fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 456
مشترکین
+824 ساعت
+657 روز
+91030 روز
آرشیو پست ها
ሰበር ዜና! 5ተኛ ቀኑን የያዘው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በታላቅ ድል ታጅቦ እንደቀጠለ ነው። ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና መብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አሃድ ጋር በመቀናጀት ትናንት ለዛሬ ሌሊት በመካነሰላም ግንባር የጠላትን ኃይል በመደምሰስ፣ በማቁሰል፣ በመበተን እና በመማረክ ከጥቅም ውጭ አድርገው መካነሰላም ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውለዋል:: በኦፕሬሽኑ የአድማ ብተና 23ተኛ ክፍለ ጦር በርካታ ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅ/ቤት አመራር የሆነው አቶ ሰይድ አብዬን ጨምሮ ሌሎች ባንዳዎች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል:: በድምሩ ከ45 ያላነሰ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል:: ውጊያው ሲጀመር ራሱን ለመከላከል አስቦ በአየር ማረፊያ፣ በለገአማራ ወንዝ እና በከተማይቱ መሀል በቡድን መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው ጠላት የጀግኖችን ክንድ ቀምሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል:: መካነሰላም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቦረና ማረሚያ ቤትን በመክበብ ፋኖ ባደረገው ትንቅንቅ በርካታ እስረኞችን ማስለቀቅም ተችሏል:: በዚሁ በመካነሰላም ግንባር ከትናንትት በስቲያ የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ ኮሎኔል ሀብታሙ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች 3 ባንዳዎችን መማረኩም ይታወሳል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 18/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ሰበር ዜና! 5ተኛ ቀኑን የያዘው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በታላቅ ድል ታጅቦ እንደቀጠለ ነው። ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና መብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አሃድ ጋር በመቀናጀት ትናንት ለዛሬ ሌሊት በመካነሰላም ግንባር የጠላትን ኃይል በመደምሰስ፣ በማቁሰል፣ በመበተን እና በመማረክ ከጥቅም ውጭ አድርገው መካነሰላም ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውለዋል:: በኦፕሬሽኑ የአድማ ብተና 23ተኛ ክፍለ ጦር በርካታ ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅ/ቤት አመራር የሆነው አቶ ሰይድ አብዬን ጨምሮ ሌሎች ባንዳዎች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል:: በድምሩ ከ45 ያላነሰ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል:: ውጊያው ሲጀመር ራሱን ለመከላከል አስቦ በአየር ማረፊያ፣ በለገአማራ ወንዝ እና በከተማይቱ መሀል በቡድን መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው ጠላት የጀግኖችን ክንድ ቀምሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል:: መካነሰላም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቦረና ማረሚያ ቤትን በመክበብ ፋኖ ባደረገው ትንቅንቅ በርካታ እስረኞችን ማስለቀቅም ተችሏል:: በዚሁ በመካነሰላም ግንባር ከትናንትት በስቲያ የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ ኮሎኔል ሀብታሙ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች 3 ባንዳዎችን መማረኩም ይታወሳል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 18/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

‎      ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ ‎ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክ/ጦር ከመዝገበ ጮቄ ብርጌድ የሻለቃ አመራሮችና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት ጥልቅ የሆነ ውይይትና ግምገማ አካሄደ። ‎ ‎ከ2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር አመራሮች ማለትም፦ ‎ 1ኛ ፲/አ ደርሳችሁ አትንኩት - የክፍለጦሩ አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ ‎2ኛ አርበኛ አንዳርጌ ዘገየ - የክፍለጦሩ ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ ኃላፊ ‎3ኛ ፲/አ ታፈረ - የክፍለጦሩ የሰው ኃይል መምሪያ ኃላፊ በተገኙበት እስከ አሁን የነበሩ መቀጠል ያለባቸው ጥንካራ ጎኖች ለማስቀጠልና የነበሩ ደካማ ጎኖችን ነቅሶ በማውጣት ወደ ፊት ለማስተካከል መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል ። ብርጌዱ ላይ የጎደሉ አመራሮች ላይ ምደባ በአደረጃጀቱ በኩል ሟሟላት ተችሏል። ‎ ‎በተመሳሳይ ለሻለቃና ለብርጌድ አመራሮች ስልጠና መስጠት ተችሏል። ‎        ➳ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ‎        ➳ መሪነት በሚሉ ሰነዶች ላይ አንድ አይነት እይታ እንዲኖርና የሚመራውን ጦር በአግባቡ እንዲመራ የሚያስችል ስልጠና ከክፍለ ጦር በመጡ አመራሮች ስለጠና ተሰጥቶ ውይይትና አስተያየት ተሰጥቶባቸው በመርህ የታገዘና ወጥ የሆነ ስራ ለመስራት በመግባባት ስልጠናው ተጠናቋል። ‎ ‎ድል ለአማራ ፋኖ‼️ ‎ክብር በጀግንነት ለተሰው ሰማዕታት‼️ ‎ ‎ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ‎ 2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክ/ጦር ‎ከመዝገበ ጮቄ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ‎     ፋኖ መንግስቱ ታረቀኝ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የዛሬ ነው ጎበዜ እየገቡ ነው! ወሎ ይችላል
የዛሬ ነው ጎበዜ እየገቡ ነው! ወሎ ይችላል

"የአንድ መከረኛ ህዝብ ልጆች ነን" ይሔ የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት ብዙ ልዩነቶችን አቀራርቧል፣የተኳረፉትን አነጋግሯል የተራራቁትን አቀራርቧል ከመሪያችን ታሪካዊ መልዕክት በኋላ የአፋብኃ ድርጅታዊ ጉዳይ በመልካም እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል በርካታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ድሎችም እየተመዘገቡ ይገኛል። የአማራ ህዝብ መሪ ማብቃትና ማውጣት ይጠበቅበታል ለህዝብና ለትግሉ በፅናት ለማቆም ሁሉም የሚሰባሰብበት አንድ ድርጅት የሚተማመንበት አንድ መሪ ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን እነዚህን ወሳኝ የትግሉ መሰረታዊ ግቦችን ለማሳካት ደግሞ ድርጅታዊ ልዩነቶች ተቀርፈው ወደ አንድ አማራዊ ግዙፍ ተቋም ሲቀየሩ እንደሆነ እንገነዘባለን ።ህዝቡም ሰራዊቱም በጉጉት የሚጠብቀው ይሔ ሁኖ ሳለ ወደ ወገን የሚሳቡ ምላጮች ፣ወደ ወንድም የሚከፈቱ ቃታዎች የሰነቅነውን ተስፋ እንደ ጉም የሚያተን ነው። "የአንድ መከረኛ ህዝብ ልጆች ነን" ትግላችን ለአማራነትና ለአማራ ህዝብ ከሆነ ያሉንን ልዩነቶች ማቻቻል ፣ መደጋገፍና መጠባበቅ ይጠበቅብናል ጊዜው በሚመጥነው ልክ ቁመን ኃይላችንን ወደ ጠላት መሰንዘር ይጠበቅብናል ወንድም በወንድሙ ላይ አይነሳ ይሔ የትግላችን ጥቁር ታሪክ ይቁም ዛሬን እንታገስ ነገ ከዛሬው የበረታ ነው እና በህብረት እንቁም የትናቱንም የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት መሸጋገሪያ ድልድይ አድርገን እንራመድ ።  የአባት አርበኞች ሚና በዚህ ወቅት ነው እና አደራችሁን ትወጡ ዘንድ ከእናተ ብዙ እንጠብቃለን። ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም አንድ አማራ !እስከ ምጽአት አማራ!

የ12ተኛ ክፍለጦር 4ተኛ ሻለቃ አመራሮች ጦሩ አልቆ ሲሸሹ በምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር 3ተኛ ሻለቃ ማርካቸዋለች!
የ12ተኛ ክፍለጦር 4ተኛ ሻለቃ አመራሮች ጦሩ አልቆ ሲሸሹ በምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር 3ተኛ ሻለቃ ማርካቸዋለች!

የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች አስቸኳይ የሆነ የቤት ስራ ተሰጥቷቸው እንቅስቃሴ ጀምረዋል። 1. ፋኖ በድሮን እንዳለቀና እንደተሸነፈ ሁሉንም ካድሬና ደጋፊ ሰብስበው እንዲያሳምኑ 2. በተቻለ አቅም ሕዝቡን
የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች አስቸኳይ የሆነ የቤት ስራ ተሰጥቷቸው እንቅስቃሴ ጀምረዋል። 1. ፋኖ በድሮን እንዳለቀና እንደተሸነፈ ሁሉንም ካድሬና ደጋፊ ሰብስበው እንዲያሳምኑ 2. በተቻለ አቅም ሕዝቡን ሰብስቦ የኤርትራና የሕወሓት ሠራዊት በፋኖ እየተመራ አማራ ክልልን የጦርነት ቀጠና እያደረገ እንደሚገኝ የፈጠራ ወሬ እንዲያወሩ 3. በቴክኖሎጂ የተሻ እውቀት ያላቸው ካድሬዎች ማንኛውንም ምስልና ቪዲዮ በመጠቀም ሶሻል ሚዲያው ላይ ፕሮፓጋንዳ በመስራት ንቁ ሆኖ እንዲሳተፉ 4. ወቅታዊውን የፋኖ አቋምና እቅድ ማወቅ ስላልተቻለ አዲስ የመረጃ አባላትን በማሠባጠር መረጃ እንዲሠበስቡ ማድረግ 5. ዋና ዋና የብልፅግና አመራሮች ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል በየከተማው እንዲዞሩ...የሚል መመሪያ መጥቶ ወደ ስራ ተገብቷል። (ለምሳሌ ትላንት ከሰዓት በሗላ በግምት ከ 1:00/1:15 ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ የቆቦ አመራሮች ሲዞሩ ነበር።) እነ ናትናኤል መኮነን እና ሌሎች የብልፅግና ልሳናት በሰፊው ከላይ የተጠቀሱ ነጥቦችን እንዲያራግቡ ታዝዘዋል።

ዶሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ በወንድሞቻችን ላይ በወሰዱት እርምጃዎች ሁላችንም አዝነናል
ዶሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ በወንድሞቻችን ላይ በወሰዱት እርምጃዎች ሁላችንም አዝነናል

#የድል_ዜና‼️ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ጀብደኛዋ የሰሜን ብርቅየ ክፍለጦር በቀን 17/1/2018 ዓ.ም በሰሜናዊ ጎንደር ዞን በጠለምት ወረዳ በተ
#የድል_ዜና‼️ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ጀብደኛዋ የሰሜን ብርቅየ ክፍለጦር በቀን 17/1/2018 ዓ.ም በሰሜናዊ ጎንደር ዞን በጠለምት ወረዳ በተል በተባለ ቀበሌ ከአገዛዙን ሰላም አስከባሪ እና ሚኒሻ ጋር በተደረገ ውጊያ ውጊያውን በድል በማጠናቀቅ  ከ50በላይ ሙት እና ከ35በላይ ቁስለኛ በማድረግ ከ50 በላይ የነብስ ወከፍ መሳሪያ መማረካቸው ታውቋል !! የክፍለጦሩ ቀጠና የኔትወርክ ችግር በመኖሩ መረጃውን ያደረሰን ጓዳቸው የ4ኛ ደጃዝማች ኮር የረመጡ ደጀን ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው አርበኛ መምህር አስፋው አደራጀው ነው። ድል ለአማራ ፋኖ 18/ዐ1/2018 ዓ.ም

የተከበራችሁ በውጭም በውስጥም የምትገኙ የኅልውና ትግላችን ደጋፊዎች የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል፣ ምኒሊክ እዝ እየፈጸመ የሚገኘውን የአርበኝነታችን ደማቅ አሻራ በሆነው ጀብድ በጎ ቅናት ተነሳስቶ ጠላት ላይ የተባበረ ክንድን ማሳረፍ ሲገባ ክረምቱን ጎንደር ላይ የገባውን ጨፍጫፊ ሠራዊት መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶ የከረመውንና አሁንም ጠላትን ማእከል ያደረጉና የታቀዱ ውጊያዎችን ለማድረግ በሚንቀሳቀሰው የተቋማችን አንደኛው (በላይ ዘለቀ) እዝ ላይ የተደረገው በርካታ ቀናትን የዘለቀውና ለአንድነት ሲባል በሆደ ሰፊነት የታለፈው ነገር ግን በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ የትኛውም አካል የጠላት ኃይል ላይ በሚረባረብበት ወቅት እንዲህ ያለው ከጠላት ጋር የተናበበ ጥቃት የአጋጣሚ ሳይሆን የታቀደና የታሰበበት ስለመሆኑ የትንኮሳዎቹና የጥቃቶቹ ተከታታይነት ምስክር ናቸው። ይህን እኩይ ድርጊት ከጅምሩ እስከ አፈጻጸሙ በንሥር ዓይን ሲከታተሉ የቆዮት የጠቅላይ ግዛት እዙ የክፍለ ጦርና የብርጌድ አመራሮች ሃሳቡንና ድርጊቱን ጭምር እየኮነኑ በላይ ዘለቀ እዝን በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ። በዚሁ አጋጣሚ ቀሪ ውስን ወንድሞቻችንም ቀጠናው ላይ ያልወን ትግል ከፍ ማድረግ የሚቻለው ከመጓትትና ከመጠላለፍ ወጥታችሁ ወደ ወንድሞቻችሁ ትቀላቀሉ ዘንድ ድርጅታችን አፋብኃ ጓዳዊ ጥሪውን ያቀርባል። በአጠቃለይ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) እንደ ተቋም በተፈጠሩብን ጎታች ድርጊቶች እጅጉን ከማዘን ባሻገር እንደዚህ ያለውን እኩይ ሴራ የሚያስተባብሩና የሚመሩ በቀጠናው የሚገኙ አመራሮች መሆናቸውን በውል ተገንዝቧል። የተቋማችን ምኒሊክ እዝ ጠላትን እያፈረሰ ባለበት በዚህ ሰአት የአፋሕድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ደግሞ ለተመሳሳይ ተልእኮ ግዳጅ የተሰጠውን በላይ ዘለቀ እዝን ከተልእኮው ለማዘገየትና ለማናጠብ ያደረገው ጥረት ለጠላት ከማበርና ከመተባበር ውጭ ሌላ ምክንያት ሊኖረው አይችልም። ስለሆነም መላው ሕዝባችንና በኅልውና ትግሉ ውስጥ የሚገኘው ታጋይ እንዲገነዘብ የምንፈልገው የተጓዝንባቸው የአንድነት መንገዶች፣ የመከርንባቸው የአንድ እንሁን ምከረ ሃሳቦች እንቅፋቱ ማን እንደሆነ ብዙ ምስክር ማቅረብ አያስፈልግም፣ በወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋና ተከታታይነት ያላቸው ትንኮሳዎችና ጥቃቶች ኅያው ምስክሮች ናቸው። አሳዛኙ የሴራ ድር እንደሚያሳየው ከወለላ ባህር፣ ከጋይንት፣ ከክምር ድንጋይ፣ ከአጊሳና ከእብናት የተውጣጡ ውስን ወንድሞች “ለኬላ ሥራ ነው እምንሄድ” በሚል ማጭበርበሪያ ወንድሞቻቸውን እንዲወጉ የታዘዙት እውነትን የሚሹ አማራ ጓዶቻችን አፈሙዜን ወንድሞቼ ላይ ሳይሆን እንዲህ ያለው እኩይ ሴራ ላይ የማገዳችሁኝን እናንተን እፋለማለሁ በሚል ሠራዊቱ ከእውነትና ከወንድሞቹ ጋር በይፋ መቀላቀሉን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከምንም በላይ አንድ ጉዳይ፣ አንድ ዓላማ ይዘን ነገር ግን የሴራ ገመድ በሚሸርቡ አካላት ትግላችንን ከመጎተት ተላቀን አንድ እንድንሆን ለአንድነት የከፈልነውን ዋጋ አጠናክረን እንደምንቀጥል እየገለጽን ትግላችንን ለመበተን የሚሠሩ አካላትን አሽቀንጥረን ጥለን አንድ እንድንሆን ለአንድነት ውድ ሕይወታቸውን በከፈሉ ሰማዕታት ስም ጥሪያችንን ማቅረብ እንፈልጋለን።  ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) 18/ዐ1/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ: ቀን፦ መስከረም 18/2018 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የተሰጠ መግለጫ “ባለጌ ያለበት ሸንጎ፣ ዝንብ ያረበበበት እርጎ” ይላል አማራው በትውፊቱ/// አማራነት ማሞኛና ማጃጃያ አይደለም፣ አማራነት ነገረ ሰሪነት አይደለም፣ አማራነት በእብሪት ወንድም ላይ መቆመሪያ አይደለም፣ አማራነት የውጭ አልጋነት የውስጥ ቀጋነት አይደለም፣ አማራነት እኔነትና ጸረ ሕዝብነትም አይደለም። ቅሉ አማራነት የሕዝባችን የማይናወጽ ከልደት እስከሞት የሚኖርበት፣ የሚመራበት ሕጉ፣ ሥርዓቱ፣ እሴቱ፣ ባህሉ፣ ሃይማኖቱ፣ ታሪኩ፣ ጀግንነቱ፣ ጥበቡ፣ እውቀቱ፣ ፍልስፍናውና መሰል ድርብርብ መገለጫዎችን እንደ ነፍስና ስጋ አዋሕዶ የያዘ እሳቤ ነው። በዚህም አማራው አማራነቱን ቅን፣ ገር ኅሊና ላላቸው አካላት ሁሉ ያለንፍገት ሲያድል አማራ ሆነው ከአማራነት የነጠፉ አላዋቂዎች፣ ሆዳሞች፣ ባንዳዎች አማራውንና አማራነትን የበደሉትን ያህል የበደለ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ምክንያቱም ጸረ አማራ ኃይሎች ሕዝባችንን ለማጥፋት የሚጠቀሙት እንደነዚህ ያሉትን ጠማማ እጀታዎች ነውና። አማራ ሆነው ከአማራነት ጥልቅ እሳቤ ያልተጸነሱና ከአማራነት ሰፊ ውቅያኖስ ያልተቀዱ አካላት ሆድ እንጅ አዕምሮ የላቸውም፣ የሚጮኹበት አፍ እንጅ የሚያዳምጡበት ጆሮ የላቸውም፣ ደረቅ ንግግር እንጅ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አመክንዮ የላቸውም። እነዚህ አካላት ከትናንት የአርበኝነት ታሪካችን እስከ ዛሬው የኅልውና ትግላችን ብቻ ሳይሆን እስከ ዓለም ፍጻሜ በባንዳነት፣ በሆዳምነት፣ በድንቁርና፣ በሴራ፣ በአስመሳይነት የሚኖሩ የትውልድና የታሪክ አራሙቻዎች ናቸው። በኅልውና ትግላችን ላይ የሚያላግጡ፣ የሚያሴሩ፣ በተላላኪነት የሚሠሩ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊስ፣ ካድሬና የመከላከያ ወታደራዊ መኮንን አማራዎች መኖራቸው ዓለም ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። በግልጽ አማራነትን ከሚታገሉት አማራዎች ባሻገር ለአማራነት ለመታገል ወጥቶ የኅልውና ትግላችንን ለማቀንጨር የሚታትሩ፣ በወደረኛነት ከተገለጠው ጠላት ጋር የሚናበቡ አካላት መኖራቸውን ስንመለከት ውስጣችን በጽኑ ይደማል። ሕዝባችንም ሠራዊታችንም እውነተኛ አንድነትን አጥብቆ በሚጠብቅበት ወቅት በሚዲያ የአንድነት ጉባኤ እያከናወኑ ከጀርባ ወንድም ላይ ጦር እያዘመቱ ሲወጉን ለአንድነት ስንል ዝም ጭጭ ብለን ታግሰናል። ጉዳዩ በየእለቱ መልኩን እየቀየረና ፍጹም አውዳሚ አካሄድን በተከተለና ከጠላትም ጋር በተናበበ መልኩ ጥቃቶች ተጠናክረው ቀጠሉ። ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የአንድነት መደላድሎችን ለመፍጠር ቅድመ አንድነት ንግግር በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” ሆኖባቸው የተቋማችን አንደኛው አሓድ በላይ ዘለቀ እዝ ላይ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በሚል የሚንቀሳቀሱ አመራሮች በሰጡት ስምሪት በሚከተለው መልኩ የተቀናጀ ትንኮሳና ጦርነት ከፍተውብናል። 1. የበላይ ዘለቀ እዝ፣ መይሰው ካሳ (፪ኛ) ኮር፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት ቤተሰቦች ላይ ከነሃሴ 20/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 07/2018 ዓ.ም ድረስ በቁጥር ከ32 በላይ አባዎራዎችን አስረው ልጆቻችሁ ወደእኛ እንዲገቡ አድርጉ በሚል ጫና ይህንን ትእዛዝ አልፈጽምላቸው ሲሉ እያንዳንዱን አባወራ ሰውነቱ እስኪቆስል ገርፈው ከ200,000 እስከ 500,000 ብር አስከፍለው ለቀዋቸዋል።  2. በተራ ቁጥር “1” ላይ ከተገለጸው አስነዋሪ ድርጊት ይታቀባሉ በሚል ተስፍ የአንድነት መንገዳችን ላይ እንቅፋት እንዳይፈጥር በሚል አፍነን በውስጥ ለመፍታት ያደረግነው ጥረት ካለመሳካቱም ባሻገር መስከረም 08/2018 ዓ.ም የበላይ ዘለቀ እዝ፣ ዳግማዊ ቴወድሮስ (፭ኛ) ኮር፣ ዞዝ አምባ ንጉሥ ክፍለ ጦር የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊውን ጨምሮ ሦስት ጓዶቻችንን እብናት፣ መልዛ ከተማ ላይ በእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦርና የጠቅላይ ግዛቱ ከፍተኛ አመራሮች እጅ በቀጥታ ተረሸኑብን። 3. በተራ ቁጥር “2” የተፈጸመው አስነዋሪ ድርጊት ጉዳዩ መስመር እያለፈ መሆኑን በውል የተረዳንበት ቢሆንም አፋሕድ መስከረም 10 እና 11/2018 ዓ.ም የአንድነት ጉባኤ በበይነ መረብ የሚያደርግበት ወቅት በመሆኑና በሆደ ሰፊነት የአንድነት በራችንን እንዳይዘጋብን በማሰብ የተፈጠረውን አንጀት የሚቆርጥ ድርጊት ታግሰን በውስጥ ለመመካከር እድል ሰጥተን ረዥምና አድካሚውን መንገድ ተጓዝን። እንደ ድርጅትም ጥያቄዎችን በውስጥ አቅርበን እንደሚታረም ተነግሮን ለማሳለፍ ሞከርን። 4. ከዚህ በኋላ የጠቅላይ ግዛቱ አመራር በሆነ ግለሰብ አማካይነት ከሚካኤል ድብር እስከ ጎንደር ያለውን ሌባ እናጸዳለን የሚል ማብራሪያ በጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን ተሰጠ። ሌባ እናጸዳለን በሚል ሰበበ ምክንያት የተቋማችን አፋብኃ፣ በላይ ዘለቀ እዝ፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር አባላት ላይ እንዲሁም መስከረም 10 እና 11/2018 ዓ.ም በአጼ እያሱ ክፍለ ጦር ሠራዊት ላይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ትንኮሳና ጦርነት ከፈቱ። ይህ አስጸያፊ ነውር የተፈጸመው ደግሞ አፋሕድ በበይነ መረብ የአማራ አንድነት ጉባኤውን እያደረገ በሚገኝበት እለት መሆኑ ሲታሰብ የአንድነት ሃገሩ ወዴት ነው? አንድነትስ ምንድነው? አንድ መሆንስ ከማን ጋር ነው? ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። አንድነት ቀይ መስመራችን ነው፣ አንድነቱን ከሞላ ጎደል ጨርሰናል የሚቀረን መሬት ላይ ካለው ኃይል ጋር ነው የሚሉ የሚዲያ ዲስኩሮች አንድ መሆንን የጨረሱት ከማን ጋር ነው? የሚል ተጠየቅ ስናነሳ ምላሹ ማጣፊያ የሚያጥረው ጉዳይ ይሆናል። 5. ሌላው አንድነት ፈላጊነታችንን፣ በፍጹም ወንድማዊና አማራዊ በውስጥ የእንፍታው ልምምጣችንን እንደ ጅል ቆጥረው ጉዳዩን ከመደበኛ ጠላት ጋር በተቀናጀ መንገድ ከመስከረም 13 ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በድርጅታችን አፋብኃ፣ በላይ ዘለቀ እዝ መይሰው ካሳ (፪ኛ) እና ዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር ላይ ትንኮሳዎችና ጥቃቶች ቀጥለው ይገኛሉ። ከምንም በላይ ደግሞ መስከረም 15 እና መስከረም 16/2018 ዓ.ም በዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር፣ ታድሎ ብርሐን ክፍለ ጦርና ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ወንድሞቻችን ላይ የተቃጣው የመከላከያና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ የሴራ ጠንሳሽ መንገድ መሪ አመራሮች ቅንጅት ጥቃት ታሪክ ይቅር የማይለው ክህደት ነው። 6. ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ቦታዎች የታችኛው የሠራዊቱ አመራሮችና የሠራዊት አባላት አንድ መሆንን አጥብቆ ሲጠይቃቸው በአንድ በኩል አንድነቱን ጨርሰናል፣ አመራሮችንም ሰይመናል፣ በቅርቡ በሚዲያ እናሳውቃለን፣ እስከዚያው ግን ጥቂት ጠብቁን የሚሉ ማጭበርበሪያዎችንና ማደናገሪያ ሃሳቦችን የሚሰጡ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ለእኩይ ሥራቸው ቀረብ ያሉትን ወንድሞች አንድ እንዳንሆን እያደረጉን የሚገኙት የአፋብኃ አመራሮች ስለሆኑ ሠራዊታቸውን ማፍረስ አለብን የሚሉ ጸረ አንድነት መርዛማ ሃሳቦችን በመርጨት ከኅልውና ትግላችንም ከአንድነትም ሊያዘገዩን ከኋላ ሆነው የመጎተት ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ።

#የጠላት_እንቅስቃሴ‼️ አሁን ከቀኑ 7:47 ከወደ ኩታበር የአገዛዙ ሰራዊት ዙ23 ይዞ ከአንድ ፓትሮል ጋር ወደ ኮምቦልቻ ወጣ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል። ሼርርርር ይደረግ 18/ዐ1/2018 ዓ.ም

🔥#ቴዎድሮስ_ዕዝ_ወንበርማ_ብርጌድ ‼️ የሻለቃ ዓባይን ደም ሳምንት ሳይሞላው ደምላሾች። ዛሬ በጥዋቱ ሸንዲ ከተማ ሰርገው በመግባት መልካሙ ፈረደ የሚባለውን አይጥቦ አይለብሰ ሚሊሻ አንቀው አውጥተው
🔥#ቴዎድሮስ_ዕዝ_ወንበርማ_ብርጌድ ‼️ የሻለቃ ዓባይን ደም ሳምንት ሳይሞላው ደምላሾች። ዛሬ በጥዋቱ ሸንዲ ከተማ ሰርገው በመግባት መልካሙ ፈረደ የሚባለውን አይጥቦ አይለብሰ ሚሊሻ አንቀው አውጥተው በአደባባይ ደሙን መልሰዋል 💪 ይቀጥላል ....‼️ 18/ዐ1/2018 ዓ.ም

ዘመቻ_አርበኛ_አደም_አሊ (አባ ናደው) የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከህልውና ትግሉ ጎን ለጎን ነፃ በወጡ ቀጠናዎች ህዝባዊ ዉይይቶችና የህዝብ አስተዳደር መዋቅር መዘርጋት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል!     መስከረም 18/2018 ዓ/ም ፋኖ ነፃ ባወጣቸው አካባቢዎች ጊዜያዊ ወታደራዊ ሲቪል መዋቅር እየተዋቀረ እና ህዝቡ በመረጠው እየተዳደረ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ላስታ ወረዳ አንዱ ነው። የላስታ ወረዳ ጊዜያዊ ወታደራዊ ሲቪል መዋቅር አስተዳዳሪ የሆኑት ፲አ/ አርበኛ ነጋ ፈንቴ የአቡነ ዮሴፍ፣የእንጃፋት፣ጠልፈጢት፣ወደብየና ታዲዮስ አምባ ቀበሌ ህዝብ፣ከሐይማኖት አባቶች፣ከሐገር ሽማግሌዎች፣ከወጣቶችና ሴቶች ጋር የተጠናከረ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ህዝቡ ራሱ የራሱን ሰላም ተደራጅቶ የሚያስጠብቅ መሆኑ፣እንደ አማራነታቸው የትግሉ ባለቤት እንደሆኑና እንደሚደግፉ፣ያሉ የህዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶችን እንደ ራሱ ንብረት ጠብቆ እንደሚይዝ እና የአማራ ህዝብ ያለበትን የህልውና ተጋድሎ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። ህዝቡም በክረምት የተዘጉ ከእጃፋት ወደብዮ እንዲሁም ከጠልፈጢት ሙቅውሃ ያሉ መኪና መንገድ ጥርጊያ የልማት ስራ በመስራት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 18/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ዘመቻ_አርበኛ_አደም_አሊ (አባ ናደው) ሙሉ ትጥቁንና መገናኛ ሬድዮውን ይዞ የመጣውን አመራር ጨምሮ 20 የአድማ ብተና አባላቶች ምኒልክ ዕዝን ተቀላቀሉ::        መስከረም 18/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ኮሎኔል ሰሎሞን አሻግሬ ሻለቃ መሪ መብራት ጌቴ አቀባበል አድርጎላቸዋል።  ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የፋኖን ጥሪ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከ20 በላይ የአድማ ብተና እና የሚኒሻ አባላት የውባንተ አባተ ክፍለጦር በመቄት ፋኖን ተቀላቅለዋል። የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ ስርዓት እንደማያዋጣቸው የተረዱ እና አማራነትን ለመረጡ የአድማ ብተና እና ሚኒሻ አባላት ምስጋና ያቀረቡት የውባንተ አባተ ክፍለ ጦር ም/አዛዥ አርበኛ ሸጋው ወርቄ ሌሎችም ሳይመሽ ትክክለኛውን መስመር በመምረጥ እስከ አሁን የበደሉትን ህዝብ እንዲክሱ ጥሪ አቅርበዋል። በፋኖ በኩል በፍፁም ወንድማዊ እና አማራዊ ስነልቦና እንቀበላችኋለን ሲሉም ም/አዛዡ አክለው ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 18/2018 ዓ.ም