ru
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Открыть в Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Канал ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 19 896 подписчиков, занимая 1 159 место в категории Медицина и 1 695 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 19 896 подписчиков.

Согласно последним данным от 02 июля, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -535, а за последние 24 часа — -9, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 14.35%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 7.01% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 2 856 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 394 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 4.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 03 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Медицина.

19 896
Подписчики
-924 часа
-987 дней
-53530 день
Архив постов
"የሴት ልጅ ወላጆች ስለወር አበባ ለልጆቻቸው ምን ማስተማር አለባቸው!!? ………ሴት ሆና ለተፈጠረች ሁለ ዕድሜዋ ሲደርስ የወር አበባ ማየት የተፈጥሮ እውነታ ነው። ሴት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባዋ ከች ሲል በሕይወቷ ከሚገጥሟት ዐቢይ ክስተቶች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ይሄን ቀንና ክስተት አንዳንድ ልጃገረዶች በደስታ እና በእርካታ ስሜት ሲቀበሉት፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ሃፍረትና ድንጋጤን በቀላቀለ ስሜት ውስጥ ሆነው ይቀበሉታል። የሆነው ሆኖ ግን ይህቺ ዕለት ታዳጊዋ ሚሚ ሴት መሆኗን የሚያበስርላት የሴትነት ቀኗ ነውና የወር አበባ ሲከሰት ከድንጋጤው ስሜት ይልቅ የደስታ ስሜቱ ምክንያታዊ ነው ማለት ይቻላል። ………ሴት ልጅ የወር-አበባ የምትጀምርበት አማካኝ ዕድሜ ከ12-13 አመት ሊሆን ቢችልም፤ ከዚህ ወቅት ቀድመው ወይንም አልፈው የወር-አበባን የሚጀምሩ ልጃገረዶች ይኖራሉ። ለምሣሌ በአደጉ ሀገራት የሚኖሩ ልጃገረዶች፤ ከኑሮው የተመቻቸ መሆንና የተመጣጠነ ምግብ እንደልብ ከማግኘት ጋር ተያይዞ ገና በዘጠኝ አመታቸው የወር አበባን ሊመለክቱ ይችላሉ። ……ይህም ማለት ልጃገረዷ በዘጠኝ አመት ዕድሜዋ አካላዊ ለውጥ በማሣየት፤ የማርገዝ ብቃት ይኖራታል ማለት እንጂ፤ መደበኛ የሆነውን የወር አበባ ዑደት ታስተናግዳለች ማለት አይደለም። የሆነው ሆኖ ታዳጊ ልጃገረዶቹ የወር-አበባ የሚጀምሩበትን ሁኔታና ሌሎች ከሥነ-ተዋልዶ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳዮችን በተመለከተ ወላጆች በግልፅ ማስተማር ይኖርባቸዋል። ………ወንዶችም ሆነ ሴቶች ልጆች ከአንደኛው የሕይወት ምዕራፍ ወደሌላኛው የሕይወት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት ሁኔታና ጊዜ የቤተሰብ ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ዕድሜ ነው ማለት ይቻላል። በተለይ የወር አበባን በተመለከተ ልጃገረዶች ገና በአፍላ የኮረድነት ዕድሜያቸው ሊገነዘቡት የሚገባ የተፈጥሮ እውነታ ሲሆን፤ ይሄን ማወቃቸው ከክስተቱ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ድንጋጤን ይቀርፍላቸዋል………ወላጆችና ቤተሰቦችም ቢቻል ስለክስተቱ ተገቢ ዕውቀት ቢኖራቸው ተመራጭ ነው። ………ለመሆኑ የወር አበባ ምንድነው?……የሚለውን ስናይ በተለምዶ አጣምረን የምንጠራቸውን ministration እና period የሚሉትን ቃላት ለይተን ማወቁ ይጠቅመናል። "ማንስትሬሽን" የደም ፍሰቱን ሊገልፅ የሚችል ቃል ሲሆን፤ "ፔሬድ" ደግሞ የማንስትሬሽን ዑደቱን የሚገልፅ ቃል ነው። በዚህ መሠረትም ከላይ እንደገለፅኩት ማንስትሬሽን ከዘጠኝ አመት ጀምሮ ሊከሰት ይችላል። ይህ ወቅትም የሴት ልጅ የመራቢያ አካላት እርግዝናን ለመጀመር እና ለማስጀመር ዝግጁ መሆናቸውን የሚያበስር ነው። መደበኛውና በአማካኝ በየ28 ቀኑ የሚከሰተውና ለአምስት ቀናት ያህል የሚቆየው የደም ፍሰት ዑደት ወይም ፔሬድ ግን ከ12 እስከ 16 ባሉት አመታት ውስጥ የሚጀምር ይሆናል። ………የወር አበባ ሊጀምር በሚችልበት ወቅት ከሴቷ የተለያዩ አካላት ሆርሞኖች መመንጨት ይጀምራሉ። እኚህ ሁኔታዎችም ሴቷን ለእርግዝና ዝግጁ እንድትሆን የሚያደርጓት ሁኔታዎች ናቸው። በመጀመሪያም ከማህፀን በስተቀኝ እና በስተግራ የሚገኙት ኦቫሪዎች……ኦስትሮጅን እና ፕሮጅስትሮን የተሰኙትን ሆርሞኖች ያመነጫሉ። እነኚህ ሆርሞኖች የማህፀን ግድግዳ ለውጦችን እንዲያሳይ ማለትም ለእርግዝና ቅድመ-ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ያደርጋሉ። የፒቱታሪ ዕጢዎችም በኦቫሪ የተዘጋጁትን እንቁላሎች እንዲወጡና………ኦቫሪን እና ማዕጸንን በሚያገናኙት የፋሎፒያን ቱቦ ውስጥ ወደ ማዕጸን እንዲጓዙ ያደርጋሉ ማለት ነው። ………ዕንቁላሎች ወደ ማዕጸን በሚጓዙበት ወቅት ከወንድዬው የዘር ፍሬ ጋር ከተገናኙ፤ ከኦቫሪ ተነስተው በደም-ክምችት ከተገነባው የማዕጸን ግድግዳ ጋር ለመገናኘት አምስት ቀን ይወስድባቸዋል። ከዚያ ፅንሱ መፈጠሩን ይቀጥላል………ዕንቁላልና ስፐርም በፋሎፒያን ቱቦ ውስጥ ካልተገናኙ ግን ዕንቁላሉ ማዕጸን ላይ ሲደርስ ይፈራርሳል፤ ይህ ሁኔታም የኤስትሮጅን እና የፕሮጀስትሮን ሆርሞኖች ምርት እንዲቀንስ ምክንያት የሚሆን ሲሆን፤ በማህፀን ግድግዳ ላይ የተከማቸው ደምም መፈረካከስ ብሎም መፍሰስ የሚጀምር ሲሆን፤ በዚህ ሁኔታም በሴቷ የመራቢያ አካላት በኩል ወደውጪ መፍሰስ የሚጀምረው የወር-አበባም ለአምስት ቀናት ይቆያል ማለት ነው። ………ወደገደለው ስንሄድ የሴት ልጅ ማሚዎች እና ዳዲዎች አስቀድማችሁ ስለወር አበባ በግልጽ ሁኔታ ዘርዝራችሁ ማስረዳቱ በድንገት በሚከሰት የወር አበባ ወቅት የሥነ-ልቦና ችግር ሴት ልጆቻችን እንዳይገጥማቸው ቀድሞ ለማዘጋጀት ይረዳል። የመጀመሪያዎቹ አካላዊ ለውጦች እንዴት ያሉ ናቸው የሚለውን ስናይ የጡቶች እድገትና የብብት ፀጉር ማብቀል፤ በመጀመሪያ በልጃገረዶቹ ላይ የሚከሰቱ አካላዊ ለውጦች ሲሆኑ እኚህን ተከትሎም ምናልባት ከአንድ አመት በኋላ የዳሌ መስፋት፤ የእግሮች ማደግና የፊት ውበት መጨመር የመሳሰሉ ፈጣን ለውጦች ይመጣሉ፤ ይሄን ለውጥ ተከትሎም የወር አበባ "እንዴት ናችሁ ሴቶችዬ?" ብሎ ስለሚመጣ እንግዲህ ማሚና ዳዲ እንዲሁም የቤተሰቡ ግብዳ አካል ከፍተኛውን ትኩረት ማድረግ አለበት ማለት ነው፤ ክስተቱ ከመጀመሩ ቀድሞ መንገሩም "የወር አበባው ከየት የመጣ መሃት ነው?" ብለው ከመሸማቀቅ ያድናቸዋል።

በድጋሚ የተፖሰተ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ በደንብ ያንብቡት የተከበራቹ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦች ጠቃሚ መልእክት ካነበቡ በኋላ ለጓደኞቾ ሼር አየድርጉ የስፐርም መጠን ማነስ ምክንያ
በድጋሚ የተፖሰተ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ በደንብ ያንብቡት የተከበራቹ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦች ጠቃሚ መልእክት ካነበቡ በኋላ ለጓደኞቾ ሼር አየድርጉ የስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እንዲሁም እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቱ ምን ይሆን ??? በአለማችን ከ60-80 ሚሊዮን የሚሆኑ ጥንዶች ልጅ ያለመውለድ ችግር ያጋጥማቸዋል ለዚህ ችግር ከሚጋለጡበት ምክንያት አንዱ ፡- • የእስፐርም መጠን ማነስ • እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ • ትክክለኛ ቅርፅ የሌለው እስፐርም • የማህፀን ቱቦ ጠባሳ መኖር • የማህፀን እጢ መኖር • የእንቁላል ምርት ላይ ችግር ካለ • የሆርሞን ችግር መኖር • ለረጅም ጊዜ መድሀኒት መውሰድ ከላይ ከጠቀስናቸው ውስጥ ለዛሬ የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ እንገልፅላችሆለን • የሆርሞን ችግር • ኢንፌክሽን ካለ • ብልት አካባቢ ጉዳት ከደረሰ • ያልወረደ የዘር ፍሬ • ከዚህ ቀደም ሰርጀሪ ተሰርተው ከነበረ • ብልት አካባቢ የሚገኝ የደምስር እብጠት • የውስጥ ደዌ ህመሞች • ካንሰር ወይም ካንሰር ያልሆኑ እባጮች መኖር • ጭንቀት ፣ ድብርት • አብዝቶ የአልኮል መጠጥ መጠቀም ፣ ማጨስ • ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መጨመር ውድ የዶክተር አለ ተከታታይ በዛሬው ፁሁፋችን የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ልንገልፅላችሁ ወደናል

መጥፎ የአፍ ጠረን (ሀሊቶሲስ) ምንድን ነው? (ዶክተር ሀሎ) በህክምና ቋንቋ ሀሊቶሲስ የምንለው መጥፎ የአፍ ጠረን የጥርስ ጤናን/ ንጽህናን ባለመጠበቅ የሚከሰት ሲሆን ምናልባት ሌሎች የጤና ችግሮች እናዳሉብን አመላካች ነው፡፡ የምንመገው የምግብ አይነት እና ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ይህ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲባባስ ያደርጋል፡፡ ✔የምንመገበው ምግብ የአፍ ጠረንን እንዴት ይቀይራል? በመጀመሪያ የተመገብነው ምግብ መሰባበር/መፈጨት የሚጀምርው አፍ ውስጥ ነው፡፡ ምግብ ከተፈጨ በኋላ ወደ ደም ዝውውር ውስጥ ይገባል ከዚያም ደም ወደ ሳንባ ይጓዛል በመጨረሻም ከትንፋሻችን ጋር አብሮ ይወጣል፡፡ ጠንካራ ሽታ ያላቸው ምግቦች(ለምሳሌ፦ ነጭ ሽንኩርት፣ ሽንኩርት)፣ ጥርስን መፋቅ ወይም ስቴኪኒ መጠቀም፣ ጥርስን መጉመጥመጥ ለጊዜውም ቢሆን ሽታውን ሊያጠፋው ይችል ይሆናል ነገር ግን ምግቦቹ ከሰውነታችን እስኪወገዱ ድረስ ሽታው ሙሉ ለሙሉ አይጠፋም፡፡ ✔መጥፎ ልምዶች እንዴት መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣሉ? ጥርስዎን በየቀኑ የማይፍቁ ወይም የማይቦርሹ ከሆነ የምግብ ቅሪቶች በአፋችን ውስጥ ይቀራሉ እነዚህ ቅሪቶች ባክቴሪያዎች በጥርሶቻችን መሀል፣ በድዶቻችን አካባቢ እና በምላሳችን ላይ እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል ይህም መጥፎ የአፍ ጠረን ያስከትላል፡፡ ፀረ-ባክቴሪያ የአፍ ማጽጃዎች መጠቀም የባክቴሪያዎቹን እድገት ይገታል፡፡ ሲጋራ ማጨስ ወይም የሚታኝኩ የትንባሆ ምርቶችን መጠቀም መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲኖረን ያደርጋል፣ የጥርስ ቀለምን ያበላሻል፣ የምግቦችን ጣዕም የመለየት ችሎታችንን ይቀንሳል፣ ድዳችን እንዲቆስሉ ያደርጋል፡፡ ✔ከመጥፎ የአፍ ጠረን ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች ቀጣይነት ያለው መጥፎ የአፍ ጠረን መጥፎ ጣዕም በአፍ ውስጥ ካለ የድድ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ የድድ በሽታ የሚከሰተው በጥርሳችን ላይ ባክቴሪያን የያዙ ቁስ አካሎች በሚኖርበት ጊዜ ነው፡፡ ባክቶሪያዎች ድዳችን እንዲቆጣ/እንዲያብጥ የሚያደርግ መርዛማ ነገር ያመርታሉ ይህ የድድ በሸታ የማንታከመው ከሆነ ድድ እና የመንጋጭላ አጥንት እንዲጎዳ ያደርገዋል፡፡ ሌላው ከጥርስ ጋር የተያያዘ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚያስከትለው በትክክል የማይገጥሙ ሰው ሰራሽ ጥርሶች፣ የአፍ በይስት ኢንፌልሽን መጠቃት ናቸው፡፡ በህክምና ቋንቋ ዚሮስቶሚያ የምንለው የአፍ መድረቅ መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣል፡፡ ምራቅ አፍን ለማርጠብ በጣም ጠቃሚ ሲሆን በባክቴሪያዎች የሚፈጠርን አሲድ ነፃ ያደርጋልበተጨማሪም በጉንጭ፣ ድድና ምላስ ውስጥ የሞቱ ሴሎችን ያፀዳል፡፡ እነዚህ የሞቱ ሴሎች በጊዜ ካልተወገዱ ይበሰብሱና መጥፎ የአፍ ጠረን ያስከትላል፡፡ የአፍ መድረቅ የመድሃኒቶች፣ የምራቅ ዕጢ ችግርና ለረጂም ጊዜ በአፍ የመተንፈስ የጎንዮሽ ጉዳት ውጤት ነው፡፡ የተለያዩ ብዙ በሽታዎች እና ህመሞች መጥፎ የአፍ ጠረን ያስከትላሉ ከነዚህ በሽታዎች መካከል፦ የመተንፈሻ አካል በሽታዎች(የሳንባ ምች ወይም ብሮንካይተስ)፣ ከባድ የሳይነስ ኢንፌክሽን፣ ፖስትናሳል ድሪፕ፣ የስኳር በሽታ፣ ከባድ የአሲድ ችግር እና የጉበት ወይም ኩላሊት ችግር ናቸው፡፡ ✔መጥፎ የአፍ ጠረንን እንዴት መከላከል እችላለሁ? መጥፎ የአፍ ጠረንን በሚከተሉት መንገዶች መቀነስ ወይም መከላከል ይቻላል፦ 1. የአፍ ንጽህናን በመጠበቅ በፍሎራይድ የጥርስ ሳሙናዎች ጥርስን በቀን ሁለት ጊዜ መቦረሽ የምግብ ቅሪቶችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ምግብ ከተመገብን በኋላ ጥርስን መቦረሽ (የጥርስ ቡርሻችንን በት/ቤትና ስራ ቦታ መያዝ)፡፡ ምላስዎንም መቦረሽ እንዳለብዎት አይርሱ፡፡ ከሁለት ወይም ሶስት ወር በኋላ ወይም ከህመም በኋላ የጥርስ ቡርሻችንን መቀየር አለብን በጥርሶቻችን መሃል ያሉትን ምግቦች ለማስወገድ በቀን አንድ ጊዜ ስቴኪኒ ወይም ሌላ ነገሮች በመጠቀም ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡ 2. የጥርስ ሃኪምዎን በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ይጎብኙ በአመት ሁለት(2) ጊዜ ወደ ጥርስ ሃኪምዎ እንዲሄድ ይመከራል፡፡ ሃኪምዎ የአፍ ምርመራ፣ የጥርስ ማጽዳት(በህክምናዊ መንገድ)፣ የተለያዩ የጥርስ በሽታዎች ምርመራና ህክምና፣የአፍ መድረቅና የተለያዩ የአፍ ጠረንን የሚያመጡ ችግሮችን መፍትሄ ያገኝልዎታል፡፡ 3. ሲጋራ ማጨስና ከትንባሆ የሚዘጋጁ የሚታኝኩ ነገሮችን መጠቀም ማቆም፡፡ 4. ብዙ ውሃ መጠጣት ይህ ሁኔታ አፋችን በማንኛውም ጊዜ እርጥበት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ማስቲካ ማኝክ(ስኳር የሌላቸው ቢሆኑ ይመረጣል) ምራቅ እንዲመረት ያደርጋል ምራቅ የምግብ ቅሪቶችንና ባህቴሪያዎች ታጥበው እንዲወገዱ በማድረግ ይጠቅመናል፡፡ ዛይሊቶል() ያላቸው ማስቲካና ሜንት መጠቀም ተመራች ነው፡፡ 5. የተመገብናቸውን ምግቦች እና የወሰድናቸውን መድሃኒቶች መዝግበን በመያዝ የትኞቹ ምግቦች ወይም መድሃኒቶች መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲከሰት መንስኤ የሆኑትን በቀላሉ በመለየት እርምጃ መውሰድ እንችላለን፡፡ ✔መጥፎ የአፍ ጠረንን ማን ሊያክም/ሊመረምር ይችላል? በአብዛኛው የጥርስ ሃኪም መጥፎ የአፍ ጠረንን ይመረምራል የጥርስ ሃኪማችን አፋችን ጤናማ መሆኑን እና ይህ መጥፎ ሽታ ከአፋችን አካባቢ እንዳልሆነ ካረጋገጠ በኋላ የመጥፎ አፍ ጠረኑን ምንጭ ለማወቅ ወደ ሌሎች ሃኪሞች ወይም ስፔሻሊስቶች ጋር ሪፈር ያደርገናል፡፡ ✔ምን አይነት የአፍ ጠረን ማጥፊያ ምርቶችን መጠቀም አለብኝ? መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ በቁጥር በዛ ያሉ የአፍ ማጠቢያዎች መግዛት ይቻላል ነገር ግን ብዙዎቹ መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ ጊዜያዊ መፍትሄ ቢሆኑም ሙሉ ለሙሉ አያስወግዱትም፡፡ ከጥርስ ሃኪምዎ ጋር በመመካከር እና የትኛው ምርት ውጤታማ እንደሆነ በመጠየቅ በገበያ ላይ የሚገኙ ፀረ-ባክቴሪያ የአፍ ማጽጃዎች መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲኖር የሚያደርገውን ጀርም የመግደል አቅም ስላላቸው ብንጠቀማቸው ጥሩ ውጤት ያስገኛሉ፡፡ @DrSofonias

-------------------''ሲጋራና መዘዙ''!------------ ሲጋራ ማጨስ ለጤና በጣም ጠንቅ ነው። ምንም አይንት አጫጫስ ጉዳቱን አይቀንሰውም፥ ሲጋራውን በፒፓ ውስጥ መክተት ሆነ በሁካ ማጨስ ጉዳቱን አይቀንስም።እንደ አሜሪካ የሳንባ ማህበር (American Lung Association)ጥናት መሰረት ሲጋራ ውስጡ ወደ 600 ሚሆኑ ንጥረ ነገሮች አሉት። በሚጨስበት ጊዜ ደግሞ ወደ 7 ሺ ኬሚካሎችን ይወልዳል ። እና ከነዛ ውስጥ አብዛኛዎቹ ኬሚካሎች መርዞች ናቸው እናም ቢያንስ 69ኙ ነቀርሳ(cancer) ያመጣሉ። ሁካና ቶባኮም አብዛኛዎቹን መርዞች አሉባችው።ሁካ ሲጨስ ከሲጋራ በላይ ጪስ ወደ ውስጥ የመሳብ እድሉ አለ። እናም ሁካ ከሲጋራ ይበልጥ ለመጥፎ መርዞች እና ለ ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ እንድትጋለጡ ያርጋችኃል። እንዲሁም ሁካ ከጎን ያለን ሰው (secondhand) ይበልጥ ያጠቃል። በሰሜን አሜሪካ ውስጥ (the United States), ሲጋራ የሚያጨስ ሰው የሞት ፍጥነት ብዛት ከማያጨሰው ሶስት እጥፍ ይበልጣል።በአለማችን በየዓመቱ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ሲጋራ በማጨስ ምክንያት በሚከሰቱ የጤና ችግሮች የሚሞቱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስድስት መቶ ሺህ የሚሆኑት እራሳቸው ሲጋራ የማያጨሱ ሆነው ከአጫሾች በሚመጣ ጭስ ምክንያት ለጤና መታወክ የሚዳረጉና የሚሞቱ ናቸው፡፡ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር በአደጉት አገራት እየቀነሰ መምጣቱንና በአንፃሩ ደግሞ በታዳጊ አገራት በከፍተኛ መጠን በመጨመር ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡የሀገራችን አመታዊ የሲጋራ ፍላጐት 4.4 ቢሊዮን ፍሬ መድረሱንም ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ ------------------------ሲጋራና መዘዙ! --------------''ማእላዊ ስርአተ ነርቭ''-------- ከሲጋራ ንጥረ ንገሮች አንዱ ኒኮቲን ይባላል። ኒኮቲን አይምሮ ጋር በሰከንድ ውስጥ ይድርሳል። ሲደርስ አይምሮን አነቃቅቶ ሃይል ለተወሰነ ጊዜ ይስጣል። ከዛን ያ ሃይል ሲጠፋ ከእንደገና ሌላ አንዲጨመር ይገፋፋል እንደዚህ ነው ሱስ የሚጀመረው። ማጨስ የአይን ጋርዶሽ እና የአይን ድክመት ያመጣል። እንዲሁም የመቅመስና የምለየትን ስሜት ይቀንሳል ስለዚህ ምግብ ያን ያህል መጣፈጡን ይቅንሳል። ጭንቀት ላይ ሰውነታችን ውስት corticosterone የሚባል ሆርሞን hormone ያመነጫል , ይህ ሆርሞን ሲጋራ ወይ ኒኮቲን የሚያመጣውን ስሜት ይቀንሰዋል ስለዚህ ነው ሰው ሲጨነቅ ብዙ ሲጋራ ካላጨሰ በስተቀር የሲጋራን ሃይል የማይስማው። ከሲጋራ መለየት ሲሞከር መረበሽ ፥ ጭንቀት፥ ራስ ምታት ለጊዜው ይመጣል። -------------ስርዓተ ትንፈሳ----- ሲጋራ ጪሱ ወደ ውስጥ ሲገባ ሳምባን የሚጎዱ ነገሮች አብረው ነው የሚገቡት። ሳምባ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የሚጎዱ ኬሚካሎችን የማጣራት ሃይሉን ይጣል። ማሳል የመተንፈሻ መንገዱን አያጠራውም ስለዚህ እንዚህ መርዞች እዛው ይቀመጣሉ ። አጫሾች መተንፈሻ ችግር እንደ ኢንፌክሽን፥ ብርድ፥ጉንፋን የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።አጫሾች የሳንባ ካንሰር፥ ብሮንካይተስ ሌላ ሌላ ችግሮች የተጋለጡ ናቸው። ወላጆች ወይ ሌሎች የሚያጭሱ ሰዎች ይሉበት ቤት የሚኖሩ ልጆች ለተለያየ የመተንፈሻ በሽታዎች፥ ብሮንካይተስ፥ ኒሞኒያ፥ አስም፥ ሳይነስ የተጋለጡ ናቸው። ------------ስርአተ ልብ ወቧንቧ----- ማጨስ የውስጥ ቧንቧን ባጠቃላይ ይጎዳል። ኒኮቲን ልክ ሰውነት ውስጥ ሲገባ ደም ውስጥ ያለን ስኳርን ከፍ ያርጋል፥የስኳሩ ከፍ ማለት ትንሽ ስሜትን ሚያነቃቃ ቢሆንም ከትንሽ ጊዜ በኃላ ድካም ያመጣል ከዛን ተጨማሪ እንዲጨስ ይገፋፋል።ኒኮቲን የደም ቧንቧ እንዲጠብ ያደርጋል ይሄ ታዲያ ደም በአግባቡ እንዳይፈስ ያግደዋል። የደም ብዛት ፥ የደም መርጋትን እንዲሁም ኮልስትሮል መጨመርን ያመጣል። የደም መርጋት ስትሮክ የመያዝ እድሉን ይጨምረዋል። ከጊዜም በኃላ የደም ካንሰር ያመጣል። ሲጨስ ከጎን ለሚሆን ሰውም ብዙ ጉዳት ያመጣል። ----------ቆዳ,ፀጉር, እና ጥፍር--------- አንዱ በቀላሉ የማጨስ ጉዳቱ ሊታይ የሚቻለው በቆዳ ላይ ነው። የሲጋራ ንጥረ ነገር የቆዳን ተፈጥሮ ይቀይራል።ማጨስ ቆዳ ላይ ጥቓቁር ነጠብጣብ ያወጣል፥ ፊትን ያጨማድዳል፥እንዲሁም አስቅድሞ ያስረጃል። የጣት ቆዳ እና ጥፍር ቢጫ ይሆናሉ። ስራት ማብላሊያ አካል አጫሾች አፍ ውስጥ ሊመጡ ሊኖሩ ይሚችሉ በሽታዎች ተጠቂዎች ናቸው። ሲጋራ የመንጋጋ በሽታ፥ ኢንፌክሽን ያመጣል። ይሄ ወደ ጥርስ መበስበስ፥ጥርስ ቡኒ እና ቢጫ እንዲሆን አልፎም እንዲወልቅ ያደርጋል። መጥፎ የአፍ ጠረንም ያመጣል። ማጭስ የአፍ ነቅርሳ ወይም ካንሰር፥ የጉሮሮ ካንሰር፥ እና የኩላሊት ካንሰር፥ የጣፊያ ካንሰር ያመጣል። የስኳር በሽታ ያመጣል።

ኪንታሮት መንስኤና መፍትሄዎች (ህክምና) የቂጥ ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡ 1) ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid) በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ 2) ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡ ✔ ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች • ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ • ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ • የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ) • ከመጠን ያለፈ ውፍረት • ዕርግዝና • የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው • በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡ ✔ የኪንታሮት ምልክቶች • ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም • በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ • ሕመም ወይንም አለመመቸት • በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡ ✔ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? • በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ • ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባዎታል፡፡ • ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✔ ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን ናቸዉ? • አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን ያስከትላል፡፡ • ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡ ✔ በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች • ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት ጊዜ መዘፍዘፍ • ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ • ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም • እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም • ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✔ ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል? • በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር - አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡ • ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ - በቀን ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃን ወይም ጭማቂን መውሰድ • ማስማጥን ማስወገድ - ሠገራን ለማስወጣት በምናምጥ ጊዜ በደም ስሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊትን ስለምንፈጥር ለሄሞሮይድ/ለኪንታሮት/ ተጋላጭንት ይጨምራል፡፡ • ሠገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያልፉ ወደ መፀዳጃ ቤት በመሄድ ያስወግዱ፡፡ አለዚያ ሠገራዎ ስለሚደርቅ ለማስወገድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘውትሩ - የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ እንድንሆን ያደርጋል፣ • ለረጅም ሰዓታት መቀመጥን ያስወግዱ፡፡ በተለይም በመፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ለሄሞሮይድ መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ @DrSofonias

በሰውነትዎ የአሲድ መጠን የመኖር ምልክትና ህክምናዎቹ ምልክቶች 👉 በቂ እንቅልፍ ቢያገኙም እንኳ የደከሙ እንደሆኑ ይሰማዎታል 👉 ጭንቀት ይሰማዎታል ወይም ቀደም ሲል በነሩትን ነገሮች ለመደሰት ይቸገራሉ ፡፡ 👉 ያለምክንያት በእራስዎን ያበሳጫሉ 👉 ብዙ ጊዜ ትኩረት ማድረግ ችግር ወይም “የአንጎል ጭጋግነት” ይገጥምዎታል 👉 ኢንፌክሽኖችን ፣ ጉንፋንን እና ፍሳሾችን ዘወትር ያዳብራሉ ጭጋግነት 👉 ሞቃታማ በሆኑት ወራትም እንኳ ቆዳዎ ደረቅ ነው 👉 የቆዳ ህመም ወይም ሌሎች የቆዳ ችግሮች አለብዎት 👉 የሆርሞን አለመመጣጠን ጉዳዮች አሉዎት 👉 ብዙውን ጊዜ የእርሾ /Yeast ኢንፌክሽኖችን ያዳብራሉ 👉 የምግብ መፈጨትዎ እንደዘገየ ወይም በተደጋጋሚ የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ የመሰለ ስሜት ይሰማዎታል 👉 ብዙውን ጊዜ የትንፋሽ እጥረት ያድርብዎታል 👉 ብዙውን ጊዜ መገጣጠሚያ ህመም ይሰማዎታል 👉 ብዙውን ጊዜ ራስ ምታት ያጋጥሙዎታል 👉 ሥር የሰደደ አለርጂ ወይም የ sinus ህመም ይሰማዎታል 👉 በደረሰበት ጉዳት/Injury ወይም በሕክምና ሁኔታ ምክንያት በማይሆን ሥር የሰደደ ህመም ይሰቃያሉ 👉 አንገትዎ ብዙውን ጊዜ የግትርነት ስሜት ወይም ህመም ይሰማዋል 👉 ስሜታዊ የድድ እና የጥርስ ህመም ይኖራል 👉 በዚህ ዝርዝር ውስጥ ብዙ ምልክቶችን እያዩ እንደሆነ ካዩ ፒኤችዎን ለመመርመር ጊዜው አሁን ነው መፍትሄው -የውሃ ሕክምና 👉 ስለ የውሃ ሕክምና ሰምተው ያውቃሉ እና ጥቅሞች አሉት? አንዳንድ ጥቅሞች እዚህ አሉ ከፍተኛ የደም ግፊት - 30 ቀናት የጨጓራ ቅባት - 10 ቀናት የስኳር በሽታ - 30 ቀናት የሆድ ድርቀት - 10 ቀናት ካንሰር - 180 ቀናት ቲቢ - 90 ቀናት ወዘተ ... የሕክምና ዘዴ 👉 ጥርሶችን ከመቦረሽ በፊት ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ስትነቁ 4 x 160ml ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ 👉 አፍን ብሩሽ ያድርጉ እና ያፅዱ ነገር ግን ምንም ነገር አይበሉ ወይም አይጠጡ ለ 45 ደቂቃዎች ፡፡ 👉 ከ 45 ደቂቃዎች በኋላ መብላትና መጠጣት ትችላላችሁ 👉 ከቁርስ ፣ ምሳ እና እራት ከ 15 ደቂቃዎች በኋላ፦ ለ 2 ሰዓታት ምንም ነገር አይበሉም ወይም አይጠጡ መሰረታዊ ፕሮቶኮል በባለሙያዎች መሠረታዊው የፕሮቶኮሉ ምክር እንደሚከተለው ነው- 1. ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ስትነሱ ከ5-6 ብርጭቆዎች ውሃ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ 1.50 ሊትር ውሃ ይጠጡ 2. ውሃውን ከመጠጡ በፊት እና በኋላ ለ 1 ሰዓት ያህል ሌላ ነገር አይበሉ ወይም አይጠጡ ፡ @DrSofonias

ጠቃሚ መልእክት ስለሆነ በደንብ ያንብቡት ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ #ኩላሊታችን #የቱ #ጋር #ነው,,? የኩላሊት ህመም ወይም መድከም ዛሬ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ላይ በሽታ ይስተዋላል። ብዙዎች የኩላሊት ህመምን እንደቀላል በማየት ብርድ ነው፣ጨጓራ ነው፣ ወገቤን ነው በማለት የቀኝና የግራ ኩላሊት በየት አካባቢ የሰውነት ክፍላችን እንደሚቀመጥ ለማሳየት ነው። ህመም ሲሰማን በማስታገሻ ሰውነታችንን ማለማመድ ለኩላሊት መድከም ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በተለይ አመጋገባችን ለጤንነታችን ሰፊ ድርሻ አለው ለምሳሌ ,,,የታሸጉ ምግቦች በየቀኑ ስጋና ቅባት ምግቦችን ማዘውተር። የፖልም ዘይት መጠቀም ሌላው በመኝታ ሰዓት መመገብና እንቅስቃሴ ሳናደግ መተኛት ለከፍተኛ ጉዳት ይዳርጋል። በመጠጥ ደረጃ አልኮል መጠጦችን ቅባትነት ያላቸው ውስኪ የመሳሰሉ መጠጦች ለበሽታው ተጋላጭ ያደርጋል። ጣፋጭ ለስላሳ መጠጦችም ከፍተኛ ስኳርነት ስላላቸው አይመከሩም ሁሉንም በልክና አልፎ አልፎ መጠቀሙ ይመከራል። ኩላሊት ሲጎዳ የሚታዩ 8 ምልክቶች 1. ኩላሊታችን ችግር ሲያጋጥመው የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ ትንፋሽ ሊያሳጥረን ይችላል 2. ምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም መሰማት - የኩላሊት ችግርን ተከትሎ በደም ውስጥ የንጥረ ነገሮች ይዘት ላይ ለውጥ ስለሚኖር በምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም ከመሰማት ጀምሮ እስከ ጠቅላላ የምግብ ጣዕም ለውጥ ሊኖር ይችላል፡፡ የደም ይዘት ለውጥን ተከትሎ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ችግርም ያጋጥማል፡፡ 3. የውሃ ሽንት ቀለም ለውጥ - የሽንት ከለር ለውጥ አንዱ የኩላሊት ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይም የውሃ ሽንት ከለር ጠቆር ወዳለ ብጫ ከለር በተደጋጋሚ ከተስተዋለ የኩላሊት ጉዳት ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡ 4. የትኩረት መቀነስ - የኩላሊት መጎዳት ኦክሲጅን በአግባቡ ወደ ጭንቅላት እንዳይሄድ ስለሚያደርግ የማስታወስ ችግርና የትኩረት ማጣትን ያስከትላል፡፡ 5. የሰውነት አካል እብጠት - የኩላሊት ጉዳት በሰውነታችን የሚገኙ ፈሳሾች በአግባቡ እንዳይወገዱ ስለሚያደርግ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በተለይም እግር ፣ መገጣጠሚያና ፊት ላይ እብጠት ሊከሰት ይችላል፡፡ 6. የሰውነት መዛል - የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ የሰውነት ማዛልን ጨምሮ የአዕይምሮና የጡንቻዎች ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡ 7. የቆዳ አለርጂ - የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ በሰውነታችን የመርዛማ ንጥረ ነገሮች ክምችት ስለሚጨምር የቆዳ አለርጂ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ 8. የኩላሊት አካባቢ ህመም የኩላሊት ኢንፌክሽን ኩላሊት አካባቢ ህመም እንዲሰማ ያደርጋል፡፡ ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የኩላሊት ጉዳት ችግር ሊሆን ስለሚችል ኩላሊቶን በመመርመር ሊታደጉት ይገባል ይላል የናሽናል ኪድኒ ፋውንዴሽን መረጃ በማድረግ ብዙዎችን ከጉዳት እንታደግ አሁን ልንመክርዎት የፈለግነው አንደኛ በመንግስት መስሪያ በግል፣በውትድርና፣በሆቴል፣በፋብሪካ በሱቅ፣በሹፍርና፣ በጉሊትም አጠቃላይ በማንኛውም ስፍራ የምንገኝ ሁሉ ሁል ጊዜ ውሀ መጎንጨትን አንርሳ አንዳዶች ሽንት ውሀ ከጠጣው ያስቸግረኛል በማለት እራሳቸውን ለጉላሊት በሽታ የሚያጋልጡ ቀላል አይደሉም። ከሁሉ በላይ ህመም ስሜት ሲሰማዎ ወደ ጤና ተቋም በጊዜ ይሂዱ። እናመሰግናለን። @DrSofonias

♨️ ድንገተኛ ሞትን እንከላከል ⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜ በምሽት ወይም በእንቅልፍ ሰአት የሚከሰትን ድንገተኛ ሞት ለመከላከል የህክምና ባለሙያወች ምክር↩️ ከእንቅልፋችን በድንገት ተነስተን ሽንታችንን ለመሽናት ከመሄዳችን በፊት ለ ሶስት (3) እና አራት (4) ደቂቃወች ማድረግ ያለብን ጥንቃቄወች አሉ! አንዳንዴ ሰወች ጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እና ቁመና ላይ ሁነው በድንገት ምሽት ላይ ህይወታቸው ያልፋል። ከዚህ ጋ ተያይዞ አንዳንድ ሰወች ትናንት እኮ አውርቸው ነበር እንዴት በድንገት ሞተ? ሲሉ ይደመጣሉ። 🔴ነገሩ እንዲህ ነው በድንገት ከእንቅልፋችን ተነስተን ወደ ሽንት ቤት በምንሄድበት ጊዜ አእምሮአችን የደም ዝውውር ላይኖረው ይችላል። ስለዚህ ሶስት(3) እና አራት (4) የሆኑ ደቂቃወች እንዴት ወሳኝ ሊሆኑ ቻሉ? በእኩለ ሌሊት ከእንቅልፋችን ተነስተን ሽንታችንን ለመሽናት በድንገት ወደ ሽንት ቤት በምንሄድበት ጊዜ የልብ ምታችን የደም ዝውውራችን ጋ በተያያዘ እክል ይገጥመዋል። በድንገት በምንነሳበት ጊዜ አእምሮአችን እና ልባችን በሚያጋጥመው የደም እጥረት ስራውን መስራት ሊያቆም ይችላል። ከዚህም ጋ በተያያዘ በተነሳንት ባሉት 3 እና 4 ደቂቃወች የሚመከሩ እና ማድረግ ያለብን ጉዳዮች 1.እንደነቃን ለ 1 ደቂቃ እና 1 ደቂቃ ከግማሽ ባሉት ደቂቃወች ከአልጋችን መቆይት። 2.እሰከ ቀጠዮ ሁለት ደቂቃ አልጋው ላይ መቀመጥ 3.እግራችንን ከአልጋው አውርደን ለ ግማሽ ደቂቃ ያክል አልጋው ጠርዝ ላይ መቀመጥ ከ ሶስት(3) እና ግማሽ ደቂቃ በኃላ አእምሯችን እና ልባችን በደም እጥረት የመጠቃት እድሉ አነስተኛ ስለሆነ በድንገት የመሞት አጋጣሚን መቀነስ ይቻላል!!! 🔊 ይህ ችግር ምንም እድሜ የማይገድበው ስለሆነ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የተሻለ ግንዛቤን እንፍጠር #Share

ቅጥ ላጣ ውፍረት የሚዳርጉ ልማዶች በሰውነታችን ውስጥ ስብ እንዲከማች ከሚያደርጉ እና ቅጥ ላጣ ውፍረት ከሚዳርጉን ምክንያቶች መካከል ዋንኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. የአመጋገብ ባህላችን፣ አብዛኛዎቻችን የምግብ ምርጫችን ወደ እንስሣት ተዋፅኦና ጣፋጭ ምግቦች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ሥጋ፣ እንቁላል፣ ቅቤና ወተት በምግባችን ውስጥ ካላካተትን የጋበዝንም የተጋበዝንም የማይመስለንና ለምግብ መመገቢያ የተወሰነ ሰዓትና ጊዜ የሌለን ከመሆኑም በተጨማሪ ምግብን የምንመገበው ስለተራብን ብቻ ሣይሆን ስለአገኘንም መሆኑ ሠውነታችን ከሚያስፈልገው የሃይል ምንጭ በላይ ምግብ እንዲወሰድና ከአስፈላጊው በላይ የሆነው በስብ መልክ እንዲከማች ምክንያት ይሆነዋል፡፡ 2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አለማድረግ ፣ ወደ ሰውነታችን ውስጥ የገባና ከአስፈላጊ በላይ የሆነው ምግብ በተለያዩ መንገዶች መቃጠልና ከሰውነታችን ውስጥ መወገድ ይኖርበታል፡፡ ያለበለዚያ ግን በስብ መልክ ያከማቻል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ አካላዊ ብቃት እንቅስቃሴ ስንልም በተደራጀ መልኩ በጄምናዚየምና መሰል ሥፍራዎች ላይ ብቻ የሚደረገውን ሳይሆን ሰው በዕለት ተዕለት ተግባሩ ራሱን በማንቀሳቀስ፣ የእግር ጉዞ በማድረግ እና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ምግቡ እንዲቃጠል ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በእርግጥ ያለንበት ዘመን ቴክኖሎጂው የተስፋፋበት መንገድን በመኪና ደረጃና በሊፍት የምናሳጥርበት ሁኔታ የተመቻቸበት ቢሆንም ማንኛውም ሰው በተለይ ደግሞ የውፍረት ችግር ያለበት ሰው ራሱን በእነዚህ ነገሮች ውስጥ በማንቀሳቀስ ደረጃዎችን በእግሩ በመውጣት፣ በአንቀሳቃሽ የቢሮ ሥራዎች ውስጥ በመሳተፍ ራሱን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሊያግዝ ይችላል፡፡ 3. በዘር የሚከሰት የውፍረት ችግር፣ የውፍረት ችግር በዘር የመተላለፍ ዕድል አለው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለከፍተኛ ክብደት የሚያጋልጡ የዘር ዝንፈቶች አሉባቸው፡፡ ይህ የዘር ዝንፈትም ሰውነት ምግብን ለሃይል ምንጭነት በማዋል ከማቃጠል ይልቅ እንዲከማችና ስብ እንዲፈጥር በማድረግ ውፍረትን ያባብሳል፡፡ መልካም ጤንነት

ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የረመዳን ጾም ይመኛል። እንኳን ለታላቁ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም የረመዳን
ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የረመዳን ጾም ይመኛል። እንኳን ለታላቁ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም የረመዳን ጾም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ረመዳን ከሪም!! Ramadan Kareem!!

ለመዳን መፍትሄው እና ማድረግ ያለብን ወሳኝ ነገሮች የጨጎራ ቁስለት/ህመም ምንድን ነው??? ~~\\~~~~ የጨጎራችን የላይኛው ሽፋን በተለያዩ ምክንያቶች መላጥ ፤መጎዳትና መቁሰል ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡ ~ ለጨጎራ ቁስለት/ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድን ናቸው??? ___ 1. የዛባ የእመጋግብ ስርአት 2. ለጨጎራ ጸር የሆኑ መድሀኒቶች NSAID,TB መድኃኒቶች…. 3. የጨጎራ ባክቴርያ በጨጎራችን ውስጥ መኖር 4. የሚያቃጥሉና የሚለበልቡ ምግቦች ማዘውተር 5. እርግዝና ~ የጨጓራ ቁስለት(ህመም)ምልክቶች _____ 1.ደረት መሀል ይም ጡትና ጡት መሀል የሚኖር፣የሚያቃጥል እና ምቾት የሚያሳጣ ህመም 2.ግሳት እና ማስታወክ 3.ሆድ መንፋትና ቃር 4.ጀርባ፣እግርና ሰውነትን የሚያቃጥል ስሜት መኖር 5.ምግብ ሲበሉ ወይም ሳይበሉ ሲቀሩ የሚኖር የደረት ህመም ~ የጨጔራ ህመም ምርመራዎች ምንድን ናቸው? ___ 1. የጨጔራ ህመም እንዳለብን ከጠረጠረ መጀመርያ የሚደረገው የባክቴርያ (H.pylory) ምርመራ ነው፡፡በደም ወይም በሰገራ የሚደረግ ምርመራ ሲሆን ውጤቱም +ve (አለ) ወይም _ve (የለም) በመባል ይገለጻል፡፡ 2. UBT(uria breath test) የትንፋሽ የጨጔራ ባክቴርያ ምርመራ ነው፡፡ 3. ENDOSCOPY ይሄ ምርመራ በአፍ በሚገባ ትቦ (ማሽን)አማካኝነት የጨጔራ ቁስለትን ወይም የጨጔራችንን የተጎዳ ክፍል በኮንፒተራይዝድ መሳሪያ የምናይ ሲሆን ህመሙ ለተደጋገመባቸውና በቀላሉ ሊድኑ ላልቻሉ የጨጔራ ህመምተኞች እንጠቀማለን፡፡ 4. syndromic approach ይህንን ዘዴ የምንጠቀመው የላብራቶሪ ምርመራዎች በሌሉበት ቦታና አንዳንዴም ጨጔራ ህመም አለ ብለን እርግጠኛ በሆንንበት ሰአት ነው፡፡ የጨጔራ መድሀኒቶች ጥቅም ምንድን ነው 1. የጨጔራ አሲድን ማቅጠን የበዛ የጨጔራ አሲድ በሚኖርበት ሰአት ጨጔራችን ራሱ በዚህ አሲድ ሊጎዳ ስለሚችል እነዚህ መድሀኒቶች ወደ ጨጔራ በመሄድ አሲዱን አቅጥነው ደረት አካባቢ የሚኖረውን ህመም ይቀንሳሉ፡፡ 2. የጨጔራ ግርግዳን በማከም ህመሙን መቀነስ 3. የጨጔራ ባክቴሪያ መድሀኒቶች በቁጥር 3 አይነቶች ሲሆኑ ባክቴሪያውን ለመግደል ብሎም ቁስለቱን ለማከም ተብለው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ -መድሀኒቶ በታዘዘልን ሁኔታና ሰአት በትክክል ካልወሰድናቸው እንዲሁም ከዛ በኋላ የአመጋግብ ስርአታችንን ካላስተካከልን የመደጋገምና ወድያው ለተመሳሳይ ህመም ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ የጨጓራዪን ጤንነት እንዴት ልጠብቅ??? ለልብሳችን እና ለመልካችን እንደምንጨነቀው ሁሉ ልጨጎራችንም ጤንነት ከምንም በላይ መጨነቅ አለብን፡፡ይህም 1. ጭንቀትን ማስወገድ 2. አመጋገባችንን ማስተካከል 3. የሚያቃጥሉ ምግቦች እና መጠጦች አለመጠቀም 4. አልኮልና ሲጋራ ማስወገድ 5. ፈሳሸ በብዛት መውስድ 6. በሃኪም የሚታዘዙልንን መድሃኒቶች ጨጎራን በማይነኩ መድሃኒቶች ማስቀየር 7. የተደጋግመ የጨጎራ ሕመም ካለብዎ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ የጨጎራ ባክቴሪያ ህክምናዎችን መውሰድ የዶክተር አለ መልእክት -“ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” የሚባለውን ብሂል ሁላችንንም ለማስተማር የታለመ ነው፡፡የጨጎራ ሕመም ከቀላል መድሃኒቶች እስከ ከባዱ ቀዶ ጥገና ድረስ ሊያደርሱ የሚችሉ የጤና መዘዞች አሉት፡፡ -በጤናችን ላይ የምናስተውላቸውን ማንኛዎችንም ለውጦች ችላ ብለን ያለፍናቸው ነገሮች ሁሉ ጤናችንን አውከው አልጋ ላይም ሊያስቀረን ትችላለች፡፡ ስለዚህም በምግብ እና በአኖኖር ዘይቤ ለውጥ ምናስተካክለውን ጨጎራ ህመም ችላ ብለን ታላቅ የጤና ቀውስ አንዲያመጣብን አንፍቀድለት፡፡ ~~ በመጨረሻም ምክር ∆∆∆∆∆∆∆\\∆∆∆∆∆ የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ወይም ህክምና የሚሆነው በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ #ጨጓራን በቤት ውስጥ እንዴት ልንከላከለው ወይም ልናክመው እንችላለን? -------- √ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ። √ከመጠን ያለፈ አልኮል አይጠጡ። √ካፌይን ያላቸው መጠጦችን አይጠጡ ለምሳሌ ቡና፣ ሻይ። √ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቆዎችን አይጠጡ ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ √ከፍተኛ የቅባት/ፋት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አይመገቡ፡፡ √በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች. ፓይሎሪ የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ ናቸው ከነዚህ ምግቦች መካከል፦ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጐመን፣ የምግብ ማጣፈጫ ተክል፣ ጦስኝ፣ ሽምብራ እና አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡ @DrSofonias

ለእርሶ ጠቃሚ መረጃ - ሆድ መነፋት - የጥጋብ ስሜት - ማቅለሽለሽ - ማስታወክ - የድካም ስሜት - እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ትንፋሽ ማጠር - ጥቁር የሚያጣብቅ ሰገራ - በሰገራ ውስጥ ጥቁር ቀይ ወይም
ለእርሶ ጠቃሚ መረጃ - ሆድ መነፋት - የጥጋብ ስሜት - ማቅለሽለሽ - ማስታወክ - የድካም ስሜት - እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ትንፋሽ ማጠር - ጥቁር የሚያጣብቅ ሰገራ - በሰገራ ውስጥ ጥቁር ቀይ ወይም ወይን ጠጅ ቀለም መታየት - ደም ወይም ጠቆር ያለ ነገር የሚታይበት ትውከት - ራስን መሳት - በሆዳችን የላይኛው ክፍል የህመም ስሜት ከእነዚህ ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ወይም ሁሉም ካሉ "Peptic Ulcer" የጨጓራ ወይንም የአንጀት ቁስለት ምልክቶች ናቸው። ቀድመን በመታከም ራሳችንን እንጠብቅ።