ru
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

Открыть в Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

Больше
1 719
Подписчики
-124 часа
-47 дней
-1430 день
Архив постов
የማይቆሙ ድምጾች - ሰይፈ ተማም.aac1.18 MB

አወይ አንቺ አወይ እኔ አንቺ ማለት’ኮ የሌሊት ጨረቃ ሰስቼ የማይሽ እንደ ድንቡሽ ጮርቃ … አንቺ ማለትማ የቀትር ፀሃይ ደፍሬ ‘ማላይሽ ያላንቺም አላይ ..እያልኩኝ ሳወድስ እኔ ማለት ለካ ምድጃ ሟቂ ነኝ የነደደ ክሰል ባመድ በተተካ @seifetemam #seifetemam

Seife Temam: እንዋዋል ስንቱን ውሎ ስንቱን አዳር ስንቱን ፍቅር ስንቱን አሳር ስንቱን ገድለን ስንቱን አስረን ስንቱን ቀብረን ስንቱን አምነን በአንዲት ቅጠል እንጠለል ከማን አብረን እንገንጠል ከማን እንሂድ ከማን እንዋል ማን ይፈርም እንዋዋል? @seifetemam #seifetemam

✍...ብዕር ለ ግጥም እጆች ሁሉ ይፅፋሉ ዓይኖች ሁሉ ያነባሉ ጆሮዎች ሁሉ ይሰማሉ Join ያርጉ ☞ https://t.me/joinchat/C_70PQ0-ZY4kCH214gXV2Q
✍...ብዕር ለ ግጥም እጆች ሁሉ ይፅፋሉ ዓይኖች ሁሉ ያነባሉ ጆሮዎች ሁሉ ይሰማሉ Join ያርጉ ☞ https://t.me/joinchat/C_70PQ0-ZY4kCH214gXV2Q

አንዷ መንገድ አንዲት መስመርብቻ በዓይኔ ፊት አለች ደሞም ከሷ ውጪ ችክችክ እና ድልዝ ለንባብ አይመች ይቺ ደማቅ መስመር ይቺ ደማቅ መንገድ እራሷን ዘርግታ ወደራሷ ምትወስድ እራሷን አንድዳ ነድዳ ‘ምትማገድ ይኧው ከሷ ውጪ ቅዠት ነው ድንብርብር ሰልፍ የሳተ ጉንዳን የማይቀድስ ደብር ጭስ የሌለው እጣን የሚያሳስቅ ቀብር የሚታለም እውን የሚላፋ ነብር እውነትን ፈለኳት እንኋት ደማምቃ አየኋት ሳልለፋ በመስመሯ መጥቃ በጉልህ ተጽፋ ማተርኩ ወደ ፍቅር ትታያለች ዘልጋ ክረምቱንም በጋ ሌሊቱን ቀን አርጋ መስመሯን አፍቅራ ፍቅር መስመር ፈጥራ ባ’ለም ካለው ሁሉ በጎውን ተመኘው በአንድነት አንድ ሁኖ አንዲት መስመር ላይ ነው ከዛች መስመር ውጭ ሁሉ ችክችክ ሁሉ ድልዝ ለንባብ አይመች እውን አልባ ውጥንቅጥ የ’ልም አለም አደንዛዥ ያለ መስሎ ሚያጥጥ ሰው በቁም ‘ሚያስቃዥ ያባይ ስጋ ቅጥቅጥ የበረሃ ሚራዥ 2008 @seifetemam #seifetemam

አጣምሮ ማጨብጨብ.aac9.10 KB

የኔ ክረምት የከረረን ጽልመት በምናቤ ሳክም በከረረ ክረምት በነጠላ ሳዘግም ጽልመቱም አልነጋ ክረምቱም አልባተ ልቤን ከገላዬ መለየት አቃተ @seifetemam #seifetemam

አበቦቹ ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች የብራ አለም ሰዎች የንጹህ አገር ዜጎች ለሃሴት አፎቱ ለፍቅርም ቤቱ ውበት ምልክቱ . . . ትናንሽ አበቦች. . . እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ ውስጠትን ሰርሳሪ በውበት አሳሪ. . . እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ (ለልጆቻችን. . .) #seifetemam @seifetemam

Seife Temam: አቻ ቃላት ሳታረቁ ነገር ሳታደቁ ያላቻ ጋብቻ ይቅር ብሎ ብቻ አቻ ደሃ አጥተን ይኸው ቆመን ቀረን ሰይፈ ተማም 2007 #seifetemam @TONETOR @TONETOR @TONETOR

አቻ ቃላት ሳታረቁ ነገር ሳታደቁ ያላቻ ጋብቻ ይቅር ብሎ ብቻ አቻ ደሃ አጥተን ይኸው ቆመን ቀረን ሰይፈ ተማም 2007 #seifetemam

ለአከራዬ ልጅ መብራት የጠፋ ለት ሻማ ስታበሪ ጥላሽን አየሁት ልብስ ስትቀይሪ ልብስ የምታጥቢም ለት ጨምረሽ ከሳፋ (መብራትስ ሁሌ ይሂድ ውሃ ግን አትጥፋ) ጦረኞቹን አየሁ ሲሉ ቀና ደፋ ቀና ደፋ እያልኩኝ ስሰራ የምታይ እንዳያልፍብኝ ነው የናትሽ ቤት ኪራይ ቤት ኪራይ ፍለጋ ጊቢያችሁ ስመጣ አንቺን ብዬ ከፈልኩ ቤቱስ አያዋጣ አያዋጣም ከቶ 'ማይከለል መስኮት የማይዘጋ በር እናትሽ ሲወጡ ካልመጣሽ በስተቀር #seifetemam #አሁን @seifetemam @seifetemam

1.98 KB

ድምጽ፣ ሽታ፣ ጣዕም ምስኪኑ ሰአሊ በወጠረው ሸራ የሳላት ጉራንጉር የሳላት መንደሯ ድምጽ የላትም ጭራሽ ምኗም አይሰማም ድምጽ ቀለም ሆኖ ከሸራው ላይ የለም እነማማ እንትና ሰውን ሲቦጭቁ እነ ጋሽ እከሌ አዳልጧቸው ሲወድቁ ወይዘሮ እከሊት ጠበል ሲጠድቁ የተሰማው ሁሉ የለም ከቀለሙ የተጠጣው አቦል ከየት አለ ጣ'ሙ ከየት አለ ሽታው የቡናው የጣኑ ድምጽ ሽታ ጣዕም በቀለም አይወጡም በብሩሽ አይሰፍሩም ወይስ አይን የለም እነዚን ለማስፈር ከሸራ አይን የለም እኒህን ለማየት ከሸራ ምስኪኑ ሰዓሊ የሳላት መንደሯ ስንቱን እንዳወጣች ስንቱን ነገር ቀብራ ወይም ድምጽ ሽታ ጣዕም ከዚህ ሰፈር የሉም አይሰሙ አይሸቱ ጨርሶም አይጥሙም እንደድሮ አይደሉም ወይም... ወይም ይጮሃሉ ወይም የገማሉ ወይም ይመርራሉ ድምጽ ሽታ ጣዕም ኑሮነን እያሉ ባለመሳል መስመር ሁሌ እየተሳሉ #seifetemam #ድምጽሽታጣዕም

ፍቅርና ደሞዝ ስራ ተቀጥሬ ከዋክብት ቆጠራ እጅግ አደከመኝ እንዴት ብዬ ልስራ ቆጥሬ ቆጥሬ እየተምታታብኝ አልሰራህም ብለው ደሞዝ ከለከሉኝ ስራዬ ፍቅር ነው ከዋክብት ውበቷ ደሞዜም እሷው ነች በጄየገባች ለታ (ለ...) ሰይፈ ተማም 1996

ውዴ ፦ እንደኔ ያለ አፍቃሪ እንደኔ ያለ ፈሪ ቃላት ካፉ ጠፍቶ ሚናገረው አጥቶ ለፍቅር እጁን ሰጥቶ ጉልበት ተቀምቶ ስርሽ ተጎልቶ ዐይን ዐይንሽን ሲያይ ቀናት በጊዜ ቦይ ዘመን ሆነው አለፉ ጨረቃና ፀሐይ በቀን ተቃቀፉ። አጠገቤ እያለሽ ከዘመናት ርቀሽ ጠፈር ሆነሽ ሰማይ ምስልሽን ስጠብቅ አንጋጥጬ ወደላይ ቀኑን አጨልመው ጉዳቸው እንዳይታይ ከንፈር ይጋራሉ ጨረቃና ፀሐይ። @TONETOR @TONETOR @TONETOR

ሃሞተ ቢስ ጀግና ዛሬ አዲስ አባ ውስጥ ብዙ ሰው መሮታል አፉ ሬት ሆኖታል የሚጠጣው ድራፍት መሪር እንደጅኑ እንደጠላው ሁሉ የሚበላውም ጫት መሪር እንደኑሮ የሚጣፍጥ መርሮ ይህን ጀግና ትውልድ እንደው በለበጣ ሃሞተ ቢስ አሉት ሃሞት እየበላ ሃሞት እየጠጣ #seifetemam

ባንቺ መንቃት ፈዝዘሃል አትበሉኝ ነቅቻለሁ በጣም ከዓይኔ 'ሚገባ የሚታይ ሰው ባጣም ስለሷ አስባለሁ እጅጉን ታትሬ መኖሯን ለከርሞ ማደሯን ለዛሬ #seifetemam

ምርጫ ==== ቤት ሥራ ፤ ተፈንከት ምርጫው የራስህ ነው ድንጋይ ሲወረወር አናትህን ስትባል ግንባር እየሰጠህ ሕይወትህን ማማረር? ወይ እየጠራረብህ በልክ እየሰተርህ ግንብህን ማበጀት አጥርህን መደርደር #የጌታነህ_ልጅ ነሐሴ 2009

አቋራጭ የኔን መጥፎ 'ሚሻ መሆኑን እያየሁ እንዴት እንደራሴ ጠላቴን ልውደደው … ይልቅስ… ከቃሉ እንዳልወጣ እንዳይቀየመኝ እራሴን ጠልቼ ጠላቴን ባልወደው አቋራጭ መሰለኝ ሰይፈ ተማም 2004 #seifetemam #አቋራጭ

ቀለበቱ ዋለ አሉኝ ከጣትሽ ገድሎ ከሚያስውበው ሊለኝ ፈለገና አንተ የልቧ ነህ እሱማ የጣቷ ነው #seifetemam