fa
Feedback
HOP Ministry

HOP Ministry

رفتن به کانال در Telegram

HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
558
مشترکین
+424 ساعت
+217 روز
+5430 روز
آرشیو پست ها
“ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።”   — መዝሙር 23፥6 https://t.me/hopministry10

#ሌላ_መንገድ_የለም! እግዚአብሔርን ለማክበር፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለማገልገል፣ እግዚአብሔርን ለመስማት፣ የመንፈስ ቅዱስ መገልገያ ለመሆን፦ ወደ እግዚአብሔ
#ሌላ_መንገድ_የለም! እግዚአብሔርን ለማክበር፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለማገልገል፣ እግዚአብሔርን ለመስማት፣ የመንፈስ ቅዱስ መገልገያ ለመሆን፦ ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ፣ ሳያቋርጡ እግዚአብሔርን ከመከታተል፣ በየዕለቱ በሚጨምር የእግዚአብሔር ረሃብና ናፍቆት ከመሞላት ውጪ #ሌላ_መንገድ_የለም! እግዚአብሔርን የፈለጉት ሲያገኙት፣ ደጁን ለጠኑት ዘንበል ሲልላቸው፣ መዝጊያውን ያንኳኩ ሲከፈትላቸው አይተናል። በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ የሚሰነብት የእርሱ የቅርብ፣ የልብ ወዳጅ ለመሆን ወደ እርሱ ከመቅረብ፣ አብዝቶ ወደ ልቡ ከመጠጋጋት፣ እርሱን ተግቶ ከመፈለግ ውጪ #ሌላ_አቋራጭ_መንገድ_የለም! ✍️ መክሊት አየለ 📆 September 6, 2024 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

ፀሎቴ__Tselote_Prayer(128k).m4a7.14 MB

ከሚያስጨንቀን ነገር፣ ከምናልፍበት ከባድ ሁኔታ በላይ የሚናገረን፣ የሚያጽናናን የእግዚአብሔር ድምጽ፤ እርሱ የሰጠን ቃል ኪዳን ይበልጣልና እግዚአብሔርን መስማት ይሁንልን!! ዘጸአት 6 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ “ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ ከግብፃውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ እቤዣችኋለሁ። ⁷ “የራሴ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላክ (ኤሎሂም) እሆናችኋለሁ ከግብፃውያን ቀንበር ያላቀቅኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኔንም ታውቃላችሁ። ⁸ ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ” ⁹ ሙሴ ይህን ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ ተስፋ ከመቍረጣቸውና ከአስከፊ እስራታቸው የተነሣ ግን አላዳመጡትም። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

ከሚያስጨንቀን ነገር፣ ከምናልፍበት ከባድ ሁኔታ በላይ የሚናገረን፣ የሚያጽናናን የእግዚአብሔር ድምጽ፤ እርሱ የሰጠን ቃል ኪዳን ይበልጣልና እግዚአብሔርን መስማት ይሁንልን!! https://t.me/hopministry10

1ኛ ቆሮንቶስ 9 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ በሩጫ ውድድር የሚሮጡ ብዙዎች እንደሆኑ፣ ሽልማቱን የሚቀበለው ግን አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁምን? ስለዚህ ሽልማቱን እንደሚቀበል ሰው ሩጡ። ²⁵ ለውድ ድር የሚዘጋጅ ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል፤ እነርሱ ዐላፊ ጠፊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ይደክማሉ፤ እኛ ግን ለዘላለም የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት እንደክማለን። ²⁶ ስለዚህ እኔ ግብ እንደሌለው ሰው በከንቱ አልሮጥም፤ ደግሞም ነፋስን እንደሚጐስም ሰው እንዲያው አልታገልም፤ ²⁷ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ ውድቅ ሆኜ እንዳልቀር፣ ሰውነቴን እየጐሰምሁ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

🏃‍♂️🥊 Run with purpose. Fight with discipline. Don’t just beat the air—train your life for an eternal reward. 🔥🏆 📖 1 Corinthians 9:24–27 (ESV) “Do you not know that in a race all the runners run, but only one receives the prize? So run that you may obtain it. Every athlete exercises self-control in all things. They do it to receive a perishable wreath, but we an imperishable. So I do not run aimlessly; I do not box as one beating the air. But I discipline my body and keep it under control, lest after preaching to others I myself should be disqualified.” #1Corinthians9 #RunTheRace #FightWithPurpose #SpiritualDiscipline #Faith #EternalReward https://t.me/hopministry10

“እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፤ “እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።””   — አሞጽ 5፥4 (አዲሱ መ.ት) “እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ”   — አሞጽ 5፥6 (አዲሱ መ.ት) #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

“For thus says the LORD to the house of Israel: “Seek me and live;”      — Amos 5: 4 (ESV) https://t.me/hopministry10

🚏 Live Like Time Is Short ⏳ Life is like a bus journey 🚌🛣️ One day, we will reach our station and have to get off 🚏⏳ So live with purpose 🎯✨ Live for your calling 🙏🔥 Live like someone who has no time to waste ⏰💨 Love deeply ❤️ Forgive quickly 🤍 and make your journey count 🌍💫 #LifeJourney 🚌 #LiveWithPurpose 🎯 #WalkInYourCalling 🙏 #LifeIsShort ⏳ #MakeYourLifeCount ✨ #LiveWisely 🌱 #PurposeDriven 🔥 #HOPMinistry 🌱 https://t.me/hopministry10

ከእኔ_ምትፈልገው_KeEne_Mitifeligew_Mesay_Birhanu_Original_Song_by_Getayawkal.m4a7.87 MB

Repost from N/a
ለመመዝገብ ሊንክ ያስቸገራችሁ ይህንን አዲስ ሊክን መጠቀም ትችላላችሁ https://docs.google.com/forms/d/17AC_3UJHS-Efr_hQu8UlXQU1lyNWC6ZgkjYJR4Ehmas/viewform

Repost from N/a
የጌታ ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን! እግዚአብሔር ረድቶን "ህማማት እና ትንሳኤ" በሚል ርዕስ በመጋቢ ሔኖክ አፈወርቅ የሚሰጥ ሁለተኛ ሴሚናር አዘጋጅተናል። ትምህሩት ቅዳሜ ነሐሴ/23 2018 ዓ.ም ከጠ
የጌታ ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን! እግዚአብሔር ረድቶን "ህማማት እና ትንሳኤ" በሚል ርዕስ በመጋቢ ሔኖክ አፈወርቅ የሚሰጥ ሁለተኛ ሴሚናር አዘጋጅተናል። ትምህሩት ቅዳሜ ነሐሴ/23 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 03፡00 ጀምሮ በኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ Room 106 ይሰጣል። ለመካፈል የምትፈልጉ ከታች ባለው google form በነጻ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን። መመዝገቢያ ፎርም https://tinyurl.com/bdf83es5 ማሳሰቢያ፦ > ያለን ቦታ አነስተኛ ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ > ከተመዝጋቢዎች ውጪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን > የምሳና የሻይ ወጪ በፕሮግራሙ አዘጋጆች ይሸፈናል > ሲመጡ መጽሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ይዘው መምጣት አይርሱ። > ተመዝጋቢዎች በሰዓቱ መገኘት ይኖርባችኋል።

ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሶ ያየ ሰው፣ አንዴ በእርሱ የተነካ ሰው፣ ወደ እርሱ በመጠጋት እግዚአብሔርን ያየ ሰው ይበልጥ በእርሱ ለመነካት፣ ለመዳሰስ፣ ከቀረበው በላይ እርሱን ለመቅረብ፣ ሁሉን ትቶ እርሱን ለመከተል ይፈጥናል እንጂ ወደ ኋላ አያፈገፍግም። ምክንያቱም የተነካበት መነካት፣ የቀመሰው የጌታ መልካምነት ከእርሱ ጋር የሚያሰነብት እንጂ ጊዜያዊ አይደለም። በእግዚአብሔር የተነኩ ሰዎች፣ እግዚአብሔር ወዳጆቼ የሚላቸው ሰዎች በምድር የሚኖሩ የሰማዩ አምላክ ወዳጆች ናቸው፤ በምድር ሆነው በሰማይ ያለውን የእርሱን ፈቃድ በምድር ለማድረግ ይተጋሉ፤ የሰማዩ አምላክም ወዳጆቹ ናቸውና ፈቃዱን ለእነርሱ ከመግለጥ፣ የልቡንም አሳብ በእነርሱ ከማኖር ወደኋላ አይልም። ✍️ መክሊት አየለ 📆 August 24, 2024 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

እግዚአብሔርን ከማመሰግንበት ምክንያቶች አንዱ፦ ቅዱስ ቃሉ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ፤ የዘወትር ምግብ፣ የሕይወት መመሪያ ማድረግ እንዴት መታደል ነው?! https://t.me/hopministry10

2ኛ ጢሞቴዎስ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤ ¹⁷ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

✨_መጽሃፍ_ቅዱሴ_ሳሙኤል_ተገኝ_Samuel_Tegegn_Amharic_Gospel_Lyric_Video_✨128k.m4a5.98 MB

ዳንኤል 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ለንጉሡ እንዲህ ብለው መለሱ፤ “ናቡከደነፆር ሆይ፤ በዚህ ጒዳይ ላይ ስለ ራሳችን መልስ መስጠት አያስፈልገንም። ¹⁷ ንጉሥ ሆይ፤ በሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ብንጣል፣ የምናመልከው አምላክ ሊያድነን ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል። ¹⁸ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል፣ ላቆምኸውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ።” https://t.me/hopministry10

ዳንኤል 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁸ ከዚያም ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፤ “መልአኩን ልኮ አገልጋዮቹን ያዳነ፣ የሲድራቅ፣ የሚሳቅና የአብደናጎ አምላክ ይባረክ፤ በእርሱ በመታመን የንጉሡን ትእዛዝ ጥሰው፣ ከአምላካቸው በቀር ሌላ አምላክ ለማገልገልም ሆነ ለእርሱ ለመስገድ ፈቃደኛ ባለመሆን ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋልና። ²⁹ ስለዚህ እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማናቸውንም ቃል የሚናገሩ ሕዝቦችም ሆኑ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ ይቈራረጣሉ፤ ቤቶቻቸውም የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ብዬ አዝዣለሁ።” #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

🔴_ተስፋዬ_ጫላ_ሚስጥር_መዝሙር_Tesfaye_Challa_Mister_Mezimur128k.m4a5.02 MB