fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 039
مشترکین
+6824 ساعت
+3957 روز
+1 39230 روز
آرشیو پست ها
ጥር ሃያ (20) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ሦስት (1913) ዓመተምህረት‼️ #ዝክረ_ታሪክ ከአንድ መቶ አምስት (105) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ታሪክን የኋሊት!! ከዛሬ አንድ መቶ አምስት (104) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት ሌፍተናት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ (የበጋው መብረቅ) የተወለዱበት ዕለት ነበር። ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ ወይም በፈረስ ስማቸው አባ ዳማ ጥር ሃያ (20) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ሦስት (1913) ዓመተምህረት በጅባትና ሜጫ አውራጃ በደንቢ ዮብዲ ወረዳ ዮብዶ በሚባል ቦታ ተወለዱ። ጃገማ የሚለው የኦሮምኛ ቃል ሲሆን በአማርኛ ሀይለኛ ማለት ነው።  ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ በአንድ ወቅት ስለ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ምን እንደሚያስቡ  ተጠይቀው ከባለቅኔው ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ስንኝ ተውሰው እንዲህ ብለው ነበር  «አገሬ ኢትዮጵያ ውዲቱ ውዲቱ፣ በሶስቱ ቀለማት የተሸለምሽቱ፣ ላንቺ የማይረዳ ካለ በህይወቱ፣ በረከትሽን ይንሳው እስከ እለተ ሞቱ።» በማለት የባለቅኔውን ስንኝ  ሰድረው ነበር። በሽምቅ (ጎሬላ) ውጊያ የተካኑት ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ በጦር ሜዳ ውሏቸው በፋሺስቱ የጣሊያን ወራሪ ጦር ላይ ካገኙት አንፀባራቂ ድል አንዱ በወረሃ ህዳር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ ሦስት (1933) ዓመተምህረት የተገኘው ነው፡፡ ይህም የአዲስ ዓለምን ጽዮን ማርያም ምሽግ በመሰበር ሰባ (70) የጣሊያንን ወታደሮች በመግደል አንድ ሺህ አምስት መቶ (1500) ጠመንጃ በመማረክ እንዲሁም ሰማኒያ (80) የወገን እስረኞችን በማስፈታት ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ ለአገራቸው ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ከንጉሥ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ አገሮች ኒሻንና ሜዳዮችን ተሸልመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የአንገት ኒሻን የቅዱስ ጊዮርጊስ የጦር ሜዳ ጀግና ሜዳይ ባለ ሁለት ዘንባባ የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን ከእናት አገራቸው ኢትዮጵያ ተጠቃሽ ሲሆኑ ከሀገር ውጭ ደግሞ ከእንግሊዝ ከዩጎዝላቪያ እና ከላይቤሪያ የተለያዩ ኒሻኖችን አግኝተዋል።  ሌፍትናንት ጀነራል ጃካማ ኬሎ መጋቢት ሃያ ዘጠኝ (29) ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ (2009) ዓመተምህረት በአዲስ አበባ ከተማ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በዘጠና ስድስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። #የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️ #ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️ 20/ዐ5/2018 ዓ.ም

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የ2 ወር የግዳጅ አፈጻጸሞችን ገመገመ:- ============================== ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በ3 ግዙፍ ክ/ጦሮች የተዋቀረ ሲሆን መልሶ ማደራጀቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅና በስሩ የሚገኙ ክ/ጦሮችን በመገምገም እና ለአመራሩ አጭር ስልጠና በመስጠት ማጠናቀቁ ይታወቃል። ኮሩ በመልሶ ማደራጀቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ጠንካራ ጎኖች በማንሳት ለ2 ቀናት ጥልቅ ግምገማ ያደረገ ሲሆን የወደፊት የትግል አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቋል። ስለሆነም የውስጥና የውጭውን የጠላትን ከፍተኛ ጫና በመቋቋም የ109ኛ ኮር መልሶ ማደራጀት በተሳካ ሁኔታ እውን እንዲሆን ተግታችሁ ለሰራችሁ ለቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለ109ኛ ኮር አመራሮች፣ ለ88ኛ፣ ለ99ኛ እና ለ77ኛ ክፍለጦር አመራሮች፣ በሁሉም ክ/ጦሮች ስር ተጠርንፋችሁ እየታገላችሁ ላላችሁ አባሎች፣ ለቴዎድሮስ ዕዝ ኮማንዶ ዩኒት እንዲሁም ለአካባቢው ማሕብረሰብ የ109ኛ ኮር ስራ አመራር ከፍተኛ አክብሮት እና ላቀ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 20/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ትግል ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ውጣ ውረዶችን አስተናግዷል። በትጥቅ ትግል ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ማኅበረሰባዊ መሠረት የያዘው ይህ ኃይል፣ ዋነኛው ፈተና ሆኖ የቆየው "የአንድ ማዕከላዊ ዕዝ" አለመኖር ነበር። ይሁን እንጂ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም የተመሠረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ይህንን ታሪካዊ ክፍተት ለመድፈን መምጣቱን አብስሯል። ከንቅናቄው ከፍተኛ አመራር አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ጋር የተደረገው ቆይታ እንደሚያሳየው፣ አፋብን ከመደበኛ ታጣቂ ቡድንነት ባለፈ፣ የሕዝብን የህልውና ጥያቄ ወደ ተደራጀ ፖለቲካዊ ኃይል የመለወጥ ትልቅ ተልእኮ ተሸክሟል። ይህ ትንታኔ የአፋብን ምስረታ በሀገሪቱ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሚዛን ላይ የሚያመጣውን ለውጥ በዝርዝር ይፈትሻል። 1. የአፋብን ምስረታ እና የሕዝቡ የሥነ-ልቦና ድል አርበኛ ሳሙኤል ባለድል እንደገለጹት፣ የድርጅቱ ምስረታ በሕዝቡና በሠራዊቱ ላይ የፈጠረው ስሜት "በቃል ለመግለጽ የሚከብድ" ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የአማራ ሕዝብ ለዘመናት "ወካይ ድርጅት አጥቶ" ሲቆስል በመቆየቱ ነው። አፋብን ሲመሠረት የታየው ደስታ፣ ሕዝቡ ከጠመንጃው ድል ይልቅ የልጆቹን አንድነት አጥብቆ ይፈልግ እንደነበር ማሳያ ነው። አንድነት ማለት ለፋኖ ወታደራዊ ስልት ብቻ አይደለም፤ ለሕዝቡ ደግሞ የመከታ ምልክት ነው። አርበኛው እንደሚሉት፣ የአንድ ድርጅት መኖር በትግሉ ውስጥ ያሉ "የግል ጀግንነት" ስሜቶችን ወደ "የጋራ ዓላማ" ቀይሯቸዋል። ይህም ሠራዊቱ በተደራጀ መንገድ እንዲዋጋ፣ ሕዝቡም በአንድ ማዕከል እንዲደግፍ በር ከፍቷል። 2. የጠላት ስልት እና የ"ኮሪደር ፖለቲካ" ውድቀት ሰሞኑን መንግሥት "እጅ የሰጡ ፋኖዎች" እያለ የሚያሳያቸውን ግለሰቦች በተመለከተ አርበኛ ሳሙኤል የሰጡት ትንታኔ ለሮያል ኒውስ ታዳሚዎች ግልጽ ምስል ይሰጣል። እንደ አርበኛው ገለጻ፣ እነዚህ ግለሰቦች ትግሉን ጥለው የገቡት አላማ ስለተሳካ ሳይሆን፣ የትግሉ "ማጣሪያ" (Sieve) ስላነጠራቸው ነው። ሀ) የተላላኪዎች መጋለጥ፦ ገና ከጅምሩ በሥርዓቱ ተልከው የፋኖን ስም አጥፊ ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ አካላት፣ አሁን አንድነቱ ሲመጣ መደበቂያ አጥተዋል። "ጠርቃቃ" ውስጥ ገብተዋል ይላቸዋል አርበኛው። ለ) የኮሪደር ልማት ማድነቅ፦ ለህልውናው የሚታገል ሕዝብን ጥሎ ሄዶ አዲስ አበባ ላይ መንገድ ማድነቅ "የሆድ አምላኩነት" ምልክት መሆኑን ያስረዳሉ። አርበኛው "ዝንብና ንብ" በሚል የመሰሏቸው እነዚህ አካላት፣ ትግሉን ከውስጥ ከሚበክሉ አሁን ወጥተው መሄዳቸው ለፋኖ ትልቅ ዕድል መሆኑን ይገልጻሉ። 3. ወታደራዊ አቅም፦ ከመከላከል ወደ ማጥቃት መንግሥት ፋኖ ተዳክሟል በሚል የሚነዛውን ወሬ አርበኛ ሳሙኤል በተግባር ምላሽ ይሰጡታል። ዛሬ ፋኖ በወሎ፣ በሸዋ፣ በጎጃም እና በጎንደር የመንግሥትን ሠራዊት "እንደ በግ እየነዳው" መሆኑን ይናገራሉ። የወታደራዊ አቅሙን ጥንካሬ በሚከተሉት ነጥቦች ማየት ይቻላል፦ * የማያቋርጥ ሥልጠና፦ ፋኖ ዛሬ በየጫካው መደበኛ የኮማንዶ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ነው። * ወጥ የሆነ ሥርዓተ-ትምህርት (Manual)፦ የአፋብን ምስረታ ተከትሎ፣ ሁሉም የፋኖ አባላት በአንድ ዓይነት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠና እንዲያልፉ እየተደረገ ነው። ይህም ሠራዊቱን ከመደበኛ መንግሥታዊ ሠራዊት በላቀ ዲስፕሊን እንዲመራ ያደርገዋል። * የደጀን ሕዝብ ድጋፍ፦ ሠራዊቱ አቅም ያገኘው ከሕዝቡ በፈሰሰለት ወተትና ስንቅ በመሆኑ፣ ይህ ጥምረት እስካለ ድረስ ፋኖ አይዳከምም ባይ ናቸው። 4. የዲያስፖራው ሚና፦ ከአክቲቪዝም ወደ ዲፕሎማሲ አርበኛ ሳሙኤል ለውጭ ሀገር ዲያስፖራ የሰጡት መልዕክት እጅግ ጥልቅና ወቅታዊ ነው። እስካሁን ዲያስፖራው በየቡድኑና በየግል አክቲቪስቱ ተከፋፍሎ መቆየቱ በትግሉ ላይ ትልቅ እንቅፋት ነበር። አሁን ግን አፋብን እንደ አንድ ማዕከል መፈጠሩ ለዲያስፖራው አዲስ የቤት ሥራ ሰጥቷል። * አንድ ድርጅት፣ አንድ ድጋፍ፦ ዲያስፖራው አሁን "የእኔ ፋኖ" እና "የእነሱ ፋኖ" የሚል ክፍፍል ውስጥ ሳይገባ፣ ለአፋብን የፖለቲካ ማዕከል እውቅና ሰጥቶ መንቀሳቀስ አለበት። * የዲፕሎማሲ ዘመቻ፦ የአማራ ሕዝብ እየደረሰበት ያለው ጀኖሳይድ በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲታወቅ በተቀናጀ መንገድ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። * የፋይናንስ ጥንካሬ፦ ትግሉን ወደ መንግሥት ምስረታ ለማሸጋገር የዲያስፖራው የፋይናንስ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አርበኛው ሳይጠቅሱ አላለፉም። 5. የውስጥ ጽዳት እና ሥነ-ምግባር አፋብን እንደ ድርጅት ትልቅ ትኩረት የሰጠው ጉዳይ "የፋኖን ስም ማስከበር" ነው። በፋኖ ስም ተደብቀው ሕዝብን የሚዘርፉ፣ መንገድ የሚዘጉና ሰላማዊ ዜጎችን የሚያውኩ "የጥፋት ኃይሎች" ላይ ድርጅቱ ምሕረት የሌለው እርምጃ እንደሚወስድ አርበኛ ሳሙኤል በቁርጠኝነት ተናግረዋል። ይህ እርምጃ ለምን አስፈለገ? * የሕዝቡን ሙሉ አመኔታ ለማግኘት። * ጠላት በፋኖ ስም የሚፈጽመውን ሴራ ለማክሸፍ። * የፋኖን የሞራልና የዲሲፕሊን ልዕልና ለመጠበቅ። 6. ፋኖነት ለኢትዮጵያ፦ የሰላም ተስፋ ወይስ ስጋት? መንግሥት "ፋኖ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ይሰጣል" በሚል የሚሰነዝረውን ክስ አርበኛው በምክንያት ውድቅ ያደርጉታል። "ሀገር ማለት ተራራና ድንጋይ ሳይሆን ሕዝብ ነው" የሚሉት አርበኛው፣ በገዛ ሕዝቡ ላይ ድሮንና ታንክ የሚያዘንብ ሥርዓት ስለ ብሔራዊ ጥቅም የማውራት ሞራል የለውም ይላሉ።የፋኖ ዓላማ ለአማራ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በሰፊው ተንትነዋል። ዛሬ በአፋር፣ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል የሚታዩ የትጥቅ ትግሎችን እንደ ምሳሌ በማንሳት፣ የፋኖነት መንፈስ (ለነፃነት ዋጋ የመክፈል መንፈስ) መላውን ሀገር እያነቃቃ መሆኑን ገልጸዋል። የአፋብን መጨረሻ ግብ፦ "ሁሉንም እኩል የሚያይ፣ የዜጎችን መብት የሚያስከብርና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓተ-መንግሥት መገንባት" ነው። 7. የታሪክ ጥሪ ለወጣቱ በመጨረሻም አርበኛ ሳሙኤል ባለድል እስካሁን "አንድነት የላችሁም" በሚል ምክንያት ዳር ቆሞ ለነበረው የአማራ ወጣት ጥሪ አቅርበዋል። አሁን ድርጅት ተመሥርቷል፣ ዕዝ ተፈጥሯል፣ ዓላማውም ግልጽ ሆኗል። ስለዚህ ወጣቱ ወደ ሥልጠና ማዕከላት በመግባት የታሪክ አደራውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። አርበኛ ሳሙኤል ባለድል

ብልፅግናዎች እና ፀረ-አማራዎች ትግሉን ለማንኮላሸት በርካታ ስራ ሲሰሩ ነበር። በዚህም የቀድሞው የአንደኛ ክ/ጦር ዘመቻ መምርያ ኃላፊ የነበረውን ኮማንዶ ላመነው ሰጤ ከወንድሞቹ እንደተለየ፣ እንደተነ
+1
ብልፅግናዎች እና ፀረ-አማራዎች ትግሉን ለማንኮላሸት በርካታ ስራ ሲሰሩ ነበር። በዚህም የቀድሞው የአንደኛ ክ/ጦር ዘመቻ መምርያ ኃላፊ የነበረውን ኮማንዶ ላመነው ሰጤ ከወንድሞቹ እንደተለየ፣ እንደተነጠለ እና ለግድያ እንደሚፈላለጉ ከዚህ አልፎም ለብልፅግና ሊገባ ነው የሚሉ ፀረ-አማራዎች ነበሩ። አንድነትን ለማጠናከር ሳይሆን ትንሽ ችግር ስትኖር ያቺን ለማስፋት ብዙዎች ደክመዋል። ለማንኛውም ስናይፐር እንደ ጊታር የሚጫወተው የባህርዳር ዘቡ ኮማንዶ ላመነው ሰጤ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ም/ዘመቻ በመሆን ኃላፊነት ተሰጦታል። መልካም የኃላፊነት ጊዜ ይሁንልህ!

የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት መቶ አለቃን ጨምሮ ሌሎች ወታደሮች ተደመሰሱ!! ከጥር 18ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ጠላት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሰበሰበውን ኃይል ወደ ምዕራብ ወሎ ሲያንቀሳቅስ በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት ጥቃት እየተሰነዘረበት ይገኛል። በዚህም መሰረት ከትናንት በስቲያ ማለትም ጥር 1ቀን 2018 ዓ/ም በለጩማ ላይ ታሪክ ተሰርቷል። በበርካታ ተሽከርካሪዎች ጭኖ ወታደሮችን ወደ ምዕራብ ወሎ እያጓጓዘ ያለው ፋሽስታዊው መንግሥት በለጩማ ሲደርስ ያልታሰበ አደጋ ገጥሞታል። የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት የምዕራብ ወሎ ቀጠና ሰሞኑን ብዛት ያለው የጠላት ኃይል ከከባድ መሳሪያ ጋር እየተጋጓዘ እንደሆነ ይታወቃል። በቀጠናው የነበረው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር ሰራዊት ድጋፍ የፋኖን ጫና መቋቋም ስላልቻለ በቅርቡ የተመሰረተው 11ኛ ዕዝ ሰራዊት በድጋፍ ሰጭነት ወደ ቀጠናው ሲገባ  የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 4ተኛ ሻለቃ ፋኖዎች በሰነዘሩበት የደፈጣ ጥቃት ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል። ከደሴ ተነስቶ በስተ ምዕራብ በኩል ሲጓጓዝ ከነበረው በርካታ ኃይል መካከል ወደ አማራ ሳይንት ሊገባ በ6 ኦራል እና በ4 ፓትሮል ተጭኖ ሲጓጓዝ  የነበረ የጠላት ኃይል ላይ እነ ሞት አይፈሬ በሰነዘሩት ጥቃት የደረሰው ጉዳት የሚከተለውን ይመስላል:- የተደመሰሰ 5 የመከላከያ መስመራዊ ወታደሮች እና 1 መቶ አለቃ እንድሁም 3 አድማ ብተና፤ በድምር 9 የጠላት ኃይል እስከወድያኛው ሲሸኝ 7 መከላከያ እና 9 አድማ ብተና በድምሩ 16 ጠላት ቁስለኛ ተደርጓል። የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ደምመላሾች በብርሀን ፍጥነት በድምሩ 25 የጠላት ኃይልን ከጥቅም ውጭ አድርገዋል። ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 20 ቀን 2018 ዓ/ም

ሰበር...በአማራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ 01ቀበሌ የአስት ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን እና የፋሬታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እድሜ ጠገብ ታሪካዊ ቅርሶች በአገዛዙ ወታደርች ዘረፋ
ሰበር...በአማራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ 01ቀበሌ የአስት ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን እና የፋሬታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እድሜ ጠገብ ታሪካዊ ቅርሶች በአገዛዙ ወታደርች ዘረፋ ተፈፀመባቸው! የአገዛዙ ወታደሮች ዛሬ ጥር 20/2018 ዓ/ም አዳራቸውን በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የነበሩ ቅርሶችን መዝረፋቸውን ተከትሎ በአሁን ሰዓት በአከባቢው ከባድ ውጥረት ነግሷል። የአከባቢው ማሕበረሰብ ቅርሶቻችንን መልሱ በሚል የአገዛዙ ወታደሮችን ተቃውሞ ወደ አደባባይ የወጣ ሲሆን፡ ወታደሮቹም ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ መክፈታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል። ዘረፋ የተፈፀመባቸው የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን እና ፋሬታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከ200 ዓመታ በላይ እድሜ ያስቆጠሩ ቅርሶች መገኛ ቅዱሳን ስፍራዎች ናቸው።

አጋልጥ !! ይሔ ሁሉ ፋኖን እና አማራን ሲራገም እና ሲራገጥ የሚውል "አራት እግር አሳማ" ነው ። መሬት ላይ በወታደራዊ ኃይል የተሸነፈው ብልፅግና በማህበራዊ ሚዲያ የፋኖ አመራር ስም ማጥፋት እና አጀንዳ መስጠት ላይ ያሰማራቸው እነዚህ የፌስቡክ ገፆች ናቸው ። የፌስቡክ አካውንቶች ዝርዝር፦ 1. Ethio Mereja 2. ስንቅ 3. ሁሴን ገዳ ከኦሮሚያ 3. Lula Kebede 4. ሀገሬን 5. Sebona Eliyas Tofik 6. Ethio Daily Media 7. ፍቅርተ ይበልጣል 8. Edu Lala 9. Yene Ethiopia 10. Ethio Intercept 11. Ardi Info 12. Meron Tadesse 13. Asmera Press 14. ዲጅታል ኢትዮጵያ 15. Addis Zemen 15. Selam mulugeta 16. ጥቁር አንበሶች 17. Ethio Press 18. Addis view አድስ እይታ 19. Nardos Page 20. Gohe tv ጎህ ቲቪ 21. ወደ ፍቅር ጉዞ ተያይዞ 22. ጎንደር ፋሲለደስ 23. hagere zena 24. የፍቅር መንገድ 25. Fast Mereja ፈጣን መረጃ 26. Solomon Gumba 27. Ethiopiya Adane 28. Sheger press 29. የሰላም ዘብ 30. Melat Bekele 31. Beti Tesfaye 32. Eden Hagose 33. Liya Eshetu 34. Eden Tamerat 35. አማኑኤል አወቀ 36. O U R Raya 37. One Ethiopia 38. Kelemu Taddele 39. ኢትዮፒድያ ዜና 40. Obbo Chidessa  Odda                                41. Sis Press 42. Betty Gullele 43. የበለፀገች ኢትዮጵያ 44.  Ethiopia voice 45. Gullale post 46. Lucy media 47. Maski Bekele 48. Saroon 49. Dz Ethio 50. የኛ info 51. Meri konjoooo 52. Zemed Mekonnen 53. ጧፈኛ 54. Gondar Times 55. ብሌን ሰለሞን 56. Msgei 57. ጉና ክምር ድንጋይ 58. ሰላም ለሃገሬ 59. አቦል መረጃ 60. ሰላም ለኢትዮጵያ 61. Helen Sisay 62. Nafkot Tesema 63. Thomas Jejaw 64. Abiti Ankober 65. ሮዛ ፍቅር 66. Melat Bekele 67. እውነተኛ ፋኖ 68. Wollo Gerado 69. መልህቅ የመረጃ ምንጭ 70. Yordanos Tekeste 71. Ethiopian Insight 72. Hibist Kefyalew 73. Sonan Press 74. Bole Times 75. Assab Ethiopia 76. በጌምድር-ጎንደር 77. Hiwot A Feleke 78. Meles Bisrat 79. Ethio Intercept 80. ብላቴናው ንጉስ 81. Helen Getachew 82. Tesfayehun Seme 83. Amhara Post 84. Beza Kebede 85. Bilen Mesfin 86. ጯሂት ጎርጎራ 87. Selam Alemu 88. ዲጂታል ኢትዮጵያ 89. Sonan press press 90. Pro peace press 91. Eden Nigussie 92. የሸገር ልጆች 93. የመደመር ትውል 94. አርጎባ ወሎ ጀበርቲ 95. ጀበርቲ አርጎባ አገር 96. Meron Tsegaye 97. Selam Adan 98. Medener 99. Mekides Melaku 100. Meri Konjoo 101. Geda Moti 102. ዝምተኛው ንጉስ መደመር 103. Amihara Fano 104. Wubit Seyoum Gashaw 105. አንድ አምሓራ 106. Semira Jamal 107. Tizta Melaku 108. Miser Dagne 109.አገው ነኝ 110. Lasta Agew 111.  Kidist Nega 11. የውብዳር አረጋ 112. Shebelaw Getachew 113 .ዲጂታል ጦቢያ 114. Helen Tesfa 115. ቡሬ ዳሞት ፋኖ 116. Tigist Kefale 117. Tg Love Andebt B Ali 118. እውነታ ሚድያ 119. Ethio press 120. ቀይ ባህር 121. ተዋበች ጎንደር 122. Nigat Nigat 123. አፍሮ ሚድያ 124. Selam Fentie 125. Zemed Mekonen 126. ድጅታል ፋኖ-digital fano 127. ፈጣን መረጃ 128. Dibora Mekonen Atinafu 129. Burie Damot Fano 130. Addis View አድስ እይታ 131. ጎጃሜዋ መቅደስ 132. ብሌን 133. Helina Alebachew 134 .ፀረ ሌባ ፀረ ሌባ 135.GoJam GoJam 136.Dered Der 137.ጣዝማ ማር 138. ኢትዮጵያMekete 139.Endalamawealama 140.Quarite Press 141.Nile Bluile 142.Bekalu Yehuala 143.Yehuala Yehu 144.Mihret Abewa 145.አብዱሮህማን ኢብራሂም 146.ስዩም ይዘንጋው ድንቁ 147.Indo Amhara 148.Amha Mulat 149.Addis Fikrte 150.AlemuTigist 151.Zelalem Sisay 152.Baynesagn Fentie 153.ሀሴት አየለ 154.አባይ ሚዲያ 155.ራያ ራዩማ 156.ወልቃይት ጠገዴ አማራ 157.ጦሳ ሚዲያ 158. Ghone Forces 159. Raya Price ከብልፅግና ገንዘብ የሚከፈላቸው ናቸው ። ሌሎችን ለቅሞ ማጋለጡ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ቃሉን ያከበረ ጀግና ጠረኛ! ቃሉን ያከበረ ጀግናው ጠረኛ፡ ፋኖው ኮሎኔል ፀሐይ አርበኛ። ከልጆቹ ጋር ፊት ተሰላፊ፡ ጥላት አንበረካክ ካርታ ነዳፊ። የንጹህ አደራ እንቅልፍ እንደነሳህ፡ ይኸው ፍሬ አፈ
ቃሉን ያከበረ ጀግና ጠረኛ! ቃሉን ያከበረ ጀግናው ጠረኛ፡ ፋኖው ኮሎኔል ፀሐይ አርበኛ። ከልጆቹ ጋር ፊት ተሰላፊ፡ ጥላት አንበረካክ ካርታ ነዳፊ። የንጹህ አደራ እንቅልፍ እንደነሳህ፡ ይኸው ፍሬ አፈራ እንዲህ ደመቅህ። ጀግናው አባታችን ንጹህ አማራ፡ አድርገኸናል በአንተ እንድንኮራ። የጠረ መሀንዲሱ አርበኛ ኮሎኔል ምሬ ወዳጆ ድል ላንተና ለምትሰዋለት ሕዝብህ! 👉ገጣሚ፦ ፋኖ ድምፃዊ ኪሮስ ደርቤ- ከምስራቅ ዐምሐራ ቀጠና!

ብልፅግና የመጨረሻ ያለውን ካርዱን ወልቃይት ላይ መዟል‼️ በጠለምት ዋልድባ አካባቢ ማይ-ዳጉሻን ጨምሮ በአራት ግንባር ከትናንት ጥር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ ውጊያ ተቀስቅሷል። ብልፅግና፡ በባለቤቱ
ብልፅግና የመጨረሻ ያለውን ካርዱን ወልቃይት ላይ መዟል‼️ በጠለምት ዋልድባ አካባቢ ማይ-ዳጉሻን ጨምሮ በአራት ግንባር ከትናንት ጥር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ ውጊያ ተቀስቅሷል። ብልፅግና፡ በባለቤቱ በአማራ ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ወልቃይትን ከሕወሓት ታጣቂዎች የሚከላከል መስሎ ተኩስ ከጀመረ በኋላ፡ እንደለመደው በማፈግፈግ ወልቃይትን ሙሉ ለሙሉ በሕወሓት ታጣቂዎች የማስወረር እቅድ እንዳለው ነው የተነገረው። ስልታዊ ማፈግፈግ በሚል የአማራ ሕዝብ ላይ የነበረውን የጥላቻ ጥማት የተወጣው ብልፅግና ዛሬም በዚችው ማሊያ ለመጫዎት ካርዱን መምዘዙ ታውቋል። አስወረርከን የሚል ጥያቄ ሲነሳበትም "የሕወሓት ታጣቂዎችን ከወልቃይት እንዳላስወጣ ፋኖ እንቅፋት ሆኖብኛል" የሚል ካርድ ለመምዘዝ መዘጋጀቱን የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል። ይህ ነውረኛና ፀረ አማራ ቡድን በአክቲቪስቶቹ በኩል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወልቃይትን በሕወሓት አስወረረብን የሚል የለቅሶ ፖለቲካ ለመስራት ድንኳን ተከላ ጀምሯል። 20/ዐ5/2018 ዓ.ም

አማራ መሆን መታደል ከሆኑ በሗላ አለመሆን የለም.! መታገል ማሸነፍ ብቻ ...!
አማራ መሆን መታደል ከሆኑ በሗላ አለመሆን የለም.! መታገል ማሸነፍ ብቻ ...!

ሁሌም በአራቱም ማዕዘን ጎጃም ሽዋ ወሎ እና ጎንደር እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ያሉትን መረጃ 24 ስዓት በማድርስ የሚታወቀው  የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ አዲሱን አካውንት ጆይን በማድርግ ይወዳጁን አላችሁ አማራዊያን እና ኢትዮጵያውያን https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973

ዝንታለም የማይረሳ ጀግንነትን ተላብሶ ለአማራ ህዝብ ደፋ ቀና ሲል ኖሮ የእውነት ትግል ታግሎ በእውነት የተሰዋው ሻለቃ አስቻለው ደሴ፤ የአሳምነው ግልገል! ጭንቅ የሚገላግል! የአስቻለው ደሴ ቀኝ! ለወዳጁ ታማኝ! የጎቤ ደም መላሽ! የጭቁን እንባ አባሽ! ሻለቃ አስቻለው ደሴ የኛ ዘመን አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ነው:: ሻለቃ አስቻለው ደሴ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ ምትክ ነው። የጦሩ ሙሽራ፣ እውነተኛው የነፃነት ታጋይ፣ ምሉዑ አማራ እና ሞት አይፈሬው ጀግና ወንድማችንን ያጣነው ባለመደራጀታችን ብሎም የጄኔራል አሳምነው ፅጌን "አንድ ሁኑ" የሚለውን ቃል ባለማክበራችን ነው። አንድ የሆነ ህዝብ ጀግኖቹን አሳልፎ በቀላሉ አይሰጥም። የተደራጀ ህዝብ መሀል ገብቶ ጀግናን ለይቶ ማጥቃት የሚችል አካል ሊኖር አይችልም። የመደራጀትን ጥቅም ለማወቅ የሻለቃ አስቻለው ደሴን ቤተሰቦች የደበደበው ግለሰብ አምና ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በፋኖ በአፍጢሙ መደፋቱ አስረጅ ነው። ሻለቃ አስቻለው ደሴ ከተሰዋ በኋላ ግለሰቡ "የእናንተ ልጅ በድሎናል" በሚል የሻለቃው ወላጆች ላይ ድብደባ በመፈፀም የዓይን ብርሃናቸውን እንዲያጡ አድርጓል የተባለው የወረዳው የሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና ሌሎች የወረዳው አመራሮች ናቸው አምና ከዚህ ምድር የተሰናበቱት። ይህ የመደራጀት ውጤት ነው። የተደራጀ ህዝብ አሸናፊ ነው። ነፍስ ኄር ወንድምሰው። የሞትክለትን አላማ ከዳር እናደርሳለን።

ሁሌም በአራቱም ማዕዘን ጎጃም ሽዋ ወሎ እና ጎንደር እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ያሉትን መረጃ 24 ስዓት በማድርስ የሚታወቀው  የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ አዲሱን አካውንት ጆይን በማድርግ ይወዳጁን አላችሁ አማራዊያን እና ኢትዮጵያውያን https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973

ሁሌም በአራቱም ማዕዘን ጎጃም ሽዋ ወሎ እና ጎንደር እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ያሉትን መረጃ 24 ስዓት በማድርስ የሚታወቀው  የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ አዲሱን አካውንት ጆይን በማድርግ ይወዳጁን አላችሁ አማራዊያን እና ኢትዮጵያን https://www.facebook.com/share/19D9uBuBwa/