Ethio Pulse
Открыть в Telegram
እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው። ለማስታወቂያ ስራ - @sehmf Buy ads: https://t.me/sehmf
Больше230
Подписчики
+124 часа
+67 дней
+630 дней
Архив постов
230
የዓለማችን አ'ስ*ቀ$ያሚ'ዋ ሴት ፥ ሊዚ ቬላስኬዝ !
ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበረች። እንደማንኛውም ወጣት ዩቲዩብ ላይ ስትዘዋወር፣ አንድ ቪዲዮ በአጋጣሚ አይኗ ላይ አረፈ። ርዕሱ "የዓለማችን እጅግ አስቀያሚዋ ሴት" ይላል።
በፍርሃትና በጉጉት ቪዲዮውን ስትከፍተው ግን ያየችውን ማመን አቃታት። በቪዲዮው ላይ የነበረችው ያቺ "አስቀያሚ" የተባለችው ሴት... እሷው ራሷ ነበረች። ያቺ ቅፅበት ለእሷ የዓለም ፍፃሜ ነበረች። ቪዲዮው በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ታይቷል። ጣቶቿ እየተንቀጠቀጡ፣ ልቧ በድንጋጤ እየመታ ወደ አስተያየት መስጫው (comment) ወረደች።
ምናልባት አንዲት ነፍስ እንኳን... "ኧረ ተዉ! ይሄ እኮ ስሜት ያለው የሰው ልጅ ነው" ብሎ የተከላከለላት ሰውአልነበረም። አሁንም ከሷ ወገን ሊቆም የሚችል ሰው ይኖራል ብላ ተስፋ አድርጋ ነበር። ነገር ግን አሁንም የገጠማት ልብን የሚያደሙ ፣ ጭካኔ የተሞላባቸው አስተያየቶች ብቻ ነበር።
ፈፅሞ አይተዋት የማያውቁ፣ ምን አይነት ሰው እንደሆነች የማያውቁ ሰዎች በመልኳ ተሳለቁ። "ወላጆቿ እንዴት ሊወዷት ቻሉ?" ብለው ያፌዙባትም ነበሩ። አንዳንዶች ደግሞ ባትፈጠር፣ አልያም እራሷን ብታጠፋ እንደሚሻል ሳይሳቀቁ ፃፉላት። ያቺን ለሊት ብቻዋን እንባዋን እያፈሰሰች አነጋች። ህመሟን ለቅርብ ጓደኞቿ እንኳን ማካፈል አልቻለችም።
ሊዚ የተወለደችው በሰውነቷ ውስጥ ስብ እንዳይከማች እና ክብደት እንዳትጨምር በሚያደርግ እጅግ ብርቅዬ የዘረመል (Genetic) ህመም ምክንያት ነው። በአንድ አይኗ ማየት አትችልም። ከልጅነቷ ጀምሮ የሰዎች መሳለቂያና መጠቋቆሚያ መሆን አዲስ አልነበረባትም።
ያን ሁሉ የጥላቻ ናዳ ካየች በኋላ... ከሰው ፊት መራቅ ትችል ነበር። ዳግመኛ ፊቷን ለማንም ላለማሳየት መወሰንም ትችል ነበር። እሷ ግን ያንን አላደረገችም፤ ይልቁንም፣ ማንም ያልጠበቀውን ነገር አደረገች። ብርቱዋ ሴትካሜራውን ወደ ራሷ አዞረች፤ "ሌሎች ሰዎች መልኬን አይተው ማንነቴን እና ክብሬን እንዲወስኑ አልፈቅድም” ስትል አንድ ትልቅ ውሳኔ ወሰነች።
የራሷን የዩቲዩብ ቻናል ከፈተች። ስለ መገለል፣ ስለ በራስ መተማመን፣ እና የሰዎች ጥቂት ክፉ ቃላት እንዴት ለዓመታት በአእምሮ ውስጥ ተቀርፀው እንደሚቀሩ በግልፅ መናገር ጀመረች። ከዚያም በዓለም አቀፉ የTEDx መድረክ ላይ ወጥታ ያንን ታላቅ ጥያቄ ጠየቀች።
"ለመሆኑ ራስህን የምትገልፀው በምንድን ነው፣ በሰውነትህ ቅርፅ፣ በህመምህ? በሰዎች ክፉ አስተየት፣ ወይስ አንተን ለማሳነስ በተሰጠህ ስም?" በማለት መሰረታዊና ስሜት ኮርኳሪ ጥያቄዎችን አንስታ ሞገተች።ይህ ጥያቄ አዘል ንግግር በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ ገባ።
ዛሬ ላይ ሊዚ ታዋቂ ደራሲ፣ አነቃቂ ተናጋሪ እና የፀረ-ጉልበተኝነት (Anti-bullying) ዘመቻ መሪ ነች። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደርሱ ትንኮሳዎችን ለመከላከል ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ግንባር ቀደም ሆና ትሰራለች። ብርቱዋ ሊዚ ጠንካራ የሆነችው ሰዎች ስለተሳለቁባት ወይም ስለጨከኑባት አይደለም።
የሰዎች ጭካኔ፣ ማዋረድና ማንቋሸሽ መቼም ቢሆን የጥንካሬ ምንጭ ሊሆን አይችልም። በማህበራዊ ሚዲያ ጀርባ ተደብቆ አንድን ታዳጊ "ሙት" ማለት፣ ጉዳት አልባ ተራ ቀልድ አይደለም።በአንድ ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እሷን ለማሳነስ እና በእርሷ ላይ ለማፌዝ ቪዲዮዋን ተመልከተው ነበር።
ዛሬ ግን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የእሷን ተስፋ ሰጪ ቃላት ለመስማት ይሰበሰባሉ። እንግዳ ሰዎች ዋጋ እንደሌላት ሊያሳምኗት ሞክረው ነበር።እሷ ግን ዓመታትን ሙሉ ለሌሎች ታዳጊዎች "የእናንተ ዋጋ የሚወሰነው በሰዎች ክፉ አስተያየት አይደለም" በማለት አስተማረች።
ለጥላቻ ሊሰጥ የሚችለው ትልቁ ምላሽ ምናልባት ይሄው ነው... የጎዱንን ሰዎች አለመምሰል። እኛን ሊሰብሩን የሞከሩበትን ያንኑ ድንጋይ፣ ለሌሎች ሰዎች የመጠጊያ ቤት መገንቢያ አድርጎ መጠቀም!❤️🙏
230
(ይህን_ያውቃሉ⁉
🇯🇵 ጃፓን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 አመት በላይ እድሜ ያላቸው የሰዎች ቁጥር 100,000 አልፏል❤
@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
230
👬ተመሳሳይ መንትዮች ተመሳሳይ መንትዮችን አግብተው የወለዷቸው ልጆች፡ በአንድ ጊዜ የአክስት/የአጎት ልጆችም ወንድማማቾችም ሆኑ!
🔹🔹🔹
አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩት ብሪታኒ እና ብሪያና የተባሉ ተመሳሳይ መንትያ እህቶች ጆሽ እና ጄሬሚ ከተባሉ ተመሳሳይ መንትያ ወንድማማቾች ጋር ትዳር መስረተዋል። በአንድ ላይ ተጋብተው በአንድ ቤት ውስጥ መኖር የጀመሩት እነዚህ ሁለት ባለትዳሮች በተመሳሳይ ጊዜ አካባቢ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወልደዋል።
ነገሩን ድንቅ የሚያደርገው ደግሞ የልጆቹ ጄኔቲክስ (DNA) ሁኔታ ነው። በሳይንስ ህግ መሰረት ተመሳሳይ መንትዮች ሙሉ በሙሉ አንድ አይነት DNA አላቸው። በመሆኑም የሁለቱ ህፃናት (ጃክስ እና ጄት) እናቶችም ሆኑ አባቶች አንድ አይነት ዲኤንኤ ስላላቸው፣ ህፃናቱ በህግ የአክስት/የአጎት ልጆች ሲሆኑ በጄኔቲክስ ደረጃ ግን ሙሉ ወንድማማቾች (Quaternary twins) ናቸው።
ቤተሰቦቹ በቨርጂኒያ ግዛት በአንድ ግቢ ውስጥ አብረው የሚኖሩ ሲሆን ልጆቹንም እንደ ወንድማማች አድርገው በአንድነት እያሳደጓቸው ይገኛሉ✌
@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
230
+2
በአፍሪካዋ ሀገር ቻድ ውስጥ በመዲናዋ ኒጃሚና ከዛሬ ጀምሮ መንገድ ላይ የሚፀዳዱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ጀምራለች።
ሰዎቹ ሲያዙ የተፁዳዱበትን ቦታ ራሳቸው በአፈር እንዱሸፍኑ ከተደረጉ በኃላ ወደ ፖሊስ ጣብያ እየተወሰዱ ነው 😂
ኤርሚያስ በላይነህ
@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
230
🐸😳 እንቁራሪቶች እንደ ሌሎች እንስሳት መትፋት (Vomit ) አይችሉም!
አንድ እንቁራሪት ጎጂ ወይም የማይፈጭ ነገር ሲውጥ፣ ሆዱን ሙሉ በሙሉ ከአፉ ውስጥ ወደ ውጭ በማውጣት የሆዱን ይዘት ያስወግዳል።
ከዚያም የፊት እግሮቹን በመጠቀም የሆዱን ይዘት ካስወገደ በኋላ፣ ሆዱን እንደገና ወደ ውስጥ ይመልሰዋል! 🐸🤯
ተፈጥሮ በእውነት አስገራሚ ናት! 🌍
230
🇮🇹🐶 በጣሊያን የቤት እንስሳን መጣል ወንጀል ነው!
በጣሊያን የቤት እንስሳን መንገድ ላይ መጣል ወይም መተው በሕግ የተከለከለ ሲሆን፣ እስከ 1 ዓመት እስራት ወይም ከ5,000 እስከ 10,000 ዩሮ ቅጣት ሊያስከትል ይችላል።
🐾❤️ እንስሳትን መውደድ ብቻ ሳይሆን፣ ኃላፊነትም ነው!
230
✔️አንዳንድ ጥናቶች እንደሚሉት ከሆነ ከ10 ሰዎች ውስጥ ዘጠኙ "Phantom Vibration Syndrome" እንዳለባቸው ይጠቁማሉ። ይሄ ማለት ስልካቸውን በኪሳቸው አርገው በሚጓዙበት ሰአት ስልካቸው Vibrate ሳያረግ አእምሮአቸው ግን ስልኬ Vibrate እያረገ ነው ብሎ ስልካቸውን ከፍተው ቼክ እንዲያረጉ የሚያደርጋቸው ነው።ስንቶቻቹ አጋጥሟቸዋል?
230
✅በአለም ብቸኛው ጥይት የማይበሳው ቆዳ ያለው እንስሳ Pangolin የተሰኘው የዱር እንስሳ ነው፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያም Ground Pangolin የተሰኘው የዚሁ እንስሳ ዝርያ እንዳለ ይታመናል
Share🌍
https://t.me/+tALKv1yeEogyYWY0
https://t.me/+tALKv1yeEogyYWY0
230
Repost from 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
ጭቆና ክፍዎችን ይፈጥራል !
የአዶልፍ ሂትለር ታላቅ ወንድም የአባቱ ጨካኝነትን ለማምለጥ በ13 አመቱ ነበር ከቤቱ በርሮ የጠፋው፡፡ ይህ ልጅ ከቤቱ ከሄደ በኋላ የሂትለር አባት ክፋቱን በሰባት አመቱ ለጋ ልጅ በሂትለር ላይ በእጥፍ ጨመረው፡፡ ሂትለር በአባቱ እጅ አሰቃቂ አመታትን አልፏል፡፡ ምርጫውን ተከልክሎአል፡፡ አርቲስት ለመሆን ይመኝ የነበረው ሂትለር በአባቱ አስገዳጅነት የሲቪል ሰራተኛነት አቅጣጫን እንዲከተል ተገደደ፡፡ የሂትለር ትምህርት ውጤቱ አጥጋቢ ስላልነበር የአባቱን ቁጣ እጅግ አባባሰው፡፡ የአይሁድ ዘር እንዳለበት የሚነገረው የሂትለር አባት ክፋት በሂትለር ልብ ውስጥ አይሁድን የመጥላት ዘርም እንደዘራበት ይነገራል፡፡
አባቱ ከሞተ በኋላ፣ ሂትለር በ13 አመቱ የቤት ሃላፊነትን በጫንቃው ላይ ተሸከመ፡፡ በእናቱ ሞት ምክንያት በኋላ በጉዲፈቻ ያድግ የነበረው ሂትለር ያንን ገቢ በመከልከሉ የጎዳናን ሕይወት ቀምሷል፡፡ በብዙዎች እንደሚታመነው፣ ሂትለር በልጅነቱ ያሳለፈው ስቃይ ውስጡ ከጨመረበት መራራነት እንዳልተላቀቀና በሕይወቱ ያደረጋቸው አሰቃቂ ተግባሮች የዚያ ልምምድ ተጽእኖ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ሂትለር ቢያንስ ለ46 ሚልየን ሰዎች መሞትና ለብዙ ንብረት መውደም ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡ ሂትለር የዚህ ሁሉ ውደመት ምክንያት ከሆነ በኋላ ራሱን በራሱ አጥፍቶ እስኪሞት ድረስ ይህንን እብደቱን የሚከተሉለት ከእርሱ የባሱ እብዶች ፈጽሞ አጥቶ አያውቅም ነበር፡፡
አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን በተለያዩ ለማንነት ቀውስ (Identity Crisis) አሳልፈው በሚሰጡ ልምምዶች ውስጥ አልፈው ቢያድጉም ከዚያ ሁኔታ በተሳካ መልኩ ራሳቸውን አውጥተው ለሕብረተሰቡ ጠቃሚ ዜጎች ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙዎችን ወደ አንድነት፣ ወደ መከባበርና ወደ አብሮነት የሚያመጡ የመልካም ተጽእኖ ሰዎች ናቸው፡፡
አንዳንዶች ግን በመራራነት፣ በጥላቻና በአስተዳደግ ዘመናቸው በተጎነጩት የውስጥ ቂም የተቃወሰ ማንነት ይዘው ወደ አመራር ይዘልቃሉ - እንዴት አይነት ስህተት! እንደዚህ አይነት ሰዎች በውስጣቸው ያለባቸው የማንነት ቀውስ ይህ ነው ተብሎ ሊተነበይ የማይችልን ባህሪይ እንዲገልጡ ይነዳቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጠናወታቸው የተቀባይነት ጥማትና የደጋፊ ፍለጋ ናፍቆት ምንም ነገር ከማድረግ እንዳይመለሱ አይኖቻቸውን አሳውሯቸዋል፡፡
230
አንድ ቅቤ አምራች ገበሬና ዳቦ አምራች ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡ በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡
ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት ተስማሙ፡፡
በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ዳቦ አምራች ነጋዴው ገበሬው የሚልክለት የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሄዱን አየ፡፡ በመጨረሻም ሚዛን ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም፡፡ ገበሬውንም አስጠራው፡፡
ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ ‹‹ከተስማማነው ውጭ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ገበሬውም ‹‹እኔ ፈጽሞ አልቀነስኩትም›› ሲል በአግራሞት መለሰ፡፡
ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው፡፡ 150 ግራም ነው፡፡ ገበሬውም አዘነ፡፡ ‹‹እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም መለኪያ የለኝም፡፡ አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሐን ላይ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ቅቤውን በሌላኛው ሚዛን አስቀምጠዋለሁ፡፡
ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ እልክልሃለሁ›› አለው፡፡ ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው፡፡ ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው፡፡ ነጋዴው አፈረ፡፡
‹‹የምታገኘው ለሌላው ባደረግከው ልክ ነው፡፡ 150 ሰጥተህ 300 ልታገኝ አትችልም፤ እባብ ሰጥተህ ርግብ፣ ድንጋይ ሰጥተህ ዳቦ፣ እሬት ሰጥተህ ማር ልታገኝ አትችልም፡፡
አንተ ብቻ ብልጥ ልትሆን አትችልም፡፡ ማሾውን አጥፍተህ ብርሃን ልታገኝ አትችልም፡፡ ሌላውን ገድለህ አንተ በሰላም ልትኖር አትችልም›› አለው ገበሬው፡፡
SHARE||@astemari_tarik
230
ፈሶትን አያዙ: የተከማቸ ፈስ በአፍ ሊወጣ ይችላል
አንድ ሰው የሆድ አየርን (ፈስን) ከልክ በላይ ይዞ ለመቆየት ሲሞክር አየሩ በጨጓራና አንጀት ውስጥ ታፍኖ አይቀርም።
በሰውነት ውስጣዊ መዋቅር ምክንያት አየሩ ወደ ደም ዝውውር ስርአት ውስጥ እንደገና በመመጠቅ በመጨረሻም በአፍ በሚወጣው ትንፋሽ በኩል ሊወጣ እንደሚችል የህክምና ጥናቶች ያሳያሉ።
ይህ ሂደት የሚከሰተው በአንጀት ውስጥ የታቀበው ጋዝ ግፊት እየጨመረ ሲሄድ ወደ አንጀት ግድግዳ የደም ስሮች በመግባት ነው።
ደም ወደ ሳንባ በሚሰራጭበት ወቅት እነዚህ ጋዞች ከደም ወጥተው ወደ ሳንባ አየር ከረጢቶች ስለሚሸጋገሩ፣ ግለሰቡ በሚተነፍስበት ጊዜ አየሩ በአፍ በኩል ይወጣል።
ምንም እንኳን ይህ አጋጣሚ ለብዙዎች እንግዳና የሚያስቅ ቢመስልም፣ በተፈጥሮ የሚፈጠርን የሰውነት ጋዝ አፍኖ መያዝ የሆድ እብጠት፣ ህመም እና የአንጀት ምቾት ማጣት ስለሚያስከትል ተፈጥሯዊ ሂደቶችን አለመግታት ይመረጣል።
230
የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የልደት ቀናቸውን ብሔራዊ የሕዝብ በዓል አድርገው ሰየሙ‼️
የዚምባብዌ መንግሥት የፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የልደት ቀን የሆነውን መስከረም 15 (ሴፕቴምበር 15) በየዓመቱ የሚከበር ብሔራዊ የሕዝብ በዓል አድርጎ ማወጁ ከፍተኛ ትችትና ተቃውሞ አስነሳ። “ሙንሁሙታፓ ቀን” በሚል የተሰየመው ይህ በዓል በሕግ ማዕቀፍ የወጣ ቢሆንም፣ ተቃዋሚዎች ግን እርምጃውን የፕሬዚዳንቱን ግላዊ ስልጣንና ዝና ለማገንነን የተደረገ ውሳኔ ነው ብለውታል።
እማማ አፍሪካ😂😂😂 ከሰነበትን ብዙ ታሳየናለች
230
🤯 ይህን ያውቁ ኖሯል?
💪 በዚህ ዘመን ብዙ ወንዶች 6-Pack ለማውጣት፣ ጡንቻ ለመገንባትና በጂም ውስጥ ሰዓታትን ለማሳለፍ ይሰራሉ።
😳 ነገር ግን በኢትዮጵያ ኦሞ ሸለቆ የሚኖሩ የቦዲ (Bodi/Me’en) ህዝቦች ዘንድ ነገሩ ፈጽሞ የተለየ ነው!
🥛🩸 እዚያ ትልቅ ሆድ እና የበዛ የሰውነት ክብደት እንደ ውበትና ክብር ይቆጠራል።
በየዓመቱ በሚከበረው “ካኤል” (Ka’el) ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ ያላገቡ ወጣት ወንዶች ለበርካታ ወራት ይዘጋጃሉ። ከባድ ሥራን በመቀነስ እና ከወተትና የላም ደም የተዘጋጀ ካሎሪ በለጸገ ምግብ/መጠጥ በመመገብ በተቻለ መጠን ክብደታቸውን ለመጨመር ይሞክራሉ። 😮
🏆 የበዓሉ ቀን ሲደርስ ተወዳዳሪዎቹ ከተገለሉበት ቦታ ወጥተው በማህበረሰቡ ፊት ይታያሉ። ሽማግሌዎችና ህዝቡም የአካላቸውን መጠን ይገመግማሉ።
👑 በመጨረሻ ትልቁን የአካል መጠን ያሳየው ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ከፍተኛ ክብርና ዝና ያገኛል።
😂 እኛ 6-Pack ለማውጣት ስንለፋ፣ እነሱ ግን “Big Belly” ለማውጣት ይወዳደራሉ!
📌 ይህ የቦዲ/ሜእን ህዝቦች ባህላዊ ሥነ-ሥርዓት እንጂ የዕለት ተዕለት የህይወት ዘዴ አይደለም።
#አስገራሚ_እውነታ #Ethiopia 🇪🇹 #Bodi #Meen #Kael #DidYouKnow@Asgerami_facts
230
🌿 ስለ ዕፅዋት 3 አስገራሚ እና ድንቅ እውነታዎች!
1. እርስ በርሳቸው ይነጋገራሉ (የተፈጥሮ ኢንተርኔት)! 🌐
ዕፅዋት ዝምተኛ ይመስላሉ እንጂ ስር ስራቸው በሚገኝ "Mycorhizal network" በሚባል የፈንገስ መዋቅር አማካኝነት እርስ በርሳቸው መረጃ ይለዋወጣሉ። ለምሳሌ በአቅራቢያቸው ተባይ ከተከሰተ አንዱ ተክል ለሌላው የማስጠንቀቂያ መልእክት በመላክ ኬሚካል እንዲያመርቱና እራሳቸውን እንዲከላከሉ ያደርጋል።
2. የራሳቸው የደህንነት ጥበቃ ስርዓት አላቸው! 🛡️
አንዳንድ ተክሎች ከተባይ ወይም ከተባይ ትሎች ጥቃት ሲደርስባቸው፡ ተባዮቹን የሚበሉ ሌሎች አዳኝ ፍጥረታትን (ተባዮችን) የሚስብ ልዩ ጠረን ወይም ኬሚካል ወደ አየር ይለቃሉ። በሌላ አነጋገር "የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው" በሚል መርህ አዳኝ ፍጥረታትን እርዳታ ይጠራሉ።
3. አዳኝ እና ስጋ ተመጋቢ ዕፅዋት አሉ! 🪴
እንደ Venus Flytrap ያሉ ዕፅዋት በምግብ እጥረት ምክንያት ነፍሳትን እና ትንንሽ እንስሳትን አደናቅፈው ይይዛሉ። ቅጠሎቻቸው ላይ ትናንሽ ስሜት ቀስቃሽ ፀጉሮች ሲነኩ በቅጽበት ተዘግተው ነፍሳቱን በመያዝ መግበዋቸውን ያሟላሉ።
💡 የዛሬው ጥያቄ፡ ከእነዚህ ሦስቱ የበለጠ ያስገረማችሁ የትኛው ነው? አስተ አስተያየታችሁን በኮመንት አጋሩን! 👇
Like❤
Share➾
230
ይሄንን ዜና ሰምተው ነበር? 😂
በኢንዶኔዥያ የሚገኙ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ያዋሉትን ከፍተኛ መጠን ያለው ማሪዋና ከፖሊስ ጣቢያው ውጭ በእሳት ለማቃጠል ወሰኑ። ነገር ግን ጭሱ ወደ መላው መንደር በመሰራጨቱ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ጋዜጠኞች በሙሉ በጭሱ ሰክረው በመንገድ ላይ ሲስቁ እና ሲደሰቱ ውለዋል።
እስኪ ፈገግ ያላችሁ react አድርጉ እጃችሁን ቁርጥማት አይንካው
230
ይሄንን ዜና ሰምተው ነበር? 😂
የየመን የዶሮ አውሮፕላን (1990ዎቹ)
በየመን የሚገኝ አንድ የሀገር ውስጥ አየር መንገድ መንገደኞችን ጭኖ ሊበር ሲዘጋጅ፣ ከአንድ መንገደኛ የሻንጣ ከረጢት ውስጥ ዶሮ አምልጣ በአውሮፕላኑ ውስጥ መብረር ጀመረች። አብራሪውና የበረራ አስተናጋጆቹ ዶሮዋን ለመያዝ ከሁለት ሰዓት በላይ በመታገላቸው በረራው ሙሉ በሙሉ ተሰርዞ ነበር።
230
ይሄንን ዜና ሰምተው ነበር?
የቢቢሲ የኤፕሪል ፉል (April Fools') "የስፓጌቲ ዛፍ" ዜና (1957)
የእንግሊዙ ቢቢሲ (BBC) በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ሰዎች ከዛፍ ላይ "ስፓጌቲ" ሲሰበስቡ የሚያሳይ ምስል አዘጋጅቶ በዜና ማሰራጨቱ፡ ሚሊዮኖች እውነት ነው ብለው በማመናቸው በቴሌቪዥን ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚ እና አዝናኝ ዜና ተብሎ ይጠቀሳል።
230
ይሄንን ዜና ሰምተው ነበር?
የዶሊ በግ ክሎን መደረግ (1996)
በሳይንቲስቶች አማካኝነት "ዶሊ" የተባለችው በግ ከሌላ የበግ ሴል (Cell) በቤተ-ሙከራ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ እንደገና መፈጠሯ (Cloning) በሳይንሱ ዓለም ትልቅ ማዕበል ያስነሳ ዜና ነበር።
230
ሳይንቲስቶች የፀሀይን ገፅታ እጅግ ከፍተኛ ጥራት ባለው ምስል (Highest-resolution) ለመጀመሪያ ጊዜ በካሜራ ማስቀረት ችለዋል። ይህ ምስል የፀሀይን እንግዳ እና ተለዋዋጭ ገፅታ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል።
ተመራማሪዎቹ ይህን እጅግ ሞቃታማ የሆነ የፀሀይ ክፍል ሊያዩ የቻሉት በብሄራዊ የሳይንስ ፋውንዴሽን (NSF) ስር በሚገኘው 'ዳንኤል ኬ. ኢኖይ' (Daniel K. Inouye) በተሰኘው ግዙፍ የፀሀይ ቴሌስኮፕ አማካኝነት ነው።
የሚገርመው ነገር... እነዚህ ፎቶዎች መጀመሪያ ላይ የተነሱት የቴሌስኮፑን የመቅረፅ አቅም ለመሞከር ብቻ ነበር። ነገር ግን ሳይንቲስቶቹ ያልጠበቁትን አስገራሚ ነገር አገኙበት፤ በፀሀይ የውጨኛው ክፍል ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የላባ ቅርፅ ያለው ሞገድ (feathery patterns) ሲያወዛውዝ በምስሉ ላይ ማየት ችለዋል።
ምንጭ፡- Al-Jezira
✍️ቢላል መንግስቴ (የጠቢባኑ ልጅ)
