fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ተቅዋ መርከዝ

ተቅዋ መርከዝ

رفتن به کانال در Telegram
186
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-530 روز
آرشیو پست ها
ረመዿን ነገ ነው‼ ሰበር‼ ====== ✍ የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ረቡዕ የካቲት 11, 2018 E.C. የረመዿን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል። አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን! ረመዿን ሙባረክ! ‏ || t.me/MuradTadesse

ሴት ልጅ ስትሞት በአምስት ጨርቅ ትጠቀለላለች ሞታ ጀናዛዋ ሲሰገድ  ጀናዛዋ ራቅ ብሎ ይቀመጣል ተጠግቶ አይቀመጥም አስቡት ሙታ  እኮ ነው!! ሙታ እደዚህ የሆነች አስቡት በህይወት እያለች......... ሴት ልጅ ወንድ ልጅ ምን ከጅሎ እንደሚያያት ብታውቅ ኖሮ; ከብረት በሆነ መሸፈኛ ራሷን ትከልል ነበር።

ዛሬማ ምን አለ ቢሰርቁ ቢቀሙ ይቸግራል እንጂ አሏህ ፊት ሲቆሙ ሀጂ ሙሀመድ ወሌ رحمه الله
ዛሬማ ምን አለ ቢሰርቁ ቢቀሙ ይቸግራል እንጂ አሏህ ፊት ሲቆሙ ሀጂ ሙሀመድ ወሌ رحمه الله

﴿إِنَّ هَذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ﴾ عَنْ أَبِي أُمَامَةَ الْبَاهِلِيِّ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ قَالَ : سَمِعْ
﴿إِنَّ هَذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ﴾ عَنْ أَبِي أُمَامَةَ الْبَاهِلِيِّ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ قَالَ : سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ ﷺ يَقُولُ : ((اقْرَءُوا الْقُرْآنَ ؛ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لِأَصْحَابِهِ)) صحيح مسلم. ___ አላህ (ሱ.ወ) በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦
​"ይህ ቁርአን ወደዚያች ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል..." (አል-ኢስራእ፡ 9)
​ከአቡ ኡማማህ አል-ባሂሊ (ረ.ዐ) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
​"ቁርአንን አንብቡ፤ በትንሳኤ ቀን ለጓደኞቹ (ለሚያነቡትና ለሚተገብሩት) አማላጅ ሆኖ ይመጣልና።" (ሶሒሕ ሙስሊም)

​የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ​"አንድ ሰው በጀነት ውስጥ ደረጃው ከፍ ይላል፤ እሱም 'ይህ (ደረጃ) ከየት መጣልኝ?' ብሎ ይጠይቃል። 'ልጅህ ለአንተ ባደረገልህ ኢስቲግፋር (ምህረት ል
​የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
​"አንድ ሰው በጀነት ውስጥ ደረጃው ከፍ ይላል፤ እሱም 'ይህ (ደረጃ) ከየት መጣልኝ?' ብሎ ይጠይቃል። 'ልጅህ ለአንተ ባደረገልህ ኢስቲግፋር (ምህረት ልመና) ምክንያት ነው' ይባላል።" (ሶሒሕ አል-ጃሚዕ)

🤭🤭🤭
🤭🤭🤭

​"በዚህ ሕይወት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ... ወይ ጥሎህ ይሄዳል፣ ወይም አንተ ጥለኸው ትሄዳለህ። ​ከአሏህ በስተቀር! ወደ እሱ ብትቀርብ ያብቃቃካል ፤ ከእሱ ብትርቅ ደግሞ — (ወደ እኔ ተመለስ እያ
​"በዚህ ሕይወት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ... ወይ ጥሎህ ይሄዳል፣ ወይም አንተ ጥለኸው ትሄዳለህ። ​ከአሏህ በስተቀር! ወደ እሱ ብትቀርብ ያብቃቃካል ፤ ከእሱ ብትርቅ ደግሞ — (ወደ እኔ ተመለስ እያለ) ይጠራሃል! "

👉♻️መሳጭ የሆነ ታሪክ ሙሐመድ ኢብኑ አቢ ዓሚር አል ሐጂቡል መንሱር ማነው??? 🤌ሲሞት ድፍን አውሮፖ በእልልታ ታጅባ ፈነጠዘች። አልፎንሶ ቀብሩ ላይ ድንኳን ሰርቶ "የአረቦችንና የሙስሊሞችን ንግስና ተቆጣጠርኩ" በማለትም ተኮፈሰ። 👉ከወታደሮቹ መካከል አንዱ "የዚህ ቀብር ባለቤት አንዴ ቢተነፍስ ሁላችንም ባለቀልን ነበር" ሲል ተናገረ። አልፎንሶ በንዴት ዘሎ አንገቱን ሊቀላው ሠይፉን ከሰገባው መዘዘ። ሚስቱ እጁን ያዘችውና "ልክ ነው ገድሉን ታሪክ ዘክሮታል ቀብሩ ላይ ስለተቀመጥንም የሱ ክብር ከፍ ይላል" አለቸው። 🔸ለምንስ ይሆን በመሞቱ እንዲህ የተደሰቱት!?   ✍ ነገሩ እንዲህ ነዉ እሱ ለሰላሳ ዓመታት በተከታታይ ሀምሳ አራት ዘመቻዎችን አካሂዶ አንዴም አልተሸነፈም። ራሱ እየመራ ነበር የዘመተው። ረፍት የሚባል አያውቅም አይተኛም። ጠላቶቹንም አያስተኛም። ታላቋንና መናገሻ ከተማቸውን ሊዮንን በድል ከፍቶ በከተማዋ ውስጥ አዛን አድርጓል። አውሮፓ ምርጥ ምርጥ መሪዎቿንና ጀነራሎቿን ሰብስባ ብትዘጋጅም አፈር ድሜ አስበልቷቸዋል። ስሙ ሲነሳ የፍርሀት ማዕበል ይቀስፋቸዋል። ያንቀጠቅጣቸዋል። ህፃናቶቻቸው ሲያስቸግሯቸው በስሙ ያስፈሯሯቸዋል። 🔘 በደቡብ አንደሉስ እንደ ሂጅሪያ የዘመን አቆጣጠር በ326 ዓመት ኸድራእ በምትባል ከተማ ተወለደ። አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ለአላማው የሚታክት ሰው ነበር። በወጣትነት ጊዜው በወቅቱ የአንደሉስ መናገሻ ከተማ ወደሆነችው ቁርጡባ በማምራት ወታደሩን ተቀላቀለ። በጀግንነቱ የከተማው ፓሊሶች አዛዥ ሆነ። በአስተዋይነቱ የንጉሱ የቅርብ አማካሪ ለመሆን በቃ። ንጉሱ ሲሞት ልዑሉ ህፃን ስለነበር የማስተዳደሩ ስራ የሱ ሆነ። 🔹  አንደሉስ አይታ የማታውቀውን ስልጣኔ በሱ ዘመን አየች። ዒልምን አስፋፋ፣ ሱናን አገዘ፣ ቢድዓን አጠፋ። በጂሃድ ወደር የማይገኝላቸውን ዘመቻዎች አካሄደ። ስንትና ስንት የክርስትና ጦር መሪዎች በሠይፉ አለቁ። ስንትና ስንት ምሽጎቻቸውን ተንኮታኮቱ። ሀያ ሰባት አመታት ሲያስተዳድር ሀምሳ አራት ዘመቻዎችን አካሄደ። በአንድም ዘመቻ ተሸንፎ አያውቅም።   🔥የአውሮፓ ነገስታቶች ተንበርክከውለታል። ግብር ሲቀበል እንደ ሌሎች የሙስሊም መሪዎች ከራሱ ሰው ልኮ ሳይሆን ራሳቸው ተሸክመው አምጥተው ነበር በይተልማል የሚያስገቡት። የቀሽታላው ንጉስ ለድርድር ቤተ መንግስቱ ሲገባ በፍርሃት ርዷል። ተንቀጥቅጧል። የሐጂቡል መንሱርን እግር ለመሳም ተንደርድሯል። 👉ኣህ! ምን ያህል አንበሳ ብትሆን ነው ያ ሐጂብ??? ☑️የአንድም ሙስሊም ክብር እንዲደፈር አይፈቅድም። በዘመቻ ወቅት ባንዲራውን ከፍ ያለ ቦታ ላይ የመስቀል ልምድ ነበረው። ቦታውን እስከሚለቅም ድረስ ባንዲራው ከተሰቀለበት አይወርድም። በአንድ ዘመቻ ባንዲራውን ረስተው ጥለውት ሄዱ። ከአካባቢው ሸሽተው የነበሩት ካፊሮች ባንዲራውን ከሩቅ ሲያዩ ያልተንቀሳቀሱ መስሏቸው እስከሚሄዱ ብለው ባሉበት ቆዩ። 🦾 ቀናቶች አለፉ ተጠግተው ሲያዩ ዝር የሚል ነገር የለም። ሱብሃነላህ ባንዲራውብቻ ያርበደብድ የነበረ መሪ! አሁን ለምን ፈረንጆች በሞቱ እንደጨፈሩ ተረዳችሁን?! ⁉️ 🟥ሙስሊሞች ታሪካችንን መለስ ብለን እንወቅየተወሰደ 🔸ምንጭ 📚التاريخ ابن أثير     البداية والنهاية ابن كثير ⤵️⤵️👆👆🔰👇👇👇⤵️⤵️ https://t.me/nurders/9867

👉🥀ከባለቤቴ ጋር ትዳር ከመሰረትን 21 ዓመት ሞላን ባለቤቴ አንድ እራሴን እንድፈትሽበት ያደረገኝን ጥያቄ አቀረበችልኝ 🤌ሃያ አንድ ዓመት ካንተ ጋር ስኖር አንድም ቀን ከእናትህ ጋር ለመዝናናት ስትወጣ አይቼክ አላውቅም ዛሬ ማታ እናትህን እራት ምሽት ጋብዛትና አዝናናት አለቺኝ" ውዷ ባለቤቴ ባቀረበችልኝ ሃሳብ ከመገረም በላይ መሰጠኝ ተስማማሁኝ እናም ወደ እናቴ ጋር ደወልኩላት እማ ዛሬ ካንቺ ጋር ሽርሽር መውጣት እፈልጋለሁ አልኳት ደነገጠች "ምነው ሰላም አይደል ልጆችህ ምን ሆኑ ባለቤትህስ ሰላም አይደለች እንዴ ?" በማለት የድንጋጤ ጥያቄዎቿን አርከፈከፈችብኝ..."አብሽሪ እማ ሁሉም ሰላም ነው ካንቺ ጋር ለመዝናናት ፈልጌ ነው" አልኳት በጣም ደስ አላት ተስማማች ወደ ማታ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ አልኳት በቀጠሮዬ ሰዓት ወደ እናቴ ጋር ሄድኩኝ እናቴ በረንዳው ላይ ቆማ እየጠበቀቺኝ ነበር እናቴ ሁለመናዋ ተቀያይሯል እርጅና ተጫጭኗታል  ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወደ መኪናዬ አስገብቻት ጉዞ ጀመርን እናቴ በጣም ደስታ ይነበብባታል "ልጄ ዛሬ ካንተ ጋር ሽርሽር እንደምወጣ ለሰፈር ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ለዘመድ አዝማዶቼ በሙሉ ተናግርያለሁኝ"አለቺኝ በጣም ከመደሰቷ የተነሳ አንድም የምታውቀው አልቀራትም ወሬውን ለሁሉም አዳርሳዋለች ወደ ሆቴል ይዥያት ሄድኩኝ አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ወረቀት የያዘ ኩፖን ሰጠን "ኡሚ ምረጪ" አልኳት... ፈገግ አለች ከእርጅና የተነሳ ማየት እንደማትችል ተረዳሁ ... ላንብብልሽ አልኳት "ልጅ እያለህ ሆቴል ቤት ገብተን ልንመገብ ስንል የምግብ ዝርዝር አነብልህ ነበር አሁን እዳህን ክፈል" ብላ ፈገግ አለች እኔም ፈገግ ብዬ አነበብኩላት   የለበሰችውን ልብስ ስመለከት ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በፊት የሞተው አባቴ የገዛላት የመጨረሻ ልብሷ እንደነበር አስታወስኩ ምግቡ ቀርቦ እናቴ ከደስታ የተነሳ ምንም እየበላች አልነበርም ደስታ በደስታ ሆናለች  በሕይወቴ እኔም በጣም የተደሰትኩበት አጋጣሚ ነበር ከእናቴ ጋር ተዝናንተን ስናበቃ ይህ ምሽት እንዲደገም ፈልጌ "እማ መቼ ተመልሼ ልምጣና ልውሰድሽ..?" አልኳት በእንደዚ ቀን ናአ ነገር ግን እኔ ነኝ የምጋብዝህ ከተስማማህ ና" አለቺኝ ፈገግ አልኩኝ "አብሽሪ ትጋብዥኛለሽ" አልኳትና ተለያየን በመሃል እናቴ ታመመች ከህመሟ ድናልኝ አብርያት የማሳልፍበት ምሽት ናፈቀኝ ነገር ግን ከእናቴ ጋር ዳግም አልወጣንም እናቴ ወደ ማይቀረው የሞት ጉዞ ተጓዘች በጣም አዘንኩ አለቀስኩ ከእናቴ ጋር ቀጠሮ ይዘን በነበርንበት ቀን አመሻሹ ላይ ከአንድ ታዋቂ ሆቴል ቤት ተደወለልኝ "ዛሬ እራት ከባለቤትህ ጋር በነፃ ተጋብዛቹሃል" የሚል ነበር። ግራ ተጋባው ማነው እንዴት ለማንኛውም እሺ እንመጣለን ብዬ ስልኩን ዘግቼ ምሽት ላይ ከባለቤቴ ጋር ሄድኩኝ  ግብዣው ከደብዳቤ ጋር ቀረበልን ደብዳቤውን ከፈትኩት እንዲህ ይላል:- "ልጄ ሰላም ላንተ ይሁን የእራቱን ግብዣ ስንቀጣጠር መገኘት እንደማልችል አውቅ ነበር የሞት ቀጠሮዬ እየተቃረበ እንደነበር ነፍሴ ይነግረኝ ነበር ልጄ ይኸው እኔ በቃሌ መሰረት ጋብዥሃለው  በኔ ፋንታ ውዷ ባለቤትህ አብራህ እንድትሆን ፈቅጃለሁ!" ይላል ሳይታወቀኝ እንባዬ ወረደ አለቀስኩ 21 ዓመት ሙሉ የዘነጋሁትን ውድ ዕቃ አሁን ነው ማጣቴን ያወኩት...! ስንቶቻችን ይሆን ካገባን በኋላ እናቶቻችንን የምናስታዉሳቸዉ ? ሼር በማድረግ ለሌሎች ያካፍሉ ። ረጅም እድሜ ለእናቶቻችን!! በህይወት ለሌሉት በዱአ በሰደቃ አስታዉሱዋቸዉ منقل "ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ) ⤵️⤵️👆👆⤵️👇👇⤵️⤵️ https://t.me/nurders/9855

✍ 🔥የመለከል መውት ትዝብት!!! ==================   "ከቀናቶች ውስጥ አንዲትም ቀን የለችም መለከል መውት ወደ ሁሉም ቤት በቀን 3ጊዜ እየመጣ ቢጎበኛቸው እንጂ። 🍃 ከቤተሰቦቹ መሃል.... ➷ሪዝቁን የጨረሰና ➷እድሜውን ያለቀ ካገኘ ሩሑን ይዞ ይሄዳል። 🍁ልክ ሩሑን ይዞ ሲሄድ ቤተሰቦች መጮህና ማልቀስ ይጀምራሉ። በዚህ ጊዜ መለከል መውት የቤቱን መቃን ይዝና…… «ወላሂ እኔ እንደ ሆነ ምንም ሪዝቁን አልወሰድኩበትም፤ እድሜውም አልቀነስኩበትም። ♻️ባይሆን ወደ እናንተም መመለሴ ስለ ማይቀር ተራ በተራ ሁላችሁም እወስዳችኋለሁ» ይላቸዋል። 🔥መለከል መውት ትዝብቱን ይቀጥልና…… «ወላሂ እነዚህ ሰዎች ሟቹን ያለበት ሁኔታ ቢያዩ ኖሮ እሱን ይረሱትና ስለ ራሳቸው ማልቀስ ይጀምሩ ነበር።» ይላል።منقل      [ሐሰኑል በስሪ]    🤲አላህ መጨረሻችን ያሳምርልን🤲 ♻️https://t.me/httpgoto 👇👇👇👇👇 https://t.me/nurders/9877

የማለዳ መልእክት (23) ~ ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ "እስቲ ዱንያን ግለፅልን?" ተብለው ተጠየቁ። * ''ላስረዝም ወይስ ላሳጥር? " አሉ። - "አይ አሳጥር" አሏቸው። * "ሐላሏ ሒሳብ አለበት። ሐራሟ እሳት አለበት" አሉ። [አዙህድ፣ ኢብኑ አቢ ዱንያ፡ 17] ከሐራም እንቆጠብ። በሐላል ሪዝቃችን ደግሞ አላህ ግዴታ ያደረገብንን ግዴታ እንወጣ። ባልተገባ ቦታ አናውጣው። ገንዘብ ለማይጠቅምበት ቀን ለነገ ስንቅ የሚሆነን ኸይር ስራ ላይ እንካፈልበት። (ሸዕባን 12/1447) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ሴቶች እና ረመዷን ~ 1- የወር አበባ እና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች ፆም አይፆሙም። በዚህ ሰበብ ፆም ካለፋቸው በምትኩ ሌላ ጊዜ ይፆማሉ። 2- በዚህ ሰበብ ያልፆሙ ከሆነ ለወሩ ክብር በሚል ምክን
ሴቶች እና ረመዷን ~ 1- የወር አበባ እና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች ፆም አይፆሙም። በዚህ ሰበብ ፆም ካለፋቸው በምትኩ ሌላ ጊዜ ይፆማሉ። 2- በዚህ ሰበብ ያልፆሙ ከሆነ ለወሩ ክብር በሚል ምክንያት መራብ የለባቸውም፣ መብላት መጠጣት ይችላሉ። 3- የረመዷንን ወር በወር አበባ ምክንያት ሳያቋርጡ ሙሉውን ለመፆም በማሰብ መከላከያ መጠቀም ይችላሉ። 4- አጥቢ እና ነፍሰ ጡር ከሆኑ ማፍጠር ይችላሉ። በምትኩ ሌላ ጊዜ ይፆማሉ። ቤዛ ማብላት አይጠበቅባቸውም። የብዙ ወራት ተደራራቢ ፆም ኖሮባቸው ቀዷእ ማውጣቱ የሚከብዳቸው ከሆነ በያንዳንዱ ቀን ፋንታ ምስኪን ያበላሉ። 5- ነፍሰ ጡር የሆነች ሴት መፆም ከፈለገች የማቅለሽለሽ ስሜቷን ለመከላከል የማይፈረፈር እና ከጣእም ነፃ የሆነ ማስቲካ መጠቀም ትችላለች። 6- በረመዷን የሚያደርጉትን የምግብ ዝግጅት ፆመኞችን የማስፈጠር ኒያ ቢያስቡበት የበለጠ ይጠቀማሉ። 7- በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ላይ ከመጠመድ በልክ ቢሆኑ የተሻለ ነው። 8- ሴቶች ልጆች የወር አበባ ማየት ከጀመሩ ለአቅመ ሄዋን ስለደረሱ አዋቂ ሴቶችን የሚመለከት ሁሉ ይመለከታቸዋል። 15 ዓመት እስከሚሞላቸው በመጠበቅ መዘናጋት እንዳይኖር። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor