ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Открыть в Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
320
Подписчики
+124 часа
-47 дней
+5530 дней
Архив постов
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (48)
~
መጅሊስ በታሪኩ ከመንግስት ተፅእኖ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ለዚህ ዋናው ምክንያት መጅሊሱ ላይ የሚቀመጡ አካላት ባህሪ ሳይሆን የፖለቲከኞቹ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህሪ ነው። ከዚያ የሚቀመጡ ሰዎች ድባቡን ያዩና ከ "አየር ንብረቱ" ጋር ራሳቸውን ያስማማሉ። የ1987ቱ የአንዋር መስጂድ ብጥብጥ ምክንያት ከጥቅም ግጭት ባለፈ የመንግስት አካላት ፍላጎት ከጀርባ ነበር። በሁለቱም ጎራ የተሰለፉ አካላት የተሻለ የመንግስት ድጋፍ እንዳላቸው ያስቡ ነበር። ኋላ ላይ አሕ^ባሽ ከሊባኖስ ተጋብዞ የገባውም ከመጅሊስ ሰዎች ፍላጎት ባለፈ የመንግስት ፍላጎት ስለነበር ነው።
ዛሬ ላይ ያለው የፖለቲካውን ነፋስ ተከትሎ የመጣው የመጅሊስ ለውጥም ያለቀለትና የማይነካ አይነት አይደለም። ነገ ሊቀየር ይችላል። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ አንዳንድ ደስ የማይሉ ሽታዎች ያሉ ይመስላል። መጅሊስ ላይ በየመዋቅሩ ያሉ አካላት ይህንን ተገንዝበው ለህዝባችን ዐቂዳውን ማስተማር ላይ ወይም ለማስተማር ምቹ ድባብ እንዲኖር ማድረግ ላይ መሬት የረገጠ ስራ ሊሰሩ ይገባ ነበር። ነበር የምለው በተግባር እየሆነ ስላላይደለ ነው። በተለይ አማራ ክልል ላይ ከ'ኮስሞቲክ' ስራዎች በመውጣት ዛሬ ላይ ቆፍጠን ብሎ መስራት ይሻል ነበር። ነገሮች ቢቀያየሩ ተፅእኖው ከሌሎች አካባቢዎች ይለያል።
ሌላው ቢቀር ለተሻለ መስለሓ ብላችሁ የገባችሁ ወገኖች ራሱ ከልብ በመመካከር ህዝብ ላይ ብትሰሩ መልካም ነው። ጊዜው አሁንም አልረፈደም። ብዙ መራመድ የሚያስችላችሁ አቅም ባይኖራችሁ እንኳ በአቅማችሁ ልክ የምትችሉትን ሳትሰሩ ጊዜው እንዳያልፍ ብታስቡበት ይሻላል። እውነት ለመናገር በተበላሸ ዐቂዳውም ቢሆን ሳይልፈሰፈስ ቆፍጠን በማለት እና መሬት የወረደ ስራ በመስራት በኩል ከመጅሊስ ተቋማት የተባረረው አሕ^ባሽ የተሻለ ትጋት አለው። አሕ^ባሽ የመጅሊሱ መዋቅር በእጁ ሳለም ያለምንም ይሉኝታ ህዝብን ለመለወጥ እስከ ደም ጠብታ ታግሏል። የያዘው ዐቂዳ ክር^ፋትና የመንግስት ዓይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት ነው ወደ ህዝብ ልብ ከመግባት እንቅፋት የሆነበት።
ከመሆኑም ጋር ለብልሹ ዐቂዳው በመዋደቅ ላይ ከመጅሊሱ ደጅ ርቆም አልቆመም። ዳግም ከተመለሰም ከቀደመው የበለጠ እንደሚጠቀምበት ይጠበቃል። ያ እንዳይሆን ወይም እውን ቢሆን እንኳ ጉዳት ለመቀነስ ደግሞ ፖለቲከኛ ተደግፎ መተኛት ሳይሆን ህዝብን ትክክለኛውን አስተምህሮት ማስታጠቅ ነው የሚገባው። የሹማምንትን ጫና ለመጋፈጥ ወይም ለመቀነስ ትክክለኛው መንገድ ደሞ ከአላህ በታች ህዝብን ማንቃት ነው ሁነኛው ስራ። አላህ ልብ ይስጠን።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 02/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ክብር ለዑለሞቻችን!
ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲ አል–ዓባድ ሐፊዞሁላህ፦ በዚህ ዘመን ከታላላቅ የሰለፊያ ዑለሞች መካከል በዒልምም ሆነ በእድሜ ከግንባር ቀደም የሚቆጠሩ ታላቅ የሐዲስ ሊቅ ናቸው። አይደለም ሸይኽ ዐብዱልሙሐሲን ይቅርና ተማሪዎቻቸው በዚህ ዘመን በእድሜም ሆነ በዒልም አቻ የሌላቸው ናቸው። ከተማሪወቻቸውም መካከል፦
1.የየመኑ ሙሐዲስ ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ሙቅቢል አል–ዋዲዒይ ረሒመሁላህ
2.ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል–መድኸሊይ ረሂመሁላህ
3.ሸይኽ ዑበይድ አል–ጃቢሪይ ረሂመሁላህ
4.ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሱሐይሚይ ሐፊዘሁላህ ይገኙበታል።
✍🏻 ኢብኑ ሙሐመድዘይን
📍 تفريغ دورة دراسات في المنهج (بصيغة pdf)
للشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله
ዐረበኛ የምትችሉ ኪታቡን አውርዳችሁ ብታነቡት በአላህ ፍቃድ እጅግ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ።
የተዳሰሱ ነጥቦች፦
1, መንሀጀ ሰለፍ
2, በዘመኑ ያሉ ጠማማ አንጃዎች
👉 ተብሊግ
👉 ኢኽዋን
👉 ዳዒሽ
3, ኢስላምን ያስጠሉ ግለሰቦች
(ሐሰን አል–በና፣ሰይድ ቁጥብ፣አቡ አዕላእ አል–መውዱውዲ) እና ሌሎችም የጥመት መሪዎች ረድ የተሰጠበት ዳሰሳ አካቶ ይዟል።
ኪታቡ ከላይ እተጠቀሱት ነጥቦች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሰፋ ባለሁኔታ ስለመንሀጅ የተዳሰሰበት ጥሩ ትምህርት ነው።
አላህ ተጠቃሚ ያድርገን። አሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
📌 በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደርስ ፕሮግራም
📚ተጀመረ
📚ተጀመረ
📚ተጀመረ
📖«* «مِنْهَاجُ الْفِرْقَةِ النَّاجِيَةِ وَالطَّائِفَةِ الْمَنْصُورَةِ»
لِلشَّيْخِ مُحَمَّدِ بْنِ جَمِيلٍ زِينُو (رَحِمَهُ اللَّهُ)
🎤🎤በወንድም አበል ሁበይብ(ሀፊዘሁሏህ)
t.me/sobabilelmesjide?videochat=c42d8a789a9173f8d2
📌 ጠቃሚ ዕውቀት ምልክቶች❗️
ሸይኽ ኢብን ዑሠይሚን رحمه الله እንዲህ ይላሉ፦
“ከራስህ ጋር ተመልሰህ በመጠየቅ፣ ከጠቃሚ ዕውቀት ምልክቶች ውስጥ ያለህ ድርሻ ምን ያህል ነው?”
እውቀት በመጽሐፍ ውስጥ የተሰበሰበ መረጃ ብቻ አይደለም። እውቀት በልብ ውስጥ ገብቶ በአካል ላይ የሚታይ፣ በአክላቅ የሚገለጥ እና ሰውን ወደ አላህ የሚያቀርብ ነው። ስለዚህ የተማርከው ዕውቀት ጠቃሚ መሆኑን በእነዚህ ምልክቶች መመርመር ትችላለህ፦
① በዕውቀትህ መሥራት።
የጠቃሚ ዕውቀት የመጀመሪያው ምልክት በተማርከው መሥራት ነው። ሰው ስለ ሶላት ብዙ ሊያውቅ ይችላል፤ ግን ሶላቱን ካልጠበቀ ዕውቀቱ ምን ጠቀመው? ስለ ተውሒድ ሊያስተምር ይችላል፤ ግን ልቡ ከአላህ ውጭ ከፍጥረት ጋር ከተጣበቀ ዕውቀቱ የት ነው?
ዕውቀት ወደ ተግባር ካልተለወጠ በሰው ላይ ማስረጃ ሊሆንበት ይችላል።
② ራስን ከማመስገን፣ ከመወደስና ከመኩራራት መጥላት።
ዕውቀትህ በጨመረ ቁጥር “እኔ ዐሊም ነኝ፣ እኔ ብዙ አውቃለሁ፣ እኔን ሁሉም ሊሰማኝ ይገባል” የሚል ስሜት ከመጣብህ፣ ይህ የዕውቀት በረከት ሳይሆን የነፍስ ፈተና ነውና ተጠንቀቅ።
ጠቃሚ ዕውቀት ሰውን ከፍ ያደርገዋል፤
ነገር ግን በራሱ ዓይን ከፍ አያደርገውም።
ሰዎች ሲያመሰግኑት ልቡ አይደሰትም፣ ሲያወድሱት አይኮራም፣ ሰዎችንም በዕውቀቱ አይንቅም።
③ ዕውቀትህ በጨመረ ቁጥር ትሕትናህ መጨመር።
ይህ ከጠቃሚ ዕውቀት በጣም ታላቅ ምልክት ነው። ትናንት ትንሽ ታውቅ ነበር፤ ዛሬ ብዙ ተምረሃል፤ ነገ ደግሞ ከዚያ የበለጠ ትማራለህ። ግን በዕውቀትህ ላይ ሲጨምር ትሕትናህም መጨመር አለበት።
እውነተኛ ዐሊም ዕውቀቱ በጨመረ ቁጥር የማያውቀው ነገር ምን ያህል ብዙ እንደሆነ ይገነዘባል። ስለዚህ እውቀት ወደ ትሕትና ይመራዋል፣ ወደ ኩራት አይመራውም።
④ የመሪነት፣ የዝና እና የዱንያ ፍቅርን መሸሽ።
ጧሊበል-ዒልም ራሱን በዝና ለማሳየት እውቀት አይማርም። “ሰዎች ይወቁኝ፣ ስሜ በሁሉም ቦታ ይጠራ፣ እኔ ከሁሉ በላይ ነኝ” የሚል ምኞት ከልቡ ይርቃል።
እውቀትን የሚፈልገው አላህን ለማስደሰት፣ እውነትን ለመከተል እና ሰዎችን ለመጥቀም ነው።
⑤ “እኔ ዐሊም ነኝ” ብሎ መናገርን መተው።
ጠቃሚ ዕውቀት ያለው ሰው የራሱን ደረጃ ለማሳየት አይቸኩልም። ሰዎች ሊጠሩት ይችላሉ፤ እሱ ግን ራሱን ከፍ ለማድረግ አይሞክርም።
እውነተኛ ዕውቀት ሰውን “ምን ያህል አውቃለሁ?” ከማለት ይልቅ “ከምማረው ምን ያህል ተግብሬያለሁ?” ብሎ እንዲጠይቅ ያደርገዋል።
⑥ ራስን በመጥፎ መገመትና ለሌሎች ጥሩ ጥርጣሬ ማድረግ።
ጠቃሚ ዕውቀት ያለው ሰው ራሱን አይመርጥም። ነፍሱን በጥሩ ነገር አይመሰክርም፤ ከሌሎች ግን ጥሩ ነገር ለማሰብ ይሞክራል።
ምክንያቱም ሌሎችን በመናቅ፣ በመውቀስና በመጥፎ ጥርጣሬ ውስጥ መግባት ራሱን ከእነርሱ በላይ እንደሆነ ለማየት ሊያመራው ይችላል። ጠቃሚ ዕውቀት ግን ሰውን ከኩራት ይጠብቀዋል።
🌿 እንግዲህ ጧሊበል-ዒልም ራሱን ሊጠይቅ ይገባል፦
ዕውቀቴ አላህን የበለጠ እንድፈራ አድርጎኛልን?
ሶላቴን አሻሽያለሁን?
አክላቄ ተሻሽሏልን?
ትሕትናዬ ጨምሯልን?
የዝና እና የመሪነት ፍቅር ከልቤ እየቀነሰ ነውን?
ወይስ ዕውቀቴ ሰዎችን እንድንቅ እያደረገኝ ነው?
ከዚህ በኋላ የሚጠየቀው “ስንት ኪታብ አንብበሃል?” ብቻ አይደለም። ዋናው ጥያቄ፦
“ከዚያ ሁሉ ዕውቀት ምን ያህል በልብህ፣ በአክላቅህና በሥራህ ላይ ታይቷል?”ይህ ነው የጠቃሚ ዕውቀት ፍሬ። 📘 شرح حلية طالب العلم، صـ253 t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ማነው ፖለቲካ የገባው?
~
የሰዎች የኋላ ዳራ (background)፣ ስሜት፣ ፍላጎት፣ የሚከተሉት አስተሳሰብ፣ ቡድናዊ አመለካከት፣ የንቃት መጠን፣ የትምህርት ደረጃ፣ የዲን ግንዛቤና አቋም፣ ወዘተ ይለያያሉ። ይህንን ተከትሎም የሚደግፉትና የሚቃወሙት የፖለቲካ ኃይል ይለያያል። እዚህ ድረስ መግባባት ይቻላል። የምንለያየው ይህንን እውነታ የሚያረጋግጥ ተግባራዊ ማሳያ ስንመዝ ነው።
የሚገርመው እነሱ የሚደግፉትን የማይደግፍ፣ እነሱ የሚጠሉትን የሚወድን አካል "አንተ ፖለቲካ አልገባህም" የሚሉ ሰዎች ሁኔታ ነው። ልክ ፖለቲካ መረዳት ማለት ከነሱ ስሜት ጋር መግጠም የሆነ ይመስል። ስለ ፖለቲካ ብዙ የለቀለቀ ወይም የፈተፈተ ሁሉ ፖለቲካ ገብቶታል ማለት አይደለም። ዝም ያለም ሁሉ አልገባውም ማለት አይደለም። ነጋ ጠባ ዜና መዘገብ ፖለቲካ መረዳት አይደለም። ትንሽ ትልቁን ከሴራ ጋራ እያስተሳሰሩ መጎንጎንም የፖለቲካ ችሎታ ሳይሆን የራስን ስንፍና መሸፈኛ ሰበብ ነው። ይሄ ነገር በጣም ከመብዛቱ የተነሳ "ዐረብ ልጁ ትምህርት ቤት ቢወድቅበት የአይ^ ሁድ እጅ አለበት" ከማለት አይመለስም እስከማለት የተሳለቁ አሉ። ግነቱ በውስጡ የሆነ እውነት አለው።
ለምሳሌ ያክል የሀገራችንን የዘር ፌዴራሊዝም በፅኑ የሚያወግዝ ብዙ ኃይል አለ። አሀዳዊ ስርአትን ከሺርክ በላይ የሚኮንንም ብዙ ወገን አለ። አስቡት እንግዲህ ሁሉም እየተነሳ ሌላኛውን አካል ፖለቲካ አልገባህም እያለ ሲያጣጥል። አተያያችን የተራራቀው በዋናነት በግንዛቤዎችን መበላለጥ ምክንያት አይደለም። ይልቁንም በብልጣብልጥና ስግብግል ባህሪያችን የተነሳ ነው። በትምህርት ዝግጅታቸውና ደረጃቸውም፣ በሚከተሉት እምነትም ተመሳሳይ የሆኑ ሁለት ከአማራና ከኦሮሞ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዘር ፌዴራሊዝምና በአሃዳዊ ስርአት ላይ ያላቸው ምርጫ ተቃራኒ ነው። ለምን? ግልፅ ነው። ታሪክን የሚረዱት በተራራቀ መልኩ ነው። የዛሬ ምርጫቸውም እንዲሁ የተራራቀ ነው።
ልክ እንደዚሁ እኔና አንተ ዐቂዳችንና መንሀጃችን እስከተለያየ ድረስ በሙስሊም ሀገራትና ቡድኖች ላይ ያለን ፖለቲካዊ አተያያችንና ውግንናችንም ይለያያል። ላንተ የዑመር ጠላት የሆኑ ሺዐዎችን መውደድ ኖርማል ነው። ለኔ ደግሞ ይሄ ፈፅሞ ሊያቀራርበን የማይችል ቀይ መስመር ነው። ላንተ "ሙስሊም" የሚለው ስሙ እስካለ ድረስ የፈለገውን ቢያራምድ ዋናው "ሞት ለአሜሪካ!" ማለቱ ነው። ከአሜሪካ ጋር አይንና ናጫ የሆነችው ሰሜን ኮሪያ ራሱ የአሕመዲያ መዝሀብ ተከታይ ብትሆን ኖሮ ሱኒ ሙስሊሞችን እያነቀች ብትገ ^ድል እንኳ ከመደገፍ አትመለስም ነበር።
ለማንኛውም እንደ ሙስሊም ነገሮችን ሁሉ የምንመለከትበት መነፅር ዲን ሊሆን ይገባል። የዲን መሰረቱ ደግሞ ተውሒድ ነው፣ ዐቂዳ ነው። ወላእና በራአችን ዐቂዳን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል። ይህንን ነጥብ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከኢስላም ቋጠሮዎች ሁሉ ጠንካራው" ሲሉ ነው የገለፁት። የዐቂዳ ጉዳይ ላንተ ውሃ የማያነሳበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ራስህን ጠይቅ፣ ልብህን አድምጥ። ምናልባት ለማስተዋል ከጠቀመህ - እንዲያው ምናልባት - ሺዐ እና ሱኒን ለማቀራረብ በጣም ለረጅም ዘመናት የደከመው ዩሱፍ አልቀርዷዊይ በዚህ ጥረታችን ሺ0ዎች አተረፉበት እንጂ ለሱኒው ዓለም ከጉዳት በስተቀር ያተረፈው ፋይዳ የለውም ማለቱን ያዝ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ጓደኛውን ማስተናገድ ላይ ድንበር የሚያልፍ እና ወንድሙን ችላ የሚል በርግጥም ሞኝ ነው።
የትኛውም አይነት ከባድ ሁኔታ ቢፈጠር፣ የፈለገ ግኑኝነቱ ቢከፋ በወንድሞች መሃል ሊጠፋ የማይችል የስጋና የመንፈስ ትስስር አላህ አስቀምጧል። ይህ ትስስር ምንም እንኳን በ አንዳንድ ወንድሞች ላይኖር ቢችልም ህመም ወይም ሞት ቢመጣ ወዲያው ወደ ቦታቸው ይመለሳሉ።ምን ያህል ወንድሞች ወንድማቸውን አባረው ከሞተ ቡሃላ የተጸጸቱ ናቸው? "ምናለ እንዲህ ባላደረግኩ" ብለው የተቆጩ ብዙ ናቸው።
ጓደኝነት ከሆነ ጊዜያዊ ነው። ጥንካሬው የሚወሰነው በሁኔታዎች መመቻቸት፣ ፍላጎትን በማሟላት ላይ የተመሰረተ ነው። ትንሽ ነገር ትስስራችሁን ያበላሻል።ፍላጎት ካላሟላችሁ ሁሉም ነገር ያበቃል።
ባለፉት ጊዜያት ልክ እንደማንኛውም ሰው ቅርብ ጓደኝነት ከብዞዎቹ ጋር ነበረኝ።ለአመታትም የቆየ ነበር።በምንም ተአምር ሊደክም፣ ሊቋረጥ የማይችል እስኪመስለን ድረስም ደርሶ ነበር። ያ ጓደኝነት ከወንድሞቼ ጋር ካለኝ ግኑኝነትም በላይ ነበር። ይሁን እንጂ ከግዜ ቡሃላ ከአንዳንዱ ጋር ይደክም፣ከሌላው ጋር ይቋረጥ፣ አብሮ መቀጠል ከባድ እስኪሆን ድረስ ደርሶ ነበር።
የሚገርመው ነገር ለዚህ ነገር ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም። "ምን ተፈጥሮ ይሁን የተራራቅነው?" ብላቹ አንዱን ብትጠይቁ በቂ ምላሽ አታገኙም።
ብዙ ግዜያትን መከታ የሚሆን፣ ታማኝና ወዳጅነቱ ዘላቂ የሆነ ጓደኛ ስፈልግ ቆይቻለሁ። አንድንም ማግኘት አልቻልኩም።
ከ አንድ ሰው ጋር ጓደኝነት ስንጀምር "በቃ! ይህ ነው የተበቅኩት ሰው" እንላለን። ከተወሰነ ቆያት ቡሃላ፣ ብዙ መቀላቀል ሲበዛ ጓደኛችሁ ግዴለሽ ሲሆን፣ አብራችሁ ስላላችሁ የሚሰላች፣ ጓደኝነታችሁ እንዲላላ ያለውን ፍላጎት ማየት ትጀምራላችሁ።
ከዚህ ቡሃላ ነበር ከ አንድ ፍጹም የሆነ ድምዳሜ የደረስኩት። ምን ብትወዳጁ የገዛ ወንድም አይነት ወዳጅነት የትም እንደማይገኝ፤ከወንድም ውጪ በሙሉ ልብ የሚተማመኑበት መከታ እንደሌለ፣ ላይቋረጥ የሚችል ፍቅር ከወንድም ጋር ብቻ እንደሚገኝ ረፍዶም ቢሆን ገባኝ።ከወንድማችሁ ጋር ያለው ወዳጅነት አብራችሁ ብዙ ስለቆያችሁ የሚቀንስ አይደለም።የሆነ ችግር በመሃላችሁ ቢፈጠር እንኳን መልሳችሁ ማስተካከል፣ ወደ ቀድሞ ፍቅራችሁ መመለስ ቀላል ነው።እንዲህ አይነቱን ጠንካራ ወዳጅነት ስንት ሰው ነው ወዳጅነታቸውም ለማይዘልቅ ጓደኞቹ ሲል ያላላው፣ ወንድሞቹን ያራቀው?!
እና አደራችሁን ለጓደኛ ብላችሁ የወንድማችሁን ወዳጅነት አታላሉ።"የኔው ነው የትም አይሄድም" ብላችሁ አትጣሉት። አንዳንዴ ላይመለስ መሄድም አለ። በቅርብም ይሁን በሩቅ ይጸጽታቹሃል።
ከወንድማችሁ ጋር ምን ያህል ብትቆራረጡ፣ብትጣሉ፣ መግባባት ቢያቅታችሁ በዚህ ሁሉ ውስጥ ለናንተ ያስባል፣ ስለናንተ ይጨነቃል፣ ፍቅሩን ይዞ ያቆያል። "አጥፍቻለሁ" ብላችሁ ብትመለሱ በሱ ዘንድ የነበራችሁን ክብርና ደረጃ መልሳችሁ ታገኛላችሁ።
ጓደኛ ግን አንድ ግዜ ብትጋጩ፣ ብትቆራረጡና የሆነ ነገር ብትሉት በልቡ ውስጥ ቁጣን፣ንዴትን እና ጥላቻን እንጂ ሌላ አታገኙም። ይቅርታ ብትጠይቁ እንኳን ያ የቀድሞ ክብራችሁን፣ደረጃችሁን፣ ፍቅራችሁ አይመለስም።ይህ በአብዛኛው ያለ እውነታ ነው።
ለብዙ ግዜያት የተቆራረጡ ፣ ብዙ ደረጃ የደረሱ ወንድሞች ከሆነ ግዜ ቡሃላ አንድ ሆነው፣ ጥሩ ሁኔታ ላይ የደረሱ ሰዎችን አይቻለሁ።እስከመዘላለፍና መለያየት የደረሰ ጓደኝነት ግን ወደቀድሞ ፍቅር ተመልሶ ሲመጣ አላየሁም። ሂወት ስለሚቀጥል አብሮ ተኮነ እንጂ በልብ እንደቀድሞ መሆን ከባድ ነው። በቃ ምን አለፋችሁ ከተራራቃችሁት ጓደኛችሁ ጋር ዳግም መገናኘትና እንደቀድሞ መሆን ማለት ሶስቴ የተፈታች ሴት ወደ ባሏ እደምትመለሰው ነው!…(ሌላ አግብታ ፈታ ካልሆነ ሚስቱ መሆን አትችልም)
#ትዝብት
ከደጋጎች አለም ክፍል 65
@Jemalendro33
https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16482
🔶 ታቢዒዩ ኢብራሂም አተይሚ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
﴿شيئان قطعا عني لذة الدنيا : ذكر الموت وذكر الموقف بين يدي الله تعالى﴾
“ሁለት ነገሮች የዱኒያን ጥፍጥና ከውስጤ እንዲወጣልኝ (እንዲቆርጥልኝ) አድርገውኛል። ሞትን ማስታወሴና በላቀው አላህ ፊት ለፍርድ መቆሜን ማስታወስ።”
ተዝኪራ ቢዓህዋሊል መውታ አልአኼራ፡ (125)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/DeewaSelefyya1448
https://t.me/DeewaSelefyya1448.
Repost from ስለ ዲናችን
➐ ቱን የቁረአን ተፍሲር አፕ የያዝ
🥇بن كشير
🥈القرطبى
🥉الطبرى
⓸اللغوى
⓹السعدى
➅الوسيط
➆الميسر
በጣም አስፈላጊ አፕ ነው አውርዳችሁ ተጠቀሙበት እዛውም ላይ ቁረአን የሚታይ የሚቀራ አለው ።
🇸🇦የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/KedmiyaLetewhid9
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የረሳነው መስታዎት
~~
°
አካልህ ተውቦ
ገፅታህ አብቦ
ሰውነትህ ደምቆ
መልክህ አሸብርቆ
•
መደነቅ ያማረው፣
መኮፈስ ያጓጓው፣
መስታወት ያሰኘው፣
‘እየኝ’ ያለህ ’ለታ፣
እፍኝ አፈር ዘግነህ ተመልከት በጌታ!!
ተመልከት በአላህ!
ተመልከት በቃሉ
ቋንቋ ብሄር ሰጥቶ ቢያግባባህ ጀሊሉ
ዘር እየመነዘርክ ትጎራለህ አሉ!
•
ወንድማለም!
እስኪ
ተመልከት ከጭቃው፣ ተመልከት ከምድሩ
አንተን አንተን ይላል፣
ዘመድ ከዘመዱ ሰውም ከ አፈሩ!
•
መልክህ ረጋፊ ነው፣
ቀለምህ ጠፊ ነው፣
ቋንቋህ አላፊ ነው፣
ብሄርህ ትርፍ ነው፣
አካልህ ፈራሽ ነው፣
ዋናው ማንነትህ አፈር ነው ጭቃ ነው።
•
ወንድሜ!
እስኪ አትንጠራራ
አትደርስም ተራራ!
እስኪ አትንገዳገድ
ምድር ላትሰረጉድ
አፈር ነህ ያ’ፈር ልጅ
የግም ጭቃ ውላጅ!
•
አፈር ነው መነሻህ
አፈር ነው መድረሻህ
አፈር መጀመሪያህ አፈር መጨረሻህ
ነገም ከ አፈር ነው ዳግም ’ምትወጣ
እንደተበተነ እንደ መንጋ አንበጣ!!
•
ከጭቃ ተሰርቶ፣
ከጭቃ ተነስቶ፣
በቆሻሻ መውጫ ሁለት ጊዜ ወጥቶ፣
መሬት አይንካኝ ሲል
በኩራት ሲፏልል፣
በትእቢት ሲሸልል፣
አይደንቅም ወይ ከቶ!!
አይ የሰው ልጅ!!
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሃሴ 29/2011)
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
አላህ ሆይ!....
እርዳታህን ከጅዬ - አንገቴን ደፍቼ :
ወገቤ አጎንብሶ - ሱጁድ ተደፍቼ :
ልቤ ተወክሎህ - እጆቼን አንስቼ :
ተስፋን በአንተ ጥዬ - አንብተው አይኖቼ :
እርዳኝ ጌታዬ ሆይ! - ይላል አንደበቴ :
ደስታን ከኔ አድርጋት - አውጣኝ ከጭንቀቴ :
በመልካም ስሞች - በላቁ ባህሪዎችህ :
እርዳኝ ጌታዬ ብዬ - ሁሌም ልለምንህ :
ከዱኒያ እስከ አኺራ - አንተን እስካገኘህ :
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from 𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
«ጌታዬ ሆይ! የቁርኣንን በረካ፣ የቁርኣን መጅሊሶችን እና የቁርኣን ወዳጅነትን አትንሳን። »
http://t.me/ibrahim_furii
🔶 ኢላሂ ምራኝ
➜ ኢላሂ የልቤን ሚስጥር አንተ ታውቃለህ።
በሰወች ዘንድ አስመስል ይሆናልጂ
አንተ ዘንድ ፈፅሞ አይቻለኝም።
ኢላሂ የምታውቀውን እኔነቴን ለአንተ አላስረዳም።
ከአንተ ብቻ ግን እከጅላለሁ።
ከእግድህ ላንተ ካልሆነ በቀር አንድትም እንባ እዳላፈስ እርዳኝ።
ብዙ ነገር ፈልጌ ነበር።
በፍላጎቴ ውስጥ ግን አንተን አላስቀዴምኩም እና አንድም ያገኘሁት አላስዴሰተኝም።
ኢላሂ አንተን ብቻ እፈልጋለሁ።
መቸ እንዴተሰበርኩ ምን እንደሰበረኝ
እንዴት እያሳለፍኩ እንዴሆነ ካንተ በቀር
ማንም አያውቅም
አንተ ካልሆክ በቀር ማንም አይረዳኝም።
የደካማ ደካማ የሆንኩት ባሪያህ ነኝና እገዘኝ ኢላሂ...
Umu_Faruq
አቡ ሙዓዝ ለትሚዮች በስህተት ላይ እንደሆኑ ያምናል። ሰምታችሁ ፍረዱ ምናልባት ከሱ በላይ መናገር ይዘገንናል። አሁን ላይ በነሱ ዙሪያ ምን ለውጥ አግኝቶ ነው። ነው ዱሮም በነሱ ላይ ሲናገር #በሞቅታ ነው ወላሂ ያ አባ ሙዓዝ በአለህበት ላይ ቁመህ አስብ ያለበለዚያ ሰለፊዮችን ትተህ እራስ ወዳልከው ቅሬ ላይ እንኳ የማይጠበቅ አርካባስ ጭፍራ ገብተሀል።
ሁላችንም ለራሳችን ነፍስ እንዘንላት ያጀምዓ
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me/Abulabas1444
http://t.me/Abulabas1444.
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኺላፍ ሁሉ መጠኑ አንድ አይደለም። ዑለማእ እነሱ ዘንድ ሚዛን የሚደፋውን በማስረጃ እያበጠሩ በመግለፅ የሚተላለፉባቸውን ነጥቦች በሆደ ሰፊነት ማስተናገድ ያስፈልጋል። በእንዲህ አይነት ነጥቦች ላይ ያላግባብ የከረረ አቋም መያዝ
* የዑለማእ አያያዝ አይደለም።
* ለጭቅጭቅና ልዩነት ይዳርጋል።
* በሌሎች ላይ ድንበር በማሳለፍ በደል ላይ ይጥላል።
* የሆነ ወቅት ላይ በመረጃ ገምግመን ሃሳብ ብንቀይር ለሐቅ እጅ መስጠት እንዲከብደን ያደርጋል።
* ተመሳሳይ መጠን ባላቸው ጉዳዮች ላይ የተለያየ አቋም በማራመድ ተቃርኖ ላይ ይጥላል።
ይሄ ከመሆኑ በፊት የኺላፍ ጉዳዮችን ዑለማእ በሚይዙበት መጠን እየያዝን መሆናችንን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አላህ ይጠብቅህ! ይህ ማሳሰቢያ ለእያንዳንዳችን ትልቅ የንቅናቄ ደወል ነው። በእውነትም ከሸይኽ ወይም ከኡስታዝ የሚቀሰመው ትምህርት የመነሻ ቁልፍ እንጂ የመጨረሻው ማጠቃለያ አይደለም። ይህ ያነሳኸው ነጥብ የብዙዎቻችንን ሕመም የነካ፣ የእውቀት መንገድ (ጦለቡል ዒልም) ላይ ለሌለንም ላሉም ሰዎች ትልቅ የቤት ሥራ የሚሰጥ ድንቅ ማስታወሻ ነው። የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ ታሪክ በጣም ያስደነግጣል! “አንተ ሰነፍ ስለሆንክ አታነብም” የሚለው የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂም ምላሽ ለእያንዳንዳችን የተላከ የግሳጼ መልእክት ነው። ዛሬ እኛም በተመሳሳይ የፍለጋ እና የማንበብ ሰነፍነታችን ምክንያት በትንሽ በትልቁ የሰዎችን ጊዜ እያባከንን፣ የራሳችንን አእምሮ ከማንበብ እና ከማንቆርቆር አግደነዋል። ኡስታዝ በሩን ይከፍትልናል፤ በሩን አልፈን የዒልሙን ማዕድ የምንጎበኘውና የምንመገበው ግን በራሳችን ጠንካራ የንባብና የጥናት ጥረት ነው። የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ ታሪክ ደግሞ ጥገኛ የመሆንን አደጋና የራስን ጥረት አስፈላጊነት በግልጽ ያሳያል። እንደ አላህ ፈቃድ፣ ያለፈው ዓመት የነበረንን ክፍተትና ድክመት አምነን በመቀበል፣ ከዚህ ቀንና ዓመት ጀምሮ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለዒልምና ለንባብ ለመስጠት መጣር አለብን። ወንድሞችና እህቶች! ሰነፍ መሆን የተፈጥሮ ግዴታችን አይደለም፤ ልማዳችን ነው፤ ልማድን ደግሞ በትግል መለወጥ ይቻላል። እውቀት በምኞትና በስነ-ስርዓት አልበኝነት አይገኝም። የቀረበውን ምክር መነሻ በማድረግ ራሳችንን ለመለወጥ ተግባራዊ የሆነን እርምጃዎች መውሰድ ግድ ይለናል፦ የደርስ አጥባቂነት (ኢስቲቃማ)፦ በየቀኑ የምንከታተላቸውን የቂርአት ደርሶች ያለ ምክንያት አለማቋረጥና በሰዓቱ መገኘት። ደርስ ማቋረጥ የጅህልና መጀመሪያ ነው። የቀን ተቀን የንባብ ፕሮግራም ማውጣት፦ "ጊዜ ሲኖረኝ አነባለሁ" የሚል ሰው ፈጽሞ አያነብም። ይልቁንም በቀን ቢያንስ ከ1 እስከ 2 ሰዓት ለግል ንባብና ሙራጃዐ (ክለሳ) የተወሰነ ቋሚ ጊዜ መመደብ። ከጥራዝ ነጠቅነት መራቅ፦ አንድን ኪታብ ስንጀምር ከመጨረሻው ሳናደርስ ወደ ሌላ አለመሸጋገር። ኪታቦችን ከነሐሺያቸውና ከነሸርሃቸው በጥልቀት መመርመር። ማስታወሻ መያዝ ፦ በምናነብበትና በምናጠናበት ጊዜ አዳዲስ ነጥቦችን፣ የዑለማዎችን ልዩነቶችና ማስረጃዎችን በደብተር ላይ ማስፈር። የንባብ ባህልን ማዳበር፦ በትንሽ በትልቁ ሌላውን ሰው ከመጠየቅ በፊት፣ ራሳችን ኪታቦችን ገልጠን የመፈለግና የማጣራት ልምድ ማሳደግ። የእውቀት መንገድ በትግል እና በሶብር እንጂ በምቾት እና በፍላጎት አይገኝም። ዛሬ ወጣትነታችንን በቲክቶክ ስክሪን ላይ ከምናጠፋው፣ ነገ ለአል-ኢስላምና ለኡምማው የሚጠቅሙ፣ ጥራዝ-ነጠቅ ያልሆኑ ባለሙሉ እውቀት ጧሊቦችን ለመሆን አሁኑኑ መነሳት አለብን። ባለፈው ዓመት ያጣነውን ጊዜ አንመልሰውም፤ የዚህን ዓመት እድል ግን በቁርጠኝነት እና በማንበብ እንጠቀምበት! አላህ እውነተኛና ጠቃሚ እውቀትን ይለግሰን፤ ከስንፍናም ይጠብቀን! ወንድሞቼ! ይህንን መልእክት ለእናንተ ስጽፍላችሁ እኔ ከእናንተ በላይ አውቄ ወይም የበላይ ሆኜ አይደለም፤ ነገር ግን ኡስታዝ የላከው መልዕክት ልቤን ስለነካውና ለእኔም ለእናንተም ትልቅ ማስታወሻ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ነው:: አፉ በሉኝ፤ አላህ ሁላችንንም ወደ መልካሙ መንገድ ይመራን፣ ሰነፍነታችንንም አስወግዶ ጠቃሚ እውቀትን ይለግሰን።"«الرَّاجِي رَحْمَةَ رَبِّهِ، العَبْدُ الفَقِيرُ: أَبُو مَاحِي بْنُ إِدْرِيس» https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ባለፈው ዓመት ምን ያህል ኪታብ አንብባችኋል? በዚህስ ዓመት ምን አሰባችሁ? በተለይ የሸሪዐ እውቀትን በመማርና በማስተማር ላይ የተሰማራችሁ? የማያነብ ጧሊበል ዒልም ሊለወጥ አይችልም። የእውቀት ትጥቅ ለመታጠቅ፣ የግንዛቤ አድማስን ለማስፋት፣ ከጥራዝ ነጠቅ አስተሳሰብ ለመራቅ፣ የሌሎች ጭፍን ተከታይ ከመሆን ለመትረፍ ማንበብ ወሳኝ ነው። ከሸይኽ ወይም ኡስታዝ ላይ የምትማረው ዋና መሰረት ቢሆንም እዚህ ላይ ብቻ አትንጠልጠል። ማንም ቢሆን ሁሉን ኪታብ አይማርም። የፈለገ ቢሆን የምትማረው ውስን ነው። ከዚያ በኋላ ጥልቅ የሆነ የራስ ጥረት ያስፈልጋል። መሰረታዊ ነጥቦችን ከሸይኽ ከቀሰሙ በኋላ ሳይሰለቹ ማንበብ ይገባል።
ደግሞም መጠየቅ ጥሩ ቢሆንም በትንሽ በትልቁ ሰው ላይ ጥገኛ መሆን አይገባም። በራስ መጣር፣ መድከም ያስፈልጋል። ሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ጊዜ ከዳኞች አንዱ ወደ ክቡር አያቴ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂም (አላህ ይዘንላቸውና) በፍርድ ቤት የዳኝነት ስራው ላይ ስለገጠመው አንድ ጉዳይ ብይን (ሑክም) ሊጠይቃቸው ደብዳቤ ጻፈ። ሸይኹም በሁለት መስመር ብቻ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦
'ይህ ጉዳይ በሁሉም የዑለማእ ኪታቦች ውስጥ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን አንተ ሰነፍ ስለሆንክ አትመረምርም (አታነብም)። ሰላም።' "
[ሙሂማቱን ፊ ጦለቢል ዒልም]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
