ru
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

Открыть в Telegram

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
1 376
Подписчики
+324 часа
+3607 дней
+65030 дней
Архив постов
▶️ተጀመረ  - 😂😘
አዲስ የኪታብ ደርስ
      📚ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን 📔የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 📣በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ  - - https://t.me/sefinetunuh?livestream=78ecafa74f5f278b8c

ፈጥኖ ማን ቀድሞ ይመልስ  🚀🚀 ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ  እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ። ከጀነት በሮች ውስጥ ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት ልዩ በር ረያን ይባላል ።

💎ምን አይነት ሴት ብያገቡ ይመረጣል? እንደ ኢስላም ለትዳር ሴት ሲመረጥ ዋናው መስፈርት ዲኗና ባህሪዋ መሆን አለበት። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «تُنْكَحُ الْمَرْأَةُ لِأَرْبَعٍ
💎ምን አይነት ሴት ብያገቡ ይመረጣል? እንደ ኢስላም ለትዳር ሴት ሲመረጥ ዋናው መስፈርት ዲኗና ባህሪዋ መሆን አለበት። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«تُنْكَحُ الْمَرْأَةُ لِأَرْبَعٍ: لِمَالِهَا، وَلِحَسَبِهَا، وَلِجَمَالِهَا، وَلِدِينِهَا، فَاظْفَرْ بِذَاتِ الدِّينِ تَرِبَتْ يَدَاكَ» “ሴት በንብረቷ፣ በዘርዋ፣ በውበቷ እና በዲኗ ምክንያት ትጋባለች፤ የዲን ባለቤት የሆነችዋን ምረጥ።” — ቡኻሪና ሙስሊም
ስለዚህ ለትዳር ሴት ስትመርጥ እነዚህን ተመልከት፦ 🔹ዲንና ተቅዋ — አላህን የምትፈራ፣ ሶላትን የምትጠብቅ፣ ከሐራም የምትርቅ። 🔹መልካም ባህሪ — ትሁት፣ ታጋሽ፣ አክባሪ እና በችግር ጊዜ የምትታገስ። 🔹የቤተሰብ አስተዳደር ችሎታ — ትዳርን እንደ ኃላፊነት የምትመለከት። 🔹ከባል ጋር በመልካም መኖር የምትፈልግ፣ ችግርን በውይይት የምትፈታ። 🔹የምትስማማህ — በዲን፣ በእሴቶች፣ በቤተሰብ እቅድና በወደፊት ግቦች ላይ። 🔹ውበትና መሳብ — ይህም እንደ ሚፈቀድ ነገር ይታያል፤ ነገር ግን ከዲንና ከባህሪ በላይ እንዳይሆን። 🔹ቤተሰቧንና አስተዳደጓን መመልከት — ይህ ስለ ባህሪዋ ጥሩ ግንዛቤ ሊሰጥ ይችላል። በተጨማሪም አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦
﴿إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ﴾ “ከእናንተ አላህ ዘንድ የተከበረው በተቅዋ የበለጠው ነው።” (ሱረቱል ሁጁራት 49፥13)
🗣በአጭሩ፦ ቆንጆ መሆኗን ብቻ አትመልከት፤ ሀብታም መሆኗን ብቻም አትመልከት። ዲን፣ ባህሪ፣ የአእምሮ ብስለት እና የትዳር ኃላፊነትን መሸከም ችሎታዋን ቅድሚያ ስጥ። ©https://t.me/Abuimran_alkemisse ©https://t.me/Abuimran_alkemisse

ልጆቻችን የት ላይ ናቸው? ​ዛሬ ባለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን፣ የልጆቻችን ዓለም በእጃቸው ባለው ስክሪን መጠን ያህል ጠቦ ወይም ሰፍቶ ይገኛል። ወላጆች ልጆቻቸው በምቾት ቤት ውስጥ ስለተቀመጡ ብቻ ደህና ቦታ ላይ እንደሆኑ የሚያስቡበት ዘመን አብቅቷል፤ ምክንያቱም በስክሪኑ በኩል ያለው ዓለም ወደ ልጆቻችን አእምሮና ልብ የሚያስገባው ነገር ወላጅ ከሚገምተው በላይ የሰፋ ነው:: ​ስክሪኑ የሚያስተምረው ትምህርት፡ ልጆቻችን በስልክና በኮምፒውተር የሚያዩት ነገር በቀጥታ የአስተሳሰብ፣ የባህሪና የሥነ-ምግባር መቅረጫቸው እየሆነ ነው። አልፎ አልፎ የሚታዩት አላስፈላጊና አጥፊ ይዘቶች የልጆችን ንጹህ አእምሮ የሚያበላሹና ከእሴቶቻቸው የሚያወጡ ናቸው። ​የወላጅ ተርቢያ ፡ እውነተኛ ተርቢያ ማለት ምግብ፣ አልባሳትና ምቾትን ማቅረብ ብቻ አይደለም። እውነተኛ ተርቢያ ልጆች በሌሉበትና ማንም በማያያቸው ቦታ እንኳን መልካሙን ከክፉው መለየት የሚችሉበትን መንፈሳዊና ስነ-ምግባራዊ ኮምፓስ (መሪ) በልባቸው ውስጥ መትከል ነው። ​የዲናዊና የመልካም እሴት አስተዳደግ፡ ልጆችን ገና በለጋ እድሜአቸው ከአላህ መንገድ፣ ከዲናዊ እውቀትና ከታላላቅ ዑለሞች ምክር ጋር ማስተዋወቅ የአእምሮአቸውን ሰላም፣ የስነ-ልቦናቸውን ጥንካሬና የህይወታቸውን ስኬት ያረጋግጣል። አላስፈላጊ ነገሮችን አይተው አእምሮአቸው ከሚበላሽ፣ መንፈሳዊና አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ አስተማሪ ነገሮችን እየሰሙ ማደጋቸው ለነገው ማንነታቸው ታላቅ መሰረት ይጥላል:: ​የዛሬው ጥንቃቄአችንና የምንመግባቸው መንፈሳዊ ምግብ፣ የነገውን ትውልድ ማንነትና የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን ትልቅ አደራ ነው። https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

ጧት ማለት ፀሐይ መውጣት ብቻ አይደለም… እንደገና ለመጀመር አላህዬ የሰጠን ሌላ እድል ነው። ትናንት የተሰበረውን ዛሬ ማስተካከል እንችላለን። የዘገየውን በዱዓ መጠበቅ እንችላለን። የደከመውን ልብ በ
ጧት ማለት ፀሐይ መውጣት ብቻ አይደለም… እንደገና ለመጀመር አላህዬ የሰጠን ሌላ እድል ነው። ትናንት የተሰበረውን ዛሬ ማስተካከል እንችላለን። የዘገየውን በዱዓ መጠበቅ እንችላለን። የደከመውን ልብ በአላህ ቃል ማሳረፍ እንችላለን። እናም ዛሬ ምንም ቢጠብቀን፣ አንድ ነገር እናስታውስ፦ ያለ አላህ እርዳታ አንድ ቀን እንኳን አንችልም፤ ስለዚህ ቀናችንን በእርሱ ስም እንጀምር። አላህዬ ይህን ጧት የልባችን ሰላም፣ የዱዓችን መልስ እና የቀናችን በረከት ያድርገው 🤲      https://t.me/+SpJHRe6JfQQ0NGI0

📣 ክፍት የስራ ማስታወቂያ ​አስ-ሱና ሸሪዓውን የጠበቀ የዋግምትና የቁርኣን ህክምና ማዕከል ለካርድ ክፍል 1 (አንድ) ሴት ሰራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ​📌 ማሟላት ያለባት መስፈርቶች ●​ አቂዳና ስነ-ምግባሯ የተስተካከለ፦ ሰለፊይ የሆነች፣ ታማኝ እና መልካም ስነ-ምግባር ያላት ●​ አለባበስ፦ ኒቃቢስት የሆነች (ወይም ኒቃብ ለመልበስ ሙሉ ፍቃደኛ የሆነች ኒቃብ ከነጅልባቡ ገዝተን እንሰጣታለን) ●​ የስራ ዝግጁነት፦ ታካሚዎችን በትህትና እና በፍቅር ለመርዳትና ለማስተናገድ። ዝግጁ የሆነች ​ℹ️ መረጃዎች ●​ የስራ ቦታ፦ ደሴ (መናፈሻ) ● ​የስራ ሰዓት፦ ከጁሙዓ ውጭ ባሉት ቀናት ከጠዋቱ 1:30 እስከ 11:00 ሰዓት ​ደሞዝ፦ በስምምነት ​📞 ለመመዝገብና ለማነጋገር ● ​የቴሌግራም ቦት፦ @Abu_Hibetilah_bot @Abu_Hibetilah_bot ወይም ● ​የቴሌግራም አድራሻ፦ @Abu_ameti_rahman @Abu_ameti_rahman ​የቴሌግራም ግሩፕ፦ አስ-ሱና የህክምና ማዕከል ግሩፕ t.me/As_Sunah_sleruqa_memariya_group

🪴ኢስቲቃማን እንዴት እናመጣ? በእስልምና ኢስቲቃማ (الاستقامة) ማለት በአላህ ትእዛዝ ላይ ጸንቶ መቆም፣ ከኃጢአት መራቅና በመልካም ሥራ ላይ መቀጠል ነው። በነገራችን ላይ ኢስቲቃማ ማምጣት በተለይ በችግር ጊዜ ትልቅ መፍትሔ ነው። 💎ነገር ግን ኢስቲቃማ ማለት ችግር ፈጽሞ አይመጣም ማለት አይደለም፤ ችግር ሲመጣ በአላህ ላይ ተማምኖ፣ በትዕግሥትና በትክክለኛ መንገድ መቆም ነው። ኢስቲቃማን እንዴት እናመጣ? 1. እምነትን ማስተካከል – ተውሂድን ማጠናከርና ልብን ከአላህ ጋር ማያያዝ። 2. ግዴታዎችን መጠበቅ – በተለይ አምስቱን ሶላቶች በጊዜያቸው መስገድ። 3. ኃጢአትን መተው – ትንሽ ነው ብሎ ኃጢአትን አለመናቅ። 4. በቁርአንና በሱና ላይ መጠንከር። 5. ዱዓን ማብዛት። ነቢዩ ﷺ በብዛት ይሉ ነበር፦ «يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك» “የልቦች ቀያሪ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አጽናው።” 6. መልካም ጓደኞችን መምረጥ – ሰው በሚያደርገው አካባቢና ጓደኛ በጣም ይጎዳል ወይም ይጠቀማል። 7. ትንሽ ትንሽ ቢሆንም በመልካም ሥራ መቀጠል። ዋናው ነገር ብዙ ጀምሮ ቶሎ መተው ሳይሆን በቀጣይነት መሥራት ነው። አላህ ሲል፦ > ﴿إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا﴾ “ጌታችን አላህ ነው ካሉ በኋላም ጸኑ፣ መላእክት በእነርሱ ላይ ይወርዳሉ፤ ‘አትፍሩ፣ አትዘኑም’ ይሏቸዋል።” (ፉሲለት 41፥30) ስለዚህ ኢስቲቃማ በችግር ላይ የሚሰጠን መፍትሔ ነው፣ ነገር ግን ችግሩን በአንድ ጊዜ የሚያጠፋ ፈጣን መፍትሔ አይደለም። ችግሩን እንዴት እንደምንጋፈጠው የሚያስተካክል የልብ ጥንካሬና የሕይወት መንገድ ነው። ©https://t.me/Abuimran_alkemisse

ጥንቃቄ! - ደጋግመን እንደምናሳስበው፣ በኦንላይን ቁርኣን የምንቀራው ከማን ነው? ኡስታዙስ ማን ነው? የሚለው ጉዳይ ልዩ ትኩረት የሚሻ ወሳኝ ነጥብ ነው። በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ሰው ወደ ማቅራት በገባበት ሁኔታ፣ አንድን ሰው ኡስታዛችን ከማድረጋችን በፊት ቆም ብለን ማጤን ግድ ይለናል። ● ኡስታዙ እውቀቱን ከማን ነው የቀሰመው? ቁርኣን የቀራባቸው ታማኝ ኡስታዞች እነማን ናቸው? ● በተጅዊድ፣ በመኻሪጅና በሲፋት ደረጃ ትምህርቱን በሚገባ የጨበጠና የማስተማር ብቃት ያለው (ሙትቂን) መሆኑ ተረጋግጧል? ● እውቀቱ በስርአት የተረጋገጠና ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት ብቁ የሚያደርገው መሰረት አለው ወይ? በተመሳሳይ መልኩ፣ ራሳቸውን እንደ አስተማሪ ለሚያቀርቡ ኡስታዝ ተብዬዎችም የምናስተላልፈው  መልዕክት ቢኖር...አላህን  ፍሩ! አላህን  ፍሩ! አላህን  እንፍራ! ነው የምለው። t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

ፈጥኖ ማን ቀድሞ ይመልስ  🚀🚀 ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ ለመጀመሪያ ግዜ ሳሙና ያዘጋጀው ነብይ ማነው ?

📖سورة اكهف 💭 ማራኪ የሱረቱል ከህፍ ቂርአት 🎧تــلَآوٌةّ خــآشــعــةّ

🟢 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጣችሁ ! ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል። 📱 ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ ይሸለሙ ! ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫ
🟢 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጣችሁ ! ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል። 📱   ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ ይሸለሙ ! ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫኑ  👇 👉 t.me/FKR_ESKE_JENET

የጁመዓ ጧት… ዛሬ ሌላ ቀን ብቻ አይደለም፤ ልባችንን ወደ አላህ የምንመልስበት ውብ እድል ነው። የደከመውን ልብ በዚክር እናሳርፍ፣ የተጨነቀውን ልብ በዱዓ እናረጋጋ፣ ያለፈውን በእስቲግፋር እንተወው፣
የጁመዓ ጧት… ዛሬ ሌላ ቀን ብቻ አይደለም፤ ልባችንን ወደ አላህ የምንመልስበት ውብ እድል ነው። የደከመውን ልብ በዚክር እናሳርፍ፣ የተጨነቀውን ልብ በዱዓ እናረጋጋ፣ ያለፈውን በእስቲግፋር እንተወው፣ የሚመጣውንም በአላህ እንስጠው። በዚህች የተባረከች ቀን አላህዬ የተዘጋውን በሩን ይክፈትልን፣ የተዘገየውን ምኞት በኸይር ያሟላልን፣ በልባችን ያለውን ሁሉ እርሱ የሚያውቀውን መልካም መልስ ይስጠን። ጁመዓችን በሰላም፣ በረህማን እና በበረከት የተሞላች ትሁን። اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد

አንዳንዴ ለመናገር የማይመቹ ለመተው የማይቀሉ ብዙ ስሜቶች አሉ....ለኛ የከበድ ለሌሎች የቀለሉ ነገሮች አሉ...ምን ሆነሻል ስንባል"ምንም"ብቻ ብለን የምናልፈው;በውስጣችን ብቻ የምንይዘው:እኛ ብቻ
አንዳንዴ ለመናገር የማይመቹ ለመተው የማይቀሉ  ብዙ ስሜቶች አሉ....ለኛ የከበድ ለሌሎች የቀለሉ ነገሮች አሉ...ምን ሆነሻል ስንባል"ምንም"ብቻ ብለን የምናልፈው;በውስጣችን ብቻ የምንይዘው:እኛ ብቻ የምንታመምበት ጉዳይ አለ.... አላህ ከታጋሾች ያድርገን።ላኪን ማወቅ ያለበሽ ነገር ሁሉም ያአላህ ውስኔዎች ለኸይር ናቸው።   አብሽሪ. በዱኒያ  ላይ ዘውታሪ ነገር የለም። ሁሉም ነገር  በአላህ ፍቃድ.ይቀየራል. ሀዘንሽ አላህ በደስታ ይቀየይቅርልሻል.ህመምሽ. አላህ በጤና  ይቀይርልሻል .ስብራታሽን አላህ እዳልነበር አድርጎ  ይጠግንሻል... فوضي امركي.الِله 🍃ሁሉንም ነገር ወደ አላህአስጠጊው!  قَالَ إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّهِ وَأَعْلَمُ مِنَ اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ «ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ» አላቸው፡፡ 🍃 በምን አይነት ፈተና ውስጥ ብትሆኚ በጌታሽ ላይ መቼም ተስፊ እዳትቆሮጪ ! وَلَا تَيْأَسُوا مِن رَّوْحِ اللَّهِ ۖ إِنَّهُ لَا يَيْأَسُ مِن رَّوْحِ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْكَافِرُونَ ٓከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲዎች ሕዝቦች እንጂ ተስፋ አይቆርጥም» (አለ)፡፡ 🍃إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡

እውጭ ሀገር ሁነሺ አጥበቀሺ ይዘሻት ሀገር ስትገቢ ምነው አወለቅሻት? በይ እስኪ ንገሪኝ ጀነት ገባሺደ አውልቀሺ ለመጣል ዘደ አገኘሺደ ታይጅ ውዷየ አውልቀሺ አጣያት አጥብቀሺ ያዢጅ በይ ተሰተሪባት ገ
እውጭ ሀገር ሁነሺ አጥበቀሺ ይዘሻት ሀገር ስትገቢ ምነው አወለቅሻት? በይ እስኪ ንገሪኝ ጀነት ገባሺደ አውልቀሺ ለመጣል ዘደ አገኘሺደ ታይጅ ውዷየ አውልቀሺ አጣያት አጥብቀሺ ያዢጅ በይ ተሰተሪባት ገና ስትለብሻት ቃል ገብተሺላታል መቸም ላታወልቂያት አጥብቀሽ ልትይዣት ስለዚህ አትርሺ ቃልሺን አክብሪ መቸም አታውልቂያት ቀብር እስክገቢ       ጅልባብ & ኒቃብ

ፈጥኖ ማን ቀድሞ ይመልስ  🚀🚀 ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ አል አቅሷ መስጂድን የገነባው ነብይ ማን ነው ?

✅ቁርአንን አስተካክለው መቅራት ይፈልጋሉ ➡️ የምንሰጣቸው ትምህርቶች፦        🔢 ቃኢደቱ-ኑራንያህ        🔢 ቁርአን ነዘር        🔢 ቁርአን  ሂፍዝ        🔢 የተጅዊድ ትምህርት        🫰ወርሀዊ ክፍያ 500 ብር ብቻ 📶 ትምህርት የምንሠጥባቸው መንገዶች ፦          🗂በቴሌግራም፣                 🌐እና በኢሞ 📥 በቴሌ ግራም ለመመዝገብ፦ @Daruhadi21bot @Daruhadi21bot ወይንም https://s.imoim.net/1UB9I6 📌የመክፈል አቅም የሌላቸው ተማሪዎች ስላሉን እነርሱን በነፃ ስለምናቀራ ለአላህ ብላችሁ ማገዝ የምትፈልጉ የሴትም ይሁን የወንድ ኡስታዞች ከታች ባለው ቦት አናግሩን 🗂እንድሁም ተወዳድራችሁ በቅጥር መልክ መግባት የምትፈልጉም ከታች ባለው ቦት አናግሩን 📥ማሳሰቢያ :-ቂርአቱ የሚሠጠው ለሴቶች በሴት ኡስታዛ ስለሆነ ሁላችሁም ተሳተፉ ✔️የግሩፕ እና ቻናል ባለቤቶች ሆይ ሸር ይደረግ ለበለጠ መረጃ ወደ ቻናሉ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Muhammed_Ibn_Abdillah https://t.me/Muhammed_Ibn_Abdillah

አንዳንድ ነገር የሚዘገየው ለመጥፋት አይደለም… ምናልባት አላህ ከአንተ የዘገየው ነገር አንተ ከምታስበው በላይ በሚያምር መንገድ እንዲመጣ እያዘጋጀው ይሆናል። ስለዚህ የዘገየውን አትርገም፣ የተዘጋውን
አንዳንድ ነገር የሚዘገየው ለመጥፋት አይደለም… ምናልባት አላህ ከአንተ የዘገየው ነገር አንተ ከምታስበው በላይ በሚያምር መንገድ እንዲመጣ እያዘጋጀው ይሆናል።     ስለዚህ የዘገየውን አትርገም፣ የተዘጋውን በግድ አትክፈት፣ ያልሆነውንም ለምን ብለህ ልብህን አትድክም። አላህ የጻፈልህ ነገር ከአንተ አይርቅም፤ ያላልተጻፈልህም በምንም መንገድ ወደ አንተ አይመጣም። ልብህን አሳርፍ… የአላህ እቅድ ከአንተ እቅድ ይበልጣል።