ar
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

الذهاب إلى القناة على Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

تُعد قناة ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 19 967 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 154 في فئة الطب والمرتبة 1 678 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 19 967 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 26 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -547، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -20، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 24.05‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 7.27‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 805 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 453 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 9.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 27 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الطب.

19 967
المشتركون
-2024 ساعات
-1217 أيام
-54730 أيام
أرشيف المشاركات
ኪንታሮት መንስኤና መፍትሄዎች (ህክምና) የቂጥ ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡ 1) ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid) በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ 2) ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡ ✔ ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች • ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ • ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ • የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ) • ከመጠን ያለፈ ውፍረት • ዕርግዝና • የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው • በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡ ✔ የኪንታሮት ምልክቶች • ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም • በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ • ሕመም ወይንም አለመመቸት • በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡ ✔ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? • በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ • ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባዎታል፡፡ • ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✔ ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን ናቸዉ? • አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን ያስከትላል፡፡ • ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡ ✔ በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች • ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት ጊዜ መዘፍዘፍ • ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ • ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም • እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም • ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✔ ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል? • በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር - አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡ • ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ - በቀን ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃን ወይም ጭማቂን መውሰድ • ማስማጥን ማስወገድ - ሠገራን ለማስወጣት በምናምጥ ጊዜ በደም ስሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊትን ስለምንፈጥር ለሄሞሮይድ/ለኪንታሮት/ ተጋላጭንት ይጨምራል፡፡ • ሠገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያልፉ ወደ መፀዳጃ ቤት በመሄድ ያስወግዱ፡፡ አለዚያ ሠገራዎ ስለሚደርቅ ለማስወገድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘውትሩ - የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ እንድንሆን ያደርጋል፣ • ለረጅም ሰዓታት መቀመጥን ያስወግዱ፡፡ በተለይም በመፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ለሄሞሮይድ መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ @DrSofonias

በሰውነትዎ የአሲድ መጠን የመኖር ምልክትና ህክምናዎቹ ምልክቶች 👉 በቂ እንቅልፍ ቢያገኙም እንኳ የደከሙ እንደሆኑ ይሰማዎታል 👉 ጭንቀት ይሰማዎታል ወይም ቀደም ሲል በነሩትን ነገሮች ለመደሰት ይቸገራሉ ፡፡ 👉 ያለምክንያት በእራስዎን ያበሳጫሉ 👉 ብዙ ጊዜ ትኩረት ማድረግ ችግር ወይም “የአንጎል ጭጋግነት” ይገጥምዎታል 👉 ኢንፌክሽኖችን ፣ ጉንፋንን እና ፍሳሾችን ዘወትር ያዳብራሉ ጭጋግነት 👉 ሞቃታማ በሆኑት ወራትም እንኳ ቆዳዎ ደረቅ ነው 👉 የቆዳ ህመም ወይም ሌሎች የቆዳ ችግሮች አለብዎት 👉 የሆርሞን አለመመጣጠን ጉዳዮች አሉዎት 👉 ብዙውን ጊዜ የእርሾ /Yeast ኢንፌክሽኖችን ያዳብራሉ 👉 የምግብ መፈጨትዎ እንደዘገየ ወይም በተደጋጋሚ የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ የመሰለ ስሜት ይሰማዎታል 👉 ብዙውን ጊዜ የትንፋሽ እጥረት ያድርብዎታል 👉 ብዙውን ጊዜ መገጣጠሚያ ህመም ይሰማዎታል 👉 ብዙውን ጊዜ ራስ ምታት ያጋጥሙዎታል 👉 ሥር የሰደደ አለርጂ ወይም የ sinus ህመም ይሰማዎታል 👉 በደረሰበት ጉዳት/Injury ወይም በሕክምና ሁኔታ ምክንያት በማይሆን ሥር የሰደደ ህመም ይሰቃያሉ 👉 አንገትዎ ብዙውን ጊዜ የግትርነት ስሜት ወይም ህመም ይሰማዋል 👉 ስሜታዊ የድድ እና የጥርስ ህመም ይኖራል 👉 በዚህ ዝርዝር ውስጥ ብዙ ምልክቶችን እያዩ እንደሆነ ካዩ ፒኤችዎን ለመመርመር ጊዜው አሁን ነው መፍትሄው -የውሃ ሕክምና 👉 ስለ የውሃ ሕክምና ሰምተው ያውቃሉ እና ጥቅሞች አሉት? አንዳንድ ጥቅሞች እዚህ አሉ ከፍተኛ የደም ግፊት - 30 ቀናት የጨጓራ ቅባት - 10 ቀናት የስኳር በሽታ - 30 ቀናት የሆድ ድርቀት - 10 ቀናት ካንሰር - 180 ቀናት ቲቢ - 90 ቀናት ወዘተ ... የሕክምና ዘዴ 👉 ጥርሶችን ከመቦረሽ በፊት ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ስትነቁ 4 x 160ml ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ 👉 አፍን ብሩሽ ያድርጉ እና ያፅዱ ነገር ግን ምንም ነገር አይበሉ ወይም አይጠጡ ለ 45 ደቂቃዎች ፡፡ 👉 ከ 45 ደቂቃዎች በኋላ መብላትና መጠጣት ትችላላችሁ 👉 ከቁርስ ፣ ምሳ እና እራት ከ 15 ደቂቃዎች በኋላ፦ ለ 2 ሰዓታት ምንም ነገር አይበሉም ወይም አይጠጡ መሰረታዊ ፕሮቶኮል በባለሙያዎች መሠረታዊው የፕሮቶኮሉ ምክር እንደሚከተለው ነው- 1. ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ስትነሱ ከ5-6 ብርጭቆዎች ውሃ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ 1.50 ሊትር ውሃ ይጠጡ 2. ውሃውን ከመጠጡ በፊት እና በኋላ ለ 1 ሰዓት ያህል ሌላ ነገር አይበሉ ወይም አይጠጡ ፡ @DrSofonias

ጠቃሚ መልእክት ስለሆነ በደንብ ያንብቡት ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ #ኩላሊታችን #የቱ #ጋር #ነው,,? የኩላሊት ህመም ወይም መድከም ዛሬ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ላይ በሽታ ይስተዋላል። ብዙዎች የኩላሊት ህመምን እንደቀላል በማየት ብርድ ነው፣ጨጓራ ነው፣ ወገቤን ነው በማለት የቀኝና የግራ ኩላሊት በየት አካባቢ የሰውነት ክፍላችን እንደሚቀመጥ ለማሳየት ነው። ህመም ሲሰማን በማስታገሻ ሰውነታችንን ማለማመድ ለኩላሊት መድከም ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በተለይ አመጋገባችን ለጤንነታችን ሰፊ ድርሻ አለው ለምሳሌ ,,,የታሸጉ ምግቦች በየቀኑ ስጋና ቅባት ምግቦችን ማዘውተር። የፖልም ዘይት መጠቀም ሌላው በመኝታ ሰዓት መመገብና እንቅስቃሴ ሳናደግ መተኛት ለከፍተኛ ጉዳት ይዳርጋል። በመጠጥ ደረጃ አልኮል መጠጦችን ቅባትነት ያላቸው ውስኪ የመሳሰሉ መጠጦች ለበሽታው ተጋላጭ ያደርጋል። ጣፋጭ ለስላሳ መጠጦችም ከፍተኛ ስኳርነት ስላላቸው አይመከሩም ሁሉንም በልክና አልፎ አልፎ መጠቀሙ ይመከራል። ኩላሊት ሲጎዳ የሚታዩ 8 ምልክቶች 1. ኩላሊታችን ችግር ሲያጋጥመው የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ ትንፋሽ ሊያሳጥረን ይችላል 2. ምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም መሰማት - የኩላሊት ችግርን ተከትሎ በደም ውስጥ የንጥረ ነገሮች ይዘት ላይ ለውጥ ስለሚኖር በምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም ከመሰማት ጀምሮ እስከ ጠቅላላ የምግብ ጣዕም ለውጥ ሊኖር ይችላል፡፡ የደም ይዘት ለውጥን ተከትሎ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ችግርም ያጋጥማል፡፡ 3. የውሃ ሽንት ቀለም ለውጥ - የሽንት ከለር ለውጥ አንዱ የኩላሊት ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይም የውሃ ሽንት ከለር ጠቆር ወዳለ ብጫ ከለር በተደጋጋሚ ከተስተዋለ የኩላሊት ጉዳት ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡ 4. የትኩረት መቀነስ - የኩላሊት መጎዳት ኦክሲጅን በአግባቡ ወደ ጭንቅላት እንዳይሄድ ስለሚያደርግ የማስታወስ ችግርና የትኩረት ማጣትን ያስከትላል፡፡ 5. የሰውነት አካል እብጠት - የኩላሊት ጉዳት በሰውነታችን የሚገኙ ፈሳሾች በአግባቡ እንዳይወገዱ ስለሚያደርግ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በተለይም እግር ፣ መገጣጠሚያና ፊት ላይ እብጠት ሊከሰት ይችላል፡፡ 6. የሰውነት መዛል - የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ የሰውነት ማዛልን ጨምሮ የአዕይምሮና የጡንቻዎች ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡ 7. የቆዳ አለርጂ - የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ በሰውነታችን የመርዛማ ንጥረ ነገሮች ክምችት ስለሚጨምር የቆዳ አለርጂ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ 8. የኩላሊት አካባቢ ህመም የኩላሊት ኢንፌክሽን ኩላሊት አካባቢ ህመም እንዲሰማ ያደርጋል፡፡ ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የኩላሊት ጉዳት ችግር ሊሆን ስለሚችል ኩላሊቶን በመመርመር ሊታደጉት ይገባል ይላል የናሽናል ኪድኒ ፋውንዴሽን መረጃ በማድረግ ብዙዎችን ከጉዳት እንታደግ አሁን ልንመክርዎት የፈለግነው አንደኛ በመንግስት መስሪያ በግል፣በውትድርና፣በሆቴል፣በፋብሪካ በሱቅ፣በሹፍርና፣ በጉሊትም አጠቃላይ በማንኛውም ስፍራ የምንገኝ ሁሉ ሁል ጊዜ ውሀ መጎንጨትን አንርሳ አንዳዶች ሽንት ውሀ ከጠጣው ያስቸግረኛል በማለት እራሳቸውን ለጉላሊት በሽታ የሚያጋልጡ ቀላል አይደሉም። ከሁሉ በላይ ህመም ስሜት ሲሰማዎ ወደ ጤና ተቋም በጊዜ ይሂዱ። እናመሰግናለን። @DrSofonias

♨️ ድንገተኛ ሞትን እንከላከል ⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜⚜ በምሽት ወይም በእንቅልፍ ሰአት የሚከሰትን ድንገተኛ ሞት ለመከላከል የህክምና ባለሙያወች ምክር↩️ ከእንቅልፋችን በድንገት ተነስተን ሽንታችንን ለመሽናት ከመሄዳችን በፊት ለ ሶስት (3) እና አራት (4) ደቂቃወች ማድረግ ያለብን ጥንቃቄወች አሉ! አንዳንዴ ሰወች ጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እና ቁመና ላይ ሁነው በድንገት ምሽት ላይ ህይወታቸው ያልፋል። ከዚህ ጋ ተያይዞ አንዳንድ ሰወች ትናንት እኮ አውርቸው ነበር እንዴት በድንገት ሞተ? ሲሉ ይደመጣሉ። 🔴ነገሩ እንዲህ ነው በድንገት ከእንቅልፋችን ተነስተን ወደ ሽንት ቤት በምንሄድበት ጊዜ አእምሮአችን የደም ዝውውር ላይኖረው ይችላል። ስለዚህ ሶስት(3) እና አራት (4) የሆኑ ደቂቃወች እንዴት ወሳኝ ሊሆኑ ቻሉ? በእኩለ ሌሊት ከእንቅልፋችን ተነስተን ሽንታችንን ለመሽናት በድንገት ወደ ሽንት ቤት በምንሄድበት ጊዜ የልብ ምታችን የደም ዝውውራችን ጋ በተያያዘ እክል ይገጥመዋል። በድንገት በምንነሳበት ጊዜ አእምሮአችን እና ልባችን በሚያጋጥመው የደም እጥረት ስራውን መስራት ሊያቆም ይችላል። ከዚህም ጋ በተያያዘ በተነሳንት ባሉት 3 እና 4 ደቂቃወች የሚመከሩ እና ማድረግ ያለብን ጉዳዮች 1.እንደነቃን ለ 1 ደቂቃ እና 1 ደቂቃ ከግማሽ ባሉት ደቂቃወች ከአልጋችን መቆይት። 2.እሰከ ቀጠዮ ሁለት ደቂቃ አልጋው ላይ መቀመጥ 3.እግራችንን ከአልጋው አውርደን ለ ግማሽ ደቂቃ ያክል አልጋው ጠርዝ ላይ መቀመጥ ከ ሶስት(3) እና ግማሽ ደቂቃ በኃላ አእምሯችን እና ልባችን በደም እጥረት የመጠቃት እድሉ አነስተኛ ስለሆነ በድንገት የመሞት አጋጣሚን መቀነስ ይቻላል!!! 🔊 ይህ ችግር ምንም እድሜ የማይገድበው ስለሆነ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የተሻለ ግንዛቤን እንፍጠር #Share

ቅጥ ላጣ ውፍረት የሚዳርጉ ልማዶች በሰውነታችን ውስጥ ስብ እንዲከማች ከሚያደርጉ እና ቅጥ ላጣ ውፍረት ከሚዳርጉን ምክንያቶች መካከል ዋንኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. የአመጋገብ ባህላችን፣ አብዛኛዎቻችን የምግብ ምርጫችን ወደ እንስሣት ተዋፅኦና ጣፋጭ ምግቦች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ሥጋ፣ እንቁላል፣ ቅቤና ወተት በምግባችን ውስጥ ካላካተትን የጋበዝንም የተጋበዝንም የማይመስለንና ለምግብ መመገቢያ የተወሰነ ሰዓትና ጊዜ የሌለን ከመሆኑም በተጨማሪ ምግብን የምንመገበው ስለተራብን ብቻ ሣይሆን ስለአገኘንም መሆኑ ሠውነታችን ከሚያስፈልገው የሃይል ምንጭ በላይ ምግብ እንዲወሰድና ከአስፈላጊው በላይ የሆነው በስብ መልክ እንዲከማች ምክንያት ይሆነዋል፡፡ 2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አለማድረግ ፣ ወደ ሰውነታችን ውስጥ የገባና ከአስፈላጊ በላይ የሆነው ምግብ በተለያዩ መንገዶች መቃጠልና ከሰውነታችን ውስጥ መወገድ ይኖርበታል፡፡ ያለበለዚያ ግን በስብ መልክ ያከማቻል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ አካላዊ ብቃት እንቅስቃሴ ስንልም በተደራጀ መልኩ በጄምናዚየምና መሰል ሥፍራዎች ላይ ብቻ የሚደረገውን ሳይሆን ሰው በዕለት ተዕለት ተግባሩ ራሱን በማንቀሳቀስ፣ የእግር ጉዞ በማድረግ እና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ምግቡ እንዲቃጠል ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በእርግጥ ያለንበት ዘመን ቴክኖሎጂው የተስፋፋበት መንገድን በመኪና ደረጃና በሊፍት የምናሳጥርበት ሁኔታ የተመቻቸበት ቢሆንም ማንኛውም ሰው በተለይ ደግሞ የውፍረት ችግር ያለበት ሰው ራሱን በእነዚህ ነገሮች ውስጥ በማንቀሳቀስ ደረጃዎችን በእግሩ በመውጣት፣ በአንቀሳቃሽ የቢሮ ሥራዎች ውስጥ በመሳተፍ ራሱን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሊያግዝ ይችላል፡፡ 3. በዘር የሚከሰት የውፍረት ችግር፣ የውፍረት ችግር በዘር የመተላለፍ ዕድል አለው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለከፍተኛ ክብደት የሚያጋልጡ የዘር ዝንፈቶች አሉባቸው፡፡ ይህ የዘር ዝንፈትም ሰውነት ምግብን ለሃይል ምንጭነት በማዋል ከማቃጠል ይልቅ እንዲከማችና ስብ እንዲፈጥር በማድረግ ውፍረትን ያባብሳል፡፡ መልካም ጤንነት

ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የረመዳን ጾም ይመኛል። እንኳን ለታላቁ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም የረመዳን
ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የረመዳን ጾም ይመኛል። እንኳን ለታላቁ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም የረመዳን ጾም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ረመዳን ከሪም!! Ramadan Kareem!!

ለመዳን መፍትሄው እና ማድረግ ያለብን ወሳኝ ነገሮች የጨጎራ ቁስለት/ህመም ምንድን ነው??? ~~\\~~~~ የጨጎራችን የላይኛው ሽፋን በተለያዩ ምክንያቶች መላጥ ፤መጎዳትና መቁሰል ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡ ~ ለጨጎራ ቁስለት/ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድን ናቸው??? ___ 1. የዛባ የእመጋግብ ስርአት 2. ለጨጎራ ጸር የሆኑ መድሀኒቶች NSAID,TB መድኃኒቶች…. 3. የጨጎራ ባክቴርያ በጨጎራችን ውስጥ መኖር 4. የሚያቃጥሉና የሚለበልቡ ምግቦች ማዘውተር 5. እርግዝና ~ የጨጓራ ቁስለት(ህመም)ምልክቶች _____ 1.ደረት መሀል ይም ጡትና ጡት መሀል የሚኖር፣የሚያቃጥል እና ምቾት የሚያሳጣ ህመም 2.ግሳት እና ማስታወክ 3.ሆድ መንፋትና ቃር 4.ጀርባ፣እግርና ሰውነትን የሚያቃጥል ስሜት መኖር 5.ምግብ ሲበሉ ወይም ሳይበሉ ሲቀሩ የሚኖር የደረት ህመም ~ የጨጔራ ህመም ምርመራዎች ምንድን ናቸው? ___ 1. የጨጔራ ህመም እንዳለብን ከጠረጠረ መጀመርያ የሚደረገው የባክቴርያ (H.pylory) ምርመራ ነው፡፡በደም ወይም በሰገራ የሚደረግ ምርመራ ሲሆን ውጤቱም +ve (አለ) ወይም _ve (የለም) በመባል ይገለጻል፡፡ 2. UBT(uria breath test) የትንፋሽ የጨጔራ ባክቴርያ ምርመራ ነው፡፡ 3. ENDOSCOPY ይሄ ምርመራ በአፍ በሚገባ ትቦ (ማሽን)አማካኝነት የጨጔራ ቁስለትን ወይም የጨጔራችንን የተጎዳ ክፍል በኮንፒተራይዝድ መሳሪያ የምናይ ሲሆን ህመሙ ለተደጋገመባቸውና በቀላሉ ሊድኑ ላልቻሉ የጨጔራ ህመምተኞች እንጠቀማለን፡፡ 4. syndromic approach ይህንን ዘዴ የምንጠቀመው የላብራቶሪ ምርመራዎች በሌሉበት ቦታና አንዳንዴም ጨጔራ ህመም አለ ብለን እርግጠኛ በሆንንበት ሰአት ነው፡፡ የጨጔራ መድሀኒቶች ጥቅም ምንድን ነው 1. የጨጔራ አሲድን ማቅጠን የበዛ የጨጔራ አሲድ በሚኖርበት ሰአት ጨጔራችን ራሱ በዚህ አሲድ ሊጎዳ ስለሚችል እነዚህ መድሀኒቶች ወደ ጨጔራ በመሄድ አሲዱን አቅጥነው ደረት አካባቢ የሚኖረውን ህመም ይቀንሳሉ፡፡ 2. የጨጔራ ግርግዳን በማከም ህመሙን መቀነስ 3. የጨጔራ ባክቴሪያ መድሀኒቶች በቁጥር 3 አይነቶች ሲሆኑ ባክቴሪያውን ለመግደል ብሎም ቁስለቱን ለማከም ተብለው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ -መድሀኒቶ በታዘዘልን ሁኔታና ሰአት በትክክል ካልወሰድናቸው እንዲሁም ከዛ በኋላ የአመጋግብ ስርአታችንን ካላስተካከልን የመደጋገምና ወድያው ለተመሳሳይ ህመም ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ የጨጓራዪን ጤንነት እንዴት ልጠብቅ??? ለልብሳችን እና ለመልካችን እንደምንጨነቀው ሁሉ ልጨጎራችንም ጤንነት ከምንም በላይ መጨነቅ አለብን፡፡ይህም 1. ጭንቀትን ማስወገድ 2. አመጋገባችንን ማስተካከል 3. የሚያቃጥሉ ምግቦች እና መጠጦች አለመጠቀም 4. አልኮልና ሲጋራ ማስወገድ 5. ፈሳሸ በብዛት መውስድ 6. በሃኪም የሚታዘዙልንን መድሃኒቶች ጨጎራን በማይነኩ መድሃኒቶች ማስቀየር 7. የተደጋግመ የጨጎራ ሕመም ካለብዎ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ የጨጎራ ባክቴሪያ ህክምናዎችን መውሰድ የዶክተር አለ መልእክት -“ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” የሚባለውን ብሂል ሁላችንንም ለማስተማር የታለመ ነው፡፡የጨጎራ ሕመም ከቀላል መድሃኒቶች እስከ ከባዱ ቀዶ ጥገና ድረስ ሊያደርሱ የሚችሉ የጤና መዘዞች አሉት፡፡ -በጤናችን ላይ የምናስተውላቸውን ማንኛዎችንም ለውጦች ችላ ብለን ያለፍናቸው ነገሮች ሁሉ ጤናችንን አውከው አልጋ ላይም ሊያስቀረን ትችላለች፡፡ ስለዚህም በምግብ እና በአኖኖር ዘይቤ ለውጥ ምናስተካክለውን ጨጎራ ህመም ችላ ብለን ታላቅ የጤና ቀውስ አንዲያመጣብን አንፍቀድለት፡፡ ~~ በመጨረሻም ምክር ∆∆∆∆∆∆∆\\∆∆∆∆∆ የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ወይም ህክምና የሚሆነው በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ #ጨጓራን በቤት ውስጥ እንዴት ልንከላከለው ወይም ልናክመው እንችላለን? -------- √ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ። √ከመጠን ያለፈ አልኮል አይጠጡ። √ካፌይን ያላቸው መጠጦችን አይጠጡ ለምሳሌ ቡና፣ ሻይ። √ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቆዎችን አይጠጡ ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ √ከፍተኛ የቅባት/ፋት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አይመገቡ፡፡ √በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች. ፓይሎሪ የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ ናቸው ከነዚህ ምግቦች መካከል፦ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጐመን፣ የምግብ ማጣፈጫ ተክል፣ ጦስኝ፣ ሽምብራ እና አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡ @DrSofonias

ለእርሶ ጠቃሚ መረጃ - ሆድ መነፋት - የጥጋብ ስሜት - ማቅለሽለሽ - ማስታወክ - የድካም ስሜት - እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ትንፋሽ ማጠር - ጥቁር የሚያጣብቅ ሰገራ - በሰገራ ውስጥ ጥቁር ቀይ ወይም
ለእርሶ ጠቃሚ መረጃ - ሆድ መነፋት - የጥጋብ ስሜት - ማቅለሽለሽ - ማስታወክ - የድካም ስሜት - እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ትንፋሽ ማጠር - ጥቁር የሚያጣብቅ ሰገራ - በሰገራ ውስጥ ጥቁር ቀይ ወይም ወይን ጠጅ ቀለም መታየት - ደም ወይም ጠቆር ያለ ነገር የሚታይበት ትውከት - ራስን መሳት - በሆዳችን የላይኛው ክፍል የህመም ስሜት ከእነዚህ ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ወይም ሁሉም ካሉ "Peptic Ulcer" የጨጓራ ወይንም የአንጀት ቁስለት ምልክቶች ናቸው። ቀድመን በመታከም ራሳችንን እንጠብቅ።

የማንኮራፋት መንስኤዎችና መፍትሄዎቹ ማንኮራፋት የምንለው በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት በሚመጣ ድምፅ ነው። ማንኮራፋት አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ► ለማንኮራፋት ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች የሰውንት ክብደት መጨመር:- በተፈጥሮ የሚኖር ጠባብ መተንፈሻ አየር የምናስገባበት አካል መጥበብ የምንስበው አየር ግፊት እንዲጨምር በማድረግ ድምፅን ይፈጥራል አልኮል መጠጥ ማብዛት፡- የአልኮል መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎችን በማፍታታት አየር በሚገባበት ወቅት ርግብግቢት በመፍጠር ድምፅ እንዲጨመር ያደርጋል በአፍንጫ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች፡- በአፍንጫ ላይ የሚኖሩ ተፈጥሮአዊ የአቀማመጥ ችግሮች የማንኮራፋት ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ ► ማናኮራፋት የሚያስከትላቸው ችግሮች ቀን ቀን የእንቅልፍ ስሜት መሰማት ብስጭትና ንዴት ለነገሮች ትኩረት ማጣት ለደም ግፊትና ለልብ ሕመም ማጋለጥ በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለሰው ሠራሽ አደጋዎች መጋለጥ የትዳር አጋርን እንቅልፍ ማሳጣት ናቸው፡፡ ► የሚያንኮራፉ ሰዎች ✔ በእንቅልፍ ጊዜ የሚረብሽ ድምፅ ያሰማሉ ✔ የቀን እንቅልፍ ሊያስቸግራቸው ይችላል ✔ የጉሮሮ መከርከር ይኖርባቸዋል ✔ ሰላም የሌለው እንቅልፍ ያስቸግራቸዋል ✔ በእንቅለፍ ጊዜ ትንታ እና ትንፋሽ ማጠር ያጠቃቸዋል የደረት መጨምደድና የደም ግፊት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ► ማንኮራፋትን የምንከላከልባቸው መንገዶች ✔ አስተኛኘትዎን ያስተካክሉ በጀርባዎ መተኛት ምክንያት እና ለስላሳ ላንቃዎን ወደ ጉሮሮ እንዲወርዱ ስለሚያደርግ በእንቅልፍ ጊዜ የመርገብገብ ድምፅን እንዳናሰማ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በጎን መተኛት መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡ ✔ የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ የሰውነት ክብደት የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ ያንኮራፋሉ፡፡ ነገር ግን ማንኮራፋቱ የመጣው የሰውንት ክብደት ከጨመረ በኋላ ከሆነ መንስዔው ሊሆን ስለሚችል ክብደትዎን ይቀንሱ፡፡ ✔ የአልኮል መጠጥ አይውሰዱ የአልኮል መጠጥ የምንወስድ ከሆነ በጉሮሮ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችን ስለምናፍታታ ማንኮራፋት እንጀምራለን፡፡ ከመተኛታችን በፊት ባለው ከ4 – 5 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አልኮል መጠጥን መውሰድ ማናኮራፋትን ያባብሳል፡፡ ✔ የእንቅልፍ ሰዓትዎን ያስተካክሉ ለረጅም ሰዓታት ያለዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ በኋላ የሚተኙ ከሆነ የጉሮሮ ጡንቻዎች ባጣም ስለሚፈታቱ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ✔ አፍንጫዎን ከመደፈን ይከላከሉ አፍንጫዎ በቅዝቃዜም ሆነ በአለርጂ ምክንያት ከተደፈነ የማንኮራፋት ዕድልን ሰለሚጨምር ከመተኛትዎ በፊት በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ በተጨማሪ ውሃ በጨው በማድረግ አፍንጫን ማፅዳት፡፡ ይህ የአፍንጫን ቀዳዳዎች ስለሚከፍት ማንኮራፋትን ይከላከላል፡፡ ✔ ትራሰዎን የቀይሩ በትራስዎ ውስጥ በዓይን የማይታዩ ብናኞች ተከማችተው ሊገኙ ስለሚችሉ መቀየር ተገቢ ነው፡፡ ✔ ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ ፈሳሽን በብዛት መውሰድ ከአፍንጫችን የሚመነጨውን ፈሳሽ ሰለሚያቀጥን ማነኮራፋት እንዳይኖር ይረዳል፡፡

ስለሚጥል በሽታ ምንነት መንስኤና የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው ስናገኝ ማድረግ ስላለብን የመጀመሪያ እርዳታ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? ካላወቁ ግን እንሆ አሁን ልንገርዎ፡፡ #የሚጥል በሽታ ምንድነው? የሚጥል በሽታ የአይምሮ ተግባርን በድንገት የሚያውክ ክስተት ሲሆን ይህ የሚከሰተው የአንጎል ኤሌትሪካዊ ንዝረት ጊዜያዊ መረበሽ ሲኖር ነው፡፡ክስተቱ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ማንቀጥቀጥና እራስ ምታት ያስከትላል፡፡ በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ ያለ ሰው በዚህ በሽታ ሊጠቃ ይችላል፡፡ መንስኤው ምንድነው? የሚጥል በሽታ መንስኤዎች ብዙ ናቸው ከተለመዱት ውስጥ ጥቂቶቹ በዘር፣ ተፈጥሮአዊ በሆነ የአይምሮ እክል፣ በጭንቅላት ላይ በሚደርስ አደጋ ወይም ኢንፌክሽን፣ ከፍተኛ በሆነ ትኩሳት ምክንያት በሚፈጠር እራስን መሳት ፣ የአንጎል እጢ ፤ በተራዘመና በአስቸጋሪ ምጥ ወቅትበፅንስ ላይ በሚያጋጥም የኦክስጅን እጥረት ፤ አልኮል መጠጦች አደንዛዥ እፆች ሀሺሽ ኮኬን . . . ወዘተ #የሚጥል በሽታ #በኢትዮጲያ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሚጥል በሽታ ይሰቃያሉ፤ 5% የሚሆኑት ብቻ ህክምና ያገኛሉ የሚጥል በሽታ በማህበረሰባችን የፈጣሪ ቁጣ ተብሎ ይወሰዳል በበሽታው የሚሰቃዩት በብዛትከ25 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ናቸው፡ #የሚጥል በሽታ በመንገዳችሁ ያጋጠመው ሰው ስታዩ የሚደረግ እርዳታ፡ 1 መጀመሪያ እርሶ ይረጋጉ 2 አካባቢን ይመልከቱ ሰውዬው / ሴትዮዋ የወደቁበትቦታ አደገኛ ነው አደገኛ ከሆነ ያርቁት 3 መንቀጥቀጥ የጀመረችበትን ሰዓት ይመዝግቡት 4 ሰውዬው / ሴትዮዋ መሬት ላይ ወድቀው ከሆነ ለስላሳ የሆነ ነገር ያንተርሷት 5 ሰውዬው / ሴትዮዋ ምንም ነገር ወደ አፏ አይክተቱ 6 ሰዓትዎን ይዩና መንቀጥቀጡ ከ5 ደቂቃ በላይ ከቆየ አምቡላንስ ይጥሩ 7 መንቀጥቀጡ ከቆመ ቦሃላ አተነፋፈሱ በትክክል መሆኑን ያረጋግጡ 8 ሙሉ በሙሉ እራሳቸውን እስኪያቁ ከአጠገባቸው አይራቁ 9 በወደቁ ሰዓት ከተጎዱ ወዲያው ዓምቡላንስ ይጥሩ 10 ሰውዬው / ሴትዮዋ ከንፈራቸው ከጠቆረ ወዲያው ህክምና ያስፈልጋል፡ 11 በፍፁም ክብሪት ወይም ጭስ ነገር አያሽትቷቸው - #እንግዲህ በመተጋገዝ እናምናለንና በመንገዳችሁ በሙሉ ይህ በሽታ ያጋጠመው ሰው ስታዩ በዚህ መንገድ ይርዱት፡፡ ማን ያውቃል እኛስ ነገ ማነን፡፡ ለማንኛውም ይህንን መልክት እናዳቀርብላችሁ ሙሉ የህክምና ማብራሪያ የሰጡኝን //ኬር ኢፒሊፕሲ ኢትዮጲያን// ከልብ እያመሰገንኩ ይህንን መልክት ለሁሉም ይዳረስና ህሙማን በአግባቡ ይረዱ ዘንድ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!! ☞ሼር☜ ሳያረጉ አይለፉ!!

የደም ቅባት ( ኮሌስትሮል) መጠንዎን ይቆጣጠሩ የደም ቅባት ወይም ኮሌስትሮል ሰም መሳይ ንጥረ ነገር (Waxy substance) ሲሆን ሰውነቶ ሕዋሳትን (ሴልን) ለመገንባት ይጠቀምበታል፡፡ ይህ ንጥረ ነገር ከተፈላጊው መጠን ሲያልፍ ግን የልብ በሽታን ጨምሮ የልብ ድካምና ስትሮክ ለተሰኙ የጤና ችግሮች መከሰት ዋነኛ ምክንያት ይሆናል፡፡ እንደ አሜሪካ የልብ ማህበር መረጃ መሰረት ኮሌስትሮል በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረው ከሁለት ምንጮች ሲሆን ጉበታችን ሰውነታችን የሚያስፈልገውን ሁሉንም ኮሌስተሮል የሚሰራ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የሚገኙት ከምንመገበው የእንስሳት ውጤቶች ከሆኑት ከሥጋ፣ከዶሮ እና ከወተት ውጤቶቸ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጠጣር ቅባት እና ትራንስ ፋትስ ያላቸው ምግቦች ጉበት ከፍተኛ ኮሌስትሮል እንዲያመነጭ በማደረግ ጤናማ ያልሆነ የኮሌስትሮል መጠን በሰውነታችን እንዲኖር ምክንያት ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በትሮፒካል የአየር ንብረት በስፋት የሚመረቱት ከዘንባባ ዛፍና ከኮኮናት የሚሰሩት ዘይቶት ከፍተኛ ጠጣር ቅባት የያዙ በመሆናቸው ጉበታችን ተጨማሪ ኮሌስትሮል እንዲያመርት የሚያነሳሱ ናቸው፡፡ ኮሌስትሮል በደማችን ውስጥ ይሰራጫል፡፡ የኮሌስትሮል መጠኑ በደማችን ውስጥ ሲጨምር ለጤናችን አደጋ ይፈጥራሉ፡፡ ለዚህም ነው የኮሌስትሮል መጠናችንን ለማውቅ ሰዎች የኮሌስትሮል ምርመራ እንዲያደርጉ የሚበረታቱት፡፡ በነገራችን ላይ ኮሌስትሮል ሁለት አይነት ነው፡፡ LDL የሚባለው ኮሌስትሮል መጥፎ የሚባለው ሲሆን HDL የኮሌስትሮል አይነት ደግሞ ጥሩ የሚባለው ነው፡፡ መጥፎ የሚባለው ከፍተኛ ሲሆንና ጥሩ የሚባለው አነስተኛ ሲሆን ለልብና ለአንጎል ደም የሚቀዱ ቧንቧዎች የውስጠኛ ክፍላቸው በኮሌስትሮል እንዲሞላ በማድረግ ከፍተኛ የጤና ችግር ይፈጥራል፡፡ ሕክምና ለጥቂቶች የሕይወት ዘይቤ ለውጥ፣ጤናማ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የኮሌስትሮል መጠንን ለማስተካከል ወይም ለመከላከል ሊረዳቸው ይችላል፡፡ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ግን የግድ ሕክምና ያስፈልገዋል፡፡ 1. የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ለብዙ ታካሚዎች የሚታዘዘው ስታቲንስ (Statins) ተሰኘው መድኃኒት አንዱ ነው፡፡ 2. ከአንጀት ውስጥ ኮሌስትሮልን መምጠጥ፡-ለዚህ ሕክምና Ezetimibe መድኃኒት ተመራጭ ነው፡፡ 3. Resins የተሰኘው መድኃኒት ደግሞ ጉበቶ ብዙ አሞት በማምረት ብዙ ኮሌስትሮ እንዲጠቀም በማድረግ የኮሌስትሮል መጨመርን ያስወግዳል፡፡ 4. Fibrates ( Fibric acid derivativies) ጥሩ የተባለውን HDL የኮሌስትሮል አይነት ይጨምራል፡፡ 5. Niacin ( nicotinic acid) በጉበት ያለውን የደም ቅባት መጠንን ተፅህኖ ያሳድራል፡፡ እንዴት እንከላከል 1. ጠጣር ቅባት እና ትራንስ ፋትስ ያላቸውን ምግቦች ይቀንሱ 2. ቀይ ስጋና የወተት ውጤቶችን ይቀንሱ 3. የተጠበሱ ምግቦችን ያስወግዱ 4. ምግብዎን በጤናማ ዘይት ያብስሉ 5. የፋይብር ምግብዎችን ያዘውትሩ 6. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘውትሩ 7. ሲጋራ ማጨስ ያቁሙ 8. የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ! እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share ያድርጉ ! ምስጋናችን ከልብ ነው!