fa
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
3 194
مشترکین
+4524 ساعت
+967 روز
+45930 روز
آرشیو پست ها
ብልፅግና ያዝኩት ብሎ ካሰራጨው የኮሎኔል አለሙ ሞላ መረጃ ጋር ተያይዞ መሬት ላይ ያለው ሐቅ! ኮሎኔል አለሙ ሞላ በቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖም ይሁን በአሁኑ ምኒልክ ዕዝ ምንም አይነት ሃላፊነት የሌ
ብልፅግና ያዝኩት ብሎ ካሰራጨው የኮሎኔል አለሙ ሞላ መረጃ ጋር ተያይዞ መሬት ላይ ያለው ሐቅ! ኮሎኔል አለሙ ሞላ በቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖም ይሁን በአሁኑ ምኒልክ ዕዝ ምንም አይነት ሃላፊነት  የሌለውና ከ2016 ዓ.ም ክረምት ጀምሮ ትግሉ ላይም ያልነበረ ሲሆን ሃብሩ ወረዳ ጊራና ዙሪያ ልዩ ስሙ ጎራርባ የተባለ ቦታ ላይ ትዳር መስርቶ ወልዶ እየኖረ የነበረ ነው:: መሬት ላይ ያለው እውነታ ኮሎኔሉ ከብልፅግና መከላከያ ሰራዊትም ይሁን ከፋኖ ነፃ ሆኖ የግል ህይወቱን እየኖረ ባለበት ሁኔታ ለፖለቲካና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለማዋል ሲባል ከእውነት የራቀ ነገር ማሰራጨቱ ከብልፅግና አገዛዝ የሚጠበቅና ከተለመደ ህዝብን የማደናገር ተግባር የተለየ አይደለም:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር በምርኮ የተያዙ የመከላከያ ፣የአድማ ብተና፣የፖሊስ እና ሚኒሻ አካላት ተገቢውን የተሀድሶ ስልጠና በመስ
+1
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር በምርኮ የተያዙ የመከላከያ ፣የአድማ ብተና፣የፖሊስ እና ሚኒሻ አካላት ተገቢውን የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት ተለቀዋል። መጋቢት 09/2018 ዓ.ም ጋይንት ንፋስ መውጫ ከተማ የተማረኩት አባላቶቹ በቆይታቸው ተገቢውን በክፍለ ጦር የፖለቲካ ዘርፍ ክፍል ፣ በኮሩ የህግ ክፍልና በሌሎች ስራ አስፈጻሚዎች የፖለቲካ የግንዛቤ ተሰጥቷቸው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት ምርኮኞቹ በነበራቸው ቆይታ ተገቢውን እንክብካቤ እንደተደረገላቸው በመግለጽ ለማህበረሰቡ ፣ለክፍለ ጦሩ አመራር እና ለመላው  አባላቱ ምስጋና አቅርበዋል። ድል ለአማራ ህዝብ !!! ድል ለአማራ ፋኖ !!! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!!

የጋይንት ሕዝብ ጭፍጨፋና የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸው ተሰማ የምሥራቅ ዕዝ ውስጥ ኮሎኔል ዓለሜ ታደለ የሚመራው 33ኛ ክፍለ ጦር የጋይንት ምድርን ከረገጠ ጀምሮ አያሌ የአደባባይ እና የስውር ጅምላ ግድያዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ቀሳውስትና ዲያቆናት ከቤተ መቅደስ (ቅዳሴ) ውስጥ ወጥተው ተገድለዋል። መነኮሳት ተገድለዋል። አደባባይ ላይ መረሸን አልበቃ ብሎ ወጣቶች ከቤታቸው እየወጡ ሌሊት ላይ በመረሸን ላይ ናቸው። ታፍሰው የሚወሰዱ ወጣቶች በሌሊት እያስወጡ በነፋስ መውጫ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ማለትም ቅድሥት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ፣ ኮሶ ሜዳ በታች፣ ክታክታ ጫካ፣ የኩሩጣ ማርያም አካባቢዎች ጅምላ መቃብሮች እና ሳይቀበሩ የቀሩ የብዙ ወጣቶች አስከሬን እየተገኘ ይገኛል። አሁንም ወጣቶች እየታፈሱ ይገኛሉ። የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ በጭካኔው የታወቀና ወጣቶች ታፍሰው ሲደበደቡና ሲረሸኑ እንኳን ፊት ለፊት ሆኖ ይስቃል አሉ። ሲመገብም ብቻውን ነው አሉ። ከጋርዶቹ ጋር እንኳን ተመግቦ አያውቅም ነው የሚሉት። በስሩ ያሉት የአማራ ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ አባላት ሲናገሩ "ሰውየው ፍጹም ጭራቅ ነው። ከዚህ በፊት፥ አማራ ክልል ላይ በተንቀሳቀሰባቸው ቀጠናዎች አያሌ ግፎች የሠራ፣ ወጣቶችን የረሸነ ነው። በጭካኔውና ጨፍጫፊነቱ የተነሳ ነው ጠንካራ የፋኖ መሠረት ወዳለበት እንዲንቀሳቀስ የሚታዘዘው። አካባቢውን ለቀን ወደ ሌላ ግዳጅ ቀጠና እስከምንሄድ ወጣቶች ተሰደዱ" ነው ያሉት። የዚሁ የ33ኛ ክፍለ ጦር እና አዛዡ ሞጣ ከተማ በነበረበት ሠዓት አያሌ ግፎችን ሲሠራ የነበረ ሲሆን፣ ወደ ደብረ ታቦር ተዛውሮ የለመደውን ግፍ ፈጽሞ ሲያበቃ ወደ ጋይንት ከተዘዋወበት ጀምሮ ሕዝብ እያለ ይገኛል። ከትናንት በፊት 17፣ 2018 ዓ.ም "ደምበጣ ሚካኤል" ከተባለ አካባቢ ከእናቱ ጋር ተነስቶ ወደ ነፋስ መውጫ ከተማ ቅዳሜ ገበያ የሄደ ወጣት እስከነ ሕይወቱ በእሳት አቃጥለውታል። ከእናቱ ጋር ወደ ገበያው የሄደው ወጣት ጸጉሩን ያሳደገ ነው። ወደ ገበያው ውስጥ እንደገባ የመከላከያ አባላት ያዙት። ወደ ኮሎኔል ዓለሜ ወሰዱት። ከዚያም "ጸጉርህን ያሳደከው ፋኖ ለመሆን ነው" ብሎ በጸጉሩ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ እሳት ለቀቀበት። የወጣቱ ሕይወት አላልፍ ብሎ ለሁለት ሠዓታት ያክል ተሰቃይቷል። የተቃጠለውን አስከሬን ቤተሰቦቹ ቢጠይቁም የት እንዳደረሱት አይታወቅም።

የብልፅግና ተቋም ያለ አንድ ጥይት ጩከት ስቦ በማስከዳት እያፈራረሰ ነው ==============+=========== ...........ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም ከግንደወይን (ጎንቻ) ከድተው 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለ ጦር ፋኖን ተቀላቅለዋል ። 1.ሰጡ ደርብ .............ፖሊስ 2. ደሳለኝ ካሳ .........ፖሊስ 3.ብርሐን አሞኘ .......ሚሊሻ 4.ጌትነት መልኬ .......ሚሊሻ 5.ክንዲ ሻንበል..........ሚሊሻ 6.ሀብታሙ ንጉሴ....ፓራ ኮማንዶ 54ክ/ጦር የተቀላቀለ 7.በላይ በዙ ....25ክ /ጦር.መከላከያ 54ኛን የተቀላቀሉ ሲሆን ፦ ከዚህ በላይ በሴራ ህይወታችን መስዋት ማድረግ አንፈልግም በማለት ቆንጆወቹን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን በማከናወን ላይ ይገኛል። በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣ
+1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን በማከናወን ላይ ይገኛል። በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ ከሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም በእነማይ ዲማ ከተማ፣ የቀብሀና፣ ደብረቅዱሳን ወንደሳ፣ ቁስቋም ቀሸምሽ፣ ሰቀላ ቀበሌ እና በሸበል በረንታ አራጢ፣ ከወይንየ፣ ከወረጎና አካባቢው፣ ከገደያሱ፣ ከአባሰልማ ፣ከየጠሃና፣ ከቦንያ ሰቀላ ቀበሌ የተሰባሰቡ የማህበረሰብ ክፍል በቁጥቋጥ ቀበሌ ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዶል። በፖለቲካ ግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት የህዝብ አስተዳደርን፣ የፍትህ አሰጣጥን፣ የድርጅቱን አሁናዊ ቁመና በመዳሰስ በ201ኛ ኮር እና የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ሰፊ የፖለቲካ ግንዛቤ ተሰጥቷል። በአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት የ201ኛ ኮር አመራሮች 64ኛ ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች ከክ/ጦሩ አመራሮች እና ከወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች ጋር በመሆን የህዝብ መድረክ እያካሄዱ ይገኛሉ። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!              ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት

ሰበር የድል ዜና ቢቡኝ ወረዳ የመሸገውን የአረመኔው ሰራዊት ሲደቆስ ውሏል ============================= ሚያዚያ19/2018ዓ.ም የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ ቢቡኝ ወረዳ የመሸገውን የአብይ አህመድ ሰራዊት ምሽጉ ድረስ በመሄድ ሲያናግሩት ውለዋል። የ201ኛና የ109ኛ ኮር የ54ኛና የ99ኛ ክ/ጦር ሻለቆች የጨመቆትንና የሙገር ምሽግን በመጠጋት የጠላትን መከላከል ሰብሮ በመግባት ጠላት ላይ ታሪክ ሰርተዋል። ድጎፅዮን ቀጠና ጨመቆትና ሙገር ሉባ ምሽግ በኩል የተደመሰሰ 1ኛ ምትኩ ሹመቴ -ሚኒሻ 2ኛ ዮሀንስ ሞላ-ሚኒሻ 3ኛ ደሴ አለማየው-ሚኒሻ 4ኛ አባ ደነቀው -ሚኒሻ 5ኛ ሞላ -ሚኒሻ 6ኛ አየነው ፍቃዴ-ሚኒሻ 7ኛ የኃላው መርሻ -ሚኒሻ 8ኛ በስም ያልታወቀ-ሚኒሻ 9ኛ አንድ ፖሊስ የቆሰለ 10ኛ, 04መከላከያ 12 ክላሽና በቁጥር ያልታወቀ ተተኳሽ የ201ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦርና የ54ኛ ክ/ጦርን 04ሻለቃን ቃኝ በማድረግ ወይንውሃ የመሸገውን የጠላት ሰራዊት ምሽጉን በመደምሰስ ጠላትን ተራራ ላይ ሰቅሎታል። በወይንውሃ ቀጠና 1ኛ, ጤናው አማረ-ሚኒሻና ሻለቃ መሪ 2ኛ, ይርጋ አለሙ- ሚኒሻ 3ኛ, ይበልጣል --ሚኒሻ 4ኛ,ጌቴ ዘገዬ-ሚኒሻ 5ኛ, መሌ አባተ-ሚኒሻ 6ኛ, ወንዴ ንጋቱ-ሚኒሻ 7ኛ,መቶ ዓለቃ መከለያ ከባድ ቁስለኛ 1-ምህረቱ እውነቴ -ሚኒሻ 2-ደሴ አበበ--ሚኒሻ እንዲሁም 11ክላሽና በወል ያልታወቀ ተተኳሽ ተማርኳል የ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር  የሻለቃ 4 ምክትል ሻለቃ አዛዥ  ታዘብ አንሙት ሁለት ክላሽ ማርኳል ይቀጥላል ------------------ የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ሰበር ዜና! በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ እና ምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት መርጦለ ማርያም ከተማን ተቆጣጠሩ! ​ከቴዎድሮስ ዕዝ እና ከምኒልክ ዕዝ የተውጣጡ የ105ኛ ኮር ስር የሚገኙ የ45ኛ እና የ29ኛ
ሰበር ዜና! በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ እና ምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት መርጦለ ማርያም ከተማን ተቆጣጠሩ! ​ከቴዎድሮስ ዕዝ እና ከምኒልክ ዕዝ የተውጣጡ የ105ኛ ኮር ስር የሚገኙ የ45ኛ እና የ29ኛ ክፍለ ጦር አሃዶች በምስራቅ ጎጃም ዞን በኩል መርጦለ ማርያም ከተማን ጨምሮ አካባቢው ላይ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን በመቆጣጠር ላይ ይገኛሉ:: በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የብፅግናው የሰራዊት አባላት ሰፍረውባቸው በነበሩት፣በእነብሴ ሳር ምድር ፣በወሪያ መስቀል እና በሰኞ ከተማ አካባቢዎች ምንም ዓይነት የተኩስ ልውውጥ ሳይደረግ፣ በደረሰባቸው ከፍተኛ ስጋትና ድንጋጤ ምክንያት የያዙትን ወታደራዊ ቁሳቁስና ንብረት እየጣሉ አካባቢውን ለፋኖ ለቀው ወጥተዋል። ​በተጋድሎው በሁለቱ የአፋብን ዕዝ አሃዶች መርጦለ ማርያም ከተማን መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን የቡድን መሳሪያን ጨምሮ በርካታ የነፍስ ወከፍ ክላሽ ከጠላት ላይ ተማርኳል:: ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን! ​©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

#ሰበር_ዜና‼️ የምኒልክ ዕዝ 101ኛ እና 102ኛ ኮር አሃዶች በጥምረት ራያ ቆቦ ላይ ታላቅ ድል አስመዘገቡ‼️ የምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር እና 102ኛ ኮር አሃዶች በጥምረት ራያ ቆቦ ላይ ዛሬ ሚያዚ
#ሰበር_ዜና‼️ የምኒልክ ዕዝ 101ኛ እና 102ኛ ኮር አሃዶች በጥምረት ራያ ቆቦ ላይ ታላቅ ድል አስመዘገቡ‼️ የምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር እና 102ኛ ኮር አሃዶች በጥምረት ራያ ቆቦ ላይ ዛሬ ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት 3:00 ድረስ ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ጋር ተጋድሎ በማድረግ በርካታ የጠላት ሃይል #በመደምሰስ ራያ ቆቦ #ሮቢት_ከተማን_ሙሉ_ለሙሉ_በመቆጣጠር እንዲሁም ቀዩ ጋሪያ እና መንደፈራ ላይ ታላቅ ጀብድ በመፈፀም ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከራያ ቆቦ ዞብል ሮቢት መንደፈራ እና ቀዩ ጋሪያ አካባቢዎች በመነሳት የምኒልክ ዕዝ አሃዶች ስምሪት ላይ ባሉበት ማጥቃት ያደረገ ሲሆን የ102ኛ ኮር አሃድ የሆነችው ዙ23 ማራኪዋ 49ኛ ክፍለ ጦር ሮቢት ከተማን በማጥቃትና ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ታላቅ ድል ያስመዘገቡ ሲሆን ሌሎች የሁለቱ ኮር አሃዶች በጥምረት በተጠቀሱት ቦታዎች በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም

#የጽናታችን_ሚስጥር!!!! እኛ ጫካ የወጣነው #ተገለን_ተጨፍጭፈን ነው፤ እኛ ጫካ የወጣነው #ተገደን ሰሚ አጥተን ነው!!!!!!! የሕዝባችንን የህልውና አደጋ ጥያቄ‼️‼️❗️ 👉 ምሁራኖች ሲጠየቁ #አዋሽ_አርባ በግፍ ታሰሩ፤ 👉ሰልፍ ወጥተን አትግደሉን ስንል #ሶፍት እናቀብላቸዋለን ተባልን፤ 👉ሰው እየሞተ ነው ስንል #ሰው_እየሞተ_ዛፍ እንተክላለን ተባልን፤ የአደጉት ሀገር በቀን #200 እየሞተ ነው  ብለው የሞት ምንዛሬ አስተማሩን፤ 👉አዲስ_አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት ስንል #አዲስ_አባ የኛ ውጣልን ተባልን፤ 👉ለምን የአማራውን ቤት ይፈርሳል ስንል #ህገ_ወጥ ደሀ ነበሩ ህጋዊ ደሀ አድርገናቸዋል ተባልን፤ 👉ወለጋ ሕዝብ አለቀ ስንል #እኔ_የወለጋ_ሚኒሻ አይደለሁም ሂዱና ሕዝቡን ታደጉት ተባልን!!!!! 👉#ቤተ_እምነትና ተቃጠለ ስንል ምን ታመጣላችሁ ብለው 89 ቤተ ክርስቲያን አቃጠሉ ከ35 በላይ መስጊድ አፈረሱ፤  👉#የሀይማኖት_አባቶች ታረዱ፤ #በእሳት ተቃጠሉ፤ በጥፊ ተመቱ ኧረ የመንግስት ያለህ ስንል ይለይላችሁ ተብለን #መጅሉሱ_ና_ሲኖደሱ በዱርዬዎች ፈረሰ፤ የሀገር አባት እነ ሀጂ ሙፍቲ ተሳደዱ፤ ጳጻሳት ታሰሩ ፤ ቤተ ክርስቲያን በዲሽቃ ተደበደበች............ ኧረ ስንቱ!!!!!!!! ሀገሪቷ የዱርዬዎችና #የጋጠወጦች መነሀርያ ስትሆን  ምን መንግስት አለ ብለን ከቤታችን እንቀመጥ፤ ከቤታችን ብንቀመጥም መተው ያርዱናል❗️......... ስለዚህ ከብረት የጠነከረ!!! ከአለት የጠጠረ!!! በጠንካራ መንፈስ የተገነባ!!!  ልብና ጀግንነት አለን✅ #እናሸንፋለን!! ድል ለሕዝባችን!!! ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!! Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

#የጽናታችን_ሚስጥር!!!! እኛ ጫካ የወጣነው #ተገለን_ተጨፍጭፈን ነው፤ እኛ ጫካ የወጣነው #ተገደን ሰሚ አጥተን ነው!!!!!!! የሕዝባችንን የህልውና አደጋ ጥያቄ‼️‼️❗️ 👉 ምሁራኖች ሲጠየቁ #
#የጽናታችን_ሚስጥር!!!! እኛ ጫካ የወጣነው #ተገለን_ተጨፍጭፈን ነው፤ እኛ ጫካ የወጣነው #ተገደን ሰሚ አጥተን ነው!!!!!!! የሕዝባችንን የህልውና አደጋ ጥያቄ‼️‼️❗️ 👉 ምሁራኖች ሲጠየቁ #አዋሽ_አርባ በግፍ ታሰሩ፤ 👉ሰልፍ ወጥተን አትግደሉን ስንል #ሶፍት እናቀብላቸዋለን ተባልን፤ 👉ሰው እየሞተ ነው ስንል #ሰው_እየሞተ_ዛፍ እንተክላለን ተባልን፤ የአደጉት ሀገር በቀን #200 እየሞተ ነው ብለው የሞት ምንዛሬ አስተማሩን፤ 👉አዲስ_አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት ስንል #አዲስ_አባ የኛ ውጣልን ተባልን፤ 👉ለምን የአማራውን ቤት ይፈርሳል ስንል #ህገ_ወጥ ደሀ ነበሩ ህጋዊ ደሀ አድርገናቸዋል ተባልን፤ 👉ወለጋ ሕዝብ አለቀ ስንል #እኔ_የወለጋ_ሚኒሻ አይደለሁም ሂዱና ሕዝቡን ታደጉት ተባልን!!!!! 👉#ቤተ_እምነትና ተቃጠለ ስንል ምን ታመጣላችሁ ብለው 89 ቤተ ክርስቲያን አቃጠሉ ከ35 በላይ መስጊድ አፈረሱ፤ 👉#የሀይማኖት_አባቶች ታረዱ፤ #በእሳት ተቃጠሉ፤ በጥፊ ተመቱ ኧረ የመንግስት ያለህ ስንል ይለይላችሁ ተብለን #መጅሉሱ_ና_ሲኖደሱ በዱርዬዎች ፈረሰ፤ የሀገር አባት እነ ሀጂ ሙፍቲ ተሳደዱ፤ ጳጻሳት ታሰሩ ፤ ቤተ ክርስቲያን በዲሽቃ ተደበደበች............ ኧረ ስንቱ!!!!!!!! ሀገሪቷ የዱርዬዎችና #የጋጠወጦች መነሀርያ ስትሆን ምን መንግስት አለ ብለን ከቤታችን እንቀመጥ፤ ከቤታችን ብንቀመጥም መተው ያርዱናል❗️......... ስለዚህ ከብረት የጠነከረ!!! ከአለት የጠጠረ!!! በጠንካራ መንፈስ የተገነባ!!! ልብና ጀግንነት አለን✅ #እናሸንፋለን!! ድል ለሕዝባችን!!! ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!! Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር

የአፋብን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር - መከታው ማሞ ! አለ ነገር ዘንድሮ ሸር ጆይን  አድርጉማ ችግሩ አታደርጉማ የአማራ ልጅ  በሚገርም ጥበብ ኢትዮጵያ ሊረከብና ሊያስደሰተን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል አላችሁን!!! የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአፋብን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር - መከታው ማሞ ! አለ ነገር ዘንድሮ ሸር ጆይን አድርጉማ ችግሩ አታደርጉማ የአማራ ልጅ በሚገርም ጥበብ ኢትዮጵያ ሊረከብና ሊያስደሰተን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል አላችሁን!!!

ባህርዳር ጣና ዳር ሕዝባዊ ንቅናቄው እንደቀጠለ ነው። ሕዝባችንን በፖለቲካ መር የትጥቅ ትግል ከህልውና ስጋት ነፃ እናወጣለን። (የ22ኛ ክፍለ ጦር ጊዜያዊ መንግስት መምሪያ ኃላፊ)
ባህርዳር ጣና ዳር ሕዝባዊ ንቅናቄው እንደቀጠለ ነው። ሕዝባችንን በፖለቲካ መር የትጥቅ ትግል ከህልውና ስጋት ነፃ እናወጣለን። (የ22ኛ ክፍለ ጦር ጊዜያዊ መንግስት መምሪያ ኃላፊ)

ከ270 በላይ ዜጎች በአማራ ማንነታቸው ታፍነው በግፍ እስር ላይ ሆነው ግፍና መከራ እየተፈፀመባቸው ነው! የአብይ አህመድ የአገዛዝ ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን ሁለንተናዊ ጦርነት ተከትሎ፡ በማንነታቸው ብቻ ተለይተው የታፈኑና የፍትህ ያለህ በማለት ላይ የሚገኙ ከ270 በላይ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ግፍና መከራ እየተፈፀመባቸው ነው። አገዛዙ የምርጫ ድራማ ለመተወን እየተዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት፡ በቂሊንጦ፣ በአባ ሳሙኤል፣ በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታሳሪዎች አሁንም በጨለማ ክፍል ውስጥ ለግፍ እንደተዳረጉ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙት ዜጎች ስብጥር አገዛዙ የአማራ ምሁራንን፣ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ አመራሮችን ኢላማ ያደረገ የማዳከም ስልት እየተከተለ መሆኑን ያሳያል። የእስረኞቹ ዝርዝር እንደሚያሳየው የታሰሩት ግለሰቦች የህብረተሰቡ የጀርባ አጥንት የሆኑ የሙያ ዘርፎችን ያቀፉ ናቸው። እነርሱም፦ 16 የሚሆኑ ዶክተሮችና ረዳት ፕሮፌሰሮች (ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ ረ/ፕሮፌሰር ዳኜ አበበ እና ዶ/ር ጫኔ ከበደ ይገኙበታል)። 8 ጋዜጠኞችና ደራሲያን (ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማውና ታዲዎስ ታንቱ ይገኙበታል)። እነ ክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለውን ጨምሮ 5 ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች። 7 መሪጌታዎችና ዲያቆናት እንዲሁም ጠበቆች። 4 ከፍተኛ መኮንኖችና ኢንስፔክተሮች። እስረኞቹ በተለያዩ የማጎሪያ ስፍራዎች ተከፋፍለው የሚገኙ ሲሆን፣ አሃዙም እንደሚከተለው ሰፍሯል፦ 1. ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፦** 154 እስረኞች 2.አባ ሳሙኤል (ከፍተኛ ጥበቃ)፦** 98 እስረኞች 3. ቃሊቲ ማረሚያ ቤት (ሴቶች)፦ 9 እስረኞች (መሰረታዊ መብታቸው ተገፎ የሚገኙ) 4. ዝዋይ ማረሚያ ቤት፦ 9 እስረኞች 5. በተጨማሪ፦ ከኢቢኤስ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በሽብር የተከሰሱ 9 ዜጎች። አገዛዙ "የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል" በሚል መርህ ሆነ ብሎ የፍርድ ሂደቱን በማጓተት እስረኞቹን ለከፍተኛ ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ጉዳት እየዳረገ ይገኛል። የኢትዮጵያ ህዝብና የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለእነዚህ ድምፅ አልባ ለተደረጉ ዜጎች ድምፅ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

እነብሴ ሳርምድር ወረዳ ድቦ ከተማ እና እናርጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገ ብርሀን ከተማ አብነ አይብ ድረስ ታሪክ ተሰርቷል። ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። . ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም አፋብን ቴወድሮሰ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ስር የምትገኘው 1ኛ ሬጅመንት እነብሴ ሳርምድር ወረዳ ድቦ ከተማን በማስለቀቅ ዶማ ከተማ ድረስ በማሯሯጥ በተደረገው አውደ ውጊያ ከአስራ አምስት በላይ ሚሊሻ እና አድማ በትን በመግደል ጠላት ወደ መርጡለማርያም ፈርጥጦ እንዲገባ ሆኗል። በዛሬው አውደ ውጊያ የተገኙ ምርኮወች ➺.ክላሽ = 6 ➺.አብራረው= 1 ➺.የብሬን አፈሙዝ= 1 ➺የእርድ ፍየል=2 እንዳሁም በዚሁ ወረዳ አቡነ አይብ በሚባል ንዑስ ከተማ 5ኛ ሬጅመት ለሰዓታት የቆየ ውጊያ በማድረግ ለአመታት ተይዞ የነበረውን የቁም ምሽግ በመስበር ከቤተ ክረሰስቲያን ወጥቶ እንዳፈረጥጥ ተደርጓል። በዛሬው አውደ ውጊያ ከሞቱት መካከልም... 1.ሞኝነት አያሌው ............ሚሊሻ 2.ደምሰው ..........ሚሊሻ 3.ኢ/ር እሸቴ........ ፖሊስ ኃላፊ 4.ቻሌ ተፈራ............ ፖሊስ 5.እዋወይ ደነቀው ...ከባድ ቁስለኛ ሚሊሻ ሲሆን በሌላ በኩል የክፍለጦሩ ጥምር ጦር በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገብርሐን ከተማ መሽጎ ከነበረው የአብይ መከላከያ እና ሚሊሻ ላይ ከሌሊቱ 11:ዐዐ እስከ ጠዋቱ 2:30 ድረስ በነበረው አውደ ውጊያ የአብይን ሰራዊት ከመሸገበት ቦታ ላይ በተጠና መንገድ ተኩስ በመክፈት ራሱ ምሽግ ላይ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ቅስሙን መስበር ተችሏል። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት