ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

Открыть в Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
318
Подписчики
-424 часа
-77 дней
+5430 дней
Архив постов
140 ሓዲሶች ክፍል 15.mp313.36 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 14.mp318.54 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 13.mp314.55 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 12.mp317.20 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 11.mp315.76 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 10.mp318.80 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 9.mp318.62 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 8.mp319.22 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 7.mp316.12 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 6.mp316.77 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 5.mp314.88 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 4.mp311.72 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 3.mp315.53 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 2.mp312.11 MB

140 ሓዲሶች ክፍል 1.mp316.16 MB

#የእውቀት_መጀመሪያ_130_ሐዲሦች በኡስታዝ / ሳዳት ከማል አቡ መርየም

⚠️ተውሒድ ማለት እንዲሁ የምንሸመድደው የመጽሐፍ ገጽ፣ በብዕር የምንከትበው ቃል ወይም በሚንበሮች ላይ የሚደረግ ደረቅ ንግግር ብቻ አይደለም። ተውሒድ ማለት ከልብ ጥልቀት የሚመነጭ፣ በደም ስራችን ውስጥ የሚፈስና ሙሉ ሕይወታችንን ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ብቻ የምናስገዛበት የታላቅነት መገለጫ ነው። ተውሒድ ማለት በልብ ውስጥ ከአንድ አምላክ ከአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ውጭ ሌላን ኃይል አለማስገባት፣ በምክንያቶች ሳይሆን በምክንያቶች ፈጣሪ ላይ ብቻ መመካት ነው። እወቁ... ከአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى በስተቀር አድራጊ የለም! የሚጠቅመውም፣ የሚጎዳውም፣ የሚያከብረውም፣ የሚያዋርደውም፣ የሚያበለጽገውም፣ የሚያደኸየውም፣ ሕይወት የሚሰጠውም፣ የሚገድለውም እርሱ ብቻ ነው። ፍጡራን ሁሉ ደካሞች ናቸው፤ ሐኪሞች ይታመማሉ፣ መሐንዲሶች ይሳሳታሉ፣ ኃያላን ይወድቃሉ። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ግን የዓለማቱ ጌታ፣ የሰማያትና የምድር ብቸኛ አስተናባሪ ነው። ፀሐይን ያለ ስህተት በምህዋሯ የሚያስኬደው፣ ሰማያትን ያለ ምሰሶ የጠበቃቸውና አንዲት ቅንጣት እንኳ የማታመልጠው ሐፊዝ (ጠባቂ) የሆነው ጌታ እርሱ ነው። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ለነቢዩ ሙሳ عَلَيْهِ السَّلَامُ እንዳለው፦ "ሙሳ ሆይ! እኔ ብተኛ ኖሮ ሰማያት በምድር ላይ ይወድቁ ነበር።" ነገር ግን እርሱ የማይተኛ፣ የማይረሳና ሁልጊዜም ከባሮቹ ጋር የሆነ ኃያል ጌታ ነው። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ካንተ ጋር ከሆነ ከማን ትሰጋለህ? በሕመምህ ሰዓት ወደ አላህ ተጠጋ። የትዳር አጋርህ ስታስቀይምህ ወደ አላህ ጩህ። ልጅህ ሲከዳህ ወደ አላህ ተመለስ። ጭንቀትህ ሲበዛና ሲሳዩ ሲጠብብህ የመውጫውን በር ከአላህ ዘንድ ፈልገው። ሰዎች ቢርቁህ ወደ አላህ ቅረብ፤ ምክንያቱም የሁሉ ነገር ቁልፍ ያለው በእርሱ እጅ ብቻ ነውና። እነዚያ ‹ኃያላን ነን› ያሉትን ፈርዖንንና ሰሙድን አላህ የት እንዳደረሳቸው ታሪክ ምስክር ነው? በእርሱ ፊት የትኛው ምድራዊ ኃይል ይቆማል ነገር ግን? አላህ የፈለገውን ሰሪ ነው። የእርሱ ትእዛዝ አይመለስም፣ የእርሱ ኃይል አይገታም። ስለዚህ በየትኛውም የሕይወት አጣብቂኝ ውስጥ ብንሆን፣ ልክ ነቢዩ መሐመድ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ በዋሻ ውስጥ ሆነው ለጓደኛቸው ለአቡ በክር رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ እንዳሉት እኛም ለነፍሳችን እንዲህ እንበላት፦ "አትዘን! አላህ ከእኛ ጋር ነው!"። እውነተኛ ተውሒድ ይኸው ነው! ሰላም የሚገኘው ወደ አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى በመቃረብና በእርሱ ውሳኔ በመርካት ውስጥ ብቻ ነው። ዛሬም ነገም ለስኬትና ለደስታ የሚበቃው አላህን ብቻ መከታ ያደረገ ልብ ነው። ኢላሒ..! በልባችን ውስጥ እውነተኛውን ተውሒድ ዝራብን። ካንተ ውጭ ላለ ማንኛውም ኃይል እንዳንሰግድና እንዳንዋረድ በእምነታችን አጽናን። መጨረሻችንንም በተውሒድ ቃል አሳምርልን። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

📌 قصيدة بعنوان : |المنهج السلفي| منهاجنا سلفي بالحق لا خلفي شيوخنا في العصر علومهم كالبحر منهم الألباني العالم الرباني ومنهم ابن باز الشمس كالحجاز والعذب ذو النصايح محمد بن صالح وكاشف البهتان محمد الرسلان وقامع كل مبطلي ربيع بن هادي مدخلي وكذلك [محمد] وفقيه الزمان صالح الفوزان ودرّة الزمانِ مقبل اليماني وشيخنا الهمام محمد الإمام منقول

አሰላሙ ዓለይኩም ተቋርጠው የነበሩ ደርሶች ዛሬ ይጀመራሉ ኢንሻአላህ ለነበረው የቂርአት መቆራራጥ በድጋሜ ይቅርታ ለማለት እወዳለሁ።

ከዝምታህና ከመናገርህ የትኛው ይበልጣል? ~ ሸይኽ ወይም ኡስታዝ ነህ? ለጠየቀህ ሁሉ አትመልስ። በቅንነት የሚጠይቅ እንዳለ ሁሉ ብዙ ተንኮለኛም አለ። መልሱ የሚጠቅመው እንዳለ ሁሉ የሚጎዳውም አለ። "እነ እከሌ እንዲህ አሉ" "እከሌ እንዲህ አለ" ሲሉት ለአፍታ እንኳ ፋታ ወስዶ ሳያጣራ በደመነፍስ መደንፋቱን ጀብድ የሚያደርግ ብዙ ሰባኪ አለ። ትምህርት ከጥሩዎች ብቻ ሳይሆን ከመጥፎዎች ሁኔታም ይወሰዳል። አንዳንዴ ጥያቄው የቀረበበትንም ድባብ ማየት ጥሩ ነው። ህዝብ ፊት የቀረበ ጥያቄ ለጠያቂው ቢያሳስብም ለታዳሚው ህዝብ ፈተና ሊሆን ይችላል። ከመመለስህ በፊት ምን ሊያሳድር እንደሚችል መዝነው። በአንድ ወቅት ኢማሙ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ ስለ አንድ ጉዳይ ተጠየቁ። ግን ትንሽ ዝም ብለው ቆዩ። "አትመልስምንዴ?" አሏቸው። "ዝምታዬ ነው ወይስ መልስ መስጠቴ ነው የሚሻለው የሚለውን እስከምለይ ነው" አሉ። [ኢዕላሙል ሙወቂዒን፡ 6/124] የህዝብን ስሜት እየተከተልክ እንድትፈስ፣ የሚያስደስታቸውን ብቻ እየመረጥክ እንድታወራ አይደለም የምነግርህ። ይሄማ አስተዋይነት ሳይሆን አስመሳይነት ነው። ሺርክና ቢድዐ ከተንሰራፋበት ህዝብ መሀል እየኖርክ ሁሌ እንዳላየህ በማለፍ በንፅፅር ዝቅ ባሉ ርእሶች ላይ የምትሞቅ እና አልፎም ይህንን አካሄድህን እንደ ጥበብ እየቆጠርክ ሌሎችን የምታጣጥልበት ከሆነ ይሄ አላህን መፍራትም ለወገን መቆርቆርም አይደለም። ባይሆን የምታውቀውን ሁሉ፣ የተጠየቅከውን ሁሉ በየቦታው አትዘርግፍ። የተጠየቀውን ሁሉ የሚመልስ ሰው ጤነኛ አይደለም። የማታውቀውን አላውቅም ለማለት አትፈር። ታላቁ ኢማም ሸዕቢይ ረሒመሁላህ የሆነ ጥያቄ ሲጠየቁ "አላውቀውም" አሉ። "የዒራቅ ህዝብ ሊቅ ሆነህ ሳለ 'አላውቅም' ስትል አታፍርም?!" አሏቸው። ምላሻቸው ግን እጅግ የሚገርም ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት:- لكن الملائكة لم تستحي حين قالت: {سبحانك لا علم لنا إلا ما علمتنا} "ነገር ግን መላእክት: 'ጥራት ይገባህ! አንተ ካሳወቅከን ውጭ እውቀት የለንም' ሲሉኮ አላፈሩም።" [ተዕዚሙል ፉትያ፣ ኢብኑል ጀውዚይ: 86] ስለዚህ አላውቅም የእውቀት ግማሽ ነውና አትፈርበት። የተጠራጠርክበትን ደግሞ እስከምታረጋግጥ ቆይ። ከምታውቀውም ውስጥ በሆነ ምክንያት ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያደላ ከሆነ ወይ ለጊዜው አቆየው፤ ወይ ሁነኛ ቦታ ምረጥለት። አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ግን የወቃሽ ወቀሳ አያቁምህ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor