ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

AALTO -አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

AALTO -አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Открыть в Telegram
7 361
Подписчики
+124 часа
+407 дней
+13030 дней
Архив постов
1104,2017 VAT ስለመመዝገብ የወጣ መመሪያ.pdf3.04 MB

1434_2026_የታክስ_አስተዳደር_አወጅ_የተሻሻለው.pdf8.58 KB

መስከረም 20/2019 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ግብር ዘመን የማሳወቂያ ጊዜን አስመልክቶ በኦንላይን እንዴት ማሳወቅ እንዳለባቸው እና ሲያሳውቁ ማያያዝ ስላ
+5
መስከረም  20/2019 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከፍተኛ  ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ግብር ዘመን  የማሳወቂያ ጊዜን አስመልክቶ በኦንላይን እንዴት ማሳወቅ እንዳለባቸው እና ሲያሳውቁ ማያያዝ ስላለባቸው ማስረጃዎችን በተመለከተ ለ6ኛ ዙር ሰልጣኝ ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡   የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ የስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገበየሁ አካለወልድ ከግብር አሰባሰብ ሂደት አንጻር ግብር ከፋዮች ሊኖራቸዉ ስለሚገባ መብትና መወጣት ስላለባቸዉ ግዴታ ከስነ ምግባር ጋር በማያያዝ ለግብር ከፋዮቹ ገለጻ በማድረግ የታክስ ህጋዊ አሰራርን ብቻ በመከተል የመፈለግባቸዉን ግዴታ በወቅቱ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ግብይት ድጋፍና ክትትል የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሰዒድ መሐመድ ግብር ከፋዮች በቅድመ ኦዲት ወቅት አሟልተዉ ማቅረብ ያለባቸዉን ህጋዊ ሰነዶች እና  ከእያንዳንዱ ዘርፍ የሚጠበቀው ማስረጃ ምን ምን እንደሆነ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል  የ2018 ግብር ዘመን  ዓመታዊ ግብራቸውን በአዲሱ የግብር ማሳወቂያ ቅጽ  ለማሳወቅ በኦንላይን ምን ምን ውስጥ እንደሚያስገቡ በሰነድ በማስደገፍ ስልጠናውን የሰጡት የግብር አወሳሰን የስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት  አቶ ኤርሚያስ ጌታነህ  ሲሆኑ ስልጠናውን ይበልጥ  ግልጽ ለማድረግ ናሙና በመዉሰድ አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም በቀረቡት የስልጠና ርዕሶች ላይ  ከግብር ከፋዮች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች በመድረኩ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡  የላቀ ገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና!