ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ
📈 Аналитический обзор Telegram-канала ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ
Канал ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ (@zephilosophy) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 31 568 подписчиков, занимая 2 177 место в категории Религия и духовность и 1 086 место в регионе Эфиопия.
📊 Показатели аудитории и динамика
С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 31 568 подписчиков.
Согласно последним данным от 01 августа, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 360, а за последние 24 часа — 25, при этом общий охват остаётся высоким.
- Статус верификации: Не верифицирован
- Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 19.14%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 6.27% реакций от общего числа подписчиков.
- Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 6 041 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 978 просмотров.
- Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 62.
📝 Описание и контентная политика
Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“✨Philosophy For Higher Consciousness✨”
Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 02 августа, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.
“እግዚአብሄርም አለ፡- ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር አሣዎችንና የሰማይ ወፎችን፤ እንሳሳትንና ምድርን ሁሉ፤ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ፤” (ዘፍ 1፥ 26)
"አላህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያስገዛላችሁ፤ ግልጽና ድብቅ የሆኑትንም ጸጋዎቹን በፊታችሁ ላይ ያፈሰሰላችሁ መሆኑን አታዩምን?" (ቁርአን 31፥20)እንደዚህ አይነት መንፈሳዊ አስተምህሮ እንደ ታሪክ ምሁሩ Lynn White, Jri አመለካከት፣ "የሰውን ልጅ ራሱን ከተፈጥሮ የተገነጠለና የተለየ፤ የፍጥረታት ሁሉ ማዕከልና የሁሉም የበላይ አድርጎ እንዲመለከት በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ " በሃይማኖታዊ አስተምህሮው ከተፈጥሮ ራሱን የገነጠለው አውሮፓ “ተፈጥሮን መቆጣጠርና ማስገበር ” በሚል መርህ ወደሚመራው ካፒታሊስታዊ ስልተምርት ተሸጋገረ፡፡ ካፒታሊዝምም የገበያ ውድድርን በማፋፋምና ከፍላጎት በላይ የሚጠቀም ማህበረሰብን በመፍጠር ተፈጥሮ ላይ የመጨከኑና ከመጠን በላይ የመበዝበዙን መንገድ አጠናክሮ ገፋበት፡፡ እንደ አዲሶቹ ማርክሲስቶች አመለካከት ግን የካፒታሊዝም ጦስ የሰውን ልጅ ከተፈጥሮ በመገንጠል ብቻ አያበቃም፤ "ካፒታሊዝም የሰውን ልጅ ከተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን ከራሱ ሰውነትም ገንጥሎታል፡፡ ካፒታሊዝም የሰውን ልጅ ሃይል በገበያ ብዙ ትርፍ ሊያመጣ እንደሚችል ኢንቨስትመንት በመቁጠር ሰውነትን ወደ ሸቀጥነት ቀይሮታል፡፡" እናም ወደ ሸቀጥነት የተቀየረው ሰው ለተፈጥሮ የሚያዝንበት ህሊና አጣ፡፡ የጥንቱና የምዕራብያውያን ፍልስፍና ዋነኛ ትኩረቱ ሰው ከሚኖርበት አካባቢና ከዲበ አካላዊው (ከሰማያዊው) ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያስስ ነበር፡፡ እውነትንና እውቀትን፤ ውበትንና የሕይወት ትርጉምን ሁሉ በዚህ ሂደት ውስጥ ለማግኘት ይሞክር ነበር፡፡ ይሄም ሂደት ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን ጥብቅ ቁርኝት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ የጥንቱ አውሮፓዊነት ከተፈጥሮ ጋር መቃቃር የጀመረው ግን ራሱን ከተፈጥሮ ሁሉ የበላይ አድርጎ መመልከት ሲጀመር ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ትምክህታዊ አመለካከት እንዲይዝ ካደረጉት አስተምህሮቶች ውስጥ ዋነኛው ደግሞ ክርስትና ነው፡፡ " የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።" መዝሙረ ዳዊት 115፥16 ክርስትና (እና እስልምና) እግዚአብሄር ምድርን ለሰው ልጅ መጠቀሚያ እንደፈጠረ በማስተማር የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን ህብረትና ጓደኝነት ቆረጡት፡፡ አውሮፓዊነትም በዚህ የክርስትና አስተምህሮ ተጠልፎ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግንኙነት ከሁለንተናዊ ህብርነት ወደ ገዥና ተገዥ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ፣ መለኮታዊና አለማዊ ወደሆነ “ቁጥጥር እና ጥቅም”ን ታሳቢ ወዳደረገ የሁለትዮሽ ግንኙነት ተቀየረ፡፡ የኒውተን ሜካኒክስ እንዲሁም የሆብስ፣ የላሜትሪ እና የዴካርት ፍልስፍናዎች መሰረታቸው ይሄው በሰውና በተፈጥሮ መካከል ያለው የበላይነትና የበታችነት የሁለትዮሽ ግንኙነት ነው፡፡ እነሱ የሚመኩበት “የምክንያታዊነት” እና “ተፈጥሮን በመቆጣጠር የማስገበር” አካሄድ መጨረሻ ላይ የምድራችንንና አጠቃላይ የሰውን ልጅ ህልውና የከፋ አደጋ ላይ ጣለው፡፡ አውሮፓዊነት ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን የስሜት ቁርኝት ትቶ የተጓዘበት መንገድ መጨረሻው ተፈጥሮን በማምከን የሰውን ልጅ ለከፋ አደጋ ዳረገው፡፡ 📖ፍልስፍና -2 ✍️ ብሩህ አለምነህ @zephilosophy
