ru
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Открыть в Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Канал ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 19 967 подписчиков, занимая 1 154 место в категории Медицина и 1 678 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 19 967 подписчиков.

Согласно последним данным от 26 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -547, а за последние 24 часа — -20, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 24.05%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 7.27% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 805 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 453 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 9.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 27 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Медицина.

19 967
Подписчики
-2024 часа
-1217 дней
-54730 день
Архив постов
የህክምና ስህተት ሕግ ምንድነው!! ………ህክምና ልዩ ጥንቃቄና ሙያዊ ስነ-ምግባርን የሚጠይቅ ከባድ ሙያ ነው። በሕክምና ስህተት የሚፈጠር ችግር ታማሚውን ወደሞት የሚሸኝ አሊያም ለዕድሜ ልክ የጤና ችግር የሚዳርግ በመሆኑ፤ ከዚህ ጦስ ጋር ተያይዞ የሚመጣው ማህበራዊ ቀውስ ጫን ያለ ነው። …… በተለይ በሰለጠነው ዓለም ሆስፒታሎችን ወገባቸውን ለሚገምስ ክፍያና ላልታሰበ ዕዳ የሚዳርጋቸው ከህክምና ስህተት ጋር ተያይዞ የሚፈጠር የካሳና የሞራል ክፍያ ወጪ ነው። በሀገራችን ለዘመናት እንዝላልነት በፈጠረው የሆስፒታሎችና የህክምና ባለሙያዎች ስህተት የተነሳ ቢያንስ ከቤተሰባችን አሊያም በቅርብ የምናውቀው ሰው ላይ የሞት አሊያም የአካል ጉዳት አደጋ ደርሷል። ነገር ግን ሕጉን በጥልቀት ካለማወቃችን የተነሳ ይሄን ስህተት የፈፀሙትን የህክምና አካሎች ለቅሶ ላይ ስንረግማቸው ብንሰነብት እንጂ ችሎት አቁመን እስከመጨረሻው ለተበደልነው በደል የህግ ፍርድን እና ካሣን ስንጠይቅ አንታይም። በቅርቡ የምናስታውስው እጅግ አሳፋሪ የህክምና ስህተት ተፈፅሞ የበርካቶች መነጋገሪያ የነበረው ዘውዲቱ ሆስፒታል ለዚህ ስር የሰደደ የዘመናት ችግር ማሳያ ነው ማለት ይቻላል። ለማመን ያስቸገረው የህክምና ስህተት የፈፀመው የዘውዲቱ ሆስፒታል………እንቅርቷን በቀዶ-ጥገና ለማስወጣት የሁለት አመት ቀጠሮ በተሰጣት " ሰላም-ደሞዜ" እና የሀሞት ጠጠሯን በቀዶ-ጥገና ለማስወገድ የህክምና ቀጠሮ በያዘችው " ሰላም-ሃጎስ" ላይ ላም ባልዋለበት አይነት ፋውሎች ነበር የሰራባቸው!!……… ………ጉሮሮዋ ላይ ከእንቅርት ጋር የተያያዘ የጤና ችግር ያጋጠማት "ሰላም-ደሞዜ" በዘውዲቱ ሆስፒታል ተከታታይ ህክምና ስታደርግ ቆይታ ከሁለት አመት በፊት በተሰጣት ቀጠሮ መሰረት በስፍራው ትደርሳለች። ሌላኛዋ ታካሚ "ሰላም-ሃጎስ" ደግሞ የሃሞት ጠጠሯን ለማስወጣት በቀጠሮዋ መሰረት በሆስፒታሉ 112 ቁጥር 1ኛ ፎቅ ላይ ሰላም-ደሞዜ ካለችበት ክፍል አልጋ ይሰጣታል። ማክሰኞ ሚያዚያ 11 2008 ዓ.ም እኩለ ለሊት ላይ የነርሶች-ቡድን በክፍሉ በመግባት ሰላም-ደሞዜን ወደ ቀዶ-ጥገና ክፍል በመውሰድ ቀዶ ጥገናውን ያደረጉላት ሲሆን፤ አስቂኙና አስገራሚው ነገር ያመማትን እንቅርት ትተው የሌለባትን የሀሞት ጠጠር ፍለጋ ሆዷን መቅደዳቸው ነበር። ከማደንዘዣው ነቅታ ሁኔታውን የተመለከተችውና በተፈጠረው ሁኔታ ግራ የተጋባችው……"ሰላም-ደሞዜ"……"የመጣሁት አንገቴ ላይ ያለውን እንቅርት ለማስወገድ እንጅ፤ የሀሞት ጠጠር በሚል ሰበብ እንዴት ጤናማ አካሌን ትተረትራላችሁ!?" ብላ ብትጠይቅም በተለመደ ማመናጨቅ " አፍሽን አትክፈቺ የሃሞት ጠጠር ህክምናው በነፃ ነው የተሰጠሽ!" በሚል ጉዳዩን ከህክምና ስህተት ሳይሆን ከሂሣብ ደረሰኝ ውጪ የተካሄደ የበጎ አድራጎት ውለታ ጋር አያይዘው ነበር ምላሽ የሰጧት!!! ………በዚህ ስህተት ቢበቃቸው ደግ ነበር!!……ግን ባለሃሞት ጠጠሯን ታማሚ "ሰላም-ሃጎስን" በፊና ወስደው ደግሞ አንገቷን ቀደው የሌለውን እንቅርት ሲፈልጉ አነጉ………እንዲህ አይነት በስመ-ሞክሼ ተለዋውጦ የተደረገ የቀዶ ጥገና ስህተትና የዘቀጠ የህክምና ብልሹነት እንኳን በዚህ ዘመን ይቅርና በ10ኛው ክፍለ-ዘመን ይደረጋል ብሎ ማሰብ ቢከብድም ይሄን አሳፋሪ ታሪክ ግን ሀገራችን በህክምና ተቋሟ አከናውናው አልፋለች። ፡………በየሆስፒታሉ ያለው ጉድ ተነግሮ አያልቅም!! የተገረዘ ሕፃንን የሬሳ ማድረቂያ ፎርማሊን በቁሙ ወግቶ ስጋና ደሙን እንጨት ከማድረግ በላይ ቅሌትና እንዝላልነት ምን አለ? በቅርቡ አንጀቴ ቅቤ የጠጣው በየካቲት 12 ሆስፒታል ላይ የተፈረደው የአንድ ሕፃን ኢትዮጵያዊ የህክምና ካሳ ትክክለኛ ፍትህ የተንፀባረቀበት የፍርድ-ቤት ውሣኔ ነበር። በዚህ ህፃን የተፈፀመውን የህክምና ስህተት እና እንዝላል የሙያ ግድፈትን ቤተሰቦቹ እንደሌሎች ተራግመው ከመግባት ይልቅ ሆስፒታሉን በህግ መድረክ እስከመጨረሻው ተፋለሙት!!………እናም 3,6 ሚሊየን ብር ገደማ የካሳ ክፍያ የካቲት 12 "ከየትም አምጥተህ ክፈል!" ተብሎ የችሎት መዶሻ ተደበደበበት!……ለደደብ የሚገባው ይሄው ነው። ህፃኑን በዚህ ካሳ ወደጤና ይዞታው መመለስ ባይቻል እንኳን "ጠያቂ የለብንም" ብለው ለዘመናት ለተግማሙ የጤና ተቋማቶቻችን ከጀዘቡበት የእንዝላል እንቅልፍ ማንቂያ ደውል ነው። ………"ምን እፈጥራለው?" ብሎ በተስፋ-ቢስ ስሜት ኮስሶ እና ፀፀት ተሸክሞ ወደቤት ከመግባት ሕግ መኖሩን አውቆ እስከመጨረሻው መብትን ይዞ መጋፈጥ ውጤት እንዳለው የካቲት 12 ሆስፒታል የተቀጡ እጆች ሸጋ ማስተማሪያ ናቸው!!………ሰሞኑን በተደጋጋሚ በዚያ በኩል ስመላለስ የሆስፒታሉ የአደጋ ጊዜ ዋንኛው በር ተዘግቶ ነው የማየው………ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሆን!? ……… ለመሆኑ "የሕክምና ስህተት ሕግ ምን ማለት ነው!?" የሚለውን አያይዘን ብንመለከት ወደፊት አልቅሰን ከመግባትና በሹክሹክታ ተራግመን ከመቅረት ይታደገናልና ለግንዛቤ ሕጉ የሚለውን ብንመለከት አይከፋም። ፡……… የሕክምና ስህተት ሕግ (Medical malpractice Law) ዶክተሮች ወይም ሌላ የሕክምና አገልግሎት ሰጪ አካላት፤ የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በታማሚው ላይ በቸልተኝነት ለሚያደርሱት ጉዳት ያለባቸውን ተጠያቂነት የገዛ ሕግ ነው። ይህ የሕግ ዘርፍ ከሀገር-ሀገር የተለያየ ይዘት ቢኖረውም፤ በአብዛኛው ሀገር ግን በሕክምና ስህተት ግለሰቦች ለሚደርስባቸው ጉዳት ጉዳቱን ያደረሰው አካል ተጠያቂ የሚሆንበት የአሠራር ሥነ-ሥርዓት አላቸው። አንድ የሕክምና ባለሙያ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ በተመሳሳይ ሌሎች የሕክምና ባለሙያዎች ሊያከብሯቸው ወይም ሊፈጽሟቸው የሚገባውን መደበኛ ጥንቃቄ (standard of care) ሊያከናውን ወይም ሊከተል ባለመቻሉ ምክንያት በታማሚው ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ የሕክምና ባለሙያው ለጥፋቱ ተጠያቂ የሚሆንበት አሰራር………"የሕክምና ስህተት ሕግ" ይባላል። ………በእርግጥ ሁሉም ስህተቶች የሕክምና ስህተት አይባሉም። አንድ ታካሚ የሚጠብቀውን የሕክምና-ውጤት አላገኘሁም በማለት የሕክምና ባለሙያን ለመክሰስ አይችልም። በአጭሩ የሙያ ስህተት የሚባለው በአንድ የሙያ ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ሊከተላቸው ወይም ሊመራባቸው የሚገባውን የሙያ ደንቦችና መመሪያዎች አውቆ ወይም በቸልተኝነት ሳያከብር መቅረት ወይም የሙያ ደንቦችን ባለማክበሩ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ እንደሆነ የፍትሐ-ብሔር ሕግ ቁጥር 2031 እና 2035 ይደነግጋል። …………የሕክምና ስህተት አለ ብሎ ክስ ለመመስረት የአካሚና ታካሚ ግንኙነት መኖሩ ግድ የሚል ሲሆን በሕክምና ባለሙያና በታካሚ መካከል ለሚኖረው ግንኙነት መሠረቱ የሕክምና አገልግሎት ውል ነው። ታካሚው ከሕክምና ባለሙያው ወይም ከሕክምና ተቋሙ ጋር የሚኖረው የሕክምና ግንኙነት የሚመሰረተው በውል እንደሚሆን የፍትሐ-ብሔር ሕግ ከቁጥር 2639-2652 ያስረዳል። በአንድ የመዝናኛ ሥፍራ አንድ ዶክተር በሰጣችሁ መድሃኒት ምክንያት ጉዳት ደርሶብኛል ለማለት አይቻልም። በሕክምና ተቋሙ ካርድ አውጥተው የሕክምና ባለሙያውን አግኝታችሁት ከሆነ ግን የአካሚ-ታካሚ ሕጋዊ ግንኙነት እንዳለ ማስረጃ ይሆናል። በአጭሩ ምንድ ነው ማናችሁም በሆስፒታል በተፈፀመ የእንዝላልነት ምግባር ለደረሰባችሁ ጉዳት በሕግ የመጠየቅ መብት አላችሁ………በየቤቱ ተራግሞ መቀመጥ ውጤት የለውም። @DrSofonias

ጠቃሚ መልእክት የአዮዲን እጥረት ለሰውነት የተወሰነ የአዮዲን መጠን ለሀይልና እድገት እንዲሁም አስፈላጊ የሰውነት ስራዎች እንዲሰሩ ታይሮይድ ሆርሞን ለማምረት አስፈላጊ ነው፡፡ አነስተኛ የአዮዲን መጠን ታይሮይድ ስራው በመዳከሙ ብቻ የሚመጣ አይደለም፤ የአዮዲን እጥረት ታይሮይድ ግላንድ ከጤነኛው እንዲያድግ ደርጋል፤ ይህም ጎይተር እና ሌሎች የታይሮይድ ችግሮች ያጋልጣል፡፡ ሰውነት በተፈጥሮ አዮዲን አያመርትም፤ ለዚህም እነኚህን ንጥረ ነገሮች ለማግኘት ብቸኛው መንገድ ከምግብዎ ነው፡፡ አዋቂዎች በቀን እስከ 150 ማይክሮ ግራም ያስፈልጋቸዋል፡፡ ነፍሰ ጡር ሴቶችና የሚያጠቡ ሴቶች ደግሞ በቀን 200 ማይክሮ ግራም ያስፈልጋቸዋል፡፡ አዮዲን በተለያዩ ምግቦች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምግቦች ውስጥ ደግሞ በብዛት ይገኛል፡፡ እነሱም፡- አሳ እንቁላል ስጋ ዳቦ የወተት ተዋፅኦ እና አዮዲን ያለው ጨው የአዮዲን እጥረት በአለም 2 ቢሊየን የሚሆኑ ሰዎችን ያጠቃል፡፡ ሰዎች በቂ ጤናማ ምግብ ለማግኘት በሚቸገሩበት እያደጉ ባሉ ሀገራት ደግሞ የተለመደ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በቂ የተመጣጠነ ምግብ ከሌለ እና ሰውነት አዮዲንን በትክክል ካልተጠቀመ ባደጉ ሀገራት ያሉ ሰዎችንም ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ነፍሰ ጡር ሴቶች ከሌላ ሰዎች ሁሉ ተጨማሪ አዮዲን ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለዚህም በአዮዲን የበለፀጉ ምግቦችን ትኩረት ሰጥተው ካልተመገቡ ለእጥረቱ የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው፡፡ ጤናቹ ይብዛ @DrSofonias

“ሄፒታይተስ ” (Hepatitis ) ሂፐታይተስ ቢ ምንድን ነው? ሄፒታይተስ ከጉበት መቆጣት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን፥ ከኤድስና ከቲቢ የበለጠ ገዳይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ ሄፒታይተስ አይነተ ብዙ ሲሆን እንደ ሄፒታይተስ ቢ ሁሉ ሌሎችም አይነት አሉት (ሄፒታይተስ A፣ B፣ C፣ D እና E)። እንደ አጠቃላይ ሂፐታይተስ በኬሚካሎች፣ በእጾች፣ ከመጠን በላይ አልኮል በመጠጣት ወይም በቫይረስ ሊመጣ ይችላል። ሂፐታይተስ ቢ የሚመጣው በሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ ነው። የህመሙ ምልክቶች ምንድን ናቸው? ብዙ ሰዎች በሂፐታይተስ ቢ ሲያዙ መጀመሪያ ምንም ዓይነት ምልክት አያሳዩም፤ ከነዚህም መሃል አንዳንዶቹ ከብዙ ዓመታት በኋላ ጉበታቸው ይጎዳል ወይም የጉበት ካንሰር ይይዛቸዋል። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች የበሽታው “ተሸካሚዎች” የሚባሉ ሲሆን ቫይረሱንም ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ። የህመሙ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊጨምር ይችላል፦ • ቆዳና የዓይን ነጩ ክፍል ቢጫ ይሆናሉ (ጆውንዲስ በመባል ይታወቃል) • ሽንት ጥቁር ይሆናል • ፊት ይገረጣል • ድካም ይሰማል • የሆድ እቃ ህመም ይሰማል • የምግብ ፍላጎት ይቀንሳል • ማቅለሽለሽና ማስመለስ • የመጋጠሚያ (የአንጓ) ህመም አንድ ሰው ሂፐታይተስ ቢ እንዴት ሊይዘው ይችላል? የሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ በበሽታው በተያዘ ሰው ደም፣ ጉበት እና የሰውነት ፈሳሽ ውስጥ ይገኛል። ሂፐታይተስ ቢ ተሸካሚ የሆነች ሴት በእርግዝናዋ ወቅት ወይም በወሊድ ግዜ ቫይረሱ ወደ ሕፃኑ ልጅ ሊሰራጭ ይችላል። በአውስትራሊያ ውስጥ ሕፃናት በሙሉ ከተወለዱ በኋላ የሂፐታይተስ ቢ ክትባት ይሰጣቸዋል። የሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ በሚከተለው ሁኔታም ሊሰራጭ ይችላል፦ • ንጹሕ ባልሆኑ የመርፌ መውጊያ መሳሪያዎች፣ በቀዶ ሕክምና፣ ጥርስ ሲነቀል፣ ወይም በመነቀስ • የሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ ያለው የሰው ደም ሲሰጥዎት። በብዙ አገራት ለሰዎች የሚሰጥ ማንኛውም ደም (Blood transfusion) ከሂፐታይተስ ቢ ነፃ ለመሆኑ ይመረመራል። • ሂፐታይተስ ቢ ያለው ሰውን እቃዎች ለምሳሌ ምላጩንና የጥርስ ብሩሹን (ደም ያለበት ሊሆን ይችላል) በመጠቀም። • ሂፐታይተስ ቢ ካለው ሰው ጋር ያለኮንዶም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ሂፐታይተስ ቢን እንዴት ነው መመርመር የሚቻለው? • ከዚህ ቀደም የሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ ይዞዎት እንደሆነ በደም ምርመራ ለማወቅ ይቻላል። • የደም ምርመራው ቫይረሱ ከሰውነትዎ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ እንደሆነ ያሳያል። ቫይረሱ ከሰውነትዎ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተወገደ ቢሆንም የሂፐታይተስ ቢ አንታይ-ቦዲስ (በሽታ እንዳይዘን የሚዋጉ ፕሮቲኖች) በሰውነትዎ ውስጥ ይገኛሉ። • ምርመራው እስካሁን የሂፐታይተስ ቢ ተሸካሚ መሆንዎትን ካረጋገጠ ዶክተርዎ በድጋሚ እንዲመረመሩ ያዛል ወደ ስፔሻሊስት ዶክተሮች ክሊኒክ እንዲሄዱም ይጽፍልዎታል። የሂፐታይተስ ቢ በሽተኛ ከሆኑ የሚከተሉትን በማድረግ ትንሽ ሻል ሊሎት ይችላል፦ • አልኮል መጠጣት ያቁሙ • የተመጣጠነና ስብ ያልበዛበት ምግብ መመገብ • ሳያቋርጡ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ • ሲደክሞት እረፍት ማድረግ አንድ ሰው ሂፐታይተስ ቢ እንዳይዘው ምን ማድረግ ይኖርበታል? • ከአዲስ ጓደኛ ወይም የሂፐታይተስ ቢ ክትባት ካለወሰደ ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲያደርጉ ሁል ግዜ ኮንዶም ይጠቀሙ። • መርፌዎች፣ ስሪንጅ ወይም እጽ/ድራግ/ የመወጊያ መሳሪያዎችን ከሌሎች ጋር በመጋራት አይጠቀሙ። • የጥርስ ቡሩሽ ወይም ምላጭ ከሌሎች ጋር በመጋራት አይጠቀሙ። • መከላከያ ካልኖሮት የሂፐታይተስ ቢን ክትባት ይውስዱ፣ ሂፐታይተስ ቢ ካለው ሰው ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች የሂፐታይተስ ቢ ክትባትን ማግኘት ይኖርባቸዋል። • የቫይረሱ ተሸካሚ ከሆኑ እናቶች የሚወለዱ ሕፃናት፣ ከተወለዱ በኋላ ሂፐታይተስ ቢ ኢሚኖግሎፕሊን መርፌ በመወጋት ተጨማሪ መከላከያ እንዲያገኙ ይሰጣቸዋል።

ይህ ፍራፍሬ፣ አልዛሂመር የተባለውን የመርሳት በሽታ ለመዋጋት ይረዳል፡፡ እንዲሁም፣ በደም ስር (አርቴሪቲስ) ውስጥ የደምን ዝውውር የሚያውኩ ነገሮች (Plaque) እንዳይፈጠሩ ያደርጋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የአንጀት ተግባርን ያቀላጥፋል፣ ለቆዳ ምግብ የሚያቀብሉ በጣም ደቃቅ የደም ስሮች ግድግዳን ያጠነክራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኃይ ለኛ የወሲብ ስሜት ቀስቃሽ መሆኑ በስፋት እየተሞገሰ ነው፡፡ ምን ዓይነት ሁሉን አቀፍ ምግብ ነው!! 6. ቲማቲም:- የዚህ ቀላ ያሉ ፍሬዎች ጭማቂ፣ ከካንሰርና ከልብ በሽታ የሚከላከል፣ የኮሌስትሮል መጠን የሚቀንስ ላይኮፔን (Lycopen) የተባለ ፀረ - ኦክሲደንት ይዟል፡፡ ላይኮፔን፣ ከቀይ ቃሪያና ከሀባብ (watermelons) የሚገኝ ሲሆን፣ ከጥቂት ዘይት ጋር ሲወስድ፣ ከሰውነት ጋር በቀላሉ ይዋሃዳል፡፡ በአጠቃላይ፣ ለመልካም ጤና፣ በቀን ቢያንስ አንድ የተቀቀለ ቲማቲም ይብሉ፡፡ በቲማቲም ሱጐ (ሶስ) የተሠራ ፓስታ ወይም ፒዛ፣ መብላትም ተመሳሳይ ውጤት ያስገኛል፡፡ 7. ዓሳ:- እንደ ቱና፣ ሳልሞን፣ ሰርዲን፣ መክሬል፣ ሂሪንግስ፣…የመሳሰሉ ዘይታማ ዓሳዎች፣ ኦሜጋ - 3 በተባለ በጣም አስፈላጊ ስባማ (ፋቲ) አሲድ የበለፀጉ ናቸው፡፡ እነዚህ ፋቲ አሲዶች፣ ለአንጐልና ለሰውነት ዕድገት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ፋቲ አሲዶች፣ በስትሮክ፣ በልብ በሽታ፣ በአንዳንድ ካንሰሮችና አልዛሂመር በተባለ የመርሳት በሽታ የመያዝ ስጋትን እንደሚቀንሱ ተረጋግጧል፡፡ የኦሜጋ-3 እጦት፣ የደስታ ስሜትን ይቀንሳል፤ ድባቴ (ድብርት) ይፈጥራል፣ የተለያዩ የአዕምሮና የአካል ችግሮችን ያስተካክላል፡፡ ዓሳ አይወዱም? ምንም ችግር የለም፡፡ አስፈላጊውን ኦሜጋ-3 ከተለያዩ ምግቦች ማግኘት ይችላሉ፡፡ በየቀኑ flaxseeds (linseed)፣ walnuts, rapeseed oil, seaweed, spirulina, watercress, ወይም የኦሜጋ - 3 ተጨማሪ ተብሎ ከሚታዘዝ መድኃኒት ማግኘት ይቻላል፡፡ 8. ሻይ፡- በእርግጥ ሻይ ጥምን ከማርካትም በላይ በጣም የሚጥም ነው፡፡ ነገር ግን ሻይ ከምግብነትም አልፎ በሽታ የመከላከል አቅም እንዳለው በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ ሻይ ከፍተኛ ጸረ-ኦኢክሲደንት ስላለው ካንሰርና የልብ በሽታን ይከላከላል፡፡ ነገር ግን፣ ሻይ ውስጥ ወተት ወይም ይባስ ብሎ ስኳር ከተጨመረበት፣ ለጤና የሚሰጠውን ጥቅም ያጣል፡፡ ኃይለኛ የሻይ ሱሰኞች የሆኑ ሰዎች፣ በየቀኑ በእያንዳንዱ ብርጭቆ ወይም ሲኒ የሚጨምሩት በጣም ጥቂት ወተት ሲደመር፣ በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘውን ስብ ሲያክል የፀረ ኦክሲደንቱ የመከላከል አቅም ስለሚቀንስ በልብ በሽታ የመያዝ ስጋት ይጨምራል፡፡ ስለዚህ የተጠቀሰውን ጥቅም ለማግኘት ከፈለጉ ሻይ ውስጥ ምንም ሳይጨምሩ ባዶውን ይጠጡ - እንደ እንግሊዞች፡፡ 9. ሎሚ፡- ይህ የተለያዩ ከፍተኛ ጥቅሞች የያዘው ወርቃማ ፍሬ፣ እውነትም የዓለማችን የጤና ማዕከል (power house of health) ነው፡፡ ሎሚ፣ ሰውነታችን የሚፈልጋቸውን ቫይታሚኖችና ማዕድናት ይዟል፡፡ ለምሳሌ፣ የቫይታሚን ቢ እና ኢ መገኛ ነው፡፡ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ ኮፐር (መዳብ)፣ ፎስፈረስ፣ ዚንክ፣ ብረት፣ ማንጋኒዝ ይዟል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የቫይታሚን ሲ ከፍተኛ ምንጭ ነው፡፡ ሎሚ፣ ለምግብ ስልቀጣ መስመር፣ ለመተንፈሻ ሲስተም፣ ለልብና ለደም ዝውውር በጣም ጠቃሚ በሆነው ባዮፍላቮኖይድስ (bioflavonoids) የተሞላ ነው፡፡ ሎሚ፣ የቆዳና የሰውነት ህብረ ህዋሳት (ሌሎች) ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ በትኩሱ፣ በጥሬው ወይም በፈሳሽ መልክ መወሰድ አለበት፡፡ 10. ወይን፡- የወይን ፍሬዎች፣ ፀረ-ካንሰር ይዘት ባለው ባዮፍለቮኖይድስ የበለፀጉ ናቸው፡፡ እነዚህ የሐረግ ፍሬዎች፣ የካንሰር ሴሎችን ዕድገት የሚያነቃቃውን ኤንዛይም የሚገድል ረስቨራትሮል (resrveratrol) የተባለ ኬሚካል አላቸው፡፡ ኬሚካሉ የደም ስሮችን መጥበብና መደደር ይከላከላል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው የወይን ፍሬዎች በአሰርና (ፋይበር) ፕሮቲን የተሞሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ በሳምንት አምስት ጊዜ ጥቂት የወይን ፍሬዎች ይብሉ ወይም ጨምቀው ይጠጡ፡፡ የዓይን ብርሃን ስጋት አለብዎት? እንግዲያውስ ቀይ ወይን ፍሬ ይብሉ፡፡ ምክንያቱም ቀይ ወይን ከዕድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የዓይን ጡንቻ እርጅና የሚከላከኩት ካሮቴኖይድ ሊቴይንና (carotenoids lutein) ዘዛንቲን (Zeaxanthin) መገኛ መሆናቸው በጥናት ተረጋግጧል፡፡ 11. ብሮኮሊ፡- ለተደጋጋሚ ጊዜያት የተደረጉ ጥናቶች፣ ብሮኮሊን ‹አስገራሚ ምግብ› ብለውታል፡፡ ይህ የአበባ ጎመን ፍሬ የመሰለ አረንጓዴ ፍሬ ነገር ከብስቴክ በእጥፍ የበለጠ ፕሮቲን አለው፡፡ እንዲሁም በርካታ ካንስሮችን፣ አልዛሂመር የተባለውን የመርሳት በሽታና የተቀሩትን አደገኛ በሽታዎች ለመከላከል የሚረዳው ፎሊክ አሲድ መገኛ ነው፡፡ ብሮኮሊ፣ በክሮሚየምና ብረት ማዕድናት፣ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ከመሆኑም በላይ የፊንጢጣ ካንሰር እንዳይፈጠር በሚከላከል ከፍተኛ የአሰር መጠን (ፋይበር) የተሞላ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ አረንጓዴ ነገሮች ለጤናም አሰፈላጊ ስለሆኑ በሳምንት ሶስት ጊዜ ለመብላት ያቅዱ፡፡

የትኛው ፍራፍሬ ነው የደም ግፊትዎን ለመቀነስ የሚረዳዎት? ለምንድነው ሎሚ የጤና ግምጃ ቤት (ሱፐር ሃውስ) የሆነው? የኦሜጋ-3 እጥረት እንዴት ከድባቴና (ድብርት) ከአንዳንድ አካላዊ ችግሮች ጋር ይያያዛል? በየዕለቱ ከምንመገባቸው ምግቦች እነዚህን ጠቃሚ ኦሜጋ -3 ፋቲ አሲዶች ከየትኞቹ ምግቦች እናገኛለን? ለዓይንዎ ብርሃን ይጨነቃሉ? እንግዲያውስ የትኞቹ የላቁ ምግቦች (ሱፐር ፉድ) እንደሚረዱዎት ከዚህ ጽሑፍ ያገኛሉ፡፡ 1. ሰማያዊ አጋም (Blue berries):- እነዚህ በግሩም ጣዕምና መዓዛ የተሞሉ ሰማያዊ የአጋም ፍሬዎች፣ ተፈጥሮ ከፍተኛ የመድኃኒትነት ፀጋ ከቸረቻቸው ምግቦች አንዱ ናቸው፡፡ ባክቴሪያዎች፣ ወደ ሽንት መተላለፊያ ቧንቧ ገብተው በመመረዝ፣ የሽንት መተላለፊያ አካባቢ ምርቀዛ (ዩሪናሪ ትራክት ኢንፌክሽን) እንዳይፈጠር መተላለፊያውን በመዝጋት የፀረ - ባክቴሪያ (አንቲባዮቲክ) ሚና ይጫወታሉ። አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ፍሬዎች አቀዝቅዘው መብላት ይፈልጋሉ፡፡ ለምን መሰላችሁ? ቀዝቅዘው ሲበሉ፣ ተበጥብጠው እንደሚጠጡ ጣፋጭ ነገሮች (Sherbet) ጣዕም ስለሚኖራቸው ነው፡፡ እነዚህ በቫይታሚን ሲ፣ አሰርና (fiber) በብረት ማዕድናት የበለፀጉ ፍሬዎች፣ የሰውነትን ሕዋሳት (ሴሎች) በመጉዳት እርጅና የሚያፋጥኑትን ፋቲ አሲድ የተባሉት መጥፎ ኬሚካሎች፣ የጉዳት ኃይላቸው እንዲለዝብ (neutralize) በማድረግ ባላቸው ችሎታ፣ 40 ዓይነት አትክልትና ፍራፍሬ ያስከነዳሉ፡፡ ጥቅማቸው ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ለዓይን እይታም ይረዳሉ፡፡ በዚህ ይዘታቸው የተነሳ፣ ጃፓኖች፣ “የእይታ ፍሬ” (Vision fruit) በማለት ያሞካሿቸዋል። እርስዎ ምን ይጠብቃሉ? የገጠር ልጅ ከሆኑ ከብቶች ሲያግዱ ከየቁጥቋጦ ውስጥ አጋሞ ሳይበሉ እንዳልቀሩ እገምታለሁ። ስለዚህ አገር ቤት ያሉ ዘመዶችዎ እንዲያመጡልዎት ይማፀኑ፡፡ ሌላው አማራጭ በእርሻ ዘርፍ የተሠማሩ ኢንቨስተሮች አጋም አምርተው በየሱፐርማርኬቱ ቢያቀርቡ እኛም እነሱም እንጠቀማለን፡፡ 2. አቮካዶ፡- ይህ ምግብ “የተፈጥሮ ቅቤ” በመባል ነው የሚታወቀው፡፡ አቮካዶ፣ በተለያዩ ጐጂ የቅባት ዓይነቶች (የእንስሳት ቅቤ፣ ጮማ…) የተሞላና የታጨቀ (Saturated) አይደለም፡፡ አቮካዶ የያዘው ቅባት አንድ ወይም ነጠላ (Monosaturated) ነው። ስለዚህ በምግብ ሳይንቲስቶችና ባለሙያዎች ዘንድ እንደ “ጥሩ” ቅባት ነው የሚታየው፡፡ በመሆኑም በልብ በሽታ የመያዝ ስጋትን እንደሚያስቀር ይታመናል፡፡ ታይሮይድ ዕጢ ችግር እንዳይፈጠር ከመከላከሉም በላይ፣ ቆዳን ለማሻሻል በጣም ጥሩ የሆነው የቫይታሚን ኢ ከፍተኛ መገኛ ነው። አንዳንድ ጥናቶች አቮካዶ፣ የእጅ፣ የወገብ፣ የጉልበትና የእግር መገጣጠሚያዎችን በማሳበጥ ሕመም የሚፈጥረውን Rheumatoid arthritis የተባለ በሽታ ለመከላከል እንደሚረዳ አመልክተዋል፡፡ ሌላው የአቮካዶ ጥቅም ደግሞ፣ ሉቴይን (Lutein) የተባለ ኃይለኛ ፀረ - ኦክሲደንት (ኦክሲደንት፣ ኦክሲጅን ከሌላ ነገር ጋር ሲገናኝ የሚፈጠር ነገር ወይም ዝቃጭ ማለት ነው) ስላለው፣ ዓይኖችን ካተራክትስ ከተባለ በሽታ ይከላከላል፣ የደም ስሮች እንዳይደድሩ (እንዳይጠነክሩ) ያደርጋል። አቮካዶ መብላት ወይም ጭማቂውን መጠጣት ጥሩ አይደለም ታዲያ! 3. ሙዝ፡- ይህን ጽሑፍ ያነበቡ ነጋዴዎች ጥቅሙን አውቀው ዋጋ እንዳይሰቅሉብን እንጂ፣ ሙዝ፣ በጣም ጠቃሚ ምግብ ነው፡፡ ጥቅሙን፣ እኛ ብቻ ሳንሆን ዝንጀሮችም አሳምረው ያውቁታል፡፡ ሙዝ ሲበሉ ፈጥነው ጉልበት (ኃይል) ከማግኘታቸውም በላይ፣ ተወዳጁ ምግባቸው ማግኒዝየም የተባለውን ማዕድንና B6 የተባለውን ቫይታሚን ያስገኝላቸዋል፡፡ በዚህ የተነሳ በምድር ወገብ አካባቢ፣ እጅግ ጠቃሚ የምግብ ይዘት ካላቸው ፍራፍሬዎች አንዱ መሆን ችሏል፡፡ ባልበሰለ አረንጓዴ ሙዝ ውስጥ ያለው አሰር (ፋይበር) መጥፎ ኮሌስትሮልን ይቀንሳል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሙዝ መብላት ለሆድ ሕመም ይደርጋል ሲሉ ይደመጣል፡፡ እውነቱ ግን በተቃራኒው ነው፡፡ ሆድ ሲጐረብጥ፣ መፍትሔው፣ የበሰለ ሙዝ መብላት ነው። ይህ ብቻም አይደለም፡፡ ምግብ አልፈጭ ብሎት ቃር (ሄርት በርን) ሲሰማዎት ሙዝ ቢበሉ እፎይታ ያገኛሉ፡፡ ሙዝ፣ ስትሮክ በተባለ በሽታ የመያዝ ስጋትንም ይቀንሳል፡፡ የደም ግፊትን በሚቀንሰው ፖታሲየም የተባለ ማዕድንም የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ጥቅሞቹ የተነሳ ሙዝ፣ የላቀ የጤና ምግብ መባሉ የሚበዛበት አይመስለኝም፡፡ 4. ነጭሽንኩርት፡- ይህ የቅመም ምግብ ያለውን ጥቅም የማያውቅ ሰው የለም ማለት ይቻላል። “የሚሰነፍጠው ኃይለኛ ጠረኑ አስቸገረን እንጂ ጥቅሙማ መች ጠፋን?” እንደምትሉ እገምታለሁ፡፡ እንግዲህ ክረምቱ ገባ አይደል? በዚህ ወቅት ደግሞ ጉንፋኑ፣ ኢንፉሌንዛው፣ ይበረታል፡፡ መድኃኒቱ ደግሞ ነጭ ሽንኩርት ነው፡፡ ለዚህ የነጭ ሽንኩርት መጥፎ ጠረን መላ ሲያፈላልጉ የነበሩት የምግብ ሳይንቲስቶች ምስጋና ይግባቸውና ጥረትና ድካማቸው የሰመረላቸው ይመስላል፡፡ ለነጭ ሽንኩርት መጥፎ ጠረን አገኘን ያሉትን መፍትሔ፣ ባለፈው ኤፕሪል ወር በፖሉላር መጽሄት ላይ አቅርበዋል። ሳይንቲስቶች መፍትሔ ነው ያሉት ዘዴ በዚሁ ገጽ ቀርቧልና ይሞክሩት፡፡ አሁን ወደተነሳንበት የነጭ ሽንኩርት ጥቅም ትንታኔ እንመለስ፡፡ አንዳንዶች በተለምዶ በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ነጭ ሽንኩርት መልካም ዕድል ይፈጥራል፣ መጋኛ፣ ሸረኛ፣ ቡዳ፣ መተተኛ፣ ጥንቆላ፣ በሌሊት ከመቃብራቸው እየወጡ የሰው ደም ከሚመጡ የሙታን ነፍሶች (ቫምፓየር)፣ …ከመሳሰሉ እርኩስ መናፍስት ይከላከላል፣ ያርቃል፣ የሚል እምነት አላቸው፡፡ እውነቱ ግን፣ ነጭ ሽንኩርት “የቅመሞች ንጉሥ” (King of the herbs) የሚለው ቁልምጫና ቅጽል፣ የሚገባው መሆኑ ነው፡፡ ትኩስ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት፣ በጠረኑ ብቻ 20 ሳ.ሜ ርቀት ላይ ያለ ቫክቴሪያ ይገድላል፡፡ ይህ ቅመም፣ ለበሽታ መከላከያ አቅም ግንባታ፣ ለምግብ መፈጨት፣ ለነርቭ ሲስተም፣ ለመተንፈሻና ለቆሻሻ ማስወገጃ ሲስተም ይረዳል፡፡ እንዲሁም፣ ለልብ፣ ለሳንባ፣ ለፀጉርና ለዓይን ጤንነት በጣም ጥሩ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ነጭ ሽንኩርት የበሽታ መከላከያ አቅምን ከፍ የሚያደርገው፣ አሊሲን (allicen) በተባለው ፈጣን ንጥረ ቅመሙ (ingredient) አማካይነት ነው፡፡ አንዳንድ ጥናች ደግሞ ነጭ ሽንኩርትን ከሆድ ካንሰር መቀነስ ጋር አያይዘውታል፡፡ ጉንፋን ወይም ኃይለኛው የጉንፋን ወረርሽን (ፍሉ) ሲይዝ ነጭ ሽንኩርት መብላት (መጠቀም) የበሽታውን የመቆያ ጊዜ በግማሽ ይቀንሳል፡፡ ምን ይኼ ብቻ? የነጭ ሽንኩርት ጥቅም በርካታ ስለሆነ፣ ከገበታዎ እንዳይጠፋ ካደረጉ ዘየዱ ማለት ነው፡፡ ጥሬውን ቢበላ ግን ይመረጣል፡፡ 5. Pomegranates:- ይህ ፍሬው የሚበላና የላቀ የመድኃኒትነት ይዘት ያለው ምግብ፣ ከቀይ ወይንና ከአረንጓዴ ሻይ የበለጠ ከፍተኛ ፀረ - ኦክሲደንት (አንቲ ኦክሲደንት) አቅም አለው። በዚህም የተነሳ፣ ይህ ፍራፍሬ፣ የቆዳ ካንሰር እንደሚከላከል፣ የጡትና የወንድ ዘር መተላለፊያ ቧንቧ (ፕሮስቴት) የሚያጠቃውን የካንሰር ሕዋሳት (ሴሎች) እንደሚገድል በርካታ ጥናቶች አሳይተዋል።

የፅንስ መጨናገፍ (Miscarriage) የፅንስ መጨናገፍ (Miscarriage) ምንድንነው? በአለም ጤና ድርጅት ገለፃ መሰረት አንድ ፅንስ ተጨናገፈ ወይም“miscarriage” አጋጠመው የምንለው 20 ሳምንት ላይ ወይም ከ 20 ሳምንት በታች የሚከሰት የፅንስ መቋረጥ ነው፡፡ በብዛት 80% ያህል የሚሆነው የፅንስ መጨናገፍ የሚከሰትው በመጀመርያዎቹ 3 ወራት ውስጥ ነው፡፡ 25% ከሚሆኑት እርግዝናዎች በፅንስ መቋረጥ ወይም መጨናገፍ እንደሚጠናቀቁ American College of obstetrics & gynecology ባደረጉት ጥናት ይጠቁሙናል፡፡ የፅንስ መጨናገፍ በምን ምክንያት ይከሰታል ስለ ፅንስ መጨናገፍ ትክክለኛውን ምክንያት መናገር ባንችልም ዋና ዋናዎቹ ግን በዘረ መል ላይ ያለ ችግር የሆርሞን ችግር ማህፀን አካባቢ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች የማህፀን ግርግዳ ጠንካራ አለመሆን የእናት የሱስ መጋለጥ የማህፀን እጢ መኖር የእንቅርት በሽታ የአኗኗር ዘይቤ የምግብ እጥረት ማጨስ የበዛ ቡና መጠጣት ለጨረር መጋለጥ የእናትየው እድሜ የስኳር በሽታ ሲኖር የደም መርጋት ችግር ✔ የፅንስ መጨናገፍ ምልክቶች • ከእርግዝና እስከ 20ኛው ሳምንት ድረስ የሚያጋጥም ከማህፀን የሚፈስ ቡኒ/ቀይ ደም ከቁርጠት ጋር ወይም ከቁርጠት ውጪ ሲከሰት • ከመሃከለኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ • የምጥ ቁርጠት የሚመስል ከፍተኛ ቁርጠት • ስጋ የሚመስል ወይም የጓጐለ ደም በማህፀን መውጣት • ድንገት የተከሰተ የእርግዝና ምልክቶች መጥፋት • የፅንስ እንቅስቃሴ መቅረት። ✔የፅንስ መቋረጥ እንዴት እንከላከላለን • ሀይል ያላቸው እንቅስቃሴዎችን አለማድረግ • መጠጥና ሲጋራን በእርግዝና ግዜ አለመጠቀም • ጤናማ የምግብ አመጋገብን መመገብ • የአባላዘር በሽታዎችን ቀድሞ መታከም • የሚጥል በሽታ፣ የጆሮ ደግፍና የእንቅርት በሽታ መመርመር ቀድሞ መታከም • 600 mg የሚሆን “folic acid” እና ብረት ማዕድን በየቀኑ መውሰድ • የበዛ ቡናን (200 mg በላይ) አለመውሰድ • ያልፈላ ወተትና ጥሬ ስጋን አለመውሰድ • በእርግዝና ሰዓት የጨረር ሕክምና አለማድረግ • ጭንቀት ✔ተጨማሪ ምክሮች • እርግዝና እንዳለ ካሰብንና ተመርምረን ካወቅን በኋላ ለራሳችንም ሆነ ለፅንሱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል • በአጠቃላይ አመጋገባችን የተመጣጠነና ጤናን ያገናዘበ መሆን አለበት • ፅንሱ 4 ወር ሲሆነው ወደ ጤና ተቋም ሄደን አስፈላጊውን ክትትልና ምርመራ ማድረግ ይኖርብናል • በማህፀን የሚወጣ ደምን ወይም ያልተለመደ ፍሳሽ ሲያጋጥም በዝምታ ከማለፍ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት • ድንገት የፅንሱ እንቅስቃሴ መቀነስ ከመጣ ወደ ጤና ተቋም ማምራት • ተደጋጋሚ የፅንስ መቋረጥ የሚያጋጥመን ከሆነ ለሚቀጥሉትም ላይ የመከሰት እድል ሊኖረው ስለሚችል አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ መልካም ጤንነት!!

ጎሮሯችን ውስበስብነት ባላቸው ቲሹዎች፣ ነርቮች፣ እጢዎች እንዲሁም የደም ቧንቧዎች የተሞላ የሰውነታችን አካል ክፍል በመሆኑ የተለየ ጥንቃቄ ይሻል። ================================== ስለዚህም ለጉሮሯችን ጤንነት አስፈላጊ የሚባሉ የጥንቃቄ መንገዶችን እንጠቁምዎ። 1 ጎሮሯችንን ካልተስካከለ የሙቀት ወይም የቅዝቃዜ መጠን መጠበቅ ከሰውነታችን ብዙ የሙቀት መጠን በአንገታችን ይወጣል ይህንንም ለመከላከል ስካርቭ ወይም የአንገት ሹራብ የመልበስ ልማዳችንን ብናዳብር ለአንገታችን ጤንነት የሚመከር ነው። 2 የመመገቢያ ቁሳቁሶችን ከሌሎች ጋር አለመጋራት ከሌሎች ጋር የመመገቢያም ሆነ የመጠጫ ቁሳቁሶችን ፈፅሞ አለመጋራት ምክንያቱም በቀላል ንክኪ ለሚመጡ የጎሮሮ ህመሞች ሊያጋልጠን ይችላል እና። 3 የጥርስ ቡሩሻችንን በደንብ ማፅዳት ብዙዎቻችን ልብ የማንለው ችግር ሲሆን የጥርስ ቡርሻችንን ውጪ በሚቆይበት ጊዜ ብዙ ባክቴሪያዎች ሊይዝ ይችላል። በዚህም ጥርሳችን በምንፀዳበት ጊዜ ለተለያዩ በሽታዎች መፈጠር እንደ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህም የጥርስ ቡርሻችንን ከመጠቀማችን በፊት ጨውና ሙቅ ውሀ ድብልቅ ውስጥ ለተወሰኑ ደቂቃዎች አቆይተን መጠቀም ይኖርብናል። 4 በጨው መጉመጥመጥ ይህ ዘዴ ጊዜ የማይሽረው እና ለረጅም ጊዜያት የሚታወቅ እንደሆነ ይነገራል። ማታ ላይ ለብ ባለ ውሀ እና ትንሽ ጨውን በማደባለቅ ጉሮሮ ላይ ይዞ መጉመጥመጥ ለጉሮሮ ሁነኛ መድሀኒት እንደሆነ ይነገራል። በተለይም ጉንፋን፣የጉሮሮ ኢንፌክሽን እና በመሳሰሉት በምንያዝበት ጊዜያት ይህን መንገድ መጠቀም ፍቱን እንደሆነ ይመከራል። 5 የማር እና የዝንጅብል ድብልቅ ጠዋት ጥርስዎን ከቦረሹ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ሚሊ ግራም የሚሆን ዝንጅብል በመጭመቅ ከ አምስት ሚሊ ግራም ማር ጋር ደባልቆ መጠቀም ቀኑን ሙሉ ጥሩ ስሜት እየተሰማዎት ይውላሉ። 6 የድምፅ ሟሟቂያዎችን ጠዋት ላይ መለማመድ ዘፋኞች፣አክተሮች፣ዶክተሮች፣ጋዜጠኞች የመሳሰሉ ሙያዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ይህን ልምምድ በየቀኑ ማዳበር እንደሚጠበቅባቸው ይነገራል። የዚህም ምክንያት ከሌላው ማህበረሰቦች እነኚህ ሙያዎች ውስጥ ያሉ ሰዎች ጉሮሮዋቸውን አብዝተው ስለሚጠቀሙ እንደሆነ ይነገራል።

*የጆሮ ኢንፌክን*-* በደበኞችን ጥያ መሰረት ለዛሬ የጆሮ ኢንፌክሽንና ምልክቶቹን ተመለከተ ባለያዎቹ የጻፏቸን ጽሁፎችና ያዊ አስተያየቶቻቸውን ከዚህ በታች እንመልከት። የጆሮ ኢንፌክሽን በባክቴሪያ ወይንም በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ችግር ሲሆን ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት ባሉ ሕፃናት ላይም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በህመሙ ሊጠቁ ይችላሉ፡፡የጆሮ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ የላይኛውን የአየር ቧንቧ ከሚያጠቁ በሽታዎች ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡የላይኛውን የአየር ቧንቧ የሚያጠቁ በሽታዎች በሚኖሩ ጊዜ የጆሮን የመካከለኛውን ክፍል እና ጉሮሮን የሚያገናኘው ቱቦ (eustachian tube) ያብጥና አየር ወደመካከለኛው የጆሮ ክፍል እንዳይገባ ያደርጋል፡፡ ይኼም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ውስጥ ፈሳሽ እንዲጠራቀም እና ለባክቴሪያ አመቺ የመራቢያ ሁኔታን እንዲፈጥር ያደርጋል፡፡ ባክቴሪያ ከተራባ በኋላ በአካባቢው ያሉ ህዋሶችን በመግደል መግል እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ የጆሮ የኢንፌክሽን ምልክቶች • የጆሮ ሕመም • የጆሮ መደፈን ስሜት • የራስ ምታት • ከጆሮ የሚወጣ ፈሳሽ • ጆሮ ውስጥ የሚጮህ ስሜት • የመስማት ብቃት መቀነስ እና ማቆም • አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ደግሞ በእጃቸው ወደ ጆሮ አካባቢ በተደጋጋሚ ይነካካሉ • መቅለሽለሽ እና ማስመለስ • ማስቀመጥ • ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት መጠን መጨመር እናመሰግናለን @DrSofonias

"የሴት ልጅ ወላጆች ስለወር አበባ ለልጆቻቸው ምን ማስተማር አለባቸው!!? ………ሴት ሆና ለተፈጠረች ሁለ ዕድሜዋ ሲደርስ የወር አበባ ማየት የተፈጥሮ እውነታ ነው። ሴት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባዋ ከች ሲል በሕይወቷ ከሚገጥሟት ዐቢይ ክስተቶች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ይሄን ቀንና ክስተት አንዳንድ ልጃገረዶች በደስታ እና በእርካታ ስሜት ሲቀበሉት፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ሃፍረትና ድንጋጤን በቀላቀለ ስሜት ውስጥ ሆነው ይቀበሉታል። የሆነው ሆኖ ግን ይህቺ ዕለት ታዳጊዋ ሚሚ ሴት መሆኗን የሚያበስርላት የሴትነት ቀኗ ነውና የወር አበባ ሲከሰት ከድንጋጤው ስሜት ይልቅ የደስታ ስሜቱ ምክንያታዊ ነው ማለት ይቻላል። ………ሴት ልጅ የወር-አበባ የምትጀምርበት አማካኝ ዕድሜ ከ12-13 አመት ሊሆን ቢችልም፤ ከዚህ ወቅት ቀድመው ወይንም አልፈው የወር-አበባን የሚጀምሩ ልጃገረዶች ይኖራሉ። ለምሣሌ በአደጉ ሀገራት የሚኖሩ ልጃገረዶች፤ ከኑሮው የተመቻቸ መሆንና የተመጣጠነ ምግብ እንደልብ ከማግኘት ጋር ተያይዞ ገና በዘጠኝ አመታቸው የወር አበባን ሊመለክቱ ይችላሉ። ……ይህም ማለት ልጃገረዷ በዘጠኝ አመት ዕድሜዋ አካላዊ ለውጥ በማሣየት፤ የማርገዝ ብቃት ይኖራታል ማለት እንጂ፤ መደበኛ የሆነውን የወር አበባ ዑደት ታስተናግዳለች ማለት አይደለም። የሆነው ሆኖ ታዳጊ ልጃገረዶቹ የወር-አበባ የሚጀምሩበትን ሁኔታና ሌሎች ከሥነ-ተዋልዶ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳዮችን በተመለከተ ወላጆች በግልፅ ማስተማር ይኖርባቸዋል። ………ወንዶችም ሆነ ሴቶች ልጆች ከአንደኛው የሕይወት ምዕራፍ ወደሌላኛው የሕይወት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት ሁኔታና ጊዜ የቤተሰብ ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ዕድሜ ነው ማለት ይቻላል። በተለይ የወር አበባን በተመለከተ ልጃገረዶች ገና በአፍላ የኮረድነት ዕድሜያቸው ሊገነዘቡት የሚገባ የተፈጥሮ እውነታ ሲሆን፤ ይሄን ማወቃቸው ከክስተቱ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ድንጋጤን ይቀርፍላቸዋል………ወላጆችና ቤተሰቦችም ቢቻል ስለክስተቱ ተገቢ ዕውቀት ቢኖራቸው ተመራጭ ነው። ………ለመሆኑ የወር አበባ ምንድነው?……የሚለውን ስናይ በተለምዶ አጣምረን የምንጠራቸውን ministration እና period የሚሉትን ቃላት ለይተን ማወቁ ይጠቅመናል። "ማንስትሬሽን" የደም ፍሰቱን ሊገልፅ የሚችል ቃል ሲሆን፤ "ፔሬድ" ደግሞ የማንስትሬሽን ዑደቱን የሚገልፅ ቃል ነው። በዚህ መሠረትም ከላይ እንደገለፅኩት ማንስትሬሽን ከዘጠኝ አመት ጀምሮ ሊከሰት ይችላል። ይህ ወቅትም የሴት ልጅ የመራቢያ አካላት እርግዝናን ለመጀመር እና ለማስጀመር ዝግጁ መሆናቸውን የሚያበስር ነው። መደበኛውና በአማካኝ በየ28 ቀኑ የሚከሰተውና ለአምስት ቀናት ያህል የሚቆየው የደም ፍሰት ዑደት ወይም ፔሬድ ግን ከ12 እስከ 16 ባሉት አመታት ውስጥ የሚጀምር ይሆናል። ………የወር አበባ ሊጀምር በሚችልበት ወቅት ከሴቷ የተለያዩ አካላት ሆርሞኖች መመንጨት ይጀምራሉ። እኚህ ሁኔታዎችም ሴቷን ለእርግዝና ዝግጁ እንድትሆን የሚያደርጓት ሁኔታዎች ናቸው። በመጀመሪያም ከማህፀን በስተቀኝ እና በስተግራ የሚገኙት ኦቫሪዎች……ኦስትሮጅን እና ፕሮጅስትሮን የተሰኙትን ሆርሞኖች ያመነጫሉ። እነኚህ ሆርሞኖች የማህፀን ግድግዳ ለውጦችን እንዲያሳይ ማለትም ለእርግዝና ቅድመ-ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ያደርጋሉ። የፒቱታሪ ዕጢዎችም በኦቫሪ የተዘጋጁትን እንቁላሎች እንዲወጡና………ኦቫሪን እና ማዕጸንን በሚያገናኙት የፋሎፒያን ቱቦ ውስጥ ወደ ማዕጸን እንዲጓዙ ያደርጋሉ ማለት ነው። ………ዕንቁላሎች ወደ ማዕጸን በሚጓዙበት ወቅት ከወንድዬው የዘር ፍሬ ጋር ከተገናኙ፤ ከኦቫሪ ተነስተው በደም-ክምችት ከተገነባው የማዕጸን ግድግዳ ጋር ለመገናኘት አምስት ቀን ይወስድባቸዋል። ከዚያ ፅንሱ መፈጠሩን ይቀጥላል………ዕንቁላልና ስፐርም በፋሎፒያን ቱቦ ውስጥ ካልተገናኙ ግን ዕንቁላሉ ማዕጸን ላይ ሲደርስ ይፈራርሳል፤ ይህ ሁኔታም የኤስትሮጅን እና የፕሮጀስትሮን ሆርሞኖች ምርት እንዲቀንስ ምክንያት የሚሆን ሲሆን፤ በማህፀን ግድግዳ ላይ የተከማቸው ደምም መፈረካከስ ብሎም መፍሰስ የሚጀምር ሲሆን፤ በዚህ ሁኔታም በሴቷ የመራቢያ አካላት በኩል ወደውጪ መፍሰስ የሚጀምረው የወር-አበባም ለአምስት ቀናት ይቆያል ማለት ነው። ………ወደገደለው ስንሄድ የሴት ልጅ ማሚዎች እና ዳዲዎች አስቀድማችሁ ስለወር አበባ በግልጽ ሁኔታ ዘርዝራችሁ ማስረዳቱ በድንገት በሚከሰት የወር አበባ ወቅት የሥነ-ልቦና ችግር ሴት ልጆቻችን እንዳይገጥማቸው ቀድሞ ለማዘጋጀት ይረዳል። የመጀመሪያዎቹ አካላዊ ለውጦች እንዴት ያሉ ናቸው የሚለውን ስናይ የጡቶች እድገትና የብብት ፀጉር ማብቀል፤ በመጀመሪያ በልጃገረዶቹ ላይ የሚከሰቱ አካላዊ ለውጦች ሲሆኑ እኚህን ተከትሎም ምናልባት ከአንድ አመት በኋላ የዳሌ መስፋት፤ የእግሮች ማደግና የፊት ውበት መጨመር የመሳሰሉ ፈጣን ለውጦች ይመጣሉ፤ ይሄን ለውጥ ተከትሎም የወር አበባ "እንዴት ናችሁ ሴቶችዬ?" ብሎ ስለሚመጣ እንግዲህ ማሚና ዳዲ እንዲሁም የቤተሰቡ ግብዳ አካል ከፍተኛውን ትኩረት ማድረግ አለበት ማለት ነው፤ ክስተቱ ከመጀመሩ ቀድሞ መንገሩም "የወር አበባው ከየት የመጣ መሃት ነው?" ብለው ከመሸማቀቅ ያድናቸዋል።

በድጋሚ የተፖሰተ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ በደንብ ያንብቡት የተከበራቹ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦች ጠቃሚ መልእክት ካነበቡ በኋላ ለጓደኞቾ ሼር አየድርጉ የስፐርም መጠን ማነስ ምክንያ
በድጋሚ የተፖሰተ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ በደንብ ያንብቡት የተከበራቹ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦች ጠቃሚ መልእክት ካነበቡ በኋላ ለጓደኞቾ ሼር አየድርጉ የስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እንዲሁም እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቱ ምን ይሆን ??? በአለማችን ከ60-80 ሚሊዮን የሚሆኑ ጥንዶች ልጅ ያለመውለድ ችግር ያጋጥማቸዋል ለዚህ ችግር ከሚጋለጡበት ምክንያት አንዱ ፡- • የእስፐርም መጠን ማነስ • እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ • ትክክለኛ ቅርፅ የሌለው እስፐርም • የማህፀን ቱቦ ጠባሳ መኖር • የማህፀን እጢ መኖር • የእንቁላል ምርት ላይ ችግር ካለ • የሆርሞን ችግር መኖር • ለረጅም ጊዜ መድሀኒት መውሰድ ከላይ ከጠቀስናቸው ውስጥ ለዛሬ የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ እንገልፅላችሆለን • የሆርሞን ችግር • ኢንፌክሽን ካለ • ብልት አካባቢ ጉዳት ከደረሰ • ያልወረደ የዘር ፍሬ • ከዚህ ቀደም ሰርጀሪ ተሰርተው ከነበረ • ብልት አካባቢ የሚገኝ የደምስር እብጠት • የውስጥ ደዌ ህመሞች • ካንሰር ወይም ካንሰር ያልሆኑ እባጮች መኖር • ጭንቀት ፣ ድብርት • አብዝቶ የአልኮል መጠጥ መጠቀም ፣ ማጨስ • ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መጨመር ውድ የዶክተር አለ ተከታታይ በዛሬው ፁሁፋችን የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ልንገልፅላችሁ ወደናል

መጥፎ የአፍ ጠረን (ሀሊቶሲስ) ምንድን ነው? (ዶክተር ሀሎ) በህክምና ቋንቋ ሀሊቶሲስ የምንለው መጥፎ የአፍ ጠረን የጥርስ ጤናን/ ንጽህናን ባለመጠበቅ የሚከሰት ሲሆን ምናልባት ሌሎች የጤና ችግሮች እናዳሉብን አመላካች ነው፡፡ የምንመገው የምግብ አይነት እና ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ይህ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲባባስ ያደርጋል፡፡ ✔የምንመገበው ምግብ የአፍ ጠረንን እንዴት ይቀይራል? በመጀመሪያ የተመገብነው ምግብ መሰባበር/መፈጨት የሚጀምርው አፍ ውስጥ ነው፡፡ ምግብ ከተፈጨ በኋላ ወደ ደም ዝውውር ውስጥ ይገባል ከዚያም ደም ወደ ሳንባ ይጓዛል በመጨረሻም ከትንፋሻችን ጋር አብሮ ይወጣል፡፡ ጠንካራ ሽታ ያላቸው ምግቦች(ለምሳሌ፦ ነጭ ሽንኩርት፣ ሽንኩርት)፣ ጥርስን መፋቅ ወይም ስቴኪኒ መጠቀም፣ ጥርስን መጉመጥመጥ ለጊዜውም ቢሆን ሽታውን ሊያጠፋው ይችል ይሆናል ነገር ግን ምግቦቹ ከሰውነታችን እስኪወገዱ ድረስ ሽታው ሙሉ ለሙሉ አይጠፋም፡፡ ✔መጥፎ ልምዶች እንዴት መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣሉ? ጥርስዎን በየቀኑ የማይፍቁ ወይም የማይቦርሹ ከሆነ የምግብ ቅሪቶች በአፋችን ውስጥ ይቀራሉ እነዚህ ቅሪቶች ባክቴሪያዎች በጥርሶቻችን መሀል፣ በድዶቻችን አካባቢ እና በምላሳችን ላይ እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል ይህም መጥፎ የአፍ ጠረን ያስከትላል፡፡ ፀረ-ባክቴሪያ የአፍ ማጽጃዎች መጠቀም የባክቴሪያዎቹን እድገት ይገታል፡፡ ሲጋራ ማጨስ ወይም የሚታኝኩ የትንባሆ ምርቶችን መጠቀም መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲኖረን ያደርጋል፣ የጥርስ ቀለምን ያበላሻል፣ የምግቦችን ጣዕም የመለየት ችሎታችንን ይቀንሳል፣ ድዳችን እንዲቆስሉ ያደርጋል፡፡ ✔ከመጥፎ የአፍ ጠረን ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች ቀጣይነት ያለው መጥፎ የአፍ ጠረን መጥፎ ጣዕም በአፍ ውስጥ ካለ የድድ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ የድድ በሽታ የሚከሰተው በጥርሳችን ላይ ባክቴሪያን የያዙ ቁስ አካሎች በሚኖርበት ጊዜ ነው፡፡ ባክቶሪያዎች ድዳችን እንዲቆጣ/እንዲያብጥ የሚያደርግ መርዛማ ነገር ያመርታሉ ይህ የድድ በሸታ የማንታከመው ከሆነ ድድ እና የመንጋጭላ አጥንት እንዲጎዳ ያደርገዋል፡፡ ሌላው ከጥርስ ጋር የተያያዘ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚያስከትለው በትክክል የማይገጥሙ ሰው ሰራሽ ጥርሶች፣ የአፍ በይስት ኢንፌልሽን መጠቃት ናቸው፡፡ በህክምና ቋንቋ ዚሮስቶሚያ የምንለው የአፍ መድረቅ መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣል፡፡ ምራቅ አፍን ለማርጠብ በጣም ጠቃሚ ሲሆን በባክቴሪያዎች የሚፈጠርን አሲድ ነፃ ያደርጋልበተጨማሪም በጉንጭ፣ ድድና ምላስ ውስጥ የሞቱ ሴሎችን ያፀዳል፡፡ እነዚህ የሞቱ ሴሎች በጊዜ ካልተወገዱ ይበሰብሱና መጥፎ የአፍ ጠረን ያስከትላል፡፡ የአፍ መድረቅ የመድሃኒቶች፣ የምራቅ ዕጢ ችግርና ለረጂም ጊዜ በአፍ የመተንፈስ የጎንዮሽ ጉዳት ውጤት ነው፡፡ የተለያዩ ብዙ በሽታዎች እና ህመሞች መጥፎ የአፍ ጠረን ያስከትላሉ ከነዚህ በሽታዎች መካከል፦ የመተንፈሻ አካል በሽታዎች(የሳንባ ምች ወይም ብሮንካይተስ)፣ ከባድ የሳይነስ ኢንፌክሽን፣ ፖስትናሳል ድሪፕ፣ የስኳር በሽታ፣ ከባድ የአሲድ ችግር እና የጉበት ወይም ኩላሊት ችግር ናቸው፡፡ ✔መጥፎ የአፍ ጠረንን እንዴት መከላከል እችላለሁ? መጥፎ የአፍ ጠረንን በሚከተሉት መንገዶች መቀነስ ወይም መከላከል ይቻላል፦ 1. የአፍ ንጽህናን በመጠበቅ በፍሎራይድ የጥርስ ሳሙናዎች ጥርስን በቀን ሁለት ጊዜ መቦረሽ የምግብ ቅሪቶችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ምግብ ከተመገብን በኋላ ጥርስን መቦረሽ (የጥርስ ቡርሻችንን በት/ቤትና ስራ ቦታ መያዝ)፡፡ ምላስዎንም መቦረሽ እንዳለብዎት አይርሱ፡፡ ከሁለት ወይም ሶስት ወር በኋላ ወይም ከህመም በኋላ የጥርስ ቡርሻችንን መቀየር አለብን በጥርሶቻችን መሃል ያሉትን ምግቦች ለማስወገድ በቀን አንድ ጊዜ ስቴኪኒ ወይም ሌላ ነገሮች በመጠቀም ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡ 2. የጥርስ ሃኪምዎን በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ይጎብኙ በአመት ሁለት(2) ጊዜ ወደ ጥርስ ሃኪምዎ እንዲሄድ ይመከራል፡፡ ሃኪምዎ የአፍ ምርመራ፣ የጥርስ ማጽዳት(በህክምናዊ መንገድ)፣ የተለያዩ የጥርስ በሽታዎች ምርመራና ህክምና፣የአፍ መድረቅና የተለያዩ የአፍ ጠረንን የሚያመጡ ችግሮችን መፍትሄ ያገኝልዎታል፡፡ 3. ሲጋራ ማጨስና ከትንባሆ የሚዘጋጁ የሚታኝኩ ነገሮችን መጠቀም ማቆም፡፡ 4. ብዙ ውሃ መጠጣት ይህ ሁኔታ አፋችን በማንኛውም ጊዜ እርጥበት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ማስቲካ ማኝክ(ስኳር የሌላቸው ቢሆኑ ይመረጣል) ምራቅ እንዲመረት ያደርጋል ምራቅ የምግብ ቅሪቶችንና ባህቴሪያዎች ታጥበው እንዲወገዱ በማድረግ ይጠቅመናል፡፡ ዛይሊቶል() ያላቸው ማስቲካና ሜንት መጠቀም ተመራች ነው፡፡ 5. የተመገብናቸውን ምግቦች እና የወሰድናቸውን መድሃኒቶች መዝግበን በመያዝ የትኞቹ ምግቦች ወይም መድሃኒቶች መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲከሰት መንስኤ የሆኑትን በቀላሉ በመለየት እርምጃ መውሰድ እንችላለን፡፡ ✔መጥፎ የአፍ ጠረንን ማን ሊያክም/ሊመረምር ይችላል? በአብዛኛው የጥርስ ሃኪም መጥፎ የአፍ ጠረንን ይመረምራል የጥርስ ሃኪማችን አፋችን ጤናማ መሆኑን እና ይህ መጥፎ ሽታ ከአፋችን አካባቢ እንዳልሆነ ካረጋገጠ በኋላ የመጥፎ አፍ ጠረኑን ምንጭ ለማወቅ ወደ ሌሎች ሃኪሞች ወይም ስፔሻሊስቶች ጋር ሪፈር ያደርገናል፡፡ ✔ምን አይነት የአፍ ጠረን ማጥፊያ ምርቶችን መጠቀም አለብኝ? መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ በቁጥር በዛ ያሉ የአፍ ማጠቢያዎች መግዛት ይቻላል ነገር ግን ብዙዎቹ መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ ጊዜያዊ መፍትሄ ቢሆኑም ሙሉ ለሙሉ አያስወግዱትም፡፡ ከጥርስ ሃኪምዎ ጋር በመመካከር እና የትኛው ምርት ውጤታማ እንደሆነ በመጠየቅ በገበያ ላይ የሚገኙ ፀረ-ባክቴሪያ የአፍ ማጽጃዎች መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲኖር የሚያደርገውን ጀርም የመግደል አቅም ስላላቸው ብንጠቀማቸው ጥሩ ውጤት ያስገኛሉ፡፡ @DrSofonias

-------------------''ሲጋራና መዘዙ''!------------ ሲጋራ ማጨስ ለጤና በጣም ጠንቅ ነው። ምንም አይንት አጫጫስ ጉዳቱን አይቀንሰውም፥ ሲጋራውን በፒፓ ውስጥ መክተት ሆነ በሁካ ማጨስ ጉዳቱን አይቀንስም።እንደ አሜሪካ የሳንባ ማህበር (American Lung Association)ጥናት መሰረት ሲጋራ ውስጡ ወደ 600 ሚሆኑ ንጥረ ነገሮች አሉት። በሚጨስበት ጊዜ ደግሞ ወደ 7 ሺ ኬሚካሎችን ይወልዳል ። እና ከነዛ ውስጥ አብዛኛዎቹ ኬሚካሎች መርዞች ናቸው እናም ቢያንስ 69ኙ ነቀርሳ(cancer) ያመጣሉ። ሁካና ቶባኮም አብዛኛዎቹን መርዞች አሉባችው።ሁካ ሲጨስ ከሲጋራ በላይ ጪስ ወደ ውስጥ የመሳብ እድሉ አለ። እናም ሁካ ከሲጋራ ይበልጥ ለመጥፎ መርዞች እና ለ ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ እንድትጋለጡ ያርጋችኃል። እንዲሁም ሁካ ከጎን ያለን ሰው (secondhand) ይበልጥ ያጠቃል። በሰሜን አሜሪካ ውስጥ (the United States), ሲጋራ የሚያጨስ ሰው የሞት ፍጥነት ብዛት ከማያጨሰው ሶስት እጥፍ ይበልጣል።በአለማችን በየዓመቱ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ሲጋራ በማጨስ ምክንያት በሚከሰቱ የጤና ችግሮች የሚሞቱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስድስት መቶ ሺህ የሚሆኑት እራሳቸው ሲጋራ የማያጨሱ ሆነው ከአጫሾች በሚመጣ ጭስ ምክንያት ለጤና መታወክ የሚዳረጉና የሚሞቱ ናቸው፡፡ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር በአደጉት አገራት እየቀነሰ መምጣቱንና በአንፃሩ ደግሞ በታዳጊ አገራት በከፍተኛ መጠን በመጨመር ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡የሀገራችን አመታዊ የሲጋራ ፍላጐት 4.4 ቢሊዮን ፍሬ መድረሱንም ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ ------------------------ሲጋራና መዘዙ! --------------''ማእላዊ ስርአተ ነርቭ''-------- ከሲጋራ ንጥረ ንገሮች አንዱ ኒኮቲን ይባላል። ኒኮቲን አይምሮ ጋር በሰከንድ ውስጥ ይድርሳል። ሲደርስ አይምሮን አነቃቅቶ ሃይል ለተወሰነ ጊዜ ይስጣል። ከዛን ያ ሃይል ሲጠፋ ከእንደገና ሌላ አንዲጨመር ይገፋፋል እንደዚህ ነው ሱስ የሚጀመረው። ማጨስ የአይን ጋርዶሽ እና የአይን ድክመት ያመጣል። እንዲሁም የመቅመስና የምለየትን ስሜት ይቀንሳል ስለዚህ ምግብ ያን ያህል መጣፈጡን ይቅንሳል። ጭንቀት ላይ ሰውነታችን ውስት corticosterone የሚባል ሆርሞን hormone ያመነጫል , ይህ ሆርሞን ሲጋራ ወይ ኒኮቲን የሚያመጣውን ስሜት ይቀንሰዋል ስለዚህ ነው ሰው ሲጨነቅ ብዙ ሲጋራ ካላጨሰ በስተቀር የሲጋራን ሃይል የማይስማው። ከሲጋራ መለየት ሲሞከር መረበሽ ፥ ጭንቀት፥ ራስ ምታት ለጊዜው ይመጣል። -------------ስርዓተ ትንፈሳ----- ሲጋራ ጪሱ ወደ ውስጥ ሲገባ ሳምባን የሚጎዱ ነገሮች አብረው ነው የሚገቡት። ሳምባ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የሚጎዱ ኬሚካሎችን የማጣራት ሃይሉን ይጣል። ማሳል የመተንፈሻ መንገዱን አያጠራውም ስለዚህ እንዚህ መርዞች እዛው ይቀመጣሉ ። አጫሾች መተንፈሻ ችግር እንደ ኢንፌክሽን፥ ብርድ፥ጉንፋን የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።አጫሾች የሳንባ ካንሰር፥ ብሮንካይተስ ሌላ ሌላ ችግሮች የተጋለጡ ናቸው። ወላጆች ወይ ሌሎች የሚያጭሱ ሰዎች ይሉበት ቤት የሚኖሩ ልጆች ለተለያየ የመተንፈሻ በሽታዎች፥ ብሮንካይተስ፥ ኒሞኒያ፥ አስም፥ ሳይነስ የተጋለጡ ናቸው። ------------ስርአተ ልብ ወቧንቧ----- ማጨስ የውስጥ ቧንቧን ባጠቃላይ ይጎዳል። ኒኮቲን ልክ ሰውነት ውስጥ ሲገባ ደም ውስጥ ያለን ስኳርን ከፍ ያርጋል፥የስኳሩ ከፍ ማለት ትንሽ ስሜትን ሚያነቃቃ ቢሆንም ከትንሽ ጊዜ በኃላ ድካም ያመጣል ከዛን ተጨማሪ እንዲጨስ ይገፋፋል።ኒኮቲን የደም ቧንቧ እንዲጠብ ያደርጋል ይሄ ታዲያ ደም በአግባቡ እንዳይፈስ ያግደዋል። የደም ብዛት ፥ የደም መርጋትን እንዲሁም ኮልስትሮል መጨመርን ያመጣል። የደም መርጋት ስትሮክ የመያዝ እድሉን ይጨምረዋል። ከጊዜም በኃላ የደም ካንሰር ያመጣል። ሲጨስ ከጎን ለሚሆን ሰውም ብዙ ጉዳት ያመጣል። ----------ቆዳ,ፀጉር, እና ጥፍር--------- አንዱ በቀላሉ የማጨስ ጉዳቱ ሊታይ የሚቻለው በቆዳ ላይ ነው። የሲጋራ ንጥረ ነገር የቆዳን ተፈጥሮ ይቀይራል።ማጨስ ቆዳ ላይ ጥቓቁር ነጠብጣብ ያወጣል፥ ፊትን ያጨማድዳል፥እንዲሁም አስቅድሞ ያስረጃል። የጣት ቆዳ እና ጥፍር ቢጫ ይሆናሉ። ስራት ማብላሊያ አካል አጫሾች አፍ ውስጥ ሊመጡ ሊኖሩ ይሚችሉ በሽታዎች ተጠቂዎች ናቸው። ሲጋራ የመንጋጋ በሽታ፥ ኢንፌክሽን ያመጣል። ይሄ ወደ ጥርስ መበስበስ፥ጥርስ ቡኒ እና ቢጫ እንዲሆን አልፎም እንዲወልቅ ያደርጋል። መጥፎ የአፍ ጠረንም ያመጣል። ማጭስ የአፍ ነቅርሳ ወይም ካንሰር፥ የጉሮሮ ካንሰር፥ እና የኩላሊት ካንሰር፥ የጣፊያ ካንሰር ያመጣል። የስኳር በሽታ ያመጣል።

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias - Статистика и аналитика Telegram-канала @drsofonias