ar
Feedback
Ethio Pulse

Ethio Pulse

الذهاب إلى القناة على Telegram

እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው። ለማስታወቂያ ስራ - @sehmf Buy ads: https://t.me/sehmf

إظهار المزيد
230
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+67 أيام
+530 أيام
أرشيف المشاركات
ይህንን ያውቃሉ ⁉️ ​ ​የባህር ኦተሮች (Sea Otters) በውሃ ላይ እየተንሳፈፉ በሚተኙበት ወቅት በውሃው ማዕበል ተወስደው እርስ በእርስ እንዳይራራቁ እና እንዳይጠፉ እጅ ለእጅ አጥብቀው ተያይዘ
ይህንን ያውቃሉ ⁉️ ​ ​የባህር ኦተሮች (Sea Otters) በውሃ ላይ እየተንሳፈፉ በሚተኙበት ወቅት በውሃው ማዕበል ተወስደው እርስ በእርስ እንዳይራራቁ እና እንዳይጠፉ እጅ ለእጅ አጥብቀው ተያይዘው ነው የሚተኙት ❤️ .... እነዚህ ፍጥረታት ለህይወት አጋራቸው እና ለልጆቻቸው ያላቸው ፍቅር እና እንክብካቤ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በእንቅልፍ ውስጥ እንኳን ሳይቀሩ እጃቸውን ሳይለቁ ሌሊቱን በሙሉ አብረው ያሳልፋሉ፤ ይህም በተፈጥሮ ውስጥ ከሚታዩ አስደናቂ እና ልብ የሚነኩ የፍቅር መግለጫዎች አንዱ ነው 🦦 @KE_ALEM_DINKADNK @KE_ALEM_DINKADNK

የዓለማችን አ'ስ*ቀ$ያሚ'ዋ ሴት ፥ ሊዚ ቬላስኬዝ ! ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበረች። እንደማንኛውም ወጣት ዩቲዩብ ላይ ስትዘዋወር፣ አንድ ቪዲዮ በአጋጣሚ አይኗ ላይ አረፈ። ርዕሱ "የዓለማችን እጅግ
የዓለማችን አ'ስ*ቀ$ያሚ'ዋ ሴት ፥ ሊዚ ቬላስኬዝ ! ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበረች። እንደማንኛውም ወጣት ዩቲዩብ ላይ ስትዘዋወር፣ አንድ ቪዲዮ በአጋጣሚ አይኗ ላይ አረፈ። ርዕሱ "የዓለማችን እጅግ አስቀያሚዋ ሴት" ይላል። በፍርሃትና በጉጉት ቪዲዮውን ስትከፍተው ግን ያየችውን ማመን አቃታት። በቪዲዮው ላይ የነበረችው ያቺ "አስቀያሚ" የተባለችው ሴት... እሷው ራሷ ነበረች። ያቺ ቅፅበት ለእሷ የዓለም ፍፃሜ ነበረች። ቪዲዮው በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ታይቷል። ጣቶቿ እየተንቀጠቀጡ፣ ልቧ በድንጋጤ እየመታ ወደ አስተያየት መስጫው (comment) ወረደች። ምናልባት አንዲት ነፍስ እንኳን... "ኧረ ተዉ! ይሄ እኮ ስሜት ያለው የሰው ልጅ ነው" ብሎ የተከላከለላት ሰውአልነበረም። አሁንም ከሷ ወገን ሊቆም የሚችል ሰው ይኖራል ብላ ተስፋ አድርጋ ነበር። ነገር ግን አሁንም የገጠማት ልብን የሚያደሙ ፣ ጭካኔ የተሞላባቸው አስተያየቶች ብቻ ነበር። ፈፅሞ አይተዋት የማያውቁ፣ ምን አይነት ሰው እንደሆነች የማያውቁ ሰዎች በመልኳ ተሳለቁ። "ወላጆቿ እንዴት ሊወዷት ቻሉ?" ብለው ያፌዙባትም ነበሩ። አንዳንዶች ደግሞ ባትፈጠር፣ አልያም እራሷን ብታጠፋ እንደሚሻል ሳይሳቀቁ ፃፉላት። ያቺን ለሊት ብቻዋን እንባዋን እያፈሰሰች አነጋች። ህመሟን ለቅርብ ጓደኞቿ እንኳን ማካፈል አልቻለችም። ሊዚ የተወለደችው በሰውነቷ ውስጥ ስብ እንዳይከማች እና ክብደት እንዳትጨምር በሚያደርግ እጅግ ብርቅዬ የዘረመል (Genetic) ህመም ምክንያት ነው። በአንድ አይኗ ማየት አትችልም። ከልጅነቷ ጀምሮ የሰዎች መሳለቂያና መጠቋቆሚያ መሆን አዲስ አልነበረባትም። ያን ሁሉ የጥላቻ ናዳ ካየች በኋላ... ከሰው ፊት መራቅ ትችል ነበር። ዳግመኛ ፊቷን ለማንም ላለማሳየት መወሰንም ትችል ነበር። እሷ ግን ያንን አላደረገችም፤ ይልቁንም፣ ማንም ያልጠበቀውን ነገር አደረገች። ብርቱዋ ሴትካሜራውን ወደ ራሷ አዞረች፤ "ሌሎች ሰዎች መልኬን አይተው ማንነቴን እና ክብሬን እንዲወስኑ አልፈቅድም” ስትል አንድ ትልቅ ውሳኔ ወሰነች። የራሷን የዩቲዩብ ቻናል ከፈተች። ስለ መገለል፣ ስለ በራስ መተማመን፣ እና የሰዎች ጥቂት ክፉ ቃላት እንዴት ለዓመታት በአእምሮ ውስጥ ተቀርፀው እንደሚቀሩ በግልፅ መናገር ጀመረች። ከዚያም በዓለም አቀፉ የTEDx መድረክ ላይ ወጥታ ያንን ታላቅ ጥያቄ ጠየቀች። "ለመሆኑ ራስህን የምትገልፀው በምንድን ነው፣ በሰውነትህ ቅርፅ፣ በህመምህ? በሰዎች ክፉ አስተየት፣ ወይስ አንተን ለማሳነስ በተሰጠህ ስም?" በማለት መሰረታዊና ስሜት ኮርኳሪ ጥያቄዎችን አንስታ ሞገተች።ይህ ጥያቄ አዘል ንግግር በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ ገባ። ዛሬ ላይ ሊዚ ታዋቂ ደራሲ፣ አነቃቂ ተናጋሪ እና የፀረ-ጉልበተኝነት (Anti-bullying) ዘመቻ መሪ ነች። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደርሱ ትንኮሳዎችን ለመከላከል ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ግንባር ቀደም ሆና ትሰራለች። ብርቱዋ ሊዚ ጠንካራ የሆነችው ሰዎች ስለተሳለቁባት ወይም ስለጨከኑባት አይደለም። የሰዎች ጭካኔ፣ ማዋረድና ማንቋሸሽ መቼም ቢሆን የጥንካሬ ምንጭ ሊሆን አይችልም። በማህበራዊ ሚዲያ ጀርባ ተደብቆ አንድን ታዳጊ "ሙት" ማለት፣ ጉዳት አልባ ተራ ቀልድ አይደለም።በአንድ ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እሷን ለማሳነስ እና በእርሷ ላይ ለማፌዝ ቪዲዮዋን ተመልከተው ነበር። ዛሬ ግን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የእሷን ተስፋ ሰጪ ቃላት ለመስማት ይሰበሰባሉ። እንግዳ ሰዎች ዋጋ እንደሌላት ሊያሳምኗት ሞክረው ነበር።እሷ ግን ዓመታትን ሙሉ ለሌሎች ታዳጊዎች "የእናንተ ዋጋ የሚወሰነው በሰዎች ክፉ አስተያየት አይደለም" በማለት አስተማረች። ለጥላቻ ሊሰጥ የሚችለው ትልቁ ምላሽ ምናልባት ይሄው ነው... የጎዱንን ሰዎች አለመምሰል። እኛን ሊሰብሩን የሞከሩበትን ያንኑ ድንጋይ፣ ለሌሎች ሰዎች የመጠጊያ ቤት መገንቢያ አድርጎ መጠቀም!❤️🙏

(ይህን_ያውቃሉ⁉ 🇯🇵 ጃፓን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 አመት በላይ እድሜ ያላቸው የሰዎች ቁጥር 100,000 አልፏል❤ @Amazing_fact_433 @Amazing_fact_433
(ይህን_ያውቃሉ⁉ 🇯🇵 ጃፓን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 አመት በላይ እድሜ ያላቸው የሰዎች ቁጥር 100,000 አልፏል❤ @Amazing_fact_433 @Amazing_fact_433

👬ተመሳሳይ መንትዮች ተመሳሳይ መንትዮችን አግብተው የወለዷቸው ልጆች፡ በአንድ ጊዜ የአክስት/የአጎት ልጆችም ወንድማማቾችም ሆኑ! 🔹🔹🔹 አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩት ብሪታኒ እና ብሪያና የተባሉ ተመሳ
👬ተመሳሳይ መንትዮች ተመሳሳይ መንትዮችን አግብተው የወለዷቸው ልጆች፡ በአንድ ጊዜ የአክስት/የአጎት ልጆችም ወንድማማቾችም ሆኑ! 🔹🔹🔹 አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩት ብሪታኒ እና ብሪያና የተባሉ ተመሳሳይ መንትያ እህቶች ጆሽ እና ጄሬሚ ከተባሉ ተመሳሳይ መንትያ ወንድማማቾች ጋር ትዳር መስረተዋል። በአንድ ላይ ተጋብተው በአንድ ቤት ውስጥ መኖር የጀመሩት እነዚህ ሁለት ባለትዳሮች በተመሳሳይ ጊዜ አካባቢ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወልደዋል። ነገሩን ድንቅ የሚያደርገው ደግሞ የልጆቹ ጄኔቲክስ (DNA) ሁኔታ ነው። በሳይንስ ህግ መሰረት ተመሳሳይ መንትዮች ሙሉ በሙሉ አንድ አይነት DNA አላቸው። በመሆኑም የሁለቱ ህፃናት (ጃክስ እና ጄት) እናቶችም ሆኑ አባቶች አንድ አይነት ዲኤንኤ ስላላቸው፣ ህፃናቱ በህግ የአክስት/የአጎት ልጆች ሲሆኑ በጄኔቲክስ ደረጃ ግን ሙሉ ወንድማማቾች (Quaternary twins) ናቸው። ቤተሰቦቹ በቨርጂኒያ ግዛት በአንድ ግቢ ውስጥ አብረው የሚኖሩ ሲሆን ልጆቹንም እንደ ወንድማማች አድርገው በአንድነት እያሳደጓቸው ይገኛሉ✌ @Amazing_fact_433 @Amazing_fact_433

በአፍሪካዋ ሀገር ቻድ ውስጥ በመዲናዋ ኒጃሚና ከዛሬ ጀምሮ መንገድ ላይ የሚፀዳዱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ጀምራለች። ሰዎቹ ሲያዙ የተፁዳዱበትን ቦታ ራሳቸው በአፈር እንዱሸፍኑ ከተደረጉ በኃላ ወደ
+2
በአፍሪካዋ ሀገር ቻድ ውስጥ በመዲናዋ ኒጃሚና ከዛሬ ጀምሮ መንገድ ላይ የሚፀዳዱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ጀምራለች። ሰዎቹ ሲያዙ የተፁዳዱበትን ቦታ ራሳቸው በአፈር እንዱሸፍኑ ከተደረጉ በኃላ ወደ ፖሊስ ጣብያ እየተወሰዱ ነው 😂 ኤርሚያስ በላይነህ @Amazing_fact_433 @Amazing_fact_433

🐸😳 እንቁራሪቶች እንደ ሌሎች እንስሳት መትፋት (Vomit ) አይችሉም! አንድ እንቁራሪት ጎጂ ወይም የማይፈጭ ነገር ሲውጥ፣ ሆዱን ሙሉ በሙሉ ከአፉ ውስጥ ወደ ውጭ በማውጣት የሆዱን ይዘት ያስወግ
🐸😳 እንቁራሪቶች እንደ ሌሎች እንስሳት መትፋት (Vomit ) አይችሉም! አንድ እንቁራሪት ጎጂ ወይም የማይፈጭ ነገር ሲውጥ፣ ሆዱን ሙሉ በሙሉ ከአፉ ውስጥ ወደ ውጭ በማውጣት የሆዱን ይዘት ያስወግዳል። ከዚያም የፊት እግሮቹን በመጠቀም የሆዱን ይዘት ካስወገደ በኋላ፣ ሆዱን እንደገና ወደ ውስጥ ይመልሰዋል! 🐸🤯 ተፈጥሮ በእውነት አስገራሚ ናት! 🌍

🇮🇹🐶 በጣሊያን የቤት እንስሳን መጣል ወንጀል ነው! በጣሊያን የቤት እንስሳን መንገድ ላይ መጣል ወይም መተው በሕግ የተከለከለ ሲሆን፣ እስከ 1 ዓመት እስራት ወይም ከ5,000 እስከ 10,000
🇮🇹🐶 በጣሊያን የቤት እንስሳን መጣል ወንጀል ነው! በጣሊያን የቤት እንስሳን መንገድ ላይ መጣል ወይም መተው በሕግ የተከለከለ ሲሆን፣ እስከ 1 ዓመት እስራት ወይም ከ5,000 እስከ 10,000 ዩሮ ቅጣት ሊያስከትል ይችላል። 🐾❤️ እንስሳትን መውደድ ብቻ ሳይሆን፣ ኃላፊነትም ነው!

✔️አንዳንድ ጥናቶች እንደሚሉት ከሆነ ከ10 ሰዎች ውስጥ ዘጠኙ "Phantom Vibration Syndrome" እንዳለባቸው ይጠቁማሉ። ይሄ ማለት ስልካቸውን በኪሳቸው አርገው በሚጓዙበት ሰአት ስልካቸው
✔️አንዳንድ ጥናቶች እንደሚሉት ከሆነ ከ10 ሰዎች ውስጥ ዘጠኙ "Phantom Vibration Syndrome" እንዳለባቸው ይጠቁማሉ። ይሄ ማለት ስልካቸውን በኪሳቸው አርገው በሚጓዙበት ሰአት ስልካቸው Vibrate ሳያረግ አእምሮአቸው ግን ስልኬ Vibrate እያረገ ነው ብሎ ስልካቸውን ከፍተው ቼክ እንዲያረጉ የሚያደርጋቸው ነው።ስንቶቻቹ አጋጥሟቸዋል?

✅በአለም ብቸኛው ጥይት የማይበሳው ቆዳ ያለው እንስሳ Pangolin የተሰኘው የዱር እንስሳ ነው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም Ground Pangolin የተሰኘው የዚሁ እንስሳ ዝርያ እንዳለ ይታመናል Sh
✅በአለም ብቸኛው ጥይት የማይበሳው ቆዳ ያለው እንስሳ Pangolin የተሰኘው የዱር እንስሳ ነው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም Ground Pangolin የተሰኘው የዚሁ እንስሳ ዝርያ እንዳለ ይታመናል Share🌍 https://t.me/+tALKv1yeEogyYWY0 https://t.me/+tALKv1yeEogyYWY0

ጭቆና ክፍዎችን ይፈጥራል ! የአዶልፍ ሂትለር ታላቅ ወንድም የአባቱ ጨካኝነትን ለማምለጥ በ13 አመቱ ነበር ከቤቱ በርሮ የጠፋው፡፡ ይህ ልጅ ከቤቱ ከሄደ በኋላ የሂትለር አባት ክፋቱን በሰባት አመቱ
ጭቆና ክፍዎችን ይፈጥራል ! የአዶልፍ ሂትለር ታላቅ ወንድም የአባቱ ጨካኝነትን ለማምለጥ በ13 አመቱ ነበር ከቤቱ በርሮ የጠፋው፡፡ ይህ ልጅ ከቤቱ ከሄደ በኋላ የሂትለር አባት ክፋቱን በሰባት አመቱ ለጋ ልጅ በሂትለር ላይ በእጥፍ ጨመረው፡፡ ሂትለር በአባቱ እጅ አሰቃቂ አመታትን አልፏል፡፡ ምርጫውን ተከልክሎአል፡፡ አርቲስት ለመሆን ይመኝ የነበረው ሂትለር በአባቱ አስገዳጅነት የሲቪል ሰራተኛነት አቅጣጫን እንዲከተል ተገደደ፡፡ የሂትለር ትምህርት ውጤቱ አጥጋቢ ስላልነበር የአባቱን ቁጣ እጅግ አባባሰው፡፡ የአይሁድ ዘር እንዳለበት የሚነገረው የሂትለር አባት ክፋት በሂትለር ልብ ውስጥ አይሁድን የመጥላት ዘርም እንደዘራበት ይነገራል፡፡ አባቱ ከሞተ በኋላ፣ ሂትለር በ13 አመቱ የቤት ሃላፊነትን በጫንቃው ላይ ተሸከመ፡፡ በእናቱ ሞት ምክንያት በኋላ በጉዲፈቻ ያድግ የነበረው ሂትለር ያንን ገቢ በመከልከሉ የጎዳናን ሕይወት ቀምሷል፡፡ በብዙዎች እንደሚታመነው፣ ሂትለር በልጅነቱ ያሳለፈው ስቃይ ውስጡ ከጨመረበት መራራነት እንዳልተላቀቀና በሕይወቱ ያደረጋቸው አሰቃቂ ተግባሮች የዚያ ልምምድ ተጽእኖ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ሂትለር ቢያንስ ለ46 ሚልየን ሰዎች መሞትና ለብዙ ንብረት መውደም ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡ ሂትለር የዚህ ሁሉ ውደመት ምክንያት ከሆነ በኋላ ራሱን በራሱ አጥፍቶ እስኪሞት ድረስ ይህንን እብደቱን የሚከተሉለት ከእርሱ የባሱ እብዶች ፈጽሞ አጥቶ አያውቅም ነበር፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን በተለያዩ ለማንነት ቀውስ (Identity Crisis) አሳልፈው በሚሰጡ ልምምዶች ውስጥ አልፈው ቢያድጉም ከዚያ ሁኔታ በተሳካ መልኩ ራሳቸውን አውጥተው ለሕብረተሰቡ ጠቃሚ ዜጎች ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙዎችን ወደ አንድነት፣ ወደ መከባበርና ወደ አብሮነት የሚያመጡ የመልካም ተጽእኖ ሰዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶች ግን በመራራነት፣ በጥላቻና በአስተዳደግ ዘመናቸው በተጎነጩት የውስጥ ቂም የተቃወሰ ማንነት ይዘው ወደ አመራር ይዘልቃሉ - እንዴት አይነት ስህተት! እንደዚህ አይነት ሰዎች በውስጣቸው ያለባቸው የማንነት ቀውስ ይህ ነው ተብሎ ሊተነበይ የማይችልን ባህሪይ እንዲገልጡ ይነዳቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጠናወታቸው የተቀባይነት ጥማትና የደጋፊ ፍለጋ ናፍቆት ምንም ነገር ከማድረግ እንዳይመለሱ አይኖቻቸውን አሳውሯቸዋል፡፡