ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
899
Подписчики
-224 часа
-167 дней
+2730 дней
Архив постов
ኢላሂ! መንገድ የሳቱ ወንድሞቻችንን ሁሉ አንተው መልሳቸው።

▫️ ለምን ቅድሚያ ለተውሒድ እንላለን? በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር በኡስታዝ ሳዳት ከማል በኡስታዝ ሰዒድ ሙሳ ሐፊዘሁሙላሁ ተዓላ t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

🛑☞ተቀርተዉ ያለቁ እና በጅምር ላይ ያሉ ኪታብ ደርስ ሰሰብስብ ! ~~ ☞ሹሩጡ ላኢላሀኢለሏህ ወነዋቂዱል ኢስላም⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/214 https://t.me/durus_abu_reyyis/214 ☞ቀዋኢዱል አርበዕ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/224 https://t.me/durus_abu_reyyis/224 ☞20ምክሮች ለእህቴ ከማግባቷ በፊት⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/232 https://t.me/durus_abu_reyyis/232 ☞ላኢላ ሀኢለሏህ ወማእናሀ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/272 https://t.me/durus_abu_reyyis/272 ☞ኩን ሰለፍያ አለል ጃዳህ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/314 https://t.me/durus_abu_reyyis/314 ☞ሙዛከራት አህካም ፂያም⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/361 https://t.me/durus_abu_reyyis/361 ☞ኡሱሉ ሰላሳ ወአዲለቱሀ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/512 https://t.me/durus_abu_reyyis/512 ☞ቱህፈቱል አጥፋል ኪታብ ደርስ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/543 https://t.me/durus_abu_reyyis/543 ☞በይቁኒያ ኪታብ ደርስ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1015 https://t.me/durus_abu_reyyis/1015 ☞ከሽፉ ሹቡሃት ኪታብ ደርስ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1051 https://t.me/durus_abu_reyyis/1051 ☞ወረቃት ኪታብ ደርስ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1066 https://t.me/durus_abu_reyyis/1066 ☞ኪታቡ ተዉሂድ ደርስ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1096 https://t.me/durus_abu_reyyis/1096 ☞ኡርጅዘቱል ሚእያ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1148 https://t.me/durus_abu_reyyis/1148 ☞ሚንሀጅ ፊርቀቱ ናጂያ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1173 https://t.me/durus_abu_reyyis/1173 ☞አልቀዋዒዱል ፊቅሂያ በጅምር ያለ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1221 https://t.me/durus_abu_reyyis/1221 ☞ቡሉغ አል መራም በጅምር ያለ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1240 https://t.me/durus_abu_reyyis/1240 ☞ሙንከራት ኪታብ ደርስ ⇓⇓ https://t.me/durus_abu_reyyis/1294 https://t.me/durus_abu_reyyis/1294 = 🎙በአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢብኑ ኢማም ሀፊዘሁሏህ

«ስኬታችንን ሳናሳያቸው መሞት የሌለባቸው ሰዎች አሉ ባልዋልንበት ያዋሉን….! = t.me/https_Asselefya1

የሱረቱል ፋቲሐህ ስሞች ~ 1- ኡሙልኪታብ 2- አልፋቲሐህ 3- አሰብዑል መሣኒ 4- አልቁርኣኑል ዐዚም = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor

ምርጥ ሪሳላ ነች። ብታነቧት ትጠቀማላችሁ ኢንሻአላህ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

العذر_بالجهل_بين_الغلو_والجفاء_د_عبدالعزيز_بن_ريس_الريس_1445هـ_2024م.pdf8.01 KB

አልሐምዱሊላህ ወራቶችን ከወሰደ ብዙ ልፋትና ጥረት በኋላ አዲሱ አፕ ተለቀቀ። ሸር አድርጉልን ባረከላሁ ፊኩም

Repost from HUDA SOFT
«አህሉል አሠር» የሞባይል አፕልኬሽን ይህ መተግበሪያ የተለያዩ ኢስላማዊ ደርሶችን በደረጃና በስርዓት ለመማር እጅግ አመቺ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ጠቃሚ ይዘቶች በአንድ ላይ አካቶ ይዟል
«አህሉል አሠር» የሞባይል አፕልኬሽን ይህ መተግበሪያ የተለያዩ ኢስላማዊ ደርሶችን በደረጃና በስርዓት ለመማር እጅግ አመቺ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ጠቃሚ ይዘቶች በአንድ ላይ አካቶ ይዟል፦ ዘርፈ-ብዙ የኪታብ ደርሶች፦ የዐቂዳ፣ የመንሀጅ፣ የሲራ፣ የአደብ፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ፣ የነሕው እና የሶርፍ ትምህርቶች። እያንዳንዱ የድምፅ ቅጂ (ኦዲዮ) ከኪታቡ ሶፍት ኮፒ (PDF) ጋር አብሮ የተያያዘ ነው። አፑን ለአጠቃቀም ልዩ እና ምቹ የሚያደርጉት ባህሪያት፦   • ደርሶችን ከጀማሪ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ በቅደም-ተከተል የሚያስተምር።   • ትምህርቱን ሲጨርሱ ራሶን የሚፈሹበት ፈተናዎች ያሉት።   • በትምህርቱ መሃል አስፈላጊ ነጥቦችን በቀላሉ መፃፍ የሚያስችል ጥሩ ማስታወሻ መያዣ ያለው።   • የደርሶች ማውጫ በየዘርፉ በጥራት የተከፋፈለበት።   • የፈለጉትን ደርስ በቀላሉ መልሰው ለማግኘት ምልክት ማድረግ የሚያስችል።   • ከቅጅዎቹ መካከል የመረጡትን ለሌሎች ማጋራት (Share) የሚያስችል አማራጭ።   • አፑን ለአጠቃቀም አመቺ የሚያደርጉት ማስተካከያዎች ያሉት።   • ደርሱን አቋርጠው በሌላ ጊዜ ማዳመጥ ቢፈልጉ በትክክል ካቆሙበት ሰከንድ የሚጀምር። የአፕሊኬሽን አዘጋጅ፦ HUDASOFT https://t.me/hudasoft ይህ ስራችን የላቀው አላህን ፊት ብቻ ተፈልጎበት የተሰራ (የጠራ) ይሆን ዘንድ፤ በዚህ ስራ ላይ ለተባበሩትም ሆነ ይህንን ስራ ለሚያሰራጩት በሙሉ አላህ መልካም ስራችንን እንዲቀበለን እንማፀነዋለን። አፑን አሁኑኑ አውርደው ይጠቀሙበት፦ 🔗 የማውረጃ ሊንክ (Google Play Store)፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahlulaser.hs.app

🌐 ኑሮ ይሄ ሰው:-✋ ራያ አባሜጫማ አላህ ከፍቶለት ድንን ስላስተማረ  ተመቀኛችሁት ፤መንዙማውም ቅላፄ እና ክላሲካል የለበትም ይላል:-የለተሜዎች ሸይኽ አብደል ሀሚድ ጉድድድ 😔 ሰውየው በስሜት እና፣በሞቅታ እንደሚመራ እንደሚናገር በዚሁ ተረዱ ጠያቂው አካል ማውራት አልቻለም እኮ በየት በኩል ያሶራል ኑሮ🤦‍♀️ ታዲያ ከነዚህ ጋ ሰው እንደት ወርዶ ውይይት ኑ ይባላል ሰዎች⁉️ በረክ ሲሉ እያደሩ ቀን ቀን እኮ በአቅላቸው አደለም የሚገኙት እሚያነጋግራቸው ሌላ ነው።

ለተሚዎች! እነሆ ሸይኻችሁን እረሙት። አንድ ተራ ተማሪ ወይም ደረሳ ቢሆን፣ ይህን ዓይን ያወጣ ስህተት ፖስት ባላደረኩት ነበር። የፈትዋ ፕሮግራም የሚያዝለት ሸይኻችሁ ይሄ ነውን ? አቡ ሙዓዝ ሆይ!  'ከ100 በላይ ደረሳን ሰብስቦ ያስተምራል' እያላችሁ የምትፎክሩብን ይሄ ነውን ? ​መቼም ሻኪር ሱልጣን መሻይኾችን ሲተችና ሲዘረጥጥ ቅር ያላላችሁ ወገኖች፣ 'የወርቄውን ሸይኽ መትን እረሙት' ብትባሉ ቅር አይላችሁም!" t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

📌 ስኬትህ ጭንቅላትህ ላይ አይውጣ ፤ ውድቀትህም ልብህ ውስጥ ዘልቆ አይግባ! ሲሳካልህ ተናነስ ፤ ስትወድቅ ዳግም ቀና በል ሁሌም ይህችን የቁርአን አንቀፅ አስታውስ👇 وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاس ይህችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋውራታለን፡፡ (አል ኢምራን 140)

اللهُمَّ هَب لي مِن توفيقك ما يُبلغني غايتي.

አልሀምዱሊላህ ወደ ፈተናው ገብተዋል። ያለፋቸው ፈተናም አይኖርም እንደ አዲስ ነው የጀመሩት። መልካም ፈተና ለሙተነቂብ እህቶቻችን በሙሉ

የ12 አመት ልፋት በአንድ ቀን ሲጨልም በሀይማኖት ብቻ ሙስሊም ስለሆነች መጨረሻ ላይ ስትደርስ አንች ለሀገር አታስፈልጊም ተብላ ተባረረች።ሀገርም ዝም አለች።

የኒቃቢስት ተማሪዎች ጉዳይ ችላ ተብሏል። ሴቶች #ኒቃብ እንዲለብሱ ያልመከረ ዳዒ፣ኡስታዝ፣ሸይኽ እና ዐሊም የለም። ሁሉም እንድትሰተር እንድትሸፈን ሲመክሯት እሺ ብላ ከለበሰች ብሗላ በእንዳንድ ኢስላም እና ሙስሊም ጠል በሆኑ አካላቶች ወይም መዋቅሮች ለሚያጋጥሟት ፈተናዎች ግን ድምፅ አልባ ሆን ይህ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ ይሻል ኩፋሮች በሞራላቸው በእድሚያቸው በመብታቸው ላይ እየተጫዎቱባቸው ነው።

ነፍስ ወደ አላህ ስትጠጋ እሺ አትልም !! ነፍስ ወደ አላህ ስትጠጋ እሺ አትልም። ምክንያቱም የእርሷ እረፍት በእርሱ ዘንድ ነው። የእርሷ ሰላም በእርሱ ዘንድ ነው። የእርሷ መረጋጋት በእርሱ ዘንድ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ﴾ “ንቁ! ልቦች የሚረጋጉት በአላህ ማስታወስ ብቻ ነው።” (ሱረቱ አር-ረዕድ፥ 28) ዓለም ሁሉ ቢሰጣትም አላህን ካጣች ባዶ ትሆናለች። ነገር ግን ዓለምን ሁሉ ብታጣም አላህን ካገኘች የሚጎድላት ነገር አይኖርም። ሰው በገንዘብ ይደሰታል፣ በቤት ይደሰታል፣ በልጆች ይደሰታል፣ በስኬት ይደሰታል፤ ነገር ግን ልቡ ከአላህ ርቆ ከሆነ በውስጡ የማይሞላ ክፍተት ይቀራል። ያ ክፍተት በገንዘብ አይሞላም። በዝና አይሞላም። በሰዎች ፍቅር አይሞላም። በዓለም ደስታ አይሞላም። ያንን ቦታ የሚሞላው አላህ ብቻ ነው። ኢብኑል ቀይም እንዲህ ብለዋል፦ "በልብ ውስጥ ያለውን ባዶነት የሚሞላው ወደ አላህ መመለስ፣ እርሱን መውደድ እና እርሱን ማስታወስ ብቻ ነው።" አንድ ቀን በሌሊት ዝም ብለህ ተቀምጠህ ራስህን ጠይቅ፦ "ከአላህ ጋር ያለኝ ግንኙነት እንዴት ነው? ስለ ዱንያ የምጨነቀውን ያህል ስለ አኺራ እጨነቃለሁን? ስለ ሰዎች የምፈራውን ያህል አላህን እፈራለሁን? ሰዎች ሲያዩኝ የማስተካክለውን ያህል አላህ ሲያየኝ እጠነቀቃለሁን?" እስቲ አስብ... ስንት ሌሊቶችን በሳቅ አሳልፈናል? ስንት ሌሊቶችን በውይይት አሳልፈናል? ስንት ሰዓታትን በስልክ አሳልፈናል? ነገር ግን ስንት ጊዜ ነው በሌሊት ተነስተን፦ "ያ ረብ! ናፍቄሃለሁ። ተመልሼ መጥቻለሁ። በራሴ ላይ በድያለሁ። እባክህ ይቅር በለኝ።" ብለን ያለቀስነው? አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَنْ تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ﴾ “ለአመኑት ልቦቻቸው ለአላህ ማስታወስ የሚረጋጉበትና የሚታዘዙበት ጊዜ ገና አልደረሰምን?” (ሱረቱ አል-ሐዲድ፥ 16) አብደሏህ ኢብኑ መስኡድ ይህች አያ ስትወርድ እንዲህ ብለዋል፦ "እስልምናን ከተቀበልን ከአራት ዓመታት በኋላ አላህ በዚህች አያ ገሰጸን።" ወንድሜ ሆይ! እኛስ ከስንት ዓመታት በኋላ እንገሰጻለን? ነፍስ ወደ አላህ ስትቀርብ ሰገዳዋን ለማቋረጥ አትፈልግም። ዱዓዋን ለማቆም አትፈልግም። ቁርኣንን ለመዝጋት አትፈልግም። ምክንያቱም በዚያ ውስጥ ያላገኘችውን እረፍት አግኝታለች። ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፦ "በዱንያ ውስጥ አንዲት ጀነት አለች፤ በዚህች ዱንያ ያቺን ጀነት ያልገባ በአኺራ ያለችውን ጀነት ሙሉ ጣፋጭነቷን አያውቅም።" እርሳቸው ይህችን ጀነት ሲሉ የአላህን ቅርበት፣ ዚክርን እና የኢማንን ጣፋጭነት ነበር። ሰው ከሰው ሲርቅ ሌላ ሰው ያገኛል፤ ከአላህ ሲርቅ ግን ማንንም አያገኝም። አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿وَمَنْ أَعْرَضَ عَنْ ذِكْرِي فَإِنَّ لَهُ مَعِيشَةً ضَنْكًا﴾ “ከማስታወሴ የዞረ ሰው ጠባብና አስቸጋሪ ኑሮ ይኖረዋል።” (ሱረቱ ጣሃ፥ 124) ምናልባት ዛሬ ትስቃለህ። ምናልባት ዛሬ ጤናማ ነህ። ምናልባት ዛሬ ብዙ እቅዶች አሉህ። ነገር ግን ነገ የት እንደምትሆን ታውቃለህን? ምናልባት ዛሬ የምትተኛው የመጨረሻ ሌሊትህ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ዛሬ የምትሰማው ድምጽ የመጨረሻው ድምጽ ሊሆን ይችላል። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «أَكْثِرُوا ذِكْرَ هَادِمِ اللَّذَّاتِ» “ደስታዎችን የሚያቋርጠውን ሞት ብዙ አስቡት።” ከዚያ በኋላ ግን አንድ ምኞት ብቻ ይቀራል፦ "ጌታዬ ሆይ! ወደ ዱንያ መልሰኝ። ሁለት ረከዓ ብቻ ልስገድ። አንድ ገጽ ቁርኣን ብቻ ላንብብ። አንድ እንባ ብቻ ላፍስ።" ነገር ግን በዚያ ቀን መመለስ የለም። አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿رَبِّ ارْجِعُونِ * لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ﴾ “ጌታዬ ሆይ! መልሱኝ፤ ትቼው በመጣሁት ውስጥ መልካም ሥራ እሠራ ዘንድ።” (ሱረቱ አል-ሙእሚኑን፥ 99-100) ስለዚህ ከዛሬው በፊት ተመለስ። ልብህ ሳይጠነክር ተመለስ። ዓይኖችህ እንባ ማፍሰስ ሲችሉ ተመለስ። የምሕረት በር ክፍት ሳለ ተመለስ። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «لَلَّهُ أَفْرَحُ بِتَوْبَةِ عَبْدِهِ مِنْ أَحَدِكُمْ بِضَالَّتِهِ» “አላህ ባሪያው ተውበት ሲያደርግ ከአንዳችሁ ያጣውን ነገር ካገኘ ይልቅ ይበልጥ ይደሰታል።” ዛሬ ማታ ሁሉም ከተኙ በኋላ ተነስ። ሁለት ረከዓ ስገድ። ከዚያም በእንባ እንዲህ በል፦ "ያ አላህ! ከአንተ ርቄ ኖርያለሁ። ነገር ግን ወደ አንተ ተመልሻለሁ። በራሴ ላይ በድያለሁ። አትተወኝ። አትጣለኝ። አትከልክለኝ። ልቤን ወደ አንተ አቅርብልኝ። በፍቅርህ ሙላው። በምሕረትህ ሸፍነኝ።" ምናልባት ያቺ ሌሊት የሕይወትህ መለወጫ ትሆን ይሆናል። ምናልባት ያቺ እንባ በአላህ ዘንድ ከብዙ ሥራዎች የበለጠ ክብር ትኖራት ይሆናል። ምናልባት ያ ከልብ የወጣ ጥሪ የጀነት መንገድህን ይከፍትልህ ይሆናል። ነፍስ ወደ አላህ ስትጠጋ እሺ አትልም፤ ምክንያቱም እርሷ ወደ ቤቷ ተመልሳለች። አላህ በመጨረሻ ለተረጋጋች ነፍስ እንዲህ ይላታል፦ ﴿يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ ۝ ارْجِعِي إِلَى رَبِّكِ رَاضِيَةً مَرْضِيَّةً ۝ فَادْخُلِي فِي عِبَادِي ۝ وَادْخُلِي جَنَّتِي﴾ “አንቺ የተረጋጋሽ ነፍስ ሆይ! ወደ ጌታሽ ተመለሺ፤ አንቺም ተደስተሽ፣ እርሱም ተደስቶብሽ። በባሮቼም ውስጥ ግቢ፤ ጀነቴንም ግቢ።” (ሱረቱ አል-ፈጅር፥ 27-30) ያቺ ነፍስ እሺ አትልም፤ ምክንያቱም ወደ እረፍቷ ተመልሳለች። ወደ ፈጣሪዋ ተመልሳለች። ወደ ዘላለማዊ ሰላምዋ ተመልሳለች። https://t.me/A2mnt

ጀግናዬ «ምንም ቢፈጠር ፈገግ በል» كما جئنا إلى الدنيا نروح ولو عشنا بها ما عش نوح የኑህን እድሜ ብንኖር እንኳን ወደ ዱንያ እንደመጣን መሰናበታችን አይቀርም። t.me/nuredinal_arebi

ዛሬ ደግሞ በጧት...✍️ «ሔጃለሁ...አልመጣም»!! ------------------------------ ገራፊ ሆይ እንካ፤ የፈለከውን ልክ በጀርባዬ መትር፡ ያለ ርህራሔ፤ ቀጥቅጠኝ ግድ-የለም ፈፅሞ አታማትር፡ ያበረታል እንጅ፤ ከጉዞ አያስቀርም የክፉ ሰው ብትር፡ ------------------------------------------ ቀኘንም ድገመው በግራዬ አታቁም፡ የአንተ ግርፋቶች ከኔ ተስፋ አይልቁም፡ ወጣት ሰውነቴን በለው ሁሉን እንካ፡ ከስኬት አይቀርም ህልም ያተመ ዱካ፡ አይኔ ደም ቢያነባ ቁጭት ቢያቀርርም፡ የጨቋኞች ስቃይ ከጉዞ አያስቀርም፡ ------------------------------------------- ጉዞዬ ሆይ ፅና ህልሜን አትስበረው፡ ጠንክረህ ተራመድ ሁሉን አትሰውረው፡ በርምጃህ ቅርበት ልክ ተስፋን አትሰረው፡ አብሽር ትደርሳለህ በገፉህ ልክ ነው ምትንደረደረው፡ --------------------------------------------- ተንኮል ከጠቀመን ክፋት ከቀረፀን፡ መበዳደል በዝቶ ጌታን ካሳመፀን፡ ምጥ እንደጠናባት ነፍሰ-ጡር ማህፀን፡ ሳምነው እየከዳኝ ምን ብዬ ልማፀን፡ ----------------------------------------- ያሰብኩበት መንገድ ደርሶ ባይሳካም፡ በሰወች ጫማ ልክ የራሴን አ'ለ'ካም፡ ለብቻ እሔዳለሁ ማንንም አልነካም፡ ቂም ከማጠራቀም ብቸኝነት መልካም፡ -------------------------------------------- ያየሁትን ባረግጥ ባልሆን እንደ ቡራቅ፡ እሔዳለሁ በእግሬ ከበደል ለመራቅ፡ ቁስሌ እስከሚጠፋ የተፉብኝ ምራቅ፡ -------------------------------------------- ከጨቅላ እድሜዬ ላይ ያሳረፉት ሰንበር፡ በቂም በጥላቻ የጣሉብኝ ቀንበር፡ በንፁህ ሐቄ ላይ ያስቀመጡት ድንበር፡ እስከሚስተካከል በእግሬ ነው የምበር፡ ------------------------------------------- በደል ግፍ መከራው እስኪቀየር ድረስ ፅንፈኝነት ጠፍቶ ፍትህ እስኪወረስ፡ የውሸት ዘር ሁሉ በእውነት እስኪታረስ፡ ------------------------------------------- እግሬ እኔን ያውቀኛል መሔድ አይሰለችም፡ መድረሴ እማይቀር ነው ጉዞው ባይመችም፡ ለምን አለቅሳለሁ ለምን ይለኛል' ቅር!! መከፋቴን ውድድ መገፋቴን ፍ'ቅ'ር. ተበደልኩኝ ብዬ ማንንም አልከስም፡ ተከሳሽ ፊት ቆሜ ህልሜን አላረክስም፡ ---------------------------------------- ለጥቅም ተገዝቶ እኔን ለራቀኝ ሰው፡ ምናሻኝ ብዬ ነው የማለቃቅሰው፡ ሲፈልግ ክፋቱን ጠቅልሎ ይጉረሰው፡ ሲያሻው እንደ ጃኬት  ኮት አርጎ ይልበሰው፡ ------------------------------------------- እንኳን ነፃ ወጣሁ ከክፉወች መንደር፡ የምን ቅሬታ ነው የምን መደራደር፡ መሸሽ አማን ይሁን መራቅ ሰላም ይደር፡ ---------------------------------------- ተስፋዬ አንዱ አምላክ ነው ስኬቴን አላጣም፡ ግፍ መከራን ጥሸው ሔጃለሁ አልመጣም፡ ------------------------------------------- ✍️በኑረዲን አል አረቢ➊➍➍➍ ------------------------------------------- https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid

الشيخ صالح سندي عن النووي وابن حجر الحق أحق أن يقال