አንድ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊ ሰው አስጨንቃ ስለያዘችው መስቀሉ የሚገኝበትን ስፍራ ጠቆማት ነገር ግን ለዘመናት ቆሻሻ ሲጣልበት የነበረ ስፍራ በመሆኑ ተራራ ሰርቷል በቦታው ከነበሩት ከሦስቱ ተራሮች ውስጥ መስቀሉ የሚገኝበት የትኛው እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ንግሥት እሌኒ ከሦስቱ ተራሮች የቱ እንደሆነ ለመለየት በእግዚአብሔር ረዳትነት ደመራ አስደምራ ብዙ እጣንም በመጨመርና በማቃጠል ጸሎት ተያዘ፡፡ የእጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ በመውጣት በቀጥታ ተመልሶ መስቀሉ ወዳለበት ተራራ ላይ በማረፍ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ስፍራ አመለከታት፡፡ መስከረም አስራ ስድስት ቀን ቁፋሮው ተጀምሮ መጋቢት አስር ቀን ሦስት መስቀሎች  ተገኙ፡፡ ነገር ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል  የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ተቸገሩ፡: መስቀሎቹን ወስደው ሙት ላይ ቢያስቀምጡ ጌታችን  በዕለተ አርብ የተሰቀለበት መስቀል የሞተውን ሰው አስነሳው ሌሎቹ ሁለቱ መስቀሎች ግን ሙትን ማስነሳት  ባለመቻላቸው የጌታችንን መስቀል ለይቶ ማወቅ ተችሏል።  ንግስት እሌኒና ክርስቲያኖች ሁሉ ለመስቀሉ ሰገዱለት የመስቀሉ በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

''ሥርዓተ ቅዳሴ'' ክፍል ሁለት በዲ/ን አማኑኤል አሽኔ የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያ
''ሥርዓተ ቅዳሴ''                 ክፍል ሁለት    በዲ/ን አማኑኤል አሽኔ የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር  የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም ከምሽቱ  11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ። የቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

የሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋይ የሆነው ወንድማችን ወጣት ዮሴፍ አምሐ የእግዚአብሔር ፍቅር ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት መጽሐፍ መጋቢት 07 ቀን 2017 ዓ.ም በደብራችን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ
+9
የሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋይ የሆነው ወንድማችን ወጣት ዮሴፍ አምሐ የእግዚአብሔር ፍቅር ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት መጽሐፍ መጋቢት 07 ቀን 2017 ዓ.ም  በደብራችን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተመረቀ።  እንኳን ደስ አለህ ወንድማችን ወጣት ዮሴፍ አምሐ እግዚአብሔር ያበርታህ ። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

የዐቢይ ፆም አራተኛ ሳምንት ስያሜ ምን ይባላል?
Anonymous voting

የሐዘን መግለጫ የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ተክሉ ማሞ ወላጅ እናት አርፈዋል ሥርዓተ ፍትሐት ዛሬ መጋቢት 05/2017 ዓ.ም ጠዋት 3:00 በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ተደርጎ ከሰዓት ከቅዳሴ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ፊጋ አካባቢ ይመለሳሉ ዛሬውኑ ምሽቱን የእናታችን አስከሬን ወደ መቀሌ ሽኝት የሚደረግ በመሆኑ መገኘት የምትችሉ አባላት  በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የእናታችንን ነፍስ  ይማርልን ። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com