የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ
Открыть в Telegram
📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
3 466
Подписчики
+3924 часа
+2267 дней
+39330 дней
Архив постов
3 466
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
ከ"ሰሂህ አል-ቡኻሪ" ማብራሪያና ትንታኔ የተወሰዱ መሰረታዊ፣አንገብጋቢ አንዲሁም ወቅታዊ ወሳኝ ምክሮች፦
ꪜ ዑመር ቢን ዐብዱል-ዐዚዝ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ ❝እውነትን ከዝንባሌህ (ከስሜትህ) ጋር ስለገጠመ ብቻ የሚከተል፣እንዲሁ ከስሜትህ ጋር ሲቃረን (ሲጣረስ) ደግሞ የሚቃወም ሰው አትሁን...አንተ በዚህ ሁኔታህ እውነትን በመከተልህ ምንዳ አታገኝም...❞
ꪜ ኢብኑ ተይሚያም (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና) አዎ እውነታው ዑመር ኢብኑ ዐብዱል ዐዚዝ (ረዲየአላሁ ዐንሁ) እንዳለው ነው፣ ምክንያቱም ያ ሰው የፈለገው እውነትን መከተል ሳይሆን በሁለቱም ቦታ የራሱን ፍላጎት (ስሜት/ዝንባሌ) መከተል ነበር፣ ለአላህ ብሎም አልነበረም።
ꪜ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች (Platforms) ላይ የምታሰራጨውን (ነሽር የምታደርገውን) ነገር አላህ ይጠይቅሃል—ይህንን ያሰራጨኸው ለራስህ ዝንባሌ ነው?!ወይስ ለነፍሲያ በቀል ነው?! ወይስ ለአላህ ብለህ ነው?! እያንዳንዱ ሰው ራሱን ሊመረምር (ለጠይቅ/ከራሱ ጋር መሀሰባ ሊያደርግ ይገባል።
ꪜ አንድ ሰው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች (Platforms) ላይ ምክር አዘል ፅሁፎችን (አዲዮችን) ካሰራጨ... እገሌ እኔን ፈልጎበት ነው ወይም እገሌ እኔን ነው የፈለገው" አትበል!፤ አዎን አንተን ነው የፈለገበት አንተ ሙስሊም አይደለህም እንዴ?!...ስለዚህ፣ ነገርየው እውነት ከሆነ—የተባለው ነገር አንተን ሚመለከትህ ከሆነ አላህን በመፍራት ወደ እሱ ተመለስ። ነገርየው አንተን የማይመለከትህ ከሆነ ደግሞ አላህን አመስግን!፤ ምክንያቱም ዲን ማለት መመካከር ነውና።
ꪜ የቀደሙት ሰለፎች (ሶሃቦች፣ ታቢዒዮች...) ይህን— "እገሌ እኔን ነው የፈለገው" የሚለውን ፍልስፍና በፍጹም አያውቁትም ነበር። እነርሱ እውነትን ከታላላቆችም፣ከታናናሾችም ይቀበላሉ!፤ በቁርኣን ውስጥ ስለ ሙሽሪኮች፣ ስለ ከሃዲዎች እና ስለ ኃጢአተኞች የተጠቀሱትን ታሪኮች እንኳ ይህ እኛን ነው የሚመለከተው አላሉም፤አላህ ቁርኣንን እንድናስተነትን እንዲሁ እነሱ በወደቁበት እንዳንወድቅ አዞናል።
ꪜ ከቀደምት ሰለፎች መካከል አንዱም እንኳ አንድን ቁርኣን ወይም ሐዲስ ሲሰማ —ይህ እኔን ነው የሚመለከተው! ብሎ የተነሳ አናገኝም።
ꪜ በእኛ እና በሰለፎች መካከል ትልቅ ልዩነት አለ!፤ ሰለፎች ወደ ራሳቸው ይመለሱ ነበር (ራሳቸውን ይወቅሱና ይገስጹ ነበር)። እኛ ግን በተቃራኒው ይህንን በሽታ በሌሎች ላይ እንወረውራለን። ስለዚህ ከዚህ መጥፎ በሽታ ራቁ!፤ ከሚቀርቡላችሁ ጠቃሚ ምክሮች ተጠቀሙ፣ ነገር ግን ማንኛውንም ነገር ከመቀበላችሁ በፊት ራሳችሁን መርምሩ፣ተጠያቂ አድርጉ፣ እና ከእንደዚህ አይነት ስሜቶች (ዝንባሌዎች) እራሳችሁን አርቁ። አላህን ዓፊያን እንማፀነዋለን።
✍ትርጉም:- ሰሚር ጀማል
https://t.me/HussinAssilty/3361
3 466
من شرح صحيح البخاري.
قال عمر بن عبد العزيز :" لا تكن ممن يتبع الحق إذا وافق هواه ويخالفه إذا خالف هواه فإذا أنت لا تثاب على ما اتبعته من الحق وتعاقب على ما خالفته" قال ابن تيمية وهو كما قال رضي الله عنه لأنه في الموضعيين إنما قصد اتباع هواه لم يعمل لله.
_الفوائد التي تنشرها سيسألك الله عنها هل نشرتها انتصارا لهواك وانتقاما لنفسك كل واحد يجب أن يراجع نفسه .
لا تقل فلان يقصدني أو يريدني نعم يقصدك ألست مسلما ؟ أنت مخاطب بالكتاب والسنة فإذا كان فيك تتوب إلى الله وإذا لم يكن فيك تحمد الله لأن الدين النصيحة.السلف لا يعرفون هذه الفلسفة يقصدني لا يقصدني لأنهم يقبلون الحق من الصغير والكبير فكتاب الله فيه أخبار المشركين والكفار والعصاة وأمرنا الله بتدبر كتابه حتى لا نقع فيما وقعوا فيه.
-لم نجد أحدا من السلف إذا سمع آية أو حديثا أو أثرا قال يقصدني ويعنيني !!! نعم يقصدك ألست ضعيفا تتعرض لاتباع هواك .
-من الفوارق بيننا وبين السلف السلف يرجعون إلى أنفسهم يعاتبونها ويذمونها ويحتقرونها أما نحن فنرمي على غيرنا . تجنبوا هذه الأمراض واستفيدوا من الفوائد قبل أي أحد ففتشوا أنفسكم وحاسبوها وازجروها . نسأل الله العافية
3 466
📝የኡሱሉ አስ_ሰላሰህ ማብራሪያ
╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖 ደርስ ክፍል 001 📖
╰─••°─═•°•═─•••─
🏢በወራቤ ከተማ አስተዳደር ሻድገር ሰፈር ኢማሙ ሻፊዒይ መድረሳ የሚሰጥ ትምህርት
🎙በኡስታዝ አቡ ኑህ
📆ሐሙስ ሙሐረም 03 / 01 / 1448
የቴሌግራም ቻነል ➘➷➴➘➷
https://t.me/ibnbaz1212
https://t.me/MisbahMohammed_6682
3 466
Repost from የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ
[نصيحتي للنساء]
تأليف:
أم عبد الله بنت الشيخ مقبل بن هادي الوادعي
تقديم : العلامة الشيخ مقبل بن هادي الوادعي
3 466
➽የጠቃሚ እውቀት ባለቤቶች ምልክት
❶ ለራሳቸው ከሌሎች የተሻለ ለየት ያለ ሁኔታና ደረጃ አለን ብለው አያዩም
❷ የሰዎችን ሙገሳና ምስክርነትን በልባቸው ይጠላሉ
❸በየትኛውም አካል አይኮሩም
📚 በያኑ ፈድሊ ዒልሙል አስ_ሰለፊ ዐላ ዒልሚል አልኸለፊ 80
📝ተጨማሪ ትምህርቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም Channeሉን ይቀላቀሉ !
https://t.me/MisbahMohammed_6682
https://t.me/ibnbaz1212
3 466
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
እንዲሁ በጣም የሚያስገርመው ፡ አንዳንድ ሴቶች እና ወንዶች ከአጅነብይ (ከባእድ) ጋር በማውራት የሚስተዋለው ቸልተኛነት ነው፡፡ አስገዳጅ ነገር ሳይገጥም አጅነብይ የሆነችውን ሴት ያወራታል ፣ ያሳስቃታል እርሷም ታሳስቀዋለች በንግግሯ ይደሰታል፡፡ አንዳንድ ሴቶችም አስገዳጅ ነገር ሳይገጥም አጅነብይ ከሆነ ወንድ ጋር ያወራሉ፡፡ በለሰለሰ ቃላት ፣ ደስ የሚል ቃል ወደርሱ ትወረውራለች፡፡ በልቡ በሽታ ያለበት ሰው ይከጅላል፡፡ በተለይም በማህበራዊ ድረ ገጽ፡፡
በትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶለቱ ወሰላም - እንዲህ ብለዋል :-
إن المرأة عورة ، فإذا خرجت استشرفها الشيطان
“ሴት አውረት (አካሏ ሁሉ መታየት የማይገባት) ነች ፣ (በአደባባይ) ከወጣች ሸይጧን ይቀርባታል”
ሙስሊም በሶሂህ ሐዲስ የሚከተለውን ዘግቧል ፡
إن المرأة تقبل في صورة شيطان ، وتدبر في صورة شيطان
“ሴት ስትመጣ በሸይጧን ምስል ትመጣለች፡፡ ስትሄድም በሸይጧን ምስል ትሄዳለች፡፡”
ሁሉም ሙስሊም አላህን ሊፈራ ግዴታ አለበት፡፡ ባለትዳሮች ሚስጢራቸውን በአደባባይ ማሰራጨት ሳይሆን ችግራቸውን ከቤተሰብ ጋር ሆነው በትእግስት እና በጥበብ ተወያይተው መፍታት አለባቸው፡፡
ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! በአንተ እና በሚስትህ መካከል አለመግባባት ከተከሰተ ከማንም ጋር ግንኙነት አታድርግ ቤተሰቦችህ እንዲገኙ በማድረግ በጥበብ ፣ በትግስት ፣ በዱዓ መፍታት ትችላለህ፡፡ ለአንተ ቅርብ እና አዛኞች የአንተ እና የሚስትህ ቤተሰቦች በመሆናቸው በመካከላችሁ ተገኝተ ጉዳያችሁን እንዲፈቱ አድርግ፡፡ ይህ ካልተሳካ ወደሸሪዓ ዳኞች ጉዳዩን አቅርብ፡፡ ይህ ነው አላህ የሚወድልህ ፣ የሚስትህን ሚስጢር አትበትን ፣ በቁርዓን እና በሐዲስ ጉዳይህን ፍታ - በዱንያና በአኼራ ስኬታማ ትሆናለህና፡፡
ሙስሊም እህቴ ሆይ! ከባልሽ ጋር አለመግባባት ከተከሰተ አላህን ፍሪ ፣ ታገሽ ፣ ባልሽን በመልካም ታዘዥ፡፡ አላህ ከፍ ያደርግሻል፡፡ ከአንች ዘንድ ያለውን ይወድልሻል፡፡ የሂዎትሽ ሁኔታ ካልተስተካከለ ቤተሰቦችሽን አማክሪ እንጅ ከዚያም ከዚህም ጋር አትገናኝ - ከአላህ ቁጣ ላይ ትወድቂያለሽና፡፡
በባልና በሚስት ጉዳይ ፈትዋ የሚሰጡ ሰዎች አላህን ይፍሩ፡፡ በሁለቱ መካከል በተፈጠረው ጉዳይ የተሰጣቸውን የሸሪዓ ድንበር ሊያውቁ ይገባል፡፡
ፈትዋ የሚሰጡ ሰዎች በባልና ሚስት እርቅ ጉዳይ ከቤተሰቦች የበለጡ አይደሉም፡፡ አላህ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡ ባለትዳሮችን ባልና ሚስትን በማስማማት አላህ በቁርዓኑ ያወሳው ቤተሰብን ነው፡፡ ባለትዳሮችን መምከር ፣ ሸሪዓዊ ህጉን ግልጽ ማድረግ የሚከለክል ነገር የለውም፡፡ በፍች ጉዳይ ግን የአንዱን ወገን ብቻ መስማትና ጣልቃ መግባት ተገቢ አይደለም፡፡
የሰዎችን ቤት ሚስጢራቸውንም መከታትልና መፈተሽ አይፈቀድም፡፡ ይህ የቆሻሻ ልቦች በሽታ ነው፡፡ ሙስሊሞች ከእንዲህ አይነቱ መጽዳት ግዴታ አለባቸው፡፡
ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - እንዲህ ብለዋል:-
يا معشر من آمن بلسانه ولم يدخل الإيمان قلبه ، لا تغتابون المسلمين ، ولا تتبعوا عوراتهم ، فإنه من تتبع عورة أخيه المسلم ، تتبع الله عورته ، ومن تتبع الله عورته ، يفضحه ولو في جوف بيته
“በምላሳችሁ ያመናችሁ ፣ እምነት በልባችሁ ያልገባ ሰዎች ሆይ! ሙስሊሞችን አትሙ ፣ ነውራቸውንም አትከታተሉ ፣ የሙስሊም ወንድሙን ነውር የሚከታተል የእርሱን ነውር አላህ ይከታተለዋል፡፡ የእርሱን ነውር አላህ የተከታተለው በቤቱ ውስጥ እንኳ ቢሆን ያጋልጠዋል፡፡”
ሸይኽ ብን ኡሰይሚን - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ ፡
“የቤቶቻቸውን ጉዳይ ፣ ስለትዳራቸው ሒዎት ፣ ከባሎቻቸው ጋር ያለውን ጉዳይ ለቅርብ ዘመዶቻቸው ፣ ለጓደኞቻቸው ማውራትና ማሰራጨት በአንዳንድ ሴቶች ላይ ይበዛል፡፡ ከእነዚህ ወሬዎች ከፊሉ የቤት ሚስጢር ናቸው፡፡ ባል እንዲወራ አይፈልግም፡፡ ባል ይህን የቤት ሚስጢር አንድም ሰው እንዲያውቅ አይፈልግም፡፡ ሚስጢርን ከቤት ውጭ በማሰራጨት ወይም ለአንዳንድ የቤት ሰዎች በማውራት ላይ የተሰማሩ ሴቶች ፍርድ ምንድን ነው?
መልስ ፡ የቤትን ወሬ ፣ የትዳር ሂዎታቸውን ለቅርብ ዘመድ ፣ ለጓደኛ የሚያወሩ አንዳንድ ሴቶች ይህ ተግባራቸው ሐራም ነው፡፡ ማንኛዋም ሴት የቤቷን ሚስጢር ወይም ከባሏ ጋር ያለውን ሁኔታ ለአንድም አካል ማውራት ወይም ማሰራጨት አይገባትም፡፡ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል ፡ -
فَالصَّالِحَاتُ قَانِتَاتٌ حَافِظَاتٌ لِّلْغَيْبِ بِمَا حَفِظَ اللَّهُ ۚ
“መልካሞቹ ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች ፣ አላህ ባስጠበቀው (እንዲጠበቅ ባዘዘው) ነገር ሩቅን (ባሎቻቸው በሌሉበት አፍረተ ገላቸውን ፣ ንብረታቸውን ...) ጠባቂዎች ናቸው፡፡”
(ኒሳእ : 35)
ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ተናግረዋል :-
شر الناس منزلة عند الله يوم القيامة الرجل يفضي إلى المرآة وتفضي إليه ثم ينشر سرها"
“የትንሳኤ ቀን ከአላህ ዘንድ መጥፎ ሰው ብሎ ማለት ባል ለሚስቱ ሚስጢር ይነግራታል ፣ ሚስት ለባሏ ሚስጢር ትነግረዋለች ከዚያም ሚስጢሯን የሚያሰራጭ ነው፡፡”
انتهى من فتاوى إسلامية (211212\3)
በዶክተር ሸይኽ ሁሰይን ብን ሙሐመድ
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
3 466
🇸🇦ሰለፊዮች ሆይ የምርጥ የሰለፊይ መሻይኮች ኡስታዞች እንዲሁም ወንድሞች ቻናል እያለላቹ በየሙብተዲእ ቻናል ምን ትሰራላቹህ?
አሁን ጉዳዬ ላሳጥርላቹህ እና ከታች ጆይን የምትለዋን ምልክት ስትፈልጉ በአውራ ጣታቹ ስትፈልጉ በቀለበት ጣታቹ ብቻ በፈለጋቹት ጣታቹ ጆይን(JOIN) የምትለዋን ምልክት በመንካት ወደ ኢትዮጵያ የሰለፊዮች ቻናል ተቀላቀሉ🇸🇦
3 466
Aselamaleykum werahmetulahi
Ibnu baz medresa kenege eske ehud ke subhi behuala ተንቢሃት new yemikeraw
3 466
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
🔷የቢደዐህ ሰዎችን ቡዱንተኞችን በደምብ የሚገልጽ ምርጥ ንግግር
(أهل الأهواء يُعظِّمون من وافقهم ، وإن كان فاسقًا فاجرًا !!
ويذمّون من خالفهم ، وإن كان من أولياء الله المتقين) .
📚الفتاوى (٣/٣٤)
➥ሸይኹል ኢብኑ ተይሚየህ እንዲህ ይላል ፦
➨የቢደዐህ ሰዎች ከነሱ የተስማማውን ሁሉ ያከብራሉ ያልቁታል አመፀኛ እነ በዳይ ቢሆንም እንኳን እነሱ ጋ ክቡር ነው
➸እነሱን የማይስማማ ከሆነ ምንም እንኳን ትክክለኛና አላህን ፈሪ ከደጋጎች ቢሆንም እንኳን ይተቹታል ያነውሩታል ።
📚መጅሙዐል ፈታዋ 3/34
📝ተጨማሪ ትምህርቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም Channeሉን ይቀላቀሉ !
https://t.me/MisbahMohammed_6682
3 466
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷ምስጋና
በመዋደዳችሁ ፣ በመተዛዘናችሁ ፣ በርህራሄያችሁ የምንቀናባችሁ ባህር ዳር የምትገኙ የአህለሱና ተርጓሚዎች አሏህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ።
በሁሉም ቦታ የሚገኙ ሰለፍዮች ምን ነው (የእናንተን አካሄድ) በተከተሉ!!
ኢስላምና ሙስሊሞችን በእናንተ ይጥቀም! አሏህን በመታዘዝ ላይ እድሜያችሁን ያርዝመው! ሰለፍይ ተርጓሚዎችንም እንዲሁ! አምሳያችሁን ያብዛው! እስከሞት ድረስ በተውሂድ በሱና ያጽናችሁ!!
በዶክተር ሸይኽ ሁሰይን ብን ሙሐመድ
اللهم آمين
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
3 466
Repost from 𝐒𝐞𝐦𝐢𝐫 𝐉𝐞𝐦𝐚𝐥 (𝐀𝐛𝐮 𝐇𝐚𝐟𝐬𝐚𝐡)
እናንተ ሸይኾች ሆይ! ፣እናንተ ዳዒዮች ሆይ!፣እንዲሁም እናንተ ኡስታዞች! ኧረ ይህንን ላባዊ ምክር ሰምታችሁ ተግባራዊ እድርጉ!
—⭑⋆⋆⋆⭑—
🎙🎙 ዶክተር ሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ (ሀፊዘሁላሁ ተዓላ) በዚህ አጭር የድምፅ ፋይል ላይ የሚከተሉት አበይት ነጥቦችን ዳስሰዋል፦
ꪜ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦቻቸውን (ሶሃቦችን) ያከብሯቸው ነበር፣እንዲሁም ከእነርሱ ጋር ይሳሳቁ (ይቀልዱ) ነበር።
ꪜ ሶሃቦችም (ረዲየላሁ ዐንሁም) በተመሳሳይ መልኩ እርስ በርሳቸው ይዋደዱ ነበር። አላህም በቃሉ ይህንን መስክሮላቸዋል፡- «በመካከላቸው አዛኞች ናቸው» (ሱረቱል ፈትሕ፡ 29)።
ꪜ በተመሳሳይ መልኩ ሰባቱ ፉቀሃኦች: ሙጃሂድ፣ አል-አዕመሽ፣ መንሱር፣ ሁለቱ ሱፍያኖች (ሱፍያን አስ-ሰውሪይ እና ሱፍያን ኢብኑ ዑየይነህ)፣ኢብኑ መህዲ፣ የሕያ አል-ቀጧን፣አሕመድ፣አል-ቡኻሪ እና ሌሎችም...በሕይወት ታሪካቸው ውስጥ በእነርሱና በተማሪዎቻቸው መካከል ያለውን የፍቅር፣ የመዋደድ፣ የእውነተኛነት እና እርስ በርስ የመመካከር ሁኔታን ታገኛለህ።
ꪜ ከአቡ ደርዳእ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተወራው፡- "በሱጁዳቸው ወቅት ለሶሃባ ጓደኞቻቸው ስም እየጠሩ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።"
ꪜ እንዲሁም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሙሐዲሶች (ኢማሞች) በሱጁዳቸው ውስጥ ለ"አህሉስ-ሱናዎች"ዱዓእ ያደርጉ ነበር፤ እንደ ኢብኑ መህዲ፣ አሕመድ እና ሌሎችም።
ꪜ ሸይኽ ሰዕድ ቢን ዐብዱረሕማን አል-ሑሰይን እንዲህ ብለውኛል፡- በሱጁድ ውስጥ ለኢማሙ አሕመድ፣ ለኢብኑ ተይሚየህ፣ ለኢብኑ ባዝ፣ ለአልባኒ እና ሱናን ለሰዱ ለሌሎችም ዱዓእ ያደርጉ ነበር
ꪜ ተማሪዎቻችሁን በመካከላችሁ ባለው ፍቅርና መዋደድ ላይ አሳድጓቸው (ኮትኩቷቸው)። በአህሉስ-ሱነህ ላይ መልካምን አደራ ተባባሉ!፤ እነርሱ ከሰዎች ሁሉ በጣም ጥቂቶች ናቸውና።
ꪜ ለአንድ ሸይኽ ተማሪውን ማማት በፍጹም አይገባውም፤ ከእርሱ (ከተማሪው) አንድ ነገር ቢሰማ እንኳ ማረጋገጥ አለበት!፤ ከዚያም ትክክለኛውን አቅጣጫ ሊያሳየውና ሊመክረው ይገባል።
ꪜ ያንተ ሰለፊ ወንድምህ እና ተማሪህ ከሌላው ይልቅ ለመመከር ይበልጥ የተገባ ነው!፤ "ዲን ማለት እኮ ምክር ነው።"
ꪜ ከተንኮለኛና አደገኛ በሽታዎች ተጠንቀቁ፤ እሱም፡ በተማሪህ ፊት በአንድ ፊት (በወዳጅነት) መጥተህ፣ ከዚያ ዞር ስትል ደግሞ የምታማው መሆንህ ነው። ይህ በአንተ ውስጥ በሽታ መኖሩን ያሳያል፤ ከዚህ በሽታ ራስህን አፅዳ፣ አላህንም ፍራ።
ꪜ ሸይኽ ረቢዕ ብን ሓዲ አል-ዑመይር አል-መድኸሊ (ረሂመሁላህ)
“...እኔ መካ ሳለሁ የሆነ ቤት ተከራይቼ ነበር፤የተከራየሁበት ቤት ውስጥ ቀድሞ የነበረው ሰውዬ ቴሌቪዥን ነበረው፤ ሰውየው በጊዚያዊነት ቴሌቪዥኑን በአደራ መልክ ትቶት ሄዷል...ይህ በንዲህ እንደለ እኔ በተከራየሁበት ቤት ውስጥ ሌላ ጓደኛዬ ለሸይኽ ረቢዕ እንዲህ በማለት ይነግራቸዋል፦ "ሑሰይን ቤት ቴሌቪዥን አለ..."
ሸይኹም በሌላ ቀን እራት ከተበላ በኃላ፣ ወደ መኝታ ክፍላቸው ይዘውኝ ሄዱ መሀላችን ማንም አንነበረም...እንዲህም ብለው አሉኝ፡ "አንተ ሑሰይን ሆይ! አንተ ቤት ቴሌቪዥን አለ ሲባል ሰምቼ ነበር እውነት ነውን?!..."
ꪜ አሽ-ሸይኽ ሑሰይን ክስተቱን እንዲህ በማለት እውነታውን ነገሯቸው፡ "ሸይኽ ሆይ! እኔ በተከራየሁበት ቤት ውስጥ መጀመሪያ ተከራይቶ የነበረው የሰውዬው ቴሌቪዥን ነው እንጂ የኔ አይደለም...ሰውየው ይቀመጥ ብሎ ነው የሄደው...." በማለት ሸይኽ ሑሰይን ለቀረባለቸው ጥያቄ በአጭሩ ለሸይኽ ረቢዕ አስረዷቸው።
ꪜ በመጨረሻም አሽ-ሸይኽ ረቢዕ ለሸይኽ ሁሰይን እንዲህ አሏቸው፡ "ይቅርታ አድርግልኝ!" አቤት ፍትህ!፤አቤት ጥበብ!፤አቤት አካሄድ!...አቤት አጠያያቅ!...
ꪜ በሌላም ጊዜ (ከዚህ አዲዮ ውጪ) አሽ-ሸይኽ ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
“...አንድ ሊቢያዊ "አቡል ፈድል" የተሰኘ ሰውዬ ነበር፤ ሌለኛው ደግሞ መጥቶ ለሸይኽ ረቢዕ እንዲህ ይላቸዋል: "አቡል ፈድል እንዲህ አለ፣ይህን ፈፅመ፣እንዲህ ይላል.." ሸይኹም እንዲህ አሉት: ማስረጃ አምጣ...አቡል ፈድል እኔ ዘንድ ከበላጮቹ ነው..." ወረኛውም ተንቀጠቀጠ...”
ꪜ የሰለፊዮችን አንድነት ከሚከፋፍሉ መንገዶች መካካል ያለማስረጃ ወሬን መቀበል፣ሳያጣሩ ብይን መስጠት፣ወረኛውን አደብ አለማስያዝ...ወረኛውን "ሀ" ብሎ መስማት ዋጋ ያስከፍላል....
https://t.me/HussinAssilty/3343
3 466
Repost from N/a
🌿 ታላቅ የደዕዋ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 🌿
📢 ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም እና ለፉርቃን መስጂድ የገቢ ማሰባሰቢያ
ውድ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች፣ በዚህ ታላቅ የደዕዋ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በመገኘት የፉርቃን መስጂድን ድጋፍ እንድታደርጉ በክብር ተጋብዛችኋል።
🎙 የእለቱ ብርቅዬ ተጋባዥ መሻኢኮች እና ኡስታዞች
1️⃣ ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት — ከሀራ
2️⃣ ኡስታዝ አቡ ሙኣዝ — ከወራቤ
3️⃣ ኡስታዝ አቡ ፉረይሃን — ከጦራ
4️⃣ ኡስታዝ አቡ ቂርጣስ — ከዳሎቻ
5️⃣ ኡስታዝ አቡ ያሲር ሰለፊ — ከአዲስ አበባ
📅 ቀን: እሮብ 10/09/2018 ዓ.ም.
🤲 እንዳያመልጣችሁ! በመገኘት የደዕዋው እና የመስጂዱ ድጋፍ ተካፋይ ይሁኑ።
ፕሮግራሙ የሚካሄደው ኢሞ መድረሰቱ ዳሩል በያን ሲሆን ሊንክ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇. Click the link to join us! https://s.imoim.net/xps1iH?from=copy_linkየቴሌግራም ጉሩፕ ሊንክ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Furqanmesjidgruop2
ሼር አድ በማድረግ ሌሎችን ወደ መልካም ስራ ልንጠራቸው ይገባል ጥሪው ሁሉንም ሰለፊይ ወንድም እህቶችን በተለይም የጉሩፕ የቻናል ባለቤት የሆናቹህ ሼር አድርጉልን ስንል ከትልቅ አክብሮት ጋ ነው
3 466
الرسول صلى الله عليه وسلم يجل أصحابه ويحترمهم ويضاحكهم .
_الصحابة كذلك يحب بعضهم بعضا وشهد الله لهم بذلك بقوله (رحماء بينهم)
_وكذلك الفقهاء السبعة ومجاهد والأعمش ومنصور والسفيانان وابن مهدي ويحيى القطان وأحمد والبخاري وغيرهم تجد في تراجمهم روح المحبة والمودة والصدق والمناصحة بينهم وبين طلابهم .
-وقد ذكر عن أبي الدرداء رضي الله عنه أنه كان يدعو في سجوده لأصحابه من الصحابة.
_وكذلك عدد من أئمة الحديث كانوا يدعون في سجودهم لأهل السنة كابن مهدي وأحمد وغيرهما.
-وقد قال لي الشيخ سعد بن عبد الرحمن الحصين أنه كان يدعو في سجوده لأحمد وابن تيمية وابن باز والألباني وغيرهم ممن نصر الكتاب والسنة على منهاج النبوة.
-ربوا طلابكم على المحبة والمودة فيما بينكمواستوصوا بأهل السنة خيرا وهم أقل الناس
_لا يليق بالشيخ أن يغتاب تلميذه فعليه إن سمع عنه شيآ يتثبت فيقوم بتوجيهه ومناصحته.
_أخوك السلفي وتلميذك أحق بالنصيحة من غيره والدين النصيحة.
-تجنبوا من الأمراض الخبيثة والفتاكة تأتي إلى تلميذك بوجه ثم تروح وتغتابه وهذا يدل على مرض فيك تخلص منه واتق الله تعالى .
3 466
Repost from ጅብሪል ሱልጣን & ሙሀመድ ሰልማን
አንድ ግዜያዊ ምክር
------------
ለሁላችንም አሁን ያለንበት ግዜ በተለይ ለተማሪዎች ለልጆች እረፍት የሚያደርጉበት ግዜ ስለሆነ ግዜያችሁን በከንቱ አታበላሹት ከቻላችሁ
- የተለያዩ መድረሳዎችን በመግባት በተለያዩ ፈኖች ጀግናችሁ እረፍታችሁን መጭረስ
- ባላችሁበት ጎን ለጎን አጫጭር አካዳሚክ ኮርሶችን መውሰድ በተለይ እንደ ግዜያችን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂ ነክ ኮርሶችን መውሰድ
ምናልባት እንደኔ ግን እነዚህን አካዳሚክ የሆኑ ኮርሶችን በተለይ ቴክኖሎጂ ነክ የሆኑ አጫጭር ኮርሶችንና ትምህርቶችን ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ከተማሪ ውጭ ያላችሁም ኡስታዞችም ጭምር ብትወስዱት ባይ ነኝ ምክንያቱም አንደኛ ዲናችንንም በቻልነው አቅም ባገኘንበት አጋጣሚ ከግዜው ጋር በሚሄዱ ቴክኖሎጂዎች ልናስፋፋ ይረዳናል ያ ባይቻል እንኳን የምንኖረው ዱኒያ ላይ ነውና ከዱኒያም እጣ ፋንታህን አትርሳ ነውና ለዱኒያዊ ጥቅሞቻችንም በአላህ ፈቃድ ይጠቅመናል ያም ብቻ አይደለም የኢስላም ጠላቶች በተለያዩ በቴክኖሎጂዎች እስልምናን ለማጥቃት ሲሞክሩ እኛም ቴክኖሎጂዎችን ካወቅናቸው በዛው ልንመክትበት ይረዳናል ።
እንደው አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ የሆነ ሰሞን ታስታውሱ እንደሆነ የተለያዩ የቁርዓን ተፍሲር ፣ የኪታብ ቂርዓት ሪከርዶች ደዕዋዎችን ፈትዋዎችን ወደ አፕ ለመቀየር እስከ ስንት ብር ይጠየቅ እንደነበር ታውቃላችሁ እስከ ሀምሳ ሺህ ብር ይጠየቅ ነበር ኋላ ላይ ግን ሰለፊዮችም ይህን አፕ አሰራሩን ማወቅ ሲጀምሩ እንዲሁም ከሰለፊዮች ውጭ ያሉትም ይህን አፕ የሚሰሩት መብዛት ሲጀምሩ ምን ያህል እንደሆነ ከማናችንም አይደበቅም ።
እንደው እሱም ብቻ አይደለም እኔን የገጠመኝን ልንገራችሁ በቅርብ ቀን እራሱ ከአንድ ወንድም ጋር ሆነን አንድ የተለየ ለየት ያለ አፕ አለና ሜጋባይቱ ትንሽ የሆነ የሸይኻችንን በየቀኑ የሚቀሩ ደርሶችን ደዕዋዎችን ኹጥባዎችን እራሱ አፕዴት አድርጎ የሚጨምር አፕ ልናሰራ ስንጠይቅ አምስት መቶ ሺህ ብር ነው የተባልነው ያው እኛም አቅሙ ዬለንም አላህ ካለ አቅሙ ያለው ሲመጣ አልያ አፑን አሰራሩን የሚያውቅ ሰለፊይ ምናልባት ከመሃላችን ሲመጣ ያሰራው ይሆናል ብለን ተውነው ።
ይህን የሚነግራችሁ የቴክኖጂውን ጥቅም እንድታውቁ ነው ስለዚህ በአጭሩ ኡስታዞችም ደረሶችም ተማሪዎችም ሴቶችም ወንዶችም እንደዚህ ያሉ ክፍተቶች ሲገኙልን እነዚህን ከግዜው ጋር የሚሄዱ ኮርሶችንና ትምህርቶችን ጠንክረን ልንማር እንጂ ልንሸሻቸው አይገባም ። በመሰረቱ ይህ እያወራንበት ያለነው ቴሌግራም አፕም ቴክኖሎጂ ነው ስለዚህ ውድ ሰለፊዮች ከቴክኖሎጂ አትሽሹ ተመሩት ተመራመሩበት እወቁት ሁሉም ነገር እንደኛ አጠቃቀም ነውና ።
አላህ ዕውቀትን ይጨምርልን !! አሚን
✍አቡ ሙስዐብ ኢብን ሱልጣን
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Abumuseab
3 466
ሸይኽ ረቢይዕ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ:
"ሸይኽህ ሃቅን ከተፃረረ ሸይኽህን ተውና ሃቅን አጥብቀህ ያዝ እቺም ናት እውነተኛ ሰለፍያ""
https://t.me/ibnbaz1212
3 466
📙 عنوان الرسالة: مجمل عقيدة السلف الصالح لشيخ صالح بن فوزان الفوزان
(የሸይኽ ሷሊሃልፈውዛን ሪሳላ የሆነችው ሙጅመሉ ዓቂደቲ አሰለፍ አሷሊህ)
ክፍል ስድስት (06)
🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ
📚የኪታቡን pdf ለማግኘት👇👇
https://t.me/ibnbaz1212/66
📆 ዕለተ ጁሙዓ ዙልሂጃ 26, 1447
🕌 በመድረሰቱል ኢኽላስ ለሁልባረግ የሴቶች ጀመዓ የተሰጠ ኮርስ
የቴሌግራም ቻነል
https://t.me/ibnbaz1212
