ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
前往频道在 Telegram
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
显示更多1 676
订阅者
-124 小时
-17 天
-1630 天
帖子存档
መሄድሽን ሳስብ
ከህይወቴ መሄድሽ እኔን ግን አመጣኝ
ከፍቅር መዝገብ ላይ ሰው ሁሉ እንዳላጣኝ
መሄድሽ አልከፋም ፍቅር ላይ ካሰጣኝ
ማነው ያለው ሆዴ?
ከህይወቴ ስቴጂ ይጠፋል ወይ ገዴ?
ያላንቺ ተሳትፎ አይደምቅም መውደዴ?
ማነው ያለው ከቶ ኧረ ማነው እንዴ?
መምጣትሽን ሳስብ የፀዳው ደረጃ
ላንቺ ክብር ነፅቷል በያ በሱ ሂጃ
ሰው አለምድም አልል የነገን እኔእንጃ
መምጣትሽ ያመጣኝ መሄድሽ ያልገታኝ
የመውደድ ታላቁ የፍቅር ኩረጃ
ሆኜልሽ አለሁኝ
መሄድሽን ሳስብ መታነበር ያልኩኝ
ስትሄጂ ቀርቶ ሳቴጂም ነይና
መውደዴን ላስኪደው ቀና አርጊኝ ቀና
በሰማይ በምድሩ እንዳንቺ ባይኖርም
በሳር በቅጠሉ ስምሽን ባትምም
መሄድ አስደስቶት እግርሽም ቢያዘግም
መምጣትሽ ባነቃው ይህ ቀጥቃጣ ቀልቤ
መሄድሽ ሊያሰኬደኝ እጅግ ተቃርቤ
ስንብት በእጄ ፍቅርን ግን በልቤ
…..
መሄድሽን ሳስብ እንደህ ነው አንቺ ሴት
መሄድሽ አይደል ወይ ያረጋገጠለት
የኔም ልብ እንደሰው ፍቅር እንዳለበት
@seifetemam #seifetemam
መምጣትሽን ሳስስብ
ህይወቴ መምጣትሽ እኔኑ አምጥቶኝ
መምጣትሽን ሳስብ እኔው ነኝ የመጣሁ
ደረጃ ወልውዬ ኩሽናውን ኮሻኝ
እዚህ እሚያመጣኝ ፈልጌ እንዳላጣሁ
መምጣትሽን ሳስብ መምጣትሽ ተሰማኝ
አገር እንደሰጡት
አደብ እንደነሱት
ከሰማያት መርጠው አንዱን እንደቸሩት
ለዛውም በጥምቀት
እንዳሽሞነሞኑት
́ሚያደርገኝ ፍቅርሽ ሲመጣ ተሰማኝ
አቴጂበት ነገር ውጅንብር ጎዳና
ካይኖችሽ ታየቶኛል ያለሽበት ቀና
መጣሁ ስትይቀርቶ ሳትመጪም ነይና
መምጣቴን ላምጣልሽ ቀና በዪቀና
ስትመጪም ነይና ከከንፈርሽ ላውጋ
ስትመጪም ነይና አይንሽን አይኔጋ
ጣ́ምሽን ጣ́ሜ ጋ
ጎህ እስከሚናጋ
መምጣትሽን ሳስብ እንደዚህ ነው ሆዴ
መምጣትሽ አይደል ወይ መምጣትሽን መውደዴ
@seifetemam #seifetemam
ገራገር ገል
የተሰበረ ገል
ለጋ ገር ገራገር
ያልቦረቀ ግልገል
ካ'ለም ጋር ሲታገል
'ራሱን ያገኘው
በመከራ ነበር
መከራም ያጠናው
አልነቃም ሲነከር
ሰይፈ 2008
@seifetemam #seifetemam
ስህተቴ
ያለፈውን ትቼ ከአሁን ጋር ለመኖር
ከራሴ ስማከር
'አሁን' ጣዕም አለው ልብን የሚያሰክር
'አሁን' እውነታ ነው አለምን የሚያስር
ብዬ ፎከርኩና ትናንትናን ትቼ
ወደ ዛሬ መጣሁ ካለፈው ወጥቼ
የሰበሰብኩትን ሳልይዘው በእጆቼ
ግን በግዜ ቀመር ከቀደመው ሁሉ
ዕልፍ እና ዐዕላፍ ጥቅሞች ነበሩ
… … … ስህተት የሚባሉ
@seifetemam #seifetemam
ኋላ የቀረን ኋለኞች
“ፊተኞች ኋለኞች … ‘’
ልክነው አምነናል
ከፊት የነበርነው
ከኋላ ቀርተናል
ግና ይህ ሰልፍችን
ምነው ግፉ በዛ
መጨረሻ ስንቆም
ፊት አንሆንም ‘ሳ
@seifetemam #seifetemam
2008
አወይ አንቺ አወይ እኔ
አንቺ ማለት’ኮ የሌሊት ጨረቃ
ሰስቼ የማይሽ እንደ ድንቡሽ ጮርቃ
… አንቺ ማለትማ የቀትር ፀሃይ
ደፍሬ ‘ማላይሽ ያላንቺም አላይ
..እያልኩኝ ሳወድስ እኔ ማለት ለካ
ምድጃ ሟቂ ነኝ
የነደደ ክሰል ባመድ በተተካ
@seifetemam #seifetemam
Seife Temam:
እንዋዋል
ስንቱን ውሎ
ስንቱን አዳር
ስንቱን ፍቅር
ስንቱን አሳር
ስንቱን ገድለን
ስንቱን አስረን
ስንቱን ቀብረን
ስንቱን አምነን
በአንዲት ቅጠል እንጠለል
ከማን አብረን እንገንጠል
ከማን እንሂድ ከማን እንዋል
ማን ይፈርም እንዋዋል?
@seifetemam #seifetemam
✍...ብዕር ለ ግጥም
እጆች ሁሉ ይፅፋሉ
ዓይኖች ሁሉ ያነባሉ
ጆሮዎች ሁሉ ይሰማሉ
Join ያርጉ
☞ https://t.me/joinchat/C_70PQ0-ZY4kCH214gXV2Q
አንዷ መንገድ
አንዲት መስመርብቻ
በዓይኔ ፊት አለች
ደሞም ከሷ ውጪ
ችክችክ እና ድልዝ
ለንባብ አይመች
ይቺ ደማቅ መስመር
ይቺ ደማቅ መንገድ
እራሷን ዘርግታ
ወደራሷ ምትወስድ
እራሷን አንድዳ
ነድዳ ‘ምትማገድ
ይኧው ከሷ ውጪ
ቅዠት ነው ድንብርብር
ሰልፍ የሳተ ጉንዳን
የማይቀድስ ደብር
ጭስ የሌለው እጣን
የሚያሳስቅ ቀብር
የሚታለም እውን
የሚላፋ ነብር
እውነትን ፈለኳት
እንኋት ደማምቃ
አየኋት ሳልለፋ
በመስመሯ መጥቃ
በጉልህ ተጽፋ
ማተርኩ ወደ ፍቅር
ትታያለች ዘልጋ
ክረምቱንም በጋ
ሌሊቱን ቀን አርጋ
መስመሯን አፍቅራ
ፍቅር መስመር ፈጥራ
ባ’ለም ካለው ሁሉ
በጎውን ተመኘው
በአንድነት አንድ ሁኖ
አንዲት መስመር ላይ ነው
ከዛች መስመር ውጭ
ሁሉ ችክችክ ሁሉ ድልዝ
ለንባብ አይመች
እውን አልባ ውጥንቅጥ
የ’ልም አለም አደንዛዥ
ያለ መስሎ ሚያጥጥ
ሰው በቁም ‘ሚያስቃዥ
ያባይ ስጋ ቅጥቅጥ
የበረሃ ሚራዥ
2008
@seifetemam #seifetemam
የኔ ክረምት
የከረረን ጽልመት
በምናቤ ሳክም
በከረረ ክረምት
በነጠላ ሳዘግም
ጽልመቱም አልነጋ ክረምቱም አልባተ
ልቤን ከገላዬ መለየት አቃተ
@seifetemam
#seifetemam
አበቦቹ
ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች
የብራ አለም ሰዎች
የንጹህ አገር ዜጎች
ለሃሴት አፎቱ
ለፍቅርም ቤቱ
ውበት ምልክቱ
. . . ትናንሽ አበቦች. . .
እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ
እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ
ውስጠትን ሰርሳሪ
በውበት አሳሪ. . .
እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ
እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ
ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ
(ለልጆቻችን. . .)
#seifetemam
@seifetemam
አቻ
ቃላት ሳታረቁ
ነገር ሳታደቁ
ያላቻ ጋብቻ
ይቅር ብሎ ብቻ
አቻ ደሃ አጥተን
ይኸው ቆመን ቀረን
ሰይፈ ተማም
2007
#seifetemam
ለአከራዬ ልጅ
መብራት የጠፋ ለት ሻማ ስታበሪ
ጥላሽን አየሁት ልብስ ስትቀይሪ
ልብስ የምታጥቢም ለት ጨምረሽ ከሳፋ
(መብራትስ ሁሌ ይሂድ ውሃ ግን አትጥፋ)
ጦረኞቹን አየሁ ሲሉ ቀና ደፋ
ቀና ደፋ እያልኩኝ ስሰራ የምታይ
እንዳያልፍብኝ ነው የናትሽ ቤት ኪራይ
ቤት ኪራይ ፍለጋ ጊቢያችሁ ስመጣ
አንቺን ብዬ ከፈልኩ ቤቱስ አያዋጣ
አያዋጣም ከቶ 'ማይከለል መስኮት የማይዘጋ በር
እናትሽ ሲወጡ ካልመጣሽ በስተቀር
#seifetemam #አሁን
@seifetemam @seifetemam
ድምጽ፣ ሽታ፣ ጣዕም
ምስኪኑ ሰአሊ በወጠረው ሸራ
የሳላት ጉራንጉር የሳላት መንደሯ
ድምጽ የላትም ጭራሽ
ምኗም አይሰማም
ድምጽ ቀለም ሆኖ ከሸራው ላይ የለም
እነማማ እንትና ሰውን ሲቦጭቁ
እነ ጋሽ እከሌ አዳልጧቸው ሲወድቁ
ወይዘሮ እከሊት ጠበል ሲጠድቁ
የተሰማው ሁሉ የለም ከቀለሙ
የተጠጣው አቦል ከየት አለ ጣ'ሙ
ከየት አለ ሽታው የቡናው የጣኑ
ድምጽ ሽታ ጣዕም
በቀለም አይወጡም
በብሩሽ አይሰፍሩም
ወይስ
አይን የለም እነዚን ለማስፈር ከሸራ
አይን የለም እኒህን ለማየት ከሸራ
ምስኪኑ ሰዓሊ የሳላት መንደሯ
ስንቱን እንዳወጣች ስንቱን ነገር ቀብራ
ወይም
ድምጽ ሽታ ጣዕም ከዚህ ሰፈር የሉም
አይሰሙ አይሸቱ ጨርሶም አይጥሙም
እንደድሮ አይደሉም
ወይም...
ወይም ይጮሃሉ
ወይም የገማሉ
ወይም ይመርራሉ
ድምጽ ሽታ ጣዕም ኑሮነን እያሉ
ባለመሳል መስመር ሁሌ እየተሳሉ
#seifetemam #ድምጽሽታጣዕም
ፍቅርና ደሞዝ
ስራ ተቀጥሬ ከዋክብት ቆጠራ
እጅግ አደከመኝ እንዴት ብዬ ልስራ
ቆጥሬ ቆጥሬ እየተምታታብኝ
አልሰራህም ብለው ደሞዝ ከለከሉኝ
ስራዬ ፍቅር ነው ከዋክብት ውበቷ
ደሞዜም እሷው ነች በጄየገባች ለታ
(ለ...)
ሰይፈ ተማም 1996
