የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Открыть в Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Больше2 781
Подписчики
+124 часа
+77 дней
+1330 дней
Архив постов
ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም። እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።ማቴ ፬፥፳፩-፳፪በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
ቅድስት አርሴማ ድንግልመስከረም 29 በዚችም ቀን ቅድስት አርሴማና እመምኔቷ አጋታ ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ። ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ። እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ። ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው። ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት። የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው። ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ። አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ። ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። የቅዱሳን ሰማዕታት ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር!!
በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ዮሐ ፩፥፩በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
"ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፥ እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው፤ ለሚፈሩትም ምግብን ሰጣቸው።"መዝ.110፥4-5በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
🌹🌹🌹 ዘመነ ጽጌ 🌹🌹🌹
🌹ጽጌ መዓዛ ሠናይ!ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለውን ወቅት «ወርኃ ጽጌ» ትለዋለች። ዘመነ ክረምት በመስከረም ፳፭ ተጠናቆ፣ አሁን የአበባው ወራት ተጀምሯል። አምላክ ይክበር ይመስገን! ይህ ወቅት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደት የሚታሰብበት ቅዱስ ጊዜ ነው። ስደት አድካሚ ጉዞ፣ ረኀብና ጥም የያዘ ነው። ጠቢቡ እንዳለው፦
«እነሆ ክረምት ዐለፈ፤ ዝናቡም አልፎ ሔደ፤ አበቦችም በምድር ላይ ተገለጡ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ» (መኃ. ፪፡፲፩-፲፪)።«ክረምት ዐለፈ» ማለት የአዳም የመከራ ዘመን ማለፉን ያሳያል። ቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይላል፦
«እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፤ እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ...»ዮሴፍም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብጽ ሸሸ። ይህም «ልጄን ከግብጽ ጠራሁት» (ሆሴዕ ፲፩፡፩) የተባለው እንዲፈጸም ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ፣ ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትላ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በግብጽ አውራጃዎች ተሰደደች። በዚያም ወቅት ወደ አስራት ሀገሯ ኢትዮጵያም መጥታ በረከትን አምጥታለች። ጌታችን የተሰደደው ግብጽንና ኢትዮጵያን ለመባረክ ነው። በዚህ ምክንያት በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ወርኃ ጽጌ ልዩ ቦታ አለው። ከጅማሬው እስከ ፍጻሜው በማኅሌት፣ በዝክርና በቅዳሴ የእመቤታችን ስደት ይታሰባል። የጽጌ ጾም የፈቃድ ጾም ቢሆንም፣ የእመቤታችንን ስደት እያሰብን መጾም ትሩፋት ያሰጣል። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን እመቤታችንን «አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ» ብላ ታመሰግናታለች። የእመቤታችን ፍቅር በልባችን፣ ምስጋናዋ በአንደበታችን እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብን! ከበረከቱ ያሳትፈን፣ የእመቤታችን ረድኤትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን! 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ጽንሰቱመስከረም ሃያ ስድስት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ወደ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ልኮት መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ስለ መወለዱ አበሠረው። ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና። ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው። ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጀ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች ብሎ የእግዚአብሔርን መልአክ ተከራከረው። መልአኩም እኔ ይህን ልነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል ብሎ ገሠጸው። ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ። በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን አባት ዘካርያስን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። የቅዱሳኑ ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር!!
+1
📢የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
📜የሥራ ዘርፍ ዝርዝሮች:-
1. 💻የጽሕፈትና ጠቅላላ አገልግሎት ባለሙያ
2. 📚የቤተመጻሕፍት ባለሙያ
ዝርዝሩን በመመልከት በሰንበት ት/ብቱ ጽ/ቤት ወይንም ከላይ በተጠቀሱት የቴልግራም አድራሻዎች በአስቸኳይ እንድታመለክቱ እናሳስባለን።
‹‹እነሆ ክረምት ዐለፈ፤ ዝናቡም ዐልፎ ሔደ፡፡ አበባ በምድር ላይ ታየ፤ የመከርም ጊዜ ደረሰ፡፡ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ፤ ወይኖችም አበቡ፤ መዓዛቸውንም ሰጡ …›› /መኃ.፪፥፲፩-፲፫/በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
አቤቱ ኀይልኽን እዘዝ፤አቤቱ ይህንም ለእኛ የሠራኸውን አጽናው። በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስኽ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ። --መዝ ፷፰፥፳፰-፳፱በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
"ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እንሆ መልካም ነው እንሆም ያማረ ነው።" መዝ.132÷1
ውድ የባለትዳር አባላት እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የጉባዔያችን ቀን ደረሶ ነገ በ24/01/19 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ጀምሮ ወርሃዊ ልዩ ጉባዔያችን ላይ ልንገናኝ ነው በመሆኑም የጉባዔያችንን ሰዓት አክብረን እንድንገናኝ በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም በድጋሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን በሰላም ያገናኘን።
ብርሃን ለጻድቃን፥ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ። ፤ጻድቃን፥በእግዚአብሔር ደስ ይበላችኹ፥ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ። --መዝ ፺፮፥፲፩-፲፪በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። --ማር ፲፫፥፱-፲፫በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የሐዘን መግለጫ
የሰንበት ት/ቤታችን ሥራ አመራር ሰብሳቢ የሆነው የመ/ር ኢ/ር ዳዊት አበበ ወላጅ እናት እንዲሁም የእህታችን ሊዲያ አሰፋ አያት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ መስከረም 22/2019 ዓ.ም በለቡ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ከቀኑ 5:30-6:00 ሰዓት የሚፈጸም በመሆኑ በቀብሩ ላይ መገኘት የምትችሉ ተገኝተን እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው 43 ቀበሌ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። የእናታችንን ነፍስ ይማርልን ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
"...ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል ፡፡ ይእቲኬ ቤተ ምስኣል ፡፡ ዘአስተዐፀቡ ታቀልል ፡፡ ለኵሉ ፍጥረት ትተነብል ፡፡ በአክናፈ መላዕክት ትትኬለል ፡፡ ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ፡፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል ፡፡ መንክር ወመድምም ዕበያ ወክብራ ለድንግል ፡፡ ጽሕፍት ውስተ ወንጌል ፡፡ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትዕምርተ መስቀል ” ቅዱስ ያሬድ ትርጉሙ “…የደናግል መመኪያ የኾነች እመቤታችን ድንግል ማርያም የተጨነቁበትን ነገር ኹሉ ታቀላለች ፡፡ ለኹሉ ፍጥረት ትማየምተመሰገን። በመላእክት አክናፍ ተከባ የምትኖር የምተመሰገን። አምላካችንን የምንለምንባት የጸሎታችን ማሰረጊያ ናት ፡፡ እርሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች ፡፡ ከሱራፌልም ትልቃለች ፡፡ በወንጌል ውስጥ የተገለጸች በራሷ ላይም በትዕምርተ መስቀል የብርሃን ዘውድ የደፋች የድንግል ክብሯ ፈጽሞ እጅግ ድንቅ ነው ፡፡…” ቅዱስ ያሬድከእመቤታችን፣ ከቅዱስ መስቀሉ፣ ሃይማኖትን ካቀኑ አርዮስን ካወገዙ ከሠለስቱ ምዕት፣ በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን ሁሉ በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
መስከረም 21
#ብዙኃን_ማርያም
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡
በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡
ጉባዔ_ኒቅያ
በ325ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ከሚያዝያ 21 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ 2348 (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ (2348) መካከል (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ 318 ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት 318ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
318ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
2. ዕፀ መስቀል
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
"ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁን ተመልከቱ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኛዎች የሆኑ ብዙዎች ኀያላን የሆኑ ብዙዎች ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።" 1ኛ ቆሮ. 1÷26
