قَنَاةُ أمِ أنَسَ بِنْتْ حُسَيِنْ لِنَشْرِ اَلسُنَةِ 🇸🇦
رفتن به کانال در Telegram
وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِنِّي اللهم ارزقنا محبتك ورضاك، وألبسنا القبول في الأرض والسماء، واجعل لنا أثرًا طيبًا في القلوب ♻️
نمایش بیشتر3 701
مشترکین
+1324 ساعت
+167 روز
+4630 روز
آرشیو پست ها
«ፈተናዎችና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ከ አላህ በስተቀር ማንም እንደሌለህ ያስተምሩሃል..»
https://t.me/ibrahim_furii
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
124,000 ነቢያቶች ወደ ሰው ልጆች ተልከዋል ፡፡
✅
እውነት ነው በተለይ አሁን ላይ እየታየ ያለው ሁኔታ ነው !! የአሏህ ፊት ቀርቶ የሰወችን ፊት ፍለጋ እሰኪመስል ድርሰ! ሱበሀን አሏህ አሏህ ካዘነላቸው ከእሱ ባሪያውች ውጭ! ስናስቀራ ለስው $ ስናቀራ ለስው የሆነ መልካም ስራ ስንሰራ ለሰው በአጠቃላይ የስወች ሙገሳ ነው እኛን እየነዳን ያለ የእሱ ፊት ተርሰቶ አሏሁ ሙስተዓን ☁️
Repost from ABU~MAHI (አቡ_ማሒ)
ስምህ እንዲጠራና እውቅና ለማግኘት በየቦታው መገኘት የለብህም።
በዝምታ የምትሰራው ጥራት ያለው ሥራ በራሱ ጊዜ በከፍተኛ ድምፅ ይናገራል!
ብዙ ሰዎች ትኩረታቸውን "እንዲታዩ" እና "ስማቸው እንዲነሳ" ላይ ብቻ ያደርጋሉ።
ነገር ግን እውነተኛና ዘላቂ ስኬት የሚመጣው ከተጋነነ ማስታወቂያ ሳይሆን ከሚሰሩት ሥራ ጥራትና ውጤታማነት ነው::
ሥራህን በጥራት፣ በጥንቃቄና በታማኝነት ስራ፤ የቀረው ነገር ሁሉ በራሱ ጊዜ ይከተላል።
💡 ጥራት ያለው ሥራ ማብራሪያ አይፈልግም — ውጤቱ ራሱ ምስክር ነው!
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
🔴 መልካም ባልና መልካም ሚስት ከአላህ የሚሰጡ ታላቅ ጸጋ ናቸው።
ባልን የሚያሳንሰው ገንዘቡ አነስተኛ መሆኑ አይደለም፤
ሚስትንም የሚያሳንሳት ውበቷ አነስተኛ መሆኑ አይደለም።
እውነተኛው ጉድለት በዲን ላይ ያለ ድክመት፣ በመጥፎ ሥነ-ምግባርና በመጥፎ ባህሪ ነው።
🌿 ስለዚህ ትዳር ሲመረጥ በገንዘብና በውበት ብቻ ሳይሆን፣ በዲን፣ በሥነ-ምግባርና በመልካም ባህሪ ላይ ሊመሰረት ይገባል።
አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (50)
~
በሞት የተለዩ ወላጆቻችሁን በዱዓችሁ አትርሱ። ከቻላችሁ በሶደቃ አስታውሷቸው፤ በተለይም አገልግሎቱ የሚቆይ የሆነ ሶደቃ ቢሆን ተመራጭ ነው። ለምሳሌ አጅሩን ለነሱ በማሰብ የመስጂድ ግንባታ ላይ መሳተፍ፣ ውሃ ማውጣት፣ የደዕዋ ስራን ማገዝ፣ የወቅፍ አገልግሎት፣ ወዘተ.
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 20/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ከሳዳት ተማሩ
የሀበሻው ንጉስ ኡስታዝ ሳዳት ከማል
መርሁ ወጥ ነው እውነት ያስቀድማል
በዲን መዋሸትን በጥብቅ ይቃወማል
ወቀሳን ሳይፈራ፣ ለዲን ዘብ ይቆማል
የሽርክን ወረርሽኝ፣ በጥበብ ያክማል
የቢድዓን ተውሳክ፣ በድፍረት ያርማል
ውለታህ ብዙ ነው የተውሒዱ ጀግና
የሱናው ነፀብራቅ፣ ስምህ ነው ገናና
ድምፅህ ያስተጋባል በሁሉም ቀጠና
ጠላት ያ ደ ን ቅ ሃ ል ወዳጅ ይቅርና
የኛ ቆራጥ ጀግና፣ ግልፅ ነው ቀመሩ
እውነት አትደብቁ ውሸት አትቀባጥሩ
በዲን ስም አትዋሹ ያለዒልም አታውሩ
ሰዎች መንገድ ለቀው ውሸትን ካወሩ
መልስ ይሰጣቸዋል ሳዳት መምህሩ
አ ያ ስ ጨ ን ቀ ው ም ሀገር እና ዘሩ
ለ "ፍ ት ህ" መቆምን ከሳዳት ተማሩ
= t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from ስለ ቀልባችን
የዱንያ ልጆች አትሁኑ.....!
በኡስታዝ አቡ ሱፍያን አላህ ይጠብቀው!
ስለ ቀልባችን☑️
➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
✔️نما كان القرآن روحًا لأنه سبب حياة هذه الأمة، فلا يموت قلبٌ خالطَت نبضه آيات القرآن، ولا حياة لقلبٍ خلا منها🤍🤍
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡
🌿 የእርጉዝ ሴት አምሮት በባህሪዋ ላይ ያለው ተፅዕኖ 🌸
📌 የሞሮኮ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله ተጠየቁ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌸 ጥያቄ፦
የሴት አምሮት (الوَحَم) በሴቶች ላይ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰተው እውነተኛ ነገር ነውን? ወይስ ተራ ምናብና ቅዠት ብቻ ነው?
አላህ መልካም ዋጋ ይክፈልዎትና።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 መልስ፦
الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على من أرسله الله رحمة للعالمين، وعلى آله وصحبه وإخوانه إلى يوم الدين، أما بعد:
የእርጉዝ አምሮት (الوَحَم) በአረብኛ ቋንቋ የታወቀ ቃል ሲሆን፣ እርጉዝ ሴት የምትመኘውንና በዚያ ወቅት የምትፈልገውን ነገር ያመለክታል። ይህም በታዋቂ የአረብኛ መዝገበ ቃላት የተጠቀሰ ትርጉም ነው።
🌿 ነገር ግን ዛሬ ሰዎች ስለ «አምሮት» የሚናገሩት ሌላ ነገር አለ።
እሱም እርጉዝ ሴት አንድን ነገር በጣም ከፈለገች፣ ያ ፍላጎቷ ካልተሟላላት፣ በሆዷ ያለው ልጅም እርሷ የፈለገችውን ነገር የሚመስል ምልክት ወይም ጥቁር ምስል በሰውነቱ ላይ ይዞ ይወለዳል ይጠቁራል የሚለው እምነት ነው።
ይህንን ግን በሸሪዓ ውስጥ መሠረት የሌለው ነገር ነው። እንዲሁም ይህ እምነት በሚታመን የሸሪዓ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን አላውቅም።
🌿 ይህ ነገር በተለይ በሴቶች አንደበት የሚዘወተር እምነት ነው።
እንደዚህ ያለው ነገር በሸሪዓ ውስጥ የታወቀና አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ በዲን ውስጥ የታወቀ ይሆን ነበር፤ ነቢዩ ﷺም ለሰዎች በግልጽና በበቂ ሁኔታ ያስረዱት ነበር። ምክንያቱም ሰዎች ይህንን ጉዳይ በጣም ይፈልጉት ነበር፤ ለሁሉምም የሚመለከት ጉዳይ ነውና።
🌿 ነቢዩ ﷺ የተላኩትን መልዕክት በሙሉ አድርሰዋል፣ አደራውንም በትክክል ተወጥተዋል።
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ብሏል፦
﴿ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗاۚ﴾
“ዛሬ ዲናችሁን ለእናንተ ሞልቼላችኋለሁ፤ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ሞላሁ፤ እስልምናንም ለእናንተ ዲን አድርጌ ወደድኩላችሁ።”
📖 [ሱረቱል ማኢዳህ፡ 3]
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 ነቢዩ ﷺ መልዕክቱን በሙሉ ማድረሳቸውን እንዲህ ብለው ለሰሐቦቻቸው አረጋግጠዋል፦
«أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟»
“እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?”
እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ።
እንደገና፦ «أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟»
“እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?”
እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ።
ከዚያም ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«اللَّهُمَّ اشْهَدْ، فَلْيُبَلِّغِ الشَّاهِدُ الْغَائِبَ»
“አላህ ሆይ! መስክር! እዚህ ያለው ለሌለው ያድርስ።”
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌸 ነገር ግን እርጉዝ ሴት በዚያ ወቅት ልዩ እንክብካቤ አያስፈልጋትምን?
በእርግጥ ያስፈልጋታል። 🌷
ሸይኹ رحمه الله እንደሚገልጹት፣ ሴቷ በዚያ ወቅት ተጨማሪ እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ ርኅራኄና ትኩረት ልትፈልግ ትችላለች።
ስለዚህ ባል የባለቤቱን ሁኔታ ሊያስተውል፣ በርኅራኄ ሊያስተናግዳት፣ በተቻለውም መጠን የምትመኘውን ነገር ሊያሟላላት ይገባል። ብለዋል።
🌿 በዚህ ጊዜ እሷን ማስጨነቅ ማለት በእርግዝናዋ ላይ ተጨማሪ ጫና ማስገባት ነው።
ስለዚህ ባል ከባለቤቱ ጋር በመልካም ሁኔታ ይኑር፤ ሁኔታዋንም ያስተውል፤ የሚያስፈልጋትንም ነገር በቻለው መጠን ያሟላላት።
💎 ይህንን ሲያደርግም ከአላህ ዘንድ ምንዳን በመፈለግ ያድርገው።
አላህ سبحانه وتعالى ምንዳን የሚሰጥ ከሁሉ የተሻለ ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 ለጀግና ለባሎች የሚሆን ማስታወሻ
ሚስትህ እርጉዝ ስትሆን በሰውነቷ ውስጥ አንድ ሕይወት እየተሸከመች ነው።
ስለዚህ በዚያ ወቅት የምትፈልገውን በማድረግ ደስ ብሎህ አግዛት፤ ድካሟን በርኅራኄ ተመልከት፤ በቃልህም አጽናናት።
🌷 እርግዝናዋ የሚያልፍ ወቅት ነው፤ ነገር ግን በዚያ ወቅት ያሳየኸው ርኅራኄ በልቧ ውስጥ ረጅም ጊዜ ሊቀር ይችላል።
🌿 ትዳር የሚያምረው በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ አንዱ ሲደክም ሌላው እጁን ሲይዘው ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
اللَّهُمَّ احْفَظْ نِسَاءَ الْمُسْلِمِينَ وَأَجِنَّتَهُنَّ وَارْزُقْهُنَّ الصِّحَّةَ وَالْعَافِيَةَ، وَأَصْلِحْ بُيُوتَهُنَّ، وَاجْعَلْ بَيْنَ الْأَزْوَاجِ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً وَسَكِينَةً.
“አላህ ሆይ! የሙስሊም ሴቶችንና በማህፀናቸው ያሉትን ልጆቻቸውን ጠብቅልነረ፤ ጤናና ደህንነትን ስጣቸው፤ ቤቶቻቸውንም አስተካክልላቸው፤ በባሎችና በሚስቶች መካከልም ፍቅር፣ ምሕረትና ሰላም አድርግላቸው።” 🌸
📌 ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله
🇩🇿 አልጀሪያ — 22 ረጀብ 1426ሂ / 17 ኦገስት 2005
🌿 العِلْمُ عِنْدَ اللهِ تَعَالَى 🌿
الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለአስተውሎት
~
ፉዶይል ብኑ ዒያድ አንዱን ሰው “እድሜህ ስንት ነው” ብለው ጠየቁት።
* "ስልሳ አመት" አለ።
- "ስልሳ አመት ሙሉ ወደ ጌታህ እየተጓዝክ ነው፡፡ መድረሻህ ሳይቃረብ አይቀርም።"
* "ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!" (እኛ ለአላህ ነን፡፡ ወደሱም ተመላሾች ነን)
- “ 'ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን' የሚለውን ተፍሲሩን ታውቃለህ? ለአላህ ባሪያ እንደሆነ ወደሱም ተመላሽ እንደሆነ የሚያውቅ እንደሚቆም ይወቅ፡፡ እንደሚቆም ያወቀ እንደሚጠየቅ ይወቅ፡፡ እንደሚጠየቅ ያወቀ መልስ ያዘጋጅ፡፡”
* "ምንድን ነው መፍትሄው?"
- "ቀላል ነው!"
* "ምንድን ነው እሱ?"
- "በቀረህ እድሜ መልካም ስራ፡፡ ያለፈው ይማርልሃል፡፡ ቀሪው እድሜህን ካጠፋህ ግን ባለፈውም በቀሪውም ትያዛለህ፡፡"
ምንጭ፦ [ሒልየቱል አውሊያህ፡ 8/113]
አስተውል። ስልሳ ዓመት ከደረስክም አስተውል። ስልሳ ካልደረስክም ገና ነኝ ብለህ አትዘናጋ ነቃ በል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2005)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
.
አንዳንዴ ቅድሚያ ለሚሰጠውቅድሚያ ስጡ !!✅ ለስንቱ ባክናችሁ ትችሉታላችሁ በረቢ 💗 Invest in your own peace መጀመሪያ ✅
• قال الإمـام ابـن القـيم رحمه الله : -
« أعقَلُ الناسِ من آثر لذته وراحته الآجلة الدائمة على العاجلة المنقضية الزائلة، وأسفهُ الخلقِ من باع نعيم الأبد وطيب الحياة الدائمة واللذة العظمى التي لا تنغيص فيها ولا نقص بوجهٍ ما، بلذّة منغَّصة مشوبة بالآلام والمخاوف، وهي سريعة الزوال وشيكة الانقضاء ».
- ابن القيم | الداء والدواء صـ (٤٥٠).📚
