ru
Feedback
HOP Ministry

HOP Ministry

Открыть в Telegram

HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
445
Подписчики
+224 часа
+237 дней
+6630 день
Архив постов
#የእግዚአብሔር_አብሮነት_ከከነዓን_ይበልጣል። የእግዚአብሔር አብሮነት ከከነዓን ይበልጣል። ለእግዚአብሔር ሕዝብ፦ የእግዚአብሔር አብሮነት የሌለበት ከነዓን ሕይወት አይሆነውም፣ አይረባውም። የእግዚአብሔር ሕዝብ ልዩነትና ሞገስ፦ ያለው ሀብት፣ በረከት፣ የሚወርሰው ከነዓን ሳይሆን፤ ሁሉን ሰጪው፣ የባርኮቱ ምንጭ የሆነው አምላኩ እግዚአብሔር ነው። የእግዚአብሔር አብሮነት የሌለበት ከነዓን አይረባንም። አብሮነቱ በሌለበት ከሚሰጠን ከነዓን ይልቅ፤ ሁሉን አጥተን እግዚአብሔርን ማግኘት፣ በእርሱም መገኘት ይብዛልን!! ከእግዚአብሔር ሀልዎት ውጪ እኛን ሕያው፣ ልዩ፣ ባለ ሞገስ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያደርገን ምን አለ? ዘጸአት 33 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ እግዚአብሔር (ያህዌ) “ሀልዎቴ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” ብሎ መለሰ። ¹⁵ ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፤ “ሀልዎትህ ከእኛ ጋር ካልሄደ ከዚህ አትስደደን። ¹⁶ አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድህ፣ አንተ በእኔና በሕዝብህ መደሰትህን ሌላው እንዴት ያውቃል? እኔንና ሕዝብህንስ በገጸ ምድር ከሚገኙት ከሌሎቹ ሕዝቦች ሁሉ ልዩ የሚያደርገን ሌላ ምን አለ?” ✍️ መክሊት አየለ 📆 July 21, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

So Will I (100 Billion X) Song by Hillsong Worship and Taya ‧ 2018 "God of creation There at the start Before the beginning of time With no point of reference You spoke to the dark And fleshed out the wonder of light And as You speak A hundred billion galaxies are born In the vapour of Your breath the planets form If the stars were made to worship so will I I can see Your heart in everything You've made Every burning star A signal fire of grace If creation sings Your praises so will I God of Your promise You don't speak in vain No syllable empty or void For once You have spoken All nature and science Follow the sound of Your voice And as You speak A hundred billion creatures catch Your breath Evolving in pursuit of what You said If it all reveals Your nature so will I I can see Your heart in everything You say Every painted sky A canvas of Your grace If creation still obeys You so will I So will I If the stars were made to worship so will I If the mountains bow in reverence so will I If the oceans roar Your greatness so will I For if everything exists to lift You high so will I If the wind goes where You send it so will I If the rocks cry out in silence so will I If the sum of all our praises still falls shy Then we'll sing again a hundred billion times God of salvation You chased down my heart Through all of my failure and pride On a hill You created The light of the world Abandoned in darkness to die And as You speak A hundred billion failures diappear Where You lost Your life so I could find it here If You left the grave behind You so will I I can see Your heart in everything You've done Every part designed in a work of art called love If You gladly chose surrender so will I I can see Your heart Eight billion different ways Every precious one A child You died to save If You gave Your life to love them so will I Like You would again a hundred billion times But what measure could amount to Your desire You're the One who never leaves the one behind"

"And as You speak A hundred billion failures diappear Where You lost Your life so I could find it here If You left the grave behind You so will I I can see Your heart in everything You've done Every part designed in a work of art called love If You gladly chose surrender so will I"

4_5870647052936942063.mp35.48 MB

#ኢየሱስ_ማን_መሆኑን_በቅጡ_ማወቅ! ብዙ ነገሮች አጥተን ኖረን አይተነዋል፤ ብዙ ነገሮች ጥለውን ሄደው ስንቀጥል ራሳችንን አግኝተናል። ጌታ ኢየሱስን ላየ፣ ቸርነቱን ለቀመሰ ሰው ግን ከኢየሱስ መለየት፣ ያለ እርሱም መኖር ሞት ነው። የኢየሱስ ሁሉ በሁሉነት ሲገባን የሚያስፈልገን እርሱ ብቻ እንደሆነ፤ ያለ እርሱ መኖር፣ ምንም ማድረግ እንደማንችል እንረዳለን። ኢየሱስ ከያዕቆብ ጉድጓድ መብለጡ የእውነት ለገባው ሰው ኢየሱስ ጊዜያዊ ጥምን የሚያረካ ነገር ሳይሆን የዘላለም ውኃ ምንጭ፣ የሕይወት ውኃ ነው። ኢየሱስ ማን መሆኑን ማወቅ የዘላለም ሕይወትን ማትረፍ ነው። ያውም ትርፉ በምድር ስሌት የማይሰላ ዘላለማዊ ትርፍ ነው። ሳምራዊቷ ሴት ኢየሱስ ማን መሆኑን በቅጡ ሳትረዳ በፊት የያዕቆብ ጉድጓድ የምታዜምለት፣ ታላቅነቱን የምትመሰክርለት፣ ከእርሱ ሌላ ምንጭ ያለ እንኳ እስካይመስላት ድረስ የምትመካበት ምንጯ ነበር። የኢየሱስ የዘላለም ውኃ ምንጭነት ሲገባት ግን አይደለም ደግማ ስለ ያዕቆብ ጉድጓድ ልታወራ፣ "አንተ ይህን ጉድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን?" ብላ ኢየሱስን ከያዕቆብ ጋር ልታወዳድር ይቅርና ስለ ኢየሱስ የዘላለም ውኃ ምንጭነት መለስ ብላ ለማሰብና ለመጠራጠር እንኳ ጊዜ አላገኘችም። ለእርሷ የበራላት ብርሃን ለብዙዎች እንዲበራ፣ ያየችውን ብዙዎች እንዲያዩት፣ የገባትንና የቀመሰችውን እውነት፣ ሕይወት ብዙዎች እንዲቀምሱ፣ ብዙዎችን ወደ እርሱ ልታፈልስ ወደ ሕዝቡ ሮጠች፤ እርሱ ማን መሆኑን አውቃለችና። ኢየሱስ ማን መሆኑን በቅጡ ማወቅ፦ ከብዙ ብክነት፣ በአላስፈላጊ፣ በሰው ሰራሽ፣ ጥምን በማይቆርጡ፣ በጥቃቅን ምንጮች ከመርካት ይጠብቃል፤ እርሱን ብቻ ለመጠማት፣ ከእርሱ ብቻ ለመጠጣት፣ በእርሱ ብቻ ለመርካት ይጠቅማል። ኢየሱስን በማንነቱ ማወቅ፣ እርሱ ማን መሆኑን በቅጡ መረዳት፣ ማስተዋል ይሁንልን!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 July 19, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

Amazing_worship_ህልውና_yosefe_almerew_with_kalkidan128k.m4a9.50 MB

ዘምሬ_የማልጠግበው_zemre_yemaltegbew_ይድነቃቸው_ተካ_Yidnekachew_teka_መዝሙር128k.m4a5.40 MB

#የማያልቅ_ርዕሰ_ጉዳይ! በምድር ስላሉት ጉዳዮቻችን፣ ስለምንፈልጋቸውና ስለሚያስፈልጉን ነገሮች የምንጸልየው ፀሎት በፀሎት መልስ ይሻራል። መልሳችንን ስንቀበል፣ የጠየቅነውን ነገር ስናገኝ ፀሎቱን እንተወዋለን፣ እንቀይረዋለን። ስለ ራሱ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ መገኘቱ፣ ስለ ሕልውናው፣ ስለ መንፈሱ የሚደረግ ፀሎት ግን ጊዜ የማይሽረው፤ አሁንም፣ ዛሬም፣ ነገም፣ ከነገ በስቲያ፣ በምድር እስካለን ድረስ፣ ጌታን ፊት ለፊት እስከምናየው ድረስ የሚዘልቅ፣ መዝለቅ ያለበት ፀሎት ነው። በጊዜያዊ ነገሮች ላይ የፀና ፀሎት እንደተቀያየረ፣ እንደዋዥቀ ይኖራል፤ ድካም አለበት፣ ጉልበትን ያዝላል። ዘላለማዊውን ነገር፣ ዘላለማዊውን አምላክ ለማግኘት የሚደረግ መቃተት ግን ሕይወት አለበት፤ ጸላዩን፣ ፈላጊውን ሕያው እያደረገ፣ እያለመለመ ይሄዳል፤ በቃኝም አይባልም ሌላ እልፍ ረሃብ ይወልዳል። ጌታ በቸር እጆቹ ይንካን፤ ቸር መሆኑን ያቅምሰን፤ ያኔ እያየነው፣ እያገኘነው፣ በእርሱ እየተዳሰስንና እየተነካን፦ የያዝነው አይመስለንም፣ አብረነው ሆነን ይናፍቀናል፣ የእርሱ እልፍ ረሃብ ይበዛልናል፣ ጌታን ጌታን ብለን እየናፈቅነው፣  እያገኘነው ይርበናል፣ ይርበናል....፣ እርሱን መከተል፣ መከታተል ስራችን ይሆናል። ከምንፈልገው፣ ከሚያስፈልጉንም ነገሮች በላይ እግዚአብሔር፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ኢየሱስ ያስፈልገናል። እግዚአብሔርን እየፈለግን መፈለግ፣ እየናፈቅን መናፈቅ ይሁንልን!! የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር የምትመረምረው መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሙላን!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 July 18, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

ከምንፈልገው፣ ከሚያስፈልጉንም ነገሮች በላይ እግዚአብሔር፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ኢየሱስ ያስፈልገናል። እግዚአብሔርን እየፈለግን መፈለግ፣ እየናፈቅን መናፈቅ ይሁንልን!! 🌿 HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. https://t.me/hopministry10

ሌሎች ረሃቦቻችንን ሁሉ ተቀምተን #በአንድ_ረሃብ (በእግዚአብሔር ብቻ) ብንጠመድ፣ ሌላውን ለማየት፣ ለመስማት፣ ለመንካት፣ ለመብላት አቅም አጥተን ለሕይወት ቃል፣ ለሕይወት ውሃ፣ ለሕይወት ውሃ ምንጭ ረሃብ፣ ጥማት ብንበረታ፤ የጌታ የፍቅሩ ትኩሳት የልባችንን ጓዳ ቢያሞቀው፣ ለብታችን በፍቅሩ እሳት ግለት ቢሻር፣ ትናንት ባላየነው መንገድ ጌታ ቢያገኘን፣ መሰዊያችን ቢታደስ፣ ከማለዳ እስከ ምሽት የቃሉ አሰላስሎት አሳባችንን ቢቆጣጠረው፣ ማብቂያዋ መቼ እንደሆነ የማይታወቀው እንፋሎት ዘመናችን ለኢየሱስ እየነደደች የምታበራ መብራት ብትሆን.....ይሄ ሁሉ ልቤ የሚብሰለሰልበት፣ ጌታ በኃይሉ ችሎት ቢያደርግልን ብዬ የምናፍቀው ናፍቆቴ፣ ቁጭቴ ነው። ናፍቆቴን እንደምትጋሩኝ እምነቴ ነው፤ ይህ ሁሉ በእኛ እውን እንዲሆን የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት ያግኘን!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 April 12, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

🌿 HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. https://t.me/hopministry10

Addisu_Worku_(Alechenekem)(128k).mp34.81 MB

እግዚአብሔርን አምነን፣ ታምነን በመንገዱ ላይ እየሄድን ከሆነ፦ እርሱ አላዘገየንም፣ አላስቸኮለንም፤ እርሱ ሁሉን በፈቃዱ ምክር መሰረት እየሰራ ይገኛል። ረፈደብኝ፣ ወደኋላ ቀረሁ፤ መፍጠን ከሚገባኝ በላይ ፈጥኜ በአላስፈላጊ መንገድ ተጓዝኹ አንበል። እግዚአብሔር ብቻውን መምራት፣ ከግብ ማድረስም ያውቅበታልና ሕይወታችንን በመሪያችን እጅ ላይ በእምነት እናኑር፤ እግዚአብሔርን አምነን፣ ሳናይ እንከተለው፣ እንከታተለው። በእግዚአብሔር መንገድ ፀንተን አንጸጸትም፤ እርሱ ያሳርፈናል!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 July 16, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

🌿 HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. በእግዚአብሔር መንገድ ፀንተን አንጸጸትም፤ እርሱ ያሳርፈናል!! https://t.me/hopministry10

““እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።”   — ማቴዎስ 11፥28 (አዲሱ መ.ት) “እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”   — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 (አዲሱ መ.ት) #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

Lay It All Down Song by United Pursuit and Will Reagan ‧ 2017 " Bring your worry, grief, and pain Every cause you have for shame Lay it all down Lay it all down When your cares have buried you And there's nothing left to do Lay it all down Lay it all down At the feet of Jesus At the feet of Jesus Carried on but your heart was tired Feared the worst and felt the fire Lay it all down Lay it all down Filled with all those anxious thoughts And your doubts became your god Lay it all down Lay it all down At the feet of Jesus At the feet of Jesus Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down (won't you lay it down?) Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down (lay it all down) At the feet of Jesus Down, at the feet of Jesus When we've given up on better days There are memories we can't erase Lay it all down Lay it all down When we've come to fear what we can't explain And there's nothing here that can ease the pain Lay it all down Lay it all down At the feet of Jesus At the feet of Jesus Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down (won't you lay it all down?) Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down Down, at the feet of Jesus At the feet of Jesus Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down (won't you lay it all down?) Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down (down at the feet) Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down At the feet of Jesus (lay it down at the feet) At the feet of Jesus Lay it all down, lay it all down (lay it all down) Lay it all down, lay it all down (lay it down) Lay it all down, lay it all down (down, down, down, down) Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down Lay it all down, lay it all down (lay it down) At the feet of Jesus At the feet of Jesus"

Lay_it_All_Down__feat._Will_Reagan_(128k).m4a5.85 MB

#የምስራች፦ #እግዚአብሔር_ለደካሞች_ኃይላቸው_ነው። ደካሞች በእግዚአብሔር ይበረታሉ፣ ይታደሳሉ። ድካም በእግዚአብሔር ፊት ድካም ሆኖ አይቀጥልም፤ በብርታት ይቀየራል። እግዚአብሔር ለደካማው ኃይል ይሆናል፤ ዝለት በእግዚአብሔር ፊት እንዳልነበር ይሆናል፤ እግዚአብሔር ኃይላቸው መሆኑን አምነው የተጠጉት፣ በመተማመን የሚጠባበቁት፦ ከድካም ተፋተው፣ ኃይላቸውን አድሰው፣ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ አይደክሙም፣ አይታክቱም፤ ምክንያቱም የኃይል ሁሉ ምንጭ የሆነው ኃያል አምላክ ኃይል ይሆናቸዋልና። ድካም በእግዚአብሔር እንደሚረሳ፣ እንደሚቀየር፣ እንደሚነሳ፤ እግዚአብሔርም ለደካማ ኃይል እንደሚሆን እኔ ምስክር ነኝ። የተሰበረው ልቤን አድምጦ፣ ደክሞኛል፣ አልቻልኩም ከሚለው ቃሌ ቀድሞ ሲያነሳኝ፣ ሲጠግነኝ፣ ኃይል ሲሆነኝ እግዚአብሔርን እልፍ ጊዜ አይቼዋለሁ። በድካሜ ያላሸማቀቀኝ፤ ይልቁንም ያበረታኝ፣ ኃይል የሆነኝ እግዚአብሔር ለደካሞች ኃይላቸው ነው ስል በድፍረት እመሰክራለሁ። የምስራች:- እግዚአብሔር ለደካሞች ኃይላቸው ነው!! ኢሳይያስ 40 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁷ ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? ²⁸ አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ²⁹ ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ³⁰ ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ ³¹ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ✍️ መክሊት አየለ 📆 July 15, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

4_5864104988816447197.mp34.64 MB

እግዚአብሔርለደካሞችኃይላቸውነው.mp32.65 MB