fa
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
3 208
مشترکین
+18224 ساعت
+2627 روز
+63730 روز
آرشیو پست ها
በቲክቶክ ፕላት ፎርም ትግላችንን እና ታጋዮችን ሊያቆሽሽ ሲለፈልፍ የሚውለው የአድማ ብተና አባል ዛሬ ቲሊሊ ላይ በቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በኩል ዋጋውን አግኝቷል። ማንም በትግላች
+3
በቲክቶክ ፕላት ፎርም ትግላችንን እና ታጋዮችን ሊያቆሽሽ ሲለፈልፍ የሚውለው የአድማ ብተና አባል ዛሬ ቲሊሊ ላይ በቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በኩል ዋጋውን አግኝቷል። ማንም በትግላችን ላይ እየቀለደ አይቀጥልም። አስረስ ማረ ዳምጤ

የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ንፁሃን አማራዎችን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ!      ሚያዚያ:-17/2018 ዓ/ም የአብይ አህመድ ስልጣን አስጠባቂ ሰራዊት በእግረኛ ሰራዊት አልሳካለት ሲል የአማራን ህዝብ በከባድ መሳሪያ በመጨፍጨፍ ህዝብ ጠልነነቱን አሳይቷል። በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ግዳን ወረዳ ዙሪያ 06 እና 07 ቀበሌዎች በቀን 16/08/2018 ዓ.ም የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር አካል የሆነችውን የጥራሪ ክፍለ ጦርን አፍናለሁ ብሎ አስቦ ተንቀሳቅሶ ባካሔደው አውደ ውጊያ በአፀፋው ሽንፈትን ተከናንቦ ከ25 በላይ ሰራዊቱን በሙትና ቁስለኛ ሲያጣ በብስጭት ከባድ መሳሪያን በዘፈቀደ በመተኮስ:- 1)የአስንቆ አበጋዝን እንስሳቶች አምስት በጎች 06 ቀበሌ ላይ ፣ 016  አንበሳው ቀበሌ ላይ ከወንዳች በመወርወር  ደግሞ ወይዘሮ ሲሳይነሽ  አለልኝ በይኖ እና ወይዘሮ አንጓቼ አለልኝ ከወዬ የተባሉ በድህነት የሚሰቃዩ ቤተሰብ አሳዳሪዎችን የገደለ ሲሆንና 07 ቀበሌ በደኖት የሚባል የመኖሪያ ሰፈር በማውደም የአማራን ህዝብ ጠልነቱን አስመስክሯል። የአማራ ፋኖ በተጠናና በታቀደ አውደ ውጊያ የብልፅግናን ግብስብስ ሰራዊት እየማረከና ትጥቁን እየተቀበለ እየተደራጀ ሲሆን ብልፅግናም በመላው ሀገሪቱ ያለውን ጦሩን ጠቅልሎ በማስገባት አማራውን በኢኮኖሚ በሰብዓዊ እና የስነ ልቦና ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል።በዚህም በሰሞኑ አውደ ውጉያ በተለይ በግዳን ወረዳ 07 ቀበሌ ልዩ ስሙ ወይራ በር በሚባል አካባቢ የአፋብን 303 ኮር የጥራሪ ክፍለ ጦር ባደረገው አውደ ውጊያ የብልፅግናን ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ ያደረሰበት በመሆኑ በዘፈቀደ ማህበረሰቡን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨፈጨፈ ይገኛል። የውሸትና የሀሰት የምርጫ ድስኩር በየቀበሌዎቹ ምርጫ አካሒዳለሁ ብሎ ቢያስብም ባቀደው ልክ ሳይሆን በተቃራኒው ከፍተኛ ጉዳትን በማስተናገድ ከአስር በላይ ሙት ከአስራ አምስት በላይ ቁስለኛ ሆኖበታል። በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ ሰላሙን የሚያገኘው ብልፅግና ተነቅሎ ሲጠፋና ለመላው ኢትዮጵያዊያን የምትበቃ ሀገር መመስረት ስንችል ብቻ ነው በሚል ከጠላት ጋር ዛሬ አንገት ለአንገት ተናንቀው እየተዋጉ ያሉ የጥራሪ ክፍለ ጦር አሃዶች ሀሳባቸውን አጋርተዋል፤ መረጃውንም የክፍለ ጦሩ ቃል አቀባይ አድርሷል። በሌላ መረጃ አገዛዙ ቡግና ወረዳ አይና ከተማ ላይ የፋኖ ቤተሰቦች ናችሁ በሚል አፈና፣ እስርና እንግልት እያደረሰ ይገኛል! በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ቡግና ወረዳ አይና ከተማ ላይ መሽጎ የሚገኘው የብልፅግና ካድሬ፣ ሚሊሻ፣ ፖሊስና አድማ ብተና አባላት አማራን ለሚጨፈጭፈው ብልፅግና ታማኝ አገልጋይ ሎሌ መስለው ለመታየት የፋኖ ቤተሰብ አባላቶችን እያፈሱ ሲያስሩ፣ ሲያሰቃዩና ሲያንገላቱ ውለዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት አይና ከተማ ላይ የፋኖ ቤተሰቦች ናችሁ በሚል ከ20 በላይ ንፁሃን አማራዎች የታሰሩ ሲሆን የታሰሩበትን ምክኒያት ሲጠይቁም ልጆቻችሁ ለብልፅግና እጅ እንዲሰጡና እንዲገቡ አድርጉ፣ ለ2018 ዓ/ም የብልፅግና የጨረባ ምርጫ አስፈፃሚ የላክናቸውን ልጆች መንገድ ላይ 30ኛ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር አግቷቸዋል እናም ምርጫ አስፈፃሚዎቻችን ካልተለቀቁ እኛም አንለቅም በሚል እርባና ቢስ ምክኒያት እንደሆነ ተገልጿል። በመጨረሻም ብልፅግና ፖርቲ ዳግም አማራን ለመጨፍጨፍና መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈፀም ባዘጋጀው የምርጫ ድግስ እና ለተጨማሪ አምስት አመት የአማራን የምጥ ዘመን ለማራዘም ገብቷችሁም ይሁን ጥቅም አታሏችሁ የምትጋጋጡ ጥቁር አማራዎችን የማንታገስና ቀይ መስመራችን መሆኑን በማወቅ በንፁሃን ላይ ከምታደርሱት እንግልት፣ እስርና ወከባ እንድትታቀቡ እና በቡድንም ይሁን በግለሰብ ደረጃ ለወደፊት ጥቁር ታሪክ ጥላችሁ እንዳታልፉ ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ጥብቅ መልዕክቱን ያስተላልፋል። መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል። አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 17/2018 ዓ/ም

ምኒልክ ዕዝ በግዳን ወረዳ በወሰደው ስልታዊ የስቦ መምታት እርምጃ ከ25 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች መደምሰሳቸው ታወቀ! በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር ስር የሚገኘው የ14ኛ ክ/ጦር አርበኞች ትናንት ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም በግዳን ወረዳ ወይራ በር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የስቦ መምታትና የቆረጣ ታክቲክ በመጠቀም በወሰዱት እርምጃ፡ የጠላት ኃይልን ዶግ አመድ በማድረግ ታላቅ ገድል ፈፅመዋል። የጠላት ኃይል ሙጃ ማርያም በተጠመደ ከባድ መሣሪያ ሽፋን ታግዞ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት ለመመከት የሞከረ ቢሆንም፡ ነገር ግን የኃያላኑን ክንድ መቋቋም ባለመቻሉ ተፍረክርኮ ተበታትኗል። በክፍለ ጦሩ ስር የትዕግስቱ ሬጅመንት ፋኖዎች ከክፍለጦሩ አብሪዎች ጋር በመቀናጀት በወሰዱት በዚህ እርምጃ፡ የጠላት ኃይል ወደ ሞት ቀጡና ተስቦ እንዲገባ በማድረግ ዙሪያ ገባውን ክርችም አድርጎ በመዝጋት የጥቃት ሱናሚ አውርደውበታል። የብልፅግናው ቡድን ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚጠቀምበትን የውሸት ምርጫ ካርድ በግዳጅ ለማከፋፈልና የፋኖ አሃዶችን አፍናለሁ በሚል ቅዠት ወይራ በር አከባቢ በሚገኙ 06 እና 07 ቀበሌዎች የተንቀሳቀሰው የጠላት 45ኛ ክፍለ ጦር፡ ሳይቀደም ቀድሞ በሚጠብቀው የፋኖ ክንድ አመድ ሆኖ ተመልሷል። የምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር ስር 14ኛ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙት የትግስቱ ሬጅመንት አርበኞች ከክፍለ ጦሩ አብሪዎች ጋር በመቀናጀት፡ የጠላትን እንቅስቃሴ አስቀድመው በመሰለልና አውደ ውጊያውን በመምራት ረገድ አስደናቂ የሆነ የውጊያ ጥበብ አሳይተዋል። በዚህ አውደ ውጊያ ከ10 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ወዲያውኑ ሲገደሉ ከ15 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በከባድ ሁኔታ ቆስለው በሞትና በሕይወት መካከል እንደሚገኙ ታውቋል። የገዛ ወገናቸውን ለሚጨፈጭፈው የአገዛዝ ስርዓት በሆዳቸው ወድቀው ተላላኪ የሆኑት የሚኒሻ አባላት፡ "ባልሆነ መንገድ መርታችሁ ለጥቃት ዳርጋችሁናል" ተብለው በዱላ እና በክላሽ ሰደፍ የተደበደቡ ሲሆን፡ ጉድጓድ ምሰው የመከላከያን አስከሬን እንዲቀብሩና ቁስለኛ በጀርባቸው እየተሸከሙ ወደ ሙጃ ማርያም ከተማ እንዲያግዙ መደረጋቸው ታውቋል። በአሁኑ ሰዓት ወራሪው ሰራዊት ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ በሆነ ጭንቀት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፡ ፋኖም ውጊያውን በበላይነት በመምራት በድል ታጅቦ እርምጃውን በማስፋት ግስጋሴውን ቀጥሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! በአፋብን ወሎ-ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ! ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አሃዶች በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ጥቃት ፈፀሙ። ሚያዚያ 17/2018ዓ.ም የአማራን ህዝብ ከሚጨፈጭፈው አገዛዝ ጋር አብሮ የተሰለፈው እራሱን ጥምር ጦር እያለ የሚጠራው ስብስብ ከብልፅግናው የተበረከተለትን የእጅ መንሻ ሳይረከብ በጀግናው ሰራዊታችን ተመቶ መፈርጠጡን ኮሩ ገለፀ። በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ህዝባቸውን ለሚጨፈጭፉ ለፖሊስ፣ለሚሊሻና ለአዳማ ብተና አባላት የአርሶ አደሩን መሬት በወረራ በመያዝ ለመኖሪያ ቤት በእጅ መንሻነት ሸንሽኖ ለማስረከብ ወደ 03 ቀበሌ ልዩ ቦታው ሃይማ በተባለ አካባቢ በተንቀሳቀሰበት ወቅት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአርበኛ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ወንዱ አስቻለው ክፍለጦር እና በቀጠናው የሚገኙት የታደለ ወርቁ ብርጌድ የአርበኞች ጦር ሰራዊት በቅንጅት በወሰዱት ድንገተኛ ጥቃት በፍየል ማርቢያና ጎዜ ተራራ የሰፈረው የብልፅግናው አየር ወለድ ሰራዊት ተመቶ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ መሀል ከተማ መፈርጠጡን ኮሩ በግንባር መረጃው ገልጿል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሚያዚያ 17/2018ዓ.ም

ሁለት የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባላት ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! ​ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 46ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በተለያዩ ሀላ
+1
ሁለት የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባላት ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! ​ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 46ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በተለያዩ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአገዛዙን የጥፋት መንገድ በመቃወም ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው የምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 15ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የክፍለ ጦሩ አመራሮችም ለአባላቱ ጥሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ​የፋሽስቱን አገዛዝ በመቃወም ፋኖን የተቀላቀሉት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፡- ​ደስታው ይመር - በሰው ሃብት አስተዳደር ሀላፊነት ሲያገለግል የነበረ ​አማረ ደጉ - በህግ ክፍል ሲያገለግል የነበረ ​እነዚህ የሰራዊቱ አባላት በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ጮቢ በር ተመድበው የነበሩ ሲሆን፣ ከዛ ተነስተው በራያ ቆቦ 041 ቀበሌ አማያ በመግባት ለምኒልክ ዕዝ እጃቸውን ሰጥተዋል። አባላቱ በሰጡት ቃል "ወታደር የህዝብ ዘብ መሆን ሲገባው በተቃራኒው ህዝብን የሚደበድብ እና የሚያሰቃይ ሆኗል" በማለት አገዛዙን የካዱበትን ምክንያት ገልጸዋል። ​በሌላ በኩል የምኒልክ ዕዝ ጀግኖች በሸወይ፣ በጨፌ መንደር እንዲሁም በአምድ አንባ አቅጣጫ ጥቃት ለመክፈት የመጣውን የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሙትና ቁስለኛ አድርገው መልሰውታል። ከዚህ ወታደራዊ እርምጃ ጎን ለጎንም በጠላት ሰራዊት ላይ ሰፊ የማሳመን ስራ በመስራት የታችኛውን የሰራዊት መዋቅር የማፍረስ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። ​©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

በግሼ ራቤል ወረዳ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍና የመብት ጥሰት ወደ ክፍተኛ ችግር ውስጥ እየገባ ይገኛል!! ​በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በግሼ ራቤል ወረዳ የሚገኙ የብልፅግና ዳይፐሮች የብአዲን ቅጠርኛ አመራሮችና  አረመኔው የብልፅግና የፀጥታ አካላት በገዛ ህዝባቸው ላይ ያነጣጠረ የተቀናጀ ጥቃትና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈፀሙ ይገኛሉ። ሆኖም ​በዛሬው ዕለት የወረዳው ነዋሪዎች ወደ ገበያ በሚጓዙባቸው መንገዶች ላይ የመከላከያ፣ የሚሊሻና የፖሊስ አባላት በስፋት ተሰማርተው አርፍደዋል። ይህ የፀጥታ ኃይል በህዝቡ ላይ ድብደባና እንግልት እየፈፀመ የምርጫ ካርድ ለምን አላወጣችሁም?" በሚል ሰበብ ህዝባችን እንግልትና ስቃይ እያደረሰ ይገኛል። ​ለዚህ ድርጊት በዋና አስተባባሪነት ግንባር ቀደም ሁነው አየመሩት ያሉት 1.​ ክፍሌ አበራ — የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ 2. ​በለው ደጄኔ — የሰላምና ደህንነት ኃላፊ 3. ​ታገለ ተካ — ምክትል የሰላምና ደህንነት ኃላፊ 4. ​አያሌው — የሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ​እነዚህ ግለሰቦች ህዝቡን ለከፋ ስቃይ አሳልፈው እየሰጡ በመሆናቸው፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ ጥሪዎች  ከህዝባችን እየቀረቡ በመሆነ እነዲሁም ​ከዚሁ ጋር ተያይዞ በወረዳው ሸበቶ አካባቢ የመሸገው የመራሹ ብልፅግና የጦር ኃይል በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል። በተለይም በቁንዲ መድኃኔዓለም አካባቢ ሁለት ወጣት ልጃገረዶች በመከላከያ አባላት መደፈራቸውን የሚጠቁሙ በተጨባጭ መረጃ የተደገፉ ዘገባዎች ወጥተዋል። ይህ ድርጊት በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ሕዝብ ግንኙነት ነው !!!! ​ድላችን በተባበረ ክንዳችን! ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም

አሳዛኝ ዜና! በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ ጨፍጫፊውና አምባገነኑ የአብይ አህመድ አገዛዝ የንፁሀንን ህይወት ቀጠፈ። ዛሬ ሚያዚያ 17/2018 ዓ/ም ጧት 4:30 ላይ የአማራ ፋኖን እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ቆቦ ከተማ አቅራቢያ መንደፈራ ሆኖ ባስወነጨፈው መድፍ ኮባ 04 ቀበሌ ጦርነቱ የማይመለከታቸው ሁለት የአንድ ቤተሰብ ልጆችና አንድ ከቤቱ የተቀመጠ ሽማግሌ  ህይወት ቀጥፏል። እንደሚታወቀው ያለ ጦርነት መኖር የማይፈልገው አገዛዝ በባለፈው ሳምንት በቆቦና በአድስ ቅኝ በአማራ ፋኖ በወሎ ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በተወሰደበት ከባድ እርምጃ ብስጭት ሁለት ቤተ-ክርስቲያኖች በማውደምና አንድ የ8 አመት ህፃን በመግደል እንዲሁም የቤተ-ክርስቲያን ሰንበት ተማሪዎችን ማቁሰሉ ይታወቃል። በተጨማሪም በጌታቸው ረዳ የሚመራው ራሱን ሐራ መሬት እያለ የሚጠራው ቡድን እና የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ሰራዊት በ05 ቀበሌ ቡኩ፣ ኮረራው መንደር ፣ድንጋይ ቀበሌና 09 ቀበሌ ራማ አካባቢ የሚገኙትን አርሶ አደሮች ሽርጥ፣ ወርቅና ብር በመቀማት ወደ ተራ ዘራፊነት የተቀየረ መሆኑን በተግባር አሳይቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም

ሌላኛው የአረጋ ከበደ መንግስት ጉድ። ========================= ✍️ኮማንደር ገበየሁ ካሴ አየነው የተባለ የፖሊስ መኮነን በ2017 ዓ•ም የአንደኛ ሻለቃ አድማ ብተና አመራር ሁኖ ብዙ ሰዎችን አግቶ ገንዘብ ተቀብሏል:: ✍️ በርካቶችን ደግሞ ረ*ሽ*ኗል:: ✍️ ይህም በማስረጃና መረጃ ተረጋግጧል:: ✍️ ኮማንደር ገበየሁ ካሴ አየነው በሶስት ወንጀሎች ለባህርዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት ነበር:: ✍️ የሶስቱ የክስ መዝገቦች የወንጀሎች አይነትም 👉 👉 ሁለቱ አግቶ ገንዘብ መቀበልና 👉 ሶስተኛው የክስ ፋይል በሰው ድብደባና አካል ማጉደል ነው:: ✍️ በአንደኛው የክስ መዝገብ ማለትም ሰውን አግቶ ገንዘብ መቀበል ወንጀል ብር 300,000 መቀበሉ በባህርዳና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድቤት ተረጋግጦ ለዚህ ፅፋተኝነቱም #ሶስት (3) አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። ✍️ ዉሳኔው የተሰጠበት ቀን ህዳር 15/2018 ዓ•ም ነው ✍️ የውሳኔው መዝገብ በወ/መ/ቁጥር 0421423 ነው( የፍርድቤት ውሳኔው ተያይዟል) ✍️ ጥፋተኛ ተብሎ 3 አመት ፅኑ እስራት ቢወሰንበትም የአረጋ ከበደ መንግስት ከባህርዳር የአንደኛ ሻለቃ አመራርነት አንስቶ በደቡብ ወሎ ዞን ለምትንቀሳቀሰው #የ21ኛ ሻለቃ አድማ መከላከል ፖሊስ አዛዥ ተደርጎ ተመደበ:: ✍️ ወንጀለኛን በአዛዥነት መመደቡ fb ላይ ሲገለፅባቸው የአረጋ መንግስት ቦታ በመቀየር ከእስራት ለማስቀረት ሲባል ሰሞኑን ወደ ደ/ጎንደር ለተንቀሳቀሰችው አድማ ብተና አዛዥ ሁኖ እየሰራ ነው:: ✍️ ወቸው ጉድ ያሰኛል የአረጋ ከበደ መንግስት የሚሰራው ስራ 👉 ማለትም አስገድዶ በመሰወር 300ሺ ብር የተቀበለን ሌ*ባ(የተበየነበት ስለሆነ ነው) ያውም በፍርድቤት የተወሰነበትን ግለሰብ ቦታ እየቀያየረሩ በአዛዥነት መመደብና ማሰራት ማለት በእኔ አስተሳስብ በየሄደበት ዜጎች እንዲታገቱና ገንዘብ እንዲከግሉ እንዲሁም እናቶችና ልጃገረዶች እንዲደፈሩ የማድረግ ስልት ነው ብል ስህተት አይሆንም ። ✍️ ኮማንደር ገበየሁ የሚመራቸው የጠጥታ አካላት ከእርሱ ምንድን ነው የሚማሩት? 👉 እገታ? 👉 ድብደባ? 👉 ስርቆት? 👉 አስገድዶ መድድፈር? 👉 ወይስ ህግ ማስከበር? ✍️ ለመሆኑ የህግ ፍርደኛን ህግ ለሚያስከብር የሰራዊት አባላት አዛዥ አድርጋችሁ መድባችሁ ስለፍትህ የማውራት ሞራል ይኖራችሁኃል? ✍️የዜጎችስ ደህንነት እንዴት ሁኖ ሊጠበቅ ይችላል? 👉 ወይስ የህግ የበላይነትን ሳይሆን እኛ ከህግ በላይ ነን የሚለውን ለማስተማር አስባችህ ይሆን? መልሱን ለእናንተ:: ማስታወሻ፦ የፍርድቤቱብን የውሳኔ ወረቀት ያንብቡ ✍️በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመስርተን ማጋለጣችን ተጠናክሮ ይቀጥላለ

በቀድሞው የቡሬ ዳሞት ብርጌድ የኮማንዶ ስልጠናውን ያጠናቀቀው ኮማንዶ አበባው አጉማስ፣ የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቀለ። ​ ወደ ጠላት በመግባት መረጃ በማሰባሰብና
በቀድሞው የቡሬ ዳሞት ብርጌድ የኮማንዶ ስልጠናውን ያጠናቀቀው  ኮማንዶ አበባው አጉማስ፣ የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቀለ። ​ ወደ ጠላት  በመግባት መረጃ በማሰባሰብና የጠላትን እንቅስቃሴና ምስጢራዊ መረጃዎች ሲሰጠን ቆይቷል። ተልዕኮውን በስኬት በማጠናቀቅ  ጂንፎ ኤስኬስ ከነ ሙሉ ትጥቁን ይዞ በመውጣት፣ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር  ተቀላቅሏል። አፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴውድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት 16/08/2018

🛑"ተጠቅሞ መጣል" የውድቀት አዋጅ‼️ በትጥቅ ትግል ታሪክ ውስጥ ትልቁ ድል የጠላት ምሽግን መስበር ሳይሆን፣ በጓዶች መካከል ያለውን መተማመን መጠበቅ ነው። አንድ ታጋይ ወደ ጦር ግንባር የሚገሰግሰው ነገ ቢወድቅ የሚያነሳው፣ ቢሰዋ ቤተሰቡን የሚደግፍ የጸና ወንድማማችነት እንዳለ በማመን ነው። ይህ መንፈሳዊ ትስስር ከላላ ግን ትግሉ የሞራል መሰረቱን ያጣል። በዚህ ፈታኝ ትግል ውስጥ የታመሙትንና የቆሰሉትን ዞር ብሎ ማየት እንደ ግዴታ ሳይሆን እንደ ትግሉ አካል ሊቆጠር ይገባል። የቆሰለን ታጋይ ጥሎ ማለፍ ወይም የተሰው ቤተሰቦችን ችላ ማለት፣ የትግሉን ዋጋ ዝቅ ያደርገዋል። "አብሮ የበላን አብሮ የሞተን አለመርሳት" የኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን የታጋይነት መመሪያም ነው። ዛሬ በደምና በአጥንታቸው ለቆሙት ዋጋ አለመስጠት፣ ነገ ለሚተካው ትውልድ ተስፋ አስቆራጭ መልእክት ያስተላልፋል። በቬትናም ትግል ወቅት የቪዬት ኮንግ መሪዎች አንድ መርህ ነበራቸው፦ "አንድም ጓድ ወደኋላ አይቀርም"። የቆሰለን ጥሎ ማለፍ እንደ ትልቅ ወንጀልና የትግል ክህደት ይቆጠር ነበር። ይህ መተሳሰር ነው የአሜሪካን ግዙፍ ጦር እንዲያሸንፉ ያደረጋቸው። በአንጻሩ፣ በታሪክ ብዙዎቹ የደቡብ አሜሪካ ሽምቅ ተዋጊዎች የከሰሙት፣ መሪዎቻቸው ከድል በኋላ ወይም በትግሉ መሀል የታመሙና የደከሙ ጓዶቻቸውን ችላ በማለታቸው የውስጥ መከፋፈልና ተስፋ መቁረጥ ስለነገሰ ነው። ማንኛውም ሕዝባዊ ትግል "ተጠቅሞ የመጣል" ባህልን ሊጸየፍ ይገባል። በትጥቅ ትግል ታሪክ ውስጥ ብዙዎች የከሸፉት ጠላት በዝቶባቸው ሳይሆን፣ በትግሉ ውስጥ ለቆሰሉና ለደከሙ ጓዶቻቸው የሚሆን ልብ በማጣታቸው ነው። "የቀደመውን ያላከበረ፣ ለሚመጣው አይበጅም" እንደሚባለው፣ ለትላንት መስዋዕትነት እውቅና የማይሰጥ ጉዞ፣ የነገውን ድል የመሸከም አቅም አይኖረውም። አመራርነት ማለት በትከሻው ላይ የወደቁትን ጓዶቹን ተሸክሞ ወደ ድል መጓዝ እንጂ፣ የቆሰሉትን እየረገጡ ፊት መሮጥ አይደለም። በቁስለኛው ደም ላይ ቆሞ ስለ ድል መስበክ ፍጹም ጀግንነት ሊሆን አይችልም። የቆሰሉትን ጓዶች እንደራስ ቤተሰብ አለመቁጠር በትግሉ ውስጥ ትልቅ ክፍተት ይፈጥራል። አመራሮች ዛሬ ችላ የሚሉት እያንዳንዱ ቁስለኛ፣ ነገ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ትግሉ እንዳይቀላቀሉ የሚያደርግ 'ሕያው ምስክር' መሆኑን ማጤን ይገባል። ለቆሰለ ጓዱ የማይራራ ልብ፣ ነገ ለሚመራው ሕዝብ ይራራል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው። ትግሉ ግቡን እንዲመታ ከተፈለገ፣ የቆሰሉትንና የተሰዉትን አለማየት እንደ ትልቅ ውድቀት ሊታይ ይገባል። "ካልተያያዙ አይጸኑ፣ ካልተሳሳቡ አይበዙ" ነውና፣ ትግሉ መካከለኛውን መንገድ መርጦ፣ የደከሙትን ደግፎና የቆሰሉትን አንስቶ መጓዝ ይኖርበታል። ድል የሚገኘው በጠላት ብዛት ሳይሆን፣ በጓዶች መካከል ባለ የማይበጠስ መተሳሰብና የህሊና ንጽህና ነው። ድል ለአማራ ህዝብ

አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር በጀግናውና ልበሙሉው ፋኖ ሻለቃ አንደበት ክንዳለም የክብር መስዋዕትነት የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ !!! አርበኛ አንደበት ክንዳለም
+8
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር በጀግናውና ልበሙሉው ፋኖ ሻለቃ አንደበት ክንዳለም የክብር መስዋዕትነት የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ !!! አርበኛ አንደበት ክንዳለም አንተ ጀግና ነህ ፤አንተ ልዩ ምልክታችን ነህ፤ አንተ የአባቶችህ ልጅ ነህ ፤ አንተ ትንሹ ገብርዬ ነህ ፤ አንተ የዚህ ትውልድ ምርኩዝ የቀጣዩም ልዩ ምልክት ሁነህ ትቀጥላለህ። የጀግና ሞቱ ክብሩ ነውና በሚወደው በሚያከብረውና እንዳባቶቹ በትህትናና በአክብሮት በሚመለከተው ህዝብ ዘንድ የክብር ሽኝት ተካሂዶለታል። ፋኖ ሻለቃ አንደበት ክንዳለም በህይወት እያለም በህዝብ ዘንድ ተወዳጂ ፣ለፍትህና ለእኩልነት የታገለ ያታገለ የተዋጋና ያዋጋ የጦር ጠበብት ነበር። ልበቀናው አንደበት ክንዳለም የጠላትን ኃይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም ሳሊ ላይ የተሰዋ ሲሆን በኃይማኖት አባቶች የፍትሀት ስነ ስርዓት፣የህይወት ታሪኩ እንዲነበብ ተደርጎ፣ አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮርም ዛሬ ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም የጀግና እና የክብር ሽኝት በወታደራዊ ትርኢት አስፈጽሞለታል። ጀግና ሞቱ የጀግንነት ነው! ትግልህን እንጠብቃለን! ቃልህንም እናከብራለ! ነፍስህን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን!!! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል !!!

""ሚያዚያ 2016 ዓ.ም በጀግንነት ለአማራ ህዝብ ክብርና ነፃነት ሲል አንድያ ነፍሱን አሳልፎ የሰጠ አርበኛ ያስቀመጠው ለአማራ አርበኞች የአደራ ቃል።"""    እኔ በምድር ላይ በህይዎት የመኖር እድሌ 99% አብቅቷል በህይዎት የመኖር እድሌ ጠባብ እንደሆነ ያረጋገጥኩት ዛሬ ላይ ሳይሆን የአማራ ህዝብ መከራና ግፍ ሲበረታ የህዝቤን ክብርና ነፃነት ለማስመለስ ከትግል ጓዶቸ ጋር ምድራዊ የተደላደለ ኑሮዬን ትቸ ጫካ ዱር ቤት ካልኩበት ዕለት ጀምሮ ነው።እኔ የሚቆጨኝና ሞቼ እንኳ አፅሜ ዕረፍት የማያገኝ እንዲሁም የሞት ሞት የምሞተው የግፈኛውና የመከረኛው ህዝባችንን ነፃነት ሳናረጋግጥ የጀግና አርበኛ አባቶቻችንን ታሪክ ሳንደግም እንዲሁም ታሪክ አስወቃሽ ሆነን የጀመርነውን የህልውና ትግል ከዳር ሳናደርስ ከንቱ የቀረ እንደሁ ነው።ይህ ከሆነ ደግሞ የአማራ ህዝብ የባርነት ቀንበርን ይበልጥ እንደሚያከብደው ምንም ጥርጥር የለውም።አርበኛ መስለው እርስ በርሳችን እንድን በላላና አላማችንን ከግብ እንዳናደር ስ ሽኩቻዎች ሊገጥሙን ይችላሉ ይህ ደግሞ የትግል አንዱ ባህሪ ነው ቀድመን ልናስብበት እና መላ ልንይዝለት ይገባል።ጥበበኞችና አስተዋዮች ካልሆን ግን ትግል በባህሪ የራሱን ሰው የመብላት ሱስ አለበት።ይህ እንዳይሆን ስጋት አለኝ የሆነው ሆኖ ግን ይህ መከረኛ ህዝብ ብሏል አርበኛው በእኛ አጥንትና ደም ነፃነቱንና ክብሩን መልሰን እንዲሁም ከመከራና ግፍ አላቀን ለቀጣይ ተተኪ ትውልድ ማስረከብ አማራዊ ግዴታ አለብን ብሎ ነበር። ሚያዚያ 4/2018 ዓ.ም ዲማ ጊዮርጊስ ላይ ልክ እንደ አባቶቹ ቃሉን አክብሮ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲል የክብር መስዋዕትነትን በመክፈል የጀግንነት አክሊሉን የተቀዳጀው አርበኛ ኢንጅነር ተሾመ ለገሰ አፈሩ ይቅለለው             ተሾመ ይለዋል አባቱ ለገሰ፣              ምናው በጠዋቱ ከሞት ገሰገሰ። እናም አንባቢያን የአርበኛውን ዕይታ እንዴት አያችሁት? ፍርዱን ለእናንተ ልተው።

ሁለት ክላሽ ከአራት መቶ (400)የክላሽ ተተኳሽ ጋር በመያዝ ተቀላቅለውናል ። የአብይ አህመድ እና ብርሀኑ ጁላ ጦር ከምስራቅ ዕዝ ፣303ኛ ኮር፣99ኛ ክፍለ ጦር 3ሬጅመንት አባል የነበሩት ጽዮን ደ
ሁለት ክላሽ ከአራት መቶ (400)የክላሽ ተተኳሽ ጋር በመያዝ ተቀላቅለውናል ። የአብይ አህመድ እና ብርሀኑ ጁላ ጦር ከምስራቅ ዕዝ ፣303ኛ ኮር፣99ኛ ክፍለ ጦር 3ሬጅመንት አባል የነበሩት  ጽዮን ደምሴ እና ተሻገር ሚልኪያስ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮርን 33ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል ። ብልፅግና ጎንጅ ቆለላ ላይ የተደሠሰሰበትን ሀይል ይተኩልኛል ብሎ ከዳንግላ ካንፕ ወደጎንጅ በቅርቡ ያመጣቸው እንደሆኑ የሚናገሩት ወታደሮቹ ከመደምሰሳችን በፊት እንዲያተርፉን የተማፀንናቸው አካላት አትርፈውናል ሲሉ ከጭንቀት መውጣታቸውን አረጋግጠዋል ።  አክለውም ብልፅግና የኢትዮጵያን ወጣት ህይወት ከማስቀዘፍ ውጭ ሊያሳከካው የሚችል ግብ ያለው እና ለዛም አቅም ያለው መንግስት አይደለም ሲሉ ስርአቱን ጀንበሩ እንደጠለቀችበት አስረድተዋል  ። ▶️አዲስ ትውልድ ▶️አዲስ አስተሳሰብ ▶️አዳስ ተስፋ የ102ኛ ኮር  ህዝብ ግንኙነት