الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Открыть в Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
2 158
Подписчики
Нет данных24 часа
+1817 дней
+41530 дней
Архив постов
الســــــــــــــــلام علـــــــــــــيكم ورحمــــــــــــــــته الله وبركــــــــــــــــــته
🔴የኪታብ ዐቂደቱል_ዋሲጢያህ ደርስ
ክፍል ❻❺
አዲስ ተከታታይ ደርስ
ተ
ጀ
መ
ረ
🎙«በወንድም አቡ ዓማር» ሓፊዘሁ'ሏህ
የስርጭት ሊንክ
╭┈───────
╰┈➤ t.me/MERKEZ_ZUN_NUREYIN
ወዴ ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Abu_Amar_Mohammed ወዴ youtub ተቀላቀሉ https://youtu.be/CuBTgg1gaEM?si=xEoyyJbwpYAQvoU_ 👆👆👆👆👆👆👆
ጎደኛዬ
ታማኝ እውነተኛ ገመና ጠባቂ
ችግርን ተካፋይ ሚስጥርን አጥባቂ
መስታወት ካልሆነ ስህተትን የሚያሳይ
ለመወደድ ብለሽ ያልሆንሽው አስመሳይ
እግሬን አልመራሽው በሀራም መንገድ ላይ
ቃሌ ነው ውዴዋ መቸም ላንለያይ
ስረሳው አስታዋሽ የነገውን ቤቴን
አታሳይ ያልሽኝ መላው አካላቴን
በሂጃብ አስውበሽ ሙሉ ሰውነቴን
ሂጃብ የሾፈንሽው የኢስላም ውበቴን
ጓደኛዬ አልልሽ ያንስብሻል ቃላት
እህቴ ልበልሽ የጀነት ጎረቢት
ስላንች ላወራ ብእሬን አዘጋጀሁ
ግን አንችን የሚገልፅ ፍፁም ቃላት አጣሁ
ዉዷ ጎደኛየ የኔ ጣፋጭ ቅመም
የተውሂዷ ጀግና የሙሽሪኮች ህመም
በአሏህ ትዕዛዝ በነብዩ መንገድ
ፀንታ የበረታች የማትወላገድ
በአቋሟ ብርቱ የማትርገደገድ
በኢልም ጅማሮ ህልሟን የሰነቀች
አሊፍ .ባ .ታ. ብላ ቁርአን ያኸተመች
የመንሀጅ እህቴ የሱናዋ ኮኮብ
ቁርአንን የቀራች ጠይክራ በማንበብ
እጅግ ያስደስታል ለፍቶ ውጤት ማምጣት
በሶብር ላይ ቆሞ ችግር ችሎ መግፋት
በአሏህ ታግዞ በስኬት ላይ መውጣት
የቁርአን ሰወች ከተባሉት ተርታ
ቅድሚያ ተሰለፊ በደጅም ኮረብታ
ለኢስላምሽ ታገይ በያዝሽው እውቀትሽ
በሱናሽ ላይ በርች ሀፊዝ ይጠብቅሽ
በሰለፎች መንሀጅ በስኬቱ አውድማ
በነብያት ፈለግ በመርከቡ ማማ
በቁጥብ እናትሽ በነማሬም ካስማ
ምሳሌን ውሰጂ ታሪክን ከአሲያ
የአሏህን ቃል ያዢ ተቀበይ ወሲያ
ከምወድሽ ጎደኛሽ ኡሙ ሓቲም
ለዉዷ ጎደኛየ ኡሙ አፊፋ እወድሻለሁ🫶
የዘዋጆች የወሬ ማጣፈጫቸው ቁጥር 1 ) ላጤወችን ነካ ነካ በማድረግ ነው በቃ ላጤወች ማሻአሏህ በየትኛውም ጓዳ ሁኑ የሚረሳቹህ የለም ታድላቹህ ትልቅ የሰርግ ድግስ ውስጥ ራሱ የሌጤወች ስም በግጥምም ይሁን ብቻ በአይ ጠሪቃ ይወሳል ታዳ ሆ .......✍️ ልል የፈለኩት ገብቷቹሀል 🕶🕶 ጨርሱት 👌👌
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
! ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
በኢስላም አንድ ወንድ ከቻለ እስከ ስንት ማግባት ይቻላል ?
የለሊቱ የመጨረሻው ክፍል [አሏህ ማነው የሚለምነኝ መርሀባ የምለው ]የሚልበት ሰአት ላይ ነን ንቁ ጀዋላቹሁን ኖር አርጉና ትንሽየ ደቂቃወች ወደአሏህ ተቃረቡ ዱዓ የማይመልሰው በላዕ ያማያስተካክለው ጉዳይ የለምና እስኪ እኔንም አስቡኝ በዱአቹህ💧💧መላአክትም ላቺም ላተም በማለት ዱአ ያደርጉላቹሀል✅
قم صلّ ركعتين في جوف الليل، واخلع هموم الدنيا من قلبك، واقترب من ربك بالخضوع والدعاء؛ فإنه ينزل كل ليلة إلى السماء الدنيا يقول: "هل من داعٍ فأستجيب له
የአህባሽ ትጥቅ ይሄው ቅጠል ነው ወንድሜ 👌👌
አህባሽ የድን አፍራሽ
ማህበረሰብ ትውልድ አበላሽ
✍ ፈፅሞ አትሁን አህባሽ🕶
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
📚ኪታብ በነፃ መማር የሚፈልግ ብቻ 🎊
በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ በሪከርድ ማስተማር ተጀመረ 🌛
እንዳያመልጣቺሁ 🇪🇹
ቀጥታ ስርጪት ተጀምሯል ግቡ📢📢📢
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
ዱኒያ እና እኛ እንደዚህ ነን⤵️
عْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الأَمْوَالِ وَالأَوْلَادِ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا وَفِي الآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ وَمَا الحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلاَّ مَتَاعُ الغُرُورِ
ቅርቢቱ ህይወት ጨዋታና ዛዛታ? ማጌጫም! በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናብ ፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ናት! በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት እና ምህረትና ውዴታ ከአሏህ አለ፡፡ የቅርቢቱም ህይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም⤵️⤵️
ማጌጥ እና መመፃደቅ (زِينَةٌ وتَفَاخُرٌ): አሁን ባለንበት ዘመን ሰዎች በውጫዊ መልካቸው በለበሱት ውድ ልብስ! በሚነዱት መኪና እና በሚኖሩበት ውብ ቤት እርስ በእርሳቸው ይወዳደራሉ ይኩራራሉ። ማህበራዊ ሚዲያ የዚህ መገለጫ ዋና መድረክ ሆኗል።⤵️⤵️
መጫወት እና መዘናጋት ዛዛታ ? (لعِبٌ ولَهوٌ): ዛሬ ላይ የሰው ልጅ ጊዜውን በአብዛሀኛው የምናጠፋው በአላማ ቢስ ነገሮች? መዝናኛዎች እና ከዋናው የህይወት እውነታ ዘና በማለት ነው። ሶሻል ሚዲያ! አላስፈላጊ ውሎዎች እና ከንቱ ነገሮች የዘመኑንሰው ጊዜ ይበሉታል።
⚠️አንዲት ሴት እንዲህ ስትል ጠየቀች፦ "የተከበሩ ሸይኽ ! ለምንድነው ኢስላም እኛን ለባሎቻችን እንድንታዘዝ ያስገደደን፤ ባሎችን ግን ለእኛ እንዲታዘዙ ያላደረገው?"
🌟 ሸይኹም እንዲህ አሏት፦ "ስንት ልጆች አሉሽ?" እርሷም፦ "ሦስት ልጆች አሉኝ" ስትል መለሰችላቸው
🌟 በዚህ ጊዜ ሸይኹ እንዲህ አሏት፦ "አላህ (سبحانه وتعالى) አንቺን ለአንድ ወንድ (ለባልሽ) ብቻ እንድትታዘዢ
አዘዘሽ። ለእነዚያ ለሦስቱ ወንዶች (ለልጆችሽ) ግን አንቺን እንዲታዘዙሽ አዘዛቸው። አንቺን ካልታዘዙሽና ስነ-ምግባራቸውን አሳምረው ካልያዙሽ በስተቀር ጀነት በፍጹም አይገቡም
🌟 ታዲያ ብልጫውና ትርፉ በማን በኩል ሆነ? ስጦታውስ ለማን በዛ?" አሏት። ሴቲቱም በታላቅ እርካታ ተሞልታ፦ "በኢስላም ጸጋ ላይ አላህ (سبحانه وتعالى) ምስጋና ይገባው" በማለት መለሰች
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
.
ያለ መድሀኒት ተኝተን ያለ ህመም ያለ ድካም ከተነሳን አልሀምዱሊላህ በትልቅ ኒዕማ ውስጥ ነን::
الحمدالله 🌸
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
! ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
በኢስላም አንድ ወንድ ከቻለ እስከ ስንት ማግባት ይቻላል ?
قم صلّ ركعتين في جوف الليل، واخلع هموم الدنيا من قلبك، واقترب من ربك بالخضوع والدعاء؛ فإنه ينزل كل ليلة إلى السماء الدنيا يقول: "هل من داعٍ فأستجيب له؟"⤵️⤵️
በዚህ ምርጥየ ሰአት ተነሱ ወንድም እህቶቸ ጀዋል እንዳያታልለን ግማሽ ሰአት ወደአሏህ አንሾካሽኩ 💦 በዱዓም ውስጥ እስበሳችን እንተዋወስ ✅
ኢላሂ! የሌሊቱ ዝምታና የነፍስ ፀጥታ ባለበት በዚህ ሰዓት አሏህ ይሆ ዱዓችንንም ተቀበል።
ኢላሂ! የዕድሜያችንን ቀናት በፈቃድህ እና በታዛዥነትህ እንድንጨርሳቸው እርዳን ከሰይጣን ወጥመድ እና ከክፉ ምኞትም ጠብቀን።
ኢላሂ! በሥራችን ውስጥ ውብ የሆነ ባረካን አፍስስበት ጥረታችንንም በህዝቦች ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኝ አድርግልን።
ኢላሂ በዙሪያችን ላሉት ለወዳጅ ዘመዶቻችን እና ለምንወዳቸው ሁሉ ሰላምን ጤናን እና የልብ መረጋጋትን ለግስላቸው።
ጌታችን ሆይ! የዱንያን ፈተና አቅልልልን የኣኺራችንን መናኸሪያ ውብ አድርግልን። አንተ መሐሪ ነህና ዛሬም ነገም እኛን ከችሮታህ ለግሰን 💧✨🤲🤲🤲🤲🤲
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_አምስት(⓯)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #አይከል ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
#ምዕራፍ_ሁለት
.....
የቃል ኪዳን ጽናትና የሾርጣው ድንገቴ
ከ"ሙሐመድ ልጅ" ጋር ያለን ግንኙነት ከመላመድ አልፎ ወደ ጥልቅ ቃል ኪዳን ተሸጋገረ።
ያኔ.....ነው እንግዲህ እዝች ልጅ ላይ የወሰንኩት በቃ የትዳር" አጋሬ ይችናት ብዬ ወሰንኩ ታዳ በሚገባ መግባባት ቻልን ነገሮች' ግልፅ ተደራረግን ግንኙነታችን የሚዲያ እንደመሆኑ ከባዱን ጥንቃቄ አደረግን።
ስለ ኒካህ እያለምን፣ ስለ ወደፊት ጎጆአችን እየተመካከርን ወራት ወራትን እየተኩ እንደ ዋዛ ሱዑዲ ምድር ሁለት ዓመታት ነጎዱ። እሷ ጅዳ ናት እኔ ጅዛን ነኝ ተመካርን የጀመረችውን ቤት እንደለና እሱን እስከምጨርስ ግዜ እንድሰጣት ጠዬቀችኝ!! እሷም ቤቷን ለመጨረስ ስትደክም፣ እኔም እሱን እንድጨርስ ልታገሳት ከዛ ጅዛን ሆኜ በናፍቆት እጠብቃት ነበር።
በዚህ መሃል፣ ያቺ በኢትዮጵያ ያለችው ልጅ በትዕግሥት ማጣትና በጭቅጭቅ ሰልችታ "ብሎክ" አድርገኝ ትለኛለች" ሲፈልጋት ደሞ አኩርፋ ትሄዳለች። ያ የድሮው የሐራም ትዝታ እንዲህ ባለ መከፋት ሲደመደም፣ እኔ ግን ለሙሐመድ ልጅ ያለኝን ታማኝነት አጸናሁ። "ደካማ ማንነቴን" አርሜ፣ ለሷ የሚመጥን ወንድ ለመሆን ራሴን ቀረጽኩ። ልብ በሉ እኔ ያለሁት ዛሬላይ ስደት ስለሆነ በምኖርበት ስደት አገር አብራኝ ያለች ጥሩ የትዳር አጋር እዬመረጥኩ እንጂ ሴትልጅ ለማስለቀስ አንዳን መርጬ አንዳን አገባሻለሁ እያልኩ ያጉል ተስፋ ሰጥቼ በሴት ልጅ ላይ የለለ ግፍ ለማድረስ" አይደለም
ለማንኛውም አደራቹሁን ታሪኩን ሳጨርሱ አትፍረዱ!!"ሰው ቢሞት ይረሳል ቢቆይ ይወቀሳል" እንተባለው??ትደርሳሉቹሁ ለወቀሳው
እንቀጥል
አንድ ቀን ድንገት እንዲህ ብዬ ጠየቅኳት፦ "እኔ ብያዝ (ዲፓርት ቢደረግ) እና ወደ ኢትዮጵያ ብገባ ትፈልጊኛለሽ?"አልኳት እሷም በጽናትና በፍቅር እንዲህ አለችኝ፦ "አዎ! የትም ብትሆን አንተ የኔ ነህ፤ ግን እንዳትጎዳኝ አደራ!" ይህ ቃል በልቤ ውስጥ ትልቅ ኃይል ሆነ፤ ለእሷ ያለኝን ታማኝነት በደም አስረገጠው።
ነገር ግን... ቀድሮ (ውሳኔው) ሌላ ነበር።
ገና የንጋቱ ፀሐይ ብቅ ስትል፣ ለሥራዬ ደፋ ቀና እያልኩ፣ ለፍየሎቼ ምግባቸውን ላቀርብ ስል... የሰዑዲ "ሾርጣ" (ፖሊስ) ከኋላዬ ከተፍ አለ። ያ የሁለት ዓመት የስደት ድካም፣ ያ የፍቅር ሕልም እና የናፍቆት ተስፋ በአንዲት ቅጽበት ቆመ።
"ለሕልሜ ስሮጥ - ለፍቅሬ ስተጋ፣
የሾርጣው ጥሪ - መጣ ሳይነጋ፤
አላሁ አክበር! - አልኩኝ በድንጋጤ፣
የስደቱ ማግስት - ሆነብኝ ስርቆቴ።"
ያኔ... የመጀመርያው ትዝታዬ "የሙሐመድ ልጅ" ነበረች። ያ የሰጠችኝ አደራና የገባንበት ቃል ኪዳን በዓይኔ ላይ ብልጭ አለ። በሕግ ቁጥጥር ስር ስውል፣ የነፃነቴ ዋጋ ብቻ ሳይሆን፣ ያ የጀመርነው ትልቅ ተስፋ ምን ይሆን? የሚለው ስጋት ነፍሴን ወረራት።
ከሳዑዲ "ሲጂን" ወደ አገር ቤት ሰማይ ስር......
እንቀጥል
በሾርጣው እጅ ስወድቅ ለማምለጥ የሞከርኩት ሙከራ ከንቱ ሆኖ ቀረ፤ ቀድሮ (ውሳኔው) ጸንቷልና። መኪናው ውስጥ ገብቼ ስልኬ ሳይቀማኝ ለሙሐመድ ልጅና ለአሠሪዬ መያዜን አረዳሁ። ከዚያም ወደ ጅዛን እስር ቤት ተወረወርኩ። የሦስት ቀን አስከፊ ቆይታ በጅዛን ካሳለፍኩ በኋላ፣ እጆቻችን በካቴና ታስረው፣ በባስ ተጭነን ሳዑዲን ልንሰናበት ወደ ጅዳ አመራን።
ጅዳ እስር ቤት ሃያ ስድስት ቀናትን አሳለፍኩ። ያ ስፍራ ግን ለእኔ እስር ቤት ብቻ አልነበረም፤ ልክ በሱማሌ፣ በየመንና በራጎ ምድር እንደነበረው ሁሉ፣ እዚህም የጥያቄና መልስ መድረክ ተከፈተልኝ።
ብዙዎች ስለ ሃይማኖታቸው፣ ስለ ሽርክ ብሎም እኔም የሰከርኩበትን የሀራም፣ፍቅር" የመሳሰሉት ስለ ጫት ሐራምነትና ስለ ሕይወት ምስጢር ይጠይቁኝ ነበር። እኔም ካለኝ ዕውቀት እየቀነስኩ ስመልስላቸው፣ አንዳንዶች እስልምናን እስከመቀበል ደረሱ።አልሃምዱሊላህ በዚያ በስር ቤት ውስጥ ብዙ ታሪኮችን ሰምቻለሁ አይቻለሁ ፣፣ ያኔ....ነበር እዚያ እስር ቤት ውስጥ እንደ "ሙሽራ"ኡስታዝ ኡስታዝ እዬተባልኩ ተከብሬ ሳለሁ ግን፣ ነፍሴ እንዲህ እያለች ትወቅሰኝ ነበር፦
"በመከራው መሃል - አዋቂ ስባል፣
"የጌታዬን ትእዛዝ - ግን ልቤ ጥሷል፤
ሰው ፊት ብከበርም - እንደ ዕውቀት አምባ፣
ውስጤ ግን ፈርቷል - በጸጸት እንባ።"
በመጨረሻም "በረራ" መጣ። ሳዑዲን ተሰናብቼ አዲስ አበባ ገባሁ። አገር ቤት ስደርስ መጀመሪያ የደወልኩት ለዚያች "እንጋባለን" ብላኝ በጭቅጭቅ ስትለበልበኝ ለነበረችው ልጅ ነበር። የምትኖረው አዲስ አበባ ነው።
አሁን እዚህ ጋር ነው ትልቁ የሕይወት እንቆቅልሽ የሚፈታው። ያ ሁሉ የስደት መከራ፣ የራቢያ ፍቅር፣ የጠይባ አደራ፣ የሙሐመድ ልጅ ቃል ኪዳንና የእናቴ ምኞት... አሁን አዲስ አበባ ላይ ተከማችተዋል።
ውድ አንባቢያን ሆይ! የሰው ልጅ ጉዞው ረጅም ቢሆንም፣ መዳረሻው ግን ሁሌም ወደ ራሱ ማንነት ነው። እኔም ያንን ሁሉ አቀበትና ቁልቁለት አልፌ፣ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ቆሜ ቀጣዩን የሕይወት መስመር ለመዘርጋት ስልኬን አነሳሁ።
ቀጣዩ ክፍል ⓰
የሚከተለው ነው
የመካ መንገድ ትዝታና የወሎው ንጋት
ይ ቀ ጥ ላ ል
▫
ስለገለልተኛነትህ ምክንያት ከጠየቁህ እድህ በላቸው! የማይታዩትን ቀዳዳዎች እየሰፋሁ ነው !
የልብ ስብራት ውጭ ላይ ፀጥ ያለ ቢመስልም ከውስጥ ግን ማንም የማይሰማው ጥልቅ እና የሚያንገበግብ ድምፅ አለው።
