fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 393
مشترکین
+2924 ساعت
+2547 روز
+1 45030 روز
آرشیو پست ها
ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ የተሰጠ መግለጫ
+2
ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ የተሰጠ መግለጫ

ህዳር 22/2018 ዓ.ም #የተሸፈኑ_ሃቆች_ጫሂ_ያጡት_ድምፆች 🎤🎤‼️ ስርአቱ በBM በቢኤም ካባድ መሳሪያ እግራን ያጣችው ህፃን ፦ #ህፃን_ራሔል_ጌታቸው_አንማው ፃታ ሴት እድሜ=11 የ2ኛ ክፍል
ህዳር 22/2018 ዓ.ም #የተሸፈኑ_ሃቆች_ጫሂ_ያጡት_ድምፆች 🎤🎤‼️ ስርአቱ በBM በቢኤም ካባድ መሳሪያ እግራን ያጣችው ህፃን ፦ #ህፃን_ራሔል_ጌታቸው_አንማው ፃታ ሴት እድሜ=11 የ2ኛ ክፍል ተማሪ በቢቡኝ ወረዳ ኮረብታ ቀበሌ ወራሪው የአብይ አህመድ ስርአት ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ሀገር ሰላም ነው ብለው ህፃናት ተሰብስበው በቤታቸው በረንዳ ላይ እየተጫወቱ እየቦረቁ የነበሩ ሲሆን የስርአቱ ዙፋን አስጠባቂወች በተተኮሰ (BM ) ቢኤም ከባድ መሳሪያ ሙሉ ደሳለኝ የተባለች የ18 አመት ወጣት ወዲያው ሂወቷ ሲያፍ በጊዜው ተርፋ አንድ እግሯን ያጣችው ህፃን ራሔል ጌታቸው አንማው ዛሬ ላይ በችግር ውስጥ ያለች ሀይ ባይ ያጣች የምስኪን ቤተሰብ ልጅ ስለሆነች ይችን ህፃን እንደጎደኞቿ እሩጣ ያልጠገበች ስትሆን የተሻለ ህክምና እግር እንድታገኝ ሁላቹህም ቀና ትብብር እንድታደርጉላት በማለት መልክት እያስተላለፍኩ ለመርዳት የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩኝ ወላጅ አባቷን በቀጥታ የማገናኛቹህ ይሆናል። < 50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ነው ለ50ሰው ደግሞ ጌጥ ነው >> ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 22/2018 ዓ.ም

አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመውን ግፍ የተቃዎሙ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ! በማዕከላዊ ዕዝ 104ኛ ኮር 16ኛ ክፍለ ጦር 2ኛሬጅመንት አባል የነበሩ አራት ወታደሮች አገዛዙ በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመውን ግፍ በመቃዎም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነው ኮር ስር የምትገኘው ጥራሪ ክፍለ ጦርን ስለመቀላቀላቸው ክፍለጦሩ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መሩጃ አስታውቋል። ፋኖን የተቀላቀሉት ወታደሮቹ፡ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የብሔር ግጭት እያየለ መምጣቱንና በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሚፈርስበት ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተለይ በሰራዊቱ ውስጥ የአማራ ተወላጆች ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃና ግፍ እየደረሰባቸው ስለሆነ ሁሉም አማራ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባል ፋኖን በመቀላቀል አገዛዙን በመታገል አማራው እየደረሰበት ያለውን የብሔር ጭቆና እንዲያስቆም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ወታደሮቹ አክለውም፡ በአገዛዙ ውስጥ የሰራዊት ያለው አባል ተስፋ የቆረጠና ውጊያን የጠላ ነው፡ በዚህም አገዛዙ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብቷል ያሉ ሲሆን፡ የፋኖ ትግልም በተለይ አንድነት ላይ መስራት ከተቻለ በቅርቡ አገዛዙን መጣል እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሰተዋል።

#አስደናቂዉ_ኦፕሬሽን_ቲሊሊ‼ ልማደኞቹ 44ኛ ክ/ጦር ቲሊሊ ከተማ የሰፈረዉን ሆድ አደር አድማ ብተና ጭቃ አድርገዉታል‼ በዝርዝር .....! 22/ዐ3/2018 ዓ.ም
#አስደናቂዉ_ኦፕሬሽን_ቲሊሊ‼ ልማደኞቹ 44ኛ ክ/ጦር ቲሊሊ ከተማ የሰፈረዉን ሆድ አደር አድማ ብተና ጭቃ አድርገዉታል‼ በዝርዝር .....! 22/ዐ3/2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና በእናት ጡት ቆራጮች ተመርቶ የመጣው የአገዛዙ ኃይል በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ተደመሰሰ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር  አካል በሆነው ግዙፉ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ለመሰንዘር አዳሩን ሲጓዝ  አድሮ ዛሬ ህዳር 22/2018 ዓ/ም  ቀጠናው ላይ ተመትቷል። ሰሞኑን በፋኖ ስም የአማራ ህዝብን ሲዘርፍና ሲያዘርፍ ቆይቶ ምረሽ የገባው አብነት አለምነህ እና ግብረ አበሮቹ መሪነት በአራት አቅጣጫ ማለትም ከጎንደር፣ ከጠዳ ፣ ከማክሰኝት እና ከደጎማ ከተሞች በማሰባሰብ  ወደ ጎንደሬ በጋሻው ቀጠና የገባው የአገዛዙ ቅልብ አራዊት ዳዋ ዳሞት ፣ ምንዝሮ  እና ቡርቧክስ ላይ ተመትቶና ተዋርዶ ተመልሷል። ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት  ጀምሮ  እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በተደረገው በአውደ ውጊያው ፋሲለደስ ፣ቃኘው እና ጎንደር ብርጌድ የተሳተፉ ሲሆን በኦፕሬሽኑ ከ12 በላይ ጠላት ላይመለስ ሲሸኝ ከ17 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፋኛ  ቆስለዋል።   ለከሀዲዎችና ለዘራፊዎች የሚበረከክ ቁመና የለነም ያሉት  ጎንደሬ በጋሻዎች ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ጠላትን ከበባ ውስጥ አስገብተው  በአለበት እንዲቆም አስገድደውታል።                  ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን  !!!    የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ  ታድሎ ደሴ                                     /ካስትሮ/                ህዳር 22/2018 ዓ.ም

#ፋኖ_ከትግሉ_ጎንለጎን_የህዝባችን_መሰረተልማት #ስራወችን_የማስተባበር_ስራ_እየሰራ_ይገኛል። ‼️ ህዳር 22/2018 ዓ.ም #ከዲማ_እስከ_ጠልማ_ቀበሌ_የመንገድ_ጥገና የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር የእነማይ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት ጠላትን ስቦ ከማስወጣት፣ ከአውደ ውጊያዎች ጎን ለጎን በእነማይ ወረዳ ከዲማ እስከ ጠልማ ያለውን የፈረሱ መንገዶችን ጥገና የሚያደርጉ ተቋማት እና ድርጅቶችን ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የክትትል እናድጋፍ የማስተባበር ስራ እየሰራ ይገኛል። ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ የመሰረተልማት ጥያቄወች ለመመለስ የሚሰሩ ማንኛውንም ድርጅት እና ተቋማት ፋኖ በሚያስተዳድራቸው ቀጠናወች ሙሉጥበቃ ድጋፍ የማስተባበር ስራ የምናደርግ መሆኑን በመገንዘብ የጋራ አማራዊ ግዴታችን እንወጣ። አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስተስፋ! ህዳር 22/2018 ዓ.ም የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

ወታደሩ አንድ ስናይፐር ከነ ሙል ተተኳሹና አንድ መገናኛ ራዲዮ እንደያዘ ፋኖን ተቀላቀለ! የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ሆኖ ሲያገለግል የነበረው አስር አለቃ ደጉ ከ48ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሻለቃ የአገዛዙን
+1
ወታደሩ አንድ ስናይፐር ከነ ሙል ተተኳሹና አንድ መገናኛ ራዲዮ እንደያዘ ፋኖን ተቀላቀለ! የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ሆኖ ሲያገለግል የነበረው አስር አለቃ ደጉ ከ48ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሻለቃ የአገዛዙን ግፍና መከራ በመፀየፍ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነውን ተከዜ ክፍለ ጦርን አንድ መገናኛ ሬድዮን ጨምሮ ስናይፐር ከነ መሉ ትጥቁ በመያዝ ህዳር 22/2018 ዓ.ም ተቀላቅሏል ሲል ዕዙ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

ሂዳር 22/2018 ዓ.ም #በየቀኑ_የጠላት_ሀይልእየፈረሰ_ወደፋኖ_እየተቀላቀሉ ነው የአገዛዙ ሰራዊት 64ክ/ጦር 74ኛእና 54ክ/ጦርን ከእነ ሙሉትጥቃቸው ተቀላቅለዋለ። 1ኛ.ፍቅሩ ድረስ 2ኛ.ካቻ ፈረደ
+4
ሂዳር 22/2018 ዓ.ም #በየቀኑ_የጠላት_ሀይልእየፈረሰ_ወደፋኖ_እየተቀላቀሉ ነው የአገዛዙ ሰራዊት 64ክ/ጦር 74ኛእና 54ክ/ጦርን ከእነ ሙሉትጥቃቸው ተቀላቅለዋለ። 1ኛ.ፍቅሩ ድረስ 2ኛ.ካቻ ፈረደ 3ኛ.አበራ ጫልቂሳ 4ኛ.ሞላልኝ መልካም የተባሉ የአገዛዙ አርመኔዊ ሰራዊት አባላት ከ6ኛ ዕዝ ከ14ኛ ክ/ጦር 602ኛ ኮር 1ኛ እሬጅመንት እና 3ኛ እሬጅመንት አባል የነበሩ ህዳር 22/2018 ዓ.ም እነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ እና እናርጅ እናውጋ ፈለገ ብርሃን ከተማ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በመውጣት ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስተስፋ የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 22/2018ዓ.ም

መብረቅ ክፍለጦር ወግዲ ወረዳ ላይ ከፋሽስቱ አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ጋር በመፋለም ድል አስመዘገበ:: ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለጦር ወግዲ ወረዳ ልዩ ቦታው ወደ ጎረንጅ አቅጣጫ ማጥቃት ካደረገው ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት 105ኛ ክፍለጦር እንዲሁም አድማ ብተናና ሚሊሻ በአገዛዙ አጠራር ጥምር ጦር ጋር ህዳር 21/2018 ዓ.ም ጧት 1:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 1:00 ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል:: ሙሉ ቀን በዋለው ፍልሚያ መብረቆቹ የፋሽስቱ አገዛዝ መመኪያ የሆነውን ቅልብ ኮማንዶ ማጥቃቱን በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ በርካታ ቁጥር ያለው ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ቀጠናቸውን በማስከበር ድል አስመዝግበዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 22/2018 ዓ.ም

አሳዛኝ ዜና የቅኔ፣ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን የመጻሕፍትና የአቡሻኽር መምህር የነበሩት የናዳ ማርያምና ክብረ ደናግል ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት ሊቁ የኔታ ይባቤ አረፉ።
+1
አሳዛኝ  ዜና የቅኔ፣ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን የመጻሕፍትና የአቡሻኽር መምህር የነበሩት የናዳ ማርያምና ክብረ ደናግል ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት ሊቁ የኔታ ይባቤ አረፉ።

የነዳያን ከለላቸው፤ የሕሙማን ተስፋቸው፤ የኅዙናን መረጋጊያቸው፤ የመምህራን ሞገሣቸው፤ የምእመናን መመኪያቸው፤ ሊቀ ብርሃናት የኔታ ይባቤ ዕረፍትዎትን ስንሰማ፦"ልጆችዎ ሁሉ አልሞትነም ብለን አንዋሽም
የነዳያን ከለላቸው፤ የሕሙማን ተስፋቸው፤ የኅዙናን መረጋጊያቸው፤ የመምህራን ሞገሣቸው፤ የምእመናን መመኪያቸው፤ ሊቀ ብርሃናት የኔታ ይባቤ ዕረፍትዎትን ስንሰማ፦"ልጆችዎ ሁሉ አልሞትነም ብለን አንዋሽም።" ©የኔታ ገብረመድን እንየው

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ንፁሀን አማራዎችን በግፍ እየጨፈጨፈ ቀጥሏል። የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ አንድ አቶ ብርሀኑ ተሾመ የተባለ አባት ከባለቤቱና ከአራት ልጆቹ ፊት በግፍ የገደለ ሲሆን ሁለት ዲያ
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ንፁሀን አማራዎችን በግፍ እየጨፈጨፈ ቀጥሏል። የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ አንድ አቶ ብርሀኑ ተሾመ የተባለ አባት ከባለቤቱና ከአራት ልጆቹ ፊት በግፍ የገደለ ሲሆን ሁለት ዲያቆኖችንም ባደባባይ ረሽኗል። ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ንፁሀን አማራዎችን በግፍ ባደባባይ እየረሸነ ያለ ሲሆን ዛሬ ህዳር 21/2018 ዓ.ም ሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ መርጦ ከተማ ላይ አቶ ብርሀኑ ተሾመ የተባሉ የ48 አመት አባት ከባለቤቱና ከልጆቹ ፊት መኖሪያ ቤቱ ላይ በዱላ ደብድበዉ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዉታል። በተመሳሳይ ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ አርጎባ መደሃኒአለም ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ሁለት ዲያቆኖች በፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት በአደባባይ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተረሽነዋል። እድሜቸዉ 15 እና 18 አመት የሆኑት እነዚህ ታዳጊዎች ዲያቆንና የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሲሆኑ የቀብር ስነስርአታቸዉም እዚያዉ ሲያገለግሉበት በነበረዉ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። ፋሽስቱ አገዛዝ ወጣቶችን ዩኒቨርስቲና ትምህርት ቤቶች ብሎም ሃይማኖታዊ ቦታዎች ላይ ሳይቀር እያፈሰ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እያስገባ ያለ ሲሆን ሰሞኑን ወልዲያ ከተማ ከአፈሳዉ ለማምለጥ የሞከሩ ንፁሀን ወጣቶችን ባደባባይ በጥይት ደብድቦ መግደሉ ይታወቃል። ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ንፁሀን ላይ ነፃ እርምጃ የመውሰድና በግፍ የመጨፍጨፍ ተግባሩ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፋኖ ትላልቅ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ከተጎናፀፈበት ዘመቻ "አባ ናደዉ"በኋላ ፋኖዉይ መቋቋም ሲያቅታቸዉ ንፁሀኑን መጨፍጨፍ በሚል በርካታ የሰዉ ህይወት በተናጠል በጅምላ እያለቀ ይገኛል። አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ

#የጥንቃቄ_መረጃ‼️ የአገዛዙ አብይ አህመድ ሰራዊት በቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር በ64ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና በዚህ ሰዓት ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ከደጀን የትኖራ ቀበሌ እና ከባሶ ሊበን ወረዳ የጁ
+1
#የጥንቃቄ_መረጃ‼️ የአገዛዙ አብይ አህመድ ሰራዊት በቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር በ64ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና በዚህ ሰዓት ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ከደጀን የትኖራ ቀበሌ እና ከባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ መካናይዝድ ጦር #መድፍ እና ሌሎችም ከባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ ቢቸና ከተማ የገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ከምሽቱ 3:30 ሰዓት ከቢቸና ከተማ ወደ ሸበል በረንታ ወረዳ መስመር እንደሽት ቀበሌ ያለ የሌለ ሀይሉን በእግረኛ እና በተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እያደርገ ይገኛል።

~አሳዛኝ ዜና! አረመኔው የብልጽግና ስብስብ በንጹሐን ላይ የሚያደርሰውን ግድያ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ከሰሞኑ በበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ክፉኛ የተመታው የደብረ ኤልያሱ የብልጽግና ስብስብ ደርሰህ
~አሳዛኝ ዜና! አረመኔው የብልጽግና ስብስብ በንጹሐን ላይ የሚያደርሰውን ግድያ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ከሰሞኑ በበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ክፉኛ የተመታው የደብረ ኤልያሱ የብልጽግና ስብስብ ደርሰህ እውነቱ የተባለን አካል ጉዳተኛ ዜጋ በግፍ ረሽኖታል። ደርሰህ እውነቱ ቀደም ሲል በደረሰበት የሞተር አደጋ የአካል ጉዳት ደርሶበት በሕክምና ያገገመ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ሊድን ባለመቻሉ በክራንች እየተጓወ በደብረ ኤልያስ ሆስፒታል በር ላይ ጁስና ውሃ በመሸጥ ራሱን የሚያስተዳድርና ምንም አይነት ፖለቲካዊ ሱታፌ ያልነበረው ቢሆንም ደም ግብሩ የህነው አረመኔው የብልጽግና ሠራዊት ሕይወቱን በትናንትናው ዕለት ነጥቆታል። አካል ጉዳተኞች መረዳት ሲገባቸው በግፍ የሚገደሉበት ሥርዓት ብልጽግና። ይህ ሥርዓት ከተማዋን ከወረረ ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት በከተማዋ ይኖሩ የነበሩ የአዕምሮ ሕሙማንን ሳይቀር  በአደባባይ በግፍ መረሸኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ህዳር 21/2018 ዓ.ም የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በዛሬዉ ዕለት ከ8 በላይ የአገዛዙ ሰራዊትን በመደምሰስና ከ17 በላይ የሚሆኑ የአገዛዙ ሰራዊትን በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፏል :: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው  ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ባደረገው አውደ ዉጊያ ከ8 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ  ከ17 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት 12ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት፣የ65ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት ኃይልና የ65ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ በጥምረት አንድ ዙ-23 እና አራት ዲሽቃ በመያዝ መነሻውን ከላስታ ወረዳ ብልባላ ከተማ በማድረግ ህዳር 16/2018 ዓ/ም ዳቢያና አሞራ ደብር ድባቅ ተመትቶ መመለሱ ይታወቃል። በዚህ ሽንፈቱ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ከህዳር 18 ጀምሮ ኃይሉን ጨምሮ በድሮን ታግዞ  ውጊያ ያደረገ ቢሆንም  ተወርዋሪዎቹ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ሦስት ቀን ሙሉ ምሽግ መከላከል በማድረግ በአራተኛው ቀን ዛሬ ህዳር 21/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በጠረዛና መዛርድ ግንባር በቆረጣ በመግባት በተደረገ አውደ ውጊያ የጠላት ኃይል ወደ ነበረበት ምሽግ ተቀጥቅጦ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ  ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ህዳር 21 / 2018 ዓ.ም

ከማሕበረሰቡ ምንም አይነት አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጥ ስብሰባው ተበትኗል። በዛሬው ዕለት እነ አረጋ ከበደ(ቀንድ አውጣ) ተገኙበት በተባለው ስብሰባ ከተሰብሳቢው ማሕበረሰብ ምንም አይነት አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጥ ሰብሰባው ተበትናል። ሕዝባዊ ቅቡልነትን ያጣው የዓብይ አሽከሩ የብልጽግና ስብስብ ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ተላላኪ ሚሊሻዎቻቸውን ጋቢ አልብሰው ከሕዝቡ ጋር በመቀላቀልና ያስጠኗቸውን ሀሳብ እንዲናገሩ በማድረግ ሕዝቡ እንዲህ አለ ለማለት ሞክረዋል። በመድረኩ የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ አስመልክቶ አሉታዊ ሀሳቦች እንዲነሱ የሚጋብዙ አጀንዳዎች የተዘረጉ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ በኢ/ኦ/ተ/ቤ /በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የደብረ ኤልያስ ወረዳ የብሔረ ብጹዓን አጼ መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳምን ድጋሚ ለማውደም ብልጽግና እያደረገ ባለው ሙከራ ሕዝቡ ስለ ገዳሙ የጥላቻና አሉታዊ ሀሳቦችን እንዲያንጸባርቅ  ተሞክሯል። ይሁን እንጅ የዚህን ስብስብ እኩይ ተግባር የተረዳው ሰፊው ማሕበረሰብ ምንም አይነት ሀሳብ ሳያወጣ ከመቅረቱም በላይ በተነሱ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደ ብልጽግና ተንኮል ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን እውነታ ተናግሯል። የመሰከሩ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች አካላት በዕለቱ ስብሰባውን በመሩት አመራሮች እንዲዋከቡና ዝም እንዲሉ ተደርገዋል። በዚህም ምክንያት ያንን አሽከር ሚሊሻቸውን ጋቢ በማልበስ ከማሕበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀልና የፋኖን መልካም ገጽታ የሚያጎድፉ ሀሳቦችን በማንሳትና ገዳሙን ባልዋለበትና በማይገልጹት ክሶች በመክሰስ ድጋሚ ለጥፋትና ለውድመት እንዲዳረግ ለጸረ እምነቱ የዓቢይ መንግስት መንገድ ጠራጊ ሆነዋል። ገዳሙን በተመለከተ በብልጽግናና በደጋፊዎቹ የሚወራው ወሬ ምንም መሠረት የሌለውና ድጋሚ ገዳሙን ለማወደም ጸረ እምነቱ ብልጽግና እየሄደበት ያለው የሴራ ፖለቲካ መሆኑን ሀቁን የተናገሩ የሃይማኖት አባቶች በዕለቱ ስብሰባውን በመሩት የክልል የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲዋከቡና ዝም እንዲሉ የተደረገ ሲሆን ገዳሙ ዳግመኛ መመታት እንዳለበት እኒህ ጸረ እምነት የሆኑ ሆዳም አመራሮች በዛቻ ተናግረዋል። ይህን ጉዳይ አስመልክቶም አስቀድሞ በዞኑ አስተዳደር ኃላፊ ተብየና በከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተደረገ ሕዝባዊ ስብሰባ  ገዳሙን በተመለከተ ከማሕበረሰቡ አፍራሽ ሀሳቦች እንዲነሱ ተሞክሮ ሳይሳካ መቅረቱ ልብ ይሏል። N.B የአጀንዳው ዋና ዓላማም ጸረ እምነቱ የዓብይ መንግስት ለሚያደርሰው ጥፋት ሕዝባዊ ሽፋን ለማግኘት መሆኑ ግልጽ ነው። ህዳር 21/2018 ዓ.ም ድል ለአማራ ፋኖ! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

ኅዳር 21/2018 ዓ.ም *** በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች የመልሶ ማደራጀት አፈጻጸም ሂደትን የኮሩ አመራሮች በተገኙበት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ