es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 383
Suscriptores
+724 horas
+2667 días
+1 44330 días
Archivo de publicaciones
ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ የ64ኛ ክፍለ ጦር እግረኛ ሰራዊት በሸበል በረንታ በደማቅ ሁኔታ ተመረቁ። ህዳር 23/2018 ዓ.ም የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራት ያሰለጠናቸውን የእግረኛ ሰራዊት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ የሽፈራው ገርባው ልጆች ለ5ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ አስመረቀዋል። በቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ስር የሚገኘው 64ኛ ክፍለ  ጦር የእግረኛ ሰራዊት ለማስመረቅ በክብር የተገኙት የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበርሰብ በተገኙበት በሸበል በረንታ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል። የተከበራቹህ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች የተከበራቹህ የሸበል በረንታ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የተከበራቹህ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት የተከበራቹህ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በዚህ ፕሮግራም የተገኛቹህ የከተመዋ ኖሪዎች እንዲሁም የክብር እንግዶች የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ዙር የእግረኛ ሰራዊት የምረቃ ፕሮግራም እንኳን በሰላም አደረሳቹህ አደርሰን። በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኛቹህ የክብር እንግዶች ክብራት እና ክብሯን እንዲሁም ተመራቄ የፋኖ አባላት እኛ እናተ እንዲህ የምንሰባሰበው፣ የምንደራጀው፣ የምንሰለጥነው ለሁላችንም የጋራ የሆነ ጉዳይ በየቤታችን ስላለን ነው? ሁላችንም እንድንደራጅ እና እንድንሰባሰብ ካደረጉን አንኳር ጉዳዩች ውስጥ ሰርቶ መብላትን ያስተማረው፣ ኢትዮጵያ ከውጭ ወራሪ እና ከውስጥ ሰላቶ እና ባንዳን በማፅዳት ሀገር የገነባው የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በራሱ ሀገር፣ በእራሱ እርስት ሲያሻቸው በሀይማኖቱ፣ ሲያሻቸው በዕርስቱ፣ በማንነነቱ ጣልቃ እየገቡ የአማራን ህዝብ ከ50 ዓመት እና ከዛ በላይ እረፍት በመንሳት በገዛ ሀገሩ እንዳይኖር ተደርጓል። ሀገር መስራቹ፣ፊደል የቀረፀው፣የእራሱ እምነት፣ የእራሱ ባህል እና እሴት፣የእራሱ ወግ ያለው ለበርካታ ዘመናት የኢትዮጰያን ዳር ድንበር አስከብሮ የቆየው፣ በአራቱም መዓዘን ደሙን አፍሶ አጥንቶ የከሰከሰው ታላቁ የአማራ ህዝብ ዛሬ ላይ በገዛ ሀገሩ፣ በገዛ እርስቱ ባይተዋር ሆኖ በጅምላ ይገደላል፣ በጅምላ ይሰደዳል፣ በጅምላ ይፈናቀላል፣ ሀብት ንብርቱ በወራሪዎች እየተወረሰ ይገኛል። ኢትዩጰያን ያሻግራሉ፣ሀገር ይመራሉ በህዝብ ተወዳጅ የነበሩ የአማራ ሙህራን በጅምላ በጨለማ እስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። እንደ ምሳሌ ብንጠቅስ የመንጋው መድሀኒት የፖርላመው ንጉስ አቶ ክርስትያን ታደለ፣ አቶ ዩሀንስ ቦያለው እና መ/ር መስከረም አበራ እና ሌሎች ሙህራን በጅምላ በጨላማ እስር ቤት ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ። የአብይ አህመድ አረመኔዊ ስርዓት የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የአጭር እና የረጅም ግዜ ዕቅድ በማውጣት በአለም ላይ ተደርጎ የማይታወቅ ለማየት የሚሰቀጥጡ ዘግናኝ እና አስነዋሪ ተግባር እየፈፀሙብን እና እያስፈፀሙብን ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ድርጊት የሚፈፅሙት ከአማራነታቸው ይልቅ ሆዳቸው የግል ጥቅማቸው በልጦባቸው ባንዳ በሆኑ አመራሮች እና ሚሊሻዎች ጭምር ነው። ክቡራን እና ክቡራት እንዲሁም ተመራቂዎች ይህ ድርጊት የሚፈፀመው አማራ በመሆናችን ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ በአማራነቱ ብቻ እንዲጠፋ የተፈረደበት ህዝብ ከሆነ ውሎ አድሯል። በመሆኑም የአማራ ህዝብ ህዝብ መዳኛ መንገድ አንድም በክንዱ አንድም በእግዚአብሄር ሀይል ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የመኖር መብቱን ማስከበር የሚችለው አማራ አንድ ሆኖ በጋራ መታጋል ስንችል ብቻ ነው። በመሆኑም ይህንን የአረመኔዊ አገዛዝን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ነቅሎ ለመጣል የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጆች በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አደረጃጀት ስር ታቅፈው በተለያዩ ቦታዎች የውጊያ እቅዶችን በማቀድ እርሀቡ፣ የውሀ ጥሙ፣  ብርዱ፣ ሙቀቱ ሳይበግራቸው በረካታ ውጊያዎችን በማድርግ በርካታ ገድል ሲፈፅሙ  ቆይተዋል። በዚህ ሰዓት 64ኛ ክፍለ ጦር በድርጅቱ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የሚሰጣቸውን የትኛውም አይነት ወታደራዊ ግዳጅ/ሚሽን በብቃት ከመፈፀም ጎን ለጎን በዚህ ፈታኝ ወቅት ህዝባችንን በመልሶ ማደራጄት፣ወታደሩን በመልሶ ማሰልጠን፣ ወጣቱን በልዩ ልዩ ስልጠና እና የውትድርና ሳይንስ በመስጠት ግዙፍ ሀይል እየገነባ ይገኛል። በዚህም ለጠላት ሀይል ቅስም መስበሪያ ለወዳጅ ደስታን ይዞ መጥቷል። በሸበል በረንታ እና በእነማይ ምድር ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ሀገራችንን ከቀኝ ግዛትና ከባርነት ነፃ አድረገው ለትውልድ ያስረከቡበት የአረበኞች መሰባሰቢያ ከሆኑት ውስጥ ይህ አካባቢውን አንዱ ነው። በዛሬው እለት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ለመሰባሰባችን ምክንያት የሆናቹህ የ5ኛ ዙር እግረኛ ተመራቂ አባላት እናተ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ፣ የሽፈራው ገርባው፣ የእጅጉ ዘለቀ ልጆች ናቹህ። በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው ጀግኖች የትግል ጓዶች ከጠላት ጋር ተናንቀው ብዙ ዋጋ ከፈለው ተለይተውናል። በመሆኑም ድርጅታችንን እና መሪያችንን ከጥግል ጠላፊዎች እንድትጠብቁ አደራ እያልኩ እኛ ለእናተ አደራ የምንሰጣቹህ መሪዎቻችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ውጣ ውርድ፣ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ትግል ተቀብላቹህ የድል ባለቤት እንድታደርጉት አደራ እንላለን። በመጨረሻም በመላው አማራ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአማራን ህዝብ የአረመኔዊ ድርጊት በመስራት በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን ሁላችንም በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኝ በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ ለተመራቂ ፋኖዎች መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለሁ። እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን፣ የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!         ህዳር 23/2018 ዓ.ም ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64 ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

ቴዎድሮስ ዕዝ ዛሬ! _፩ 88ኛ ክ/ጦር በጠላት ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን አካሄደ! በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር አካል የሆነችው 88ኛ ክ/ጦር በአዲስ በተዋቀረ ማግስት በጠላት እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የተሳካ የማጥቃት ኦፕሬሽን አካሄዷል። ህዳር 22/2018 ዓ.ም ጠላት የለመደ የጥፋት በትሩን ህዝባችን ላይ ለመፈፀም ከሌሊቱ 9 ሠዓት ከወምበርማ ርዕሰ ከተማ ሽንዲ መነሻውን አድርጎ ወደ ኮኪ ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ሲሆን በ109ኛ ኮር 88ኛ ክፍለ ጦር በተደረገ የማጥቃት ኦፕሬሽን በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። የአናብስቶቹን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ መጣበት ፈርጥጧል። __፪ ሶስት(03) የአድማ ብተና አመራሮች ተረሸኑ። ብልፅግና የራሱን ጦሩን መረሸን ጀምሯል። የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ህዳር 21 ቀን በመርጡለ ማርያም ዙሪያ በተካሄደ አውደ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የብልፅግና ቅጥረኛ ሰራዊት በወቅቱ ውጊያውን ከትእዛዝ ውጭ መርታችኋል በሚል 3 የአድማ ብተና አመራሮችን ረሽኗቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ዉጊያ ላይ ከተደመሰሱት አንድ ቲም አድማ ብተና እና ምኒሻ በተጨማሪ በጠና ቆስሎ የነበረው 50 አለቃ ይርሳው የአድማ ብተና አዛዥ ተጨርሶ የቀብር ስነስርዓቱ በ22/03/20/8 ዓ/ም በመርጦለማርያም ከተማ በምትገኘው ማርያም ቤተክርስቲያን በወታደራዊ ስርዓት ከቀኑ በ6:00 ተፈፅሟል። _፫ ከ10 በላይ የአረመኔው አገዛዝ ወታደሮች በ77ኛ ክፍለ ጦር ተርቦች ተደመስሰዋል። አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር በቀን 22/03/2018 ዓ/ም ማንኩሳ ዛባ ላይ ከ10:00 -12:00 ሰዓት በተደረገ አውደ ውጊያ ከ10 በላይ የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሀይል ሲደመሰስ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የጠላት ሀይል ከባድና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። ሽንፈቱን መቀበል ያቃተው ፈሪው የአብይ ሰራዊት 01 ንፁሃን እናት በጥይት አቁስሏል። በዚህ ኦፕሬሽን ሁለት(2) ክላሽ ከእነ ተተኳሹ ተማርኳል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ህዳር 23/2018 ዓም

የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ላይ ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ማለዳ 3:00 ጀምሮ እስከ ቀን 6:00 ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር በመፋለም ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: ጠላት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ከተማን ለመቆጣጠር ከኮንና ጋሼና አንድ ክፍለጦር ዙ23ን ጨምሮ እንዲሁም ከወገል ጤና አንድ ክፍለ ጦር ዙ 23 ጋር ወደ ዳውንትና ፀሃይ መውጫ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ከምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለ ጦር እና ከደጋው መብረቅ ኮር ከፅናት መክትና ሰንጥቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ ሻለቆች እንዲሁም ሌሎች በመደራጀት ላይ ያሉ አሃዶች በጥምረት የጠላትን ሰራዊት ለጊዜው በስም ያልታወቁ አመራሮችን ጨምሮ በመደምሰስና በማቁሰል ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ብሎም ቀጠናውንና ከተሞቹን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: በዚህ በድንቅ መናበብ በተመዘገበ ታላቅ ፍልሚያና ድል የጠላት ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ የተመታ ሲሆን አስከሬንና ቁስለኛውንም እያነሳ ወደመጣበት አቅጣጫ ሽሽቷል:: በተጋድሎው በመደራጀት ላይ ያለ የልዩ ዘመቻ አሃድም የተሳተፈ ሲሆን ከልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር አንድ ጓድ በውጊያ መሃል ደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብድ ሰርተዋል:: በዚህ ታላቅ ተጋድሎ ከባድ ምት የተመታው አገዛዙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ሲሆን የደላንታና የወገል ጤና የብልፅግና ካድሬዎችና አመራሮች ተከበናል መላም የለን እያሉ ወደ ደሴ ከተማ መሸሽ ጀምረዋል:: ውጊያው አሁንም ሌሎች አሃዶች ተጨምረውበት ተጠናክሮ ቀጥሏል:: ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመጣለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 23/2018 ዓ.ም

በገባሪዎች እና በክህደት አበጋዞች የሚደናቀፍ ትግል የለም!! ************* የአማራ ህዝብ ትግል ከግለሰቦችም ከፓርቲም በላይ ነው። በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ ትግል የለም!! ትግላችን የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል ነው። እኩይ ቡድኖች እና ምስለ አማራ ታጋዮች ከውስጥ እና ከውጭ በሚያደርጉት ያልተገባ ነውር የሚቆም ትግል አልጀመርንም። የቁስ ስቀቀናሞች እና የስልጣን ጥመኞች የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ሲሰልሉ ቆይተው ወደ ጠላት ካምፕ መግባታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል የአማራ ህዝብ ከገጠመው ብሔራዊ የህልውና አደጋ ለመውጣት የተጀመረ አብዮት እንጅ ድንገት ግለሰቦች ወደ ጠላት ካምፕ ዘው ብለው ስለገቡ የሚቀለበስ የህዝብ ትግል አልጀመርንም!! አማራነት/ሞት በማለት ሲልከሰከስ የነበረው ሁሉ ራሱን በቁስ እና በስልጣን ያረካበትን ነውረኛ ሁሉ በታሪክ የምንፋረደው ይሆናል። ስለሆነም ከሃድዎች ዛሬም ነገም ይኖራሉ። ራሱን የአፋህድ መሪ ነኝ ሲል የነበረው ማስረሻ ሰጤ ለብልፅግና ዕጅ መስጠቱን ተከትሎ እዚህም አዛም የሚወሩ አሉባልታዎች መሰረተ ቢስ ናቸው። ማስረሻ ሰጤ ከጥር 2017 ዓም ጀምሮ ከመንግስት ሃይሎች ጋር እንደሚያወራ ይታወቃል። በተለይም የአማራ ፋኖን ትግል ወደ አንድ ቋት እንዳይሰበሰብ በማድረግ ረገድ ትልቁን ድርሻ የተወጣ ሲሆን ሰሞነኛው ግርግር እና እጅ መስጠትን በወገን በኩል የተደራጀ መረጃ በመኖሩ ምክንያት ተልዕኮውንም በአግባቡ የጨረሰ ሲምስለው ተሰወሮ ወደ ጠላት መግባቱ የሚጠበቅ ነው። በአማራ ህዝብ ትግል በርካታ የትግል አረሞች ተሰግስገው መግባታቸው የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ሂደቱ ጥርት እና ኩልል እያለ መጥቷል። ፅናት የሌላቸው አላማ ቢስ ግለሰቦች በሚፈፅሙት ክህደት የሚቆም ትግል አልጀመርንም። በብዙ ተግዳሮት ውስጥ ሆነን ትግላችን እናስቀጥለዋለን። ተስፋ ቆራጮች በአማራ ህዝብ ስም እየማሉ እየተገዙት የጠላት ተልዕኮ አስፈፃሚ የነበሩት ደግሞ ከትግላችን እየተነቀሉ መጥፋታቸው ይቀጥላል። ደም የተገበረበትን ትግል አዳድስ ገባሪዎች እና የስልጣን ጥመኞችም በሚያደርጉት ሴራ አሳልፈን አንሰጥም!! የብልፅግና አዳድስ ገባሪዎች በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ ተላልፈው የተሰጡ ለመምሰል የሚያደርጉት ሙከራ ተቀባይነት የለውም። በትግላችን ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉ ወዶ ገቦችንና ከሃድዎች የታሪክ ምርኮኞች ናቸው። አሰባሳቢውንና ትልቁን የአማራ ህዝብ አብዮት አሳልፎ ለመስጠት በባንዳነት ስራ ስምሪት ወስዶ ዋጋውን ማሳነስ ጥቁር ክህደት ነው። የአማራ ህዝብ ትግል ብዙ ሴራዎችን እያከሸፈ የድል ዋዜማው ላይ ይገኛል። የትግል ሾተላዮች እና ቅጥረኛ ባንዳዎችን ከትግሉ ነጥሎ ለፍርድ እንዲቀርቡ የማድረግ እንቅስቃሴያችን ተጠናክሮ ይቀጥላል። አሸናፊው ትውልድ ዋንጫውን ለመያዝ በመገስገስ ላይ ነው። መደረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል። አይበገሬው ትውልድ በፅናት ታግሎ ካሰብንበት ቦታ ይደርሳል🙏🙏 ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የመቄት ወረዳ ጊዚያዊ ሕዝብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ መምህር በሪሁን ደምሌ እና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በመቄት ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች
+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የመቄት ወረዳ ጊዚያዊ ሕዝብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ መምህር በሪሁን ደምሌ እና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በመቄት ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች በሕዝብ ሁለተናዊ ድጋፍ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን በቦታው በመገኘት አበረታቱ። በአወደ ወጊያ ጠላትን ከማንበርከክ ጎን ለጎን  ህዝብ የሚጠቅሙና የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ ልማቶች በአግባቡ እንዲከወኑ እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያለእረፍት መሰራቱ ፋኖ ህዝባዊ መሰረት እንዳለው በተግባር ያረጋገጠ ነው ሲል የዕዙ ፖለቲካ መኮነን መምህር ጋሻው ሙሉጌታ ገልጿል። የዕዙ ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ  ኃላፊ እንጅነር አራጋው ያለው በበኩሉ የመቄት ወረዳ ጊዚያዊ ሕዝብ አስተዳደር ከውይይት መድረኮች የተነሱ አስተያየቶችን ተቀብሎ በቦታው እየተገኘ  ተግባራዊ መፍትሄ መስጠቱ ትግሉን ከማህበራዊ መሰረቱ (ሕዝቡ) ጋር አስተሳስሮ ለመጓዝ በእጅጉ አስፈላጊ ነው ብሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ ህዳር 23/2018 ዓ.ም

ብልፅግና የራሱን ጦሩን መረሸን ጀምሯል! የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ህዳር 21 ቀን በመርጦለማርያም ዙሪያ በተካሄደ አውደ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው
+1
ብልፅግና የራሱን ጦሩን መረሸን ጀምሯል! የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ህዳር 21 ቀን በመርጦለማርያም ዙሪያ በተካሄደ አውደ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የብልፅግና ቅጥረኛ ሰራዊት በወቅቱ ውጊያውን ከትዛዝ ውጭ መርታችኋል በሚል 3 የአድማ ብተና አመራሮችን ረሽኗቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ዉጊያ ላይ ከተደመሰሱት 8 አድማ ብተናና ምኒሻ በተጨማሬ በጠና ቆስሎ የነበረው 50 አለቃ ይርሳው የአድማ ብተና አዛዥ ተጨርሶ የቀብር ስነስርዓቱ በ22/03/20/8 ዓ/ም በመርጦለማርያም ከተማ በምትገኘው ማርያም ቤተክርስቲያን በወታደራዊ ስርዓት ከቀኑ በ6:00 ተፈፅሟል። የአማራ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላትን እየመረጠ የመረሸን ስራውን የጀመረ ሲሆን ሁሉም አባላት በዚህ ወቅት እየተፈፀመ ያለውን የመጥፋት አዳጋ ከተቋሙ በመውጣች ከፋኖ ጋር በመቀላቀል በአማራ የተጋረጠውን የዘር ማጥፋት በጋራ እንከላከል ። አዲስትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስተስፋ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 23/2018 ዓ.ም

88ኛ ክ/ጦር የተሳካ የመጀመሪያ ኦፕሬሽኑን አካየደ! **// በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር አካል የሆነችው 88ኛ ክ/ጦር በጠላት እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የተሳካ የማጥቃት ኦፕሬሽን አካሄዷል። ህዳር 22/2018 ዓ.ም ጠላት የለመደ የጥፍት በትሩን ህዝባችን ላይ ለመፈፀም ከሌሊቱ 9 ሠዓት ከምዕ/ጎጃሟ ወምበርማ ርዕሰ ከተማ ሽንዲ መነሻውን አድርጎ ወደ ኮኪ ቀበሌ ተንቀሳቅሷል። የጠላት እንቅስቃሴ እና ፍላጎቱን በመለየት የክ/ጦሩ ወታደራዊ ኦፕሬሽናል ክፍል መሪዎች በጠላትን እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እቅድ በፍጥነት ለማቀድ ተገደዱ። ፈጣን የስምሪት ግዳጅም ተሰጠ 1ኛ ሻለቃን መሪዋ ገዳሙ መላክ የጇንቢ መስመርን ዘግቶ የመያዝ እና ማጥቃት ፣ 4ኛ ሻለቃን መሪዋ አትንኩት መግባር  የኮኪን ደቡብ አቅጣጫ በኩል በመያዝ እንዲያጠቃ፣ የክ/ጦሯ ቃኝና ማህዲስን መሪዋ ዋሲሁን ዳኛው በየርግን ዋና መስመር አድርጎ እንያጠቃ ታሳቢ ተደርጎ የጥፋት ተልዕኮን አንግቦ እራሱን የሳት ቀለበት ውስጥ የከተተውን ጠላት ኮኪ ላይ እንዲመቱ በወ/አዛዡ ቻላቸው አያና እና በዘመቻ መሪው ችሎታው አስተባባሪነት እንዲፈፀም እንዲሁም ሽንዲ ከተማ ተቆርጦ የቀረውን የጠላት ኃይል ደግሞ 2ኛ ሻለቃን መሪዋ ሐይማኖት ታዴ እና 5ኛ ሻለቃን መሪዋ አበባው ሙሉጌታ አስተባባሪነቱን የክ/ጦሩ ም/ወ/አዛዥ 50 አለቃ አብራራው ጥላሁን እና የክ/ጦ ም/ዘመቻ አብርሃም ፀጋ እንዲወስዱ ተደርጎ ሽንዲ ከተማ በመግባት ማጥቃት እንዲሁም 3ኛ ሻለቃን መሪዋ ሐይማኖት ታደሰ ሁዲት የጠላት ኃይል ተንቀሳቅሶ ስለነበር ክበባ አድርጋ እንቅስቃሴውን እንድትገታ ጠላት እንዳይወራረስ/እንዳይደጋገፍ በማድረግ 2ቱ ቦታ ላይ /ኮኪ እና ሽንዲን/ በተጠቀሰው መልኩ በደንብ መምታትን ታሳቢ ያደረገ የኦፕሬሽ ግዳጅ ተሰጥቶ በተሳካ ሁኔታ ተፈፅሟል። የክ/ጦሩ ወ/አዛዥ፣ ም/ወታደራዊ አዛዥ ዘመቻእና ም/ዘመቻ በማናበብ እና በማስተሳሰር የ3ቱን ቦታ  ግዳጅ በጥሩ ሁኔታ በበላይነት መርተውታል።  በሁኔታው የወገን ኃይል የጠላት እሳቤውን አስቶ የመታበት፤ ወታደራዊ ጠበብትነቱን ያሳየበት፣ በአጭር ጊዜ የውጊያ ዕቅድ በማውጣት ፈጣን ጥቃት መክፈት እና ውጤት ማምጣት መቻልን ያሳየበት፤ ገዢ ቦታ ከመለየት ጀምሮ ካርታ ሠርቶ እና ሠጥቶ ውጤታማ ስምሪት ማምጣትን ያሳየበት፤ ጀግንነቱን ለጠላት በድግግሞሽ በሜዳ ተግባሩ ያሳየበት፤ ጠላት ላይ የስነ ልቦና ብልጫ የወሰዱበት፤ ጠላት ሲቅረጠረጥ የታየበት ፤ ጦር መሪዎቹ  ለበላይ መሪዎቻቸው በስልክ ኃይል ካልተጨመረኝ ተከብቢያለሁ ላልቅ ነው እየለ ሲያለቅስ የተሠማበት፤ ጠላት ምሽጉ ላይ የተበላሸበት፤ .............. ወዘተ የወገን አይበገሬነት የተስተዋለበት ድንቅ ውሎ በ88ኛ ክ/ጦር ሠማይ ስር ተሰተውሏል። እንደዚህ አይነት የጠላት እሳቤን አስቶ መምታት በቀጠናው የተለመደ ሲሆን በተደጋጋሚ ሽንዲ ከተማ ተፈፅሞ ውጤት አምጧል። በዚህም ሁኔታ ጠላት ላይ ከባድ ቁሳዊ እና ሠባዊ ኪሳራ በድግግሞሽ ማድረስ ተችሏል። #አሳን ለማጥት ባህሩን ማድረቅ በሚል የክፋት እሳቤን የሚከተለው አገዛዙ በቅጥረኛ ሠራዊቱ ህዛባችን ላይ ዘርፈ ብዙ ጥፋት በተደጋጋሚ ይፈፅማል። ስለሆነም ህዳር 22/2018 ኮኪ ቀበሌ አ/አደር ፈንቴ ቸኮልን ከቤቱ ፣ሽንዲ ተዋበች ጎጥ አ/አደር ደግሰው ተረፈን ስንዴ እያጨደ እያለ ይዘው በግፍ እረሽኗቸዋል። እንዲሁም የአ/አደር ሆድሞኝ አለሙ 2 ልጆችን ኮኪ ሁኖ ወደ ዝንግስ ጎቢ ጎጥ ወርውሮ ወጣት እስቲበል አለሙና መቅደስ አለሙን( እህታማቾችን) ጤፍ አጨዳ ላይ እያሉ በሞርተር ጥቃት ከባድ ቁስለኛ አድርጓል። ቀጠናው በአዲሱ የድርጅታችን መዋቅር ለውጥን ተከትሎ የበፊቱ ወምበርማ፣ ጓጉሳ እና ወርቃቤይ ብርጌዶችን በአንድ አዋህዶ ጠንካራ እና አስፈሪ ግዙፍ ክ/ጦር ሆኖ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በአዲስ  ከተመስረተ ወዲህ የተሳካ የመጀመሪያ ኦፕሬሽን መሆኑን ክ/ጦሩ አሳውቋል።

'የትውልዱ መሪ የአማራ ፋኖ ልዩ ምልክት አቢዮተኛው አርበኛ ዘመነ ካሴ! የአማራ ፋኖ ልዩ ምልክቱ አቢዮተኛው አርበኛ ዘመነ ካሴ የትውልዱ መሪ ነው የምንለው እንዲሁ አልነበረም በዛ ጨለማ ዘመን ብቻውን ''አማራ አማራ አማራ'' እያለ አማራ ሲሏችሁ አትፍሩ ብሎ ሲናገር ብዙ ሰዎች ይሄ እብድ የሚሉም ነበሩ በጊዜው አማራ ሁኖ መገኜት በየቦታው የሚያስገድል አማራ ነኝ ብሎ መናገር ፅንፈኛ አክራሪ እየተባለ የሚሳደድበት ወቅት ነበር። ነገር ግን አቢዮተኛው አርበኛ ሩቅ አሳቢ ነውና በዚያ አስገምጋሚ ድምፁ ብቻ ጠላትን ያርደው ጀመር ብዙ ትውልድንም ከተኛበት ድንዛዜ አንቅቶ ከጎኑ እንዲሰለፍ አደረገ በሶስት ቀን የብልፅግናን መዋቅር የሚያፈራርስ አዲስ ትውልድ ፈጠረ። ነገን ቀድሞ የሚያይ መሪ በመሆኑ ዛሬ ላይ በሚሊዮን ዘመነን አፍርቷል ለዚህ ነው የትውልዱ መሪ ነው የምንለው። መሪነትን በተግባር ሜዳው ላይ በፓለቲካና ጦር ሜዳ የተዋጠለት አሰላሳይና አርቆ ማሰብ የሚችል ትግሉ ውስጥ ያለውን ሁሉ ተቋቁሞ ወደ ድል የሚገሰግስ ወታደርም ፖለቲከኛም ገንብቷል። ለዚህም ነው የአማራ ፋኖ በዚህ አጭር እድሜው በምስራቅ አፍሪካ ተገዳዳሪ ኃይል መሆን የቻለው። እስከምፃት አማራ! ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

አጭር ማሳሰቢያ ለአሽከርካሪዎች እና ለመላው ህዝባችን !! ከሰሞኑ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ መንገድ እንደሚዘጋ ተደርጎ በየ አካባቢው እየተወራ መሆኑን አረጋግጠናል ። ነገር ግን በዕዛችን መንገድ የመዝጋት ዕቅድ እንደሌለን እና መንገድ መዝጋትን በተመለከተ የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ ወይም ቴዎድሮስ ዕዝ ምንም አይነት ውሳኔ ያልወሰነ መሆኑን እየገለጽን መንገዶች ሁሉ ለተሽከርካሪዎች ክፍት መሆናቸውን እንገልፃለን ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !! በአራቱም ማዕዘን 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አገዛዙ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከከፍተኛ አመራሩ እስከ አባላት ድረስ የዕርስ በዕርስ መጠራጠር እና አለመተማመን ለመፍጠር በAI የተቀናበሩ ድምፆችን ማሰራጨቱን ተያይዞታል። በቅርቡ
አገዛዙ በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከከፍተኛ አመራሩ እስከ አባላት ድረስ የዕርስ በዕርስ መጠራጠር እና አለመተማመን ለመፍጠር በAI የተቀናበሩ ድምፆችን ማሰራጨቱን ተያይዞታል። በቅርቡ ከአፋብኃ የወረደውን የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያ መሬት ለማስነካት 7/24 እየደከሙ ያሉ አመራሮችን እርስ በእርስ እንዲጠራጠሩና በመካከላቸው አለመተማመንን ለመፍጠር የበሬ ወለደ የሀሰት ድምፅ ቅንብር ቅጅ በዲጅታል ሚሊሻዎቹ አማካኝነት እያሰራጨ ይገኛል። ከሰሞኑ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ክፍለጦር መሪ የሆነውን አርበኛ ደመላሽ መንግስቴ ከሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ አስተዳዳሪ ጋር ያደረገው ንግግር በሚል የወጣው በቴክኖሎጅ የተቀናበረ የድምፅ ቅጅ የአገዛዙን ዲጅታል ሚሊሻዎች ሸፍጥ እና ተንኮል ፍንትው አድርጎ ያሳየ ተግባር መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

#የዘጋርዲያን_ዘገባ‼️ ጓደኛዬ በወታደር (በመከላከያ) ስለተደፈረች ወደ ትግል ገባው ! ፋኖን ከተቀላቀሉ አንዷ! 👉የ83 አመት አዛውንት በድሮን ጥቃት ተገድለዋል 👉የ 5 አመት ህጻን ከመንግስት በተተኮሰ ከባድ መሳርያ በመገደሉ እናት ልቧ ተሰብሯል! በአማራ ክልል እየተፈጸሙ ስላሉ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ፣ ስላለው ሰብአዊ ቀውስ እና የፋኖ ትግል ዙርያ ዘጋድርያን (theguardian) "Inside Ethiopia’s Fano insurgency – photo essay" በሚል ርዕስ ዛሬ ባቀረበው የፎቶ ዘገባ ጸሀፊው በወሎ አከባቢ የፋኖን የማሰልጠኛ ቦታዎች እንደጎበኘ እና ህዝብ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ሰብአዊ መብት ጥሰት መረጃዎችን ማሰባሰቡን ገልጿል:: የአማራ ፋኖ አብዛኛውን (ወደ 80%) የሚሆነውን የአማራ ክልል በተለይም ገጠራማ አከባቢዎችን እያስተዳደርኩ እገኛለው ማለቱን ከመሪዎቹ መስማቱን ገልጿል:: ለምን የፋኖን ትግል እንደተቀላቀለች ከስልጠና ሜዳ ለዘጋቢው  የገለጸችው "ከዚህ ከ30 ኪ.ሜ በላይ ርቀት ላይ ካለ መንደር ነው የመጣሁት። እዚያም ከጓደኞቼ የ22 ዓመቷ ደርቤ በወታደሮች (በመከላከያ) አፍነው  እና ደፍረው ወደ ጎዳና ጥለዋታል። በዚያን ጊዜ መዋጋት እንዳለብኝ ወሰንኩኝ።" ማለቷን ዘግቦታል:: ሙሉ ዘገባውን ዘጋርዲያን ላይ ተመልከቱት። #Ethiopia: Widespread rights abuses in #Amhara region as federal forces move to battle Fano insurgency – the Guardian reveals Federal forces committed abuses in Amhara region, including kidnappings, massacres, sexual violence and attacks on humanitarian personnel, in an attempt to quell the Fano insurgency in Ethiopia’s Amhara region, the Guardian newspaper said in its photographic report. It added that the situation is out of control, with more than 2 million people in urgent need of humanitarian assistance in a region that is also hosting refugees from the war in Sudan. According to the Guardian newspaper in its photographic report, the Ethiopian federal army is regularly accused of massacres, arbitrary arrests, sexual violence and drone attacks targeting civilians in Amhara. Civilians interviewed described losing relatives to drone strikes and shelling, further fueling anger at the central government. The report notes that while the Fano militia initially enjoyed broad community support, worsening insecurity and economic collapse are gradually undermining this trust, with some Fano groups increasingly accused of extorting civilians, particularly at checkpoints. Once allies of the federal government during the Tigray war, the Fano turned against Addis Abeba after the Pretoria Agreement and the federal decision to dismantle regional special forces, which many Amhara fighters perceived as a direct threat to their security. Thousands of former special forces personnel subsequently joined the Fano, creating a fragmented armed movement estimated at nearly 20,000 fighters. The Guardian says the Fano now control large rural areas of Amhara, while federal forces are largely confined to major towns, and both sides hold alternating areas of control as fighting intensifies. https://www.theguardian.com/artanddesign/2025/dec/01/inside-ethiopia-fano-insurgency-photo-essay

ድማማ ማንጉዳ፣ አሽዋ ኬላ ፣ አዲስ ቅዳም!! ህዳር 21/2018 ዓ/ም ከለሊቱ 6:00 ጀምሮ ከአዲስ ቅዳም ፣ እንጅባራ እና ፅርጊ ከነበረዉ የጠላት ካንፕ ተለቃቅሞ የፋግታ ለኮማ ወረዳዋ ድማማ ማንጉዳን ለመዉረር በለሊት ከተንቀሳቀሰዉ የብልፅግና ታጣቂ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።  ጠላት ዛሬ ህዳር 22/2018 ዓ/ም ከሶስት የተለያዩ ቦታዎች በመነሳት ለሊት 11:00 ድማማ መድረስ ችሎ የነበረ ሲሆን ቦታዉን አስከብራ በያዘችዉ የቀጠናዉ አስተዳዳሪ የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃ  ተቀጥቅጦ ከሞት እና ምርኮ የተረፈዉ ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ ተመልሷል። በተመሳሳይ አመለኛዋ  የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃ መደበኛ ጦር ከሻለቃዋ ልዩ ተወርዋሪ ሀይል ጋር ተቀናጅታ  ከጥዋቱ 3:30 ጀምሮ አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት ከአዲስ ቅዳም ከተማ እስከ አሽዋ  ተዘርግቶ ንፁሀንን ለመዝረፍ እና ለማረድ የተሰማራውን ጡት ቆራጭ የብልፅግና ታጣቂ በእየ ጢሻዉ ስታጋድመዉ አርፍዳለች። በጠላት ላይ የደረሰዉን ሰብአዊ እና  ቁሳዊ ጉዳት  በምርኮ ከተገኘዉ ቁሳቁስ ጋር የተሟላ መረጃ እንደደረሰን የምናሳዉቃችሁ ይሆናል። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!! ህዳር 22/2018 ዓ/ም

የጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ፋኖዎች ከጉማራ ወደ ወረታ በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ኃይል ላይ ደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን አስታወቁ! በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ኮር ስር የሚገኘው የጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ፋኖዎች ከጉማራ ወደ ወረታ በወታደራዊ ፓትሮል ሲጓዙ በነበሩ የአገዛዙ ኃይሎች ላይ የሽምቅ ጥቃት በመፈፀም ድል መቀዳጀታቸውን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ተመልክቷል። ደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው ትላንት ህዳር 21/2018 ዓ/ም በጉማራ እና በወረታ መካከል ልዩ ስሙ ዝጥል ወይም ታንኳን ገብርኤል መገጠያ ተብሎ የሚጠራው አከባቢ ላይ ሲሆን፡የወታደራዊ ፓትሮሉ አሽከርካሪን ጨምሮ አራት የአድማ ብተና አባላት ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ሰባት ወታደሮች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን ነው ክፍለጦሩ ያሳወቀው የቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የስለጠና ጥሪ ማስታወቂያ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር አዲስ ሰልጣኝ የፋኖ አባላትን ለማሰለጠን በዝግጅት ላይ ይገኛል። ሆኖም ማንኛውም ከዚ
+3
የስለጠና ጥሪ ማስታወቂያ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር አዲስ ሰልጣኝ የፋኖ አባላትን ለማሰለጠን በዝግጅት ላይ ይገኛል። ሆኖም ማንኛውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ስልጣኞች መሰልጠን የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። 1. ዕድሜ ከ18 አመት በላይ/የሆነች 2. ከደባል ሱስ ነፃ የሆነ/የሆነች 3. ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ/የሆነች 4. የሚሰጠውን ማነኛውም ግዳጅ በአግባቡ መወጣት የሚችል 5. የጤና ችግር የሌለበት/የሌለባት 6. የመመዝገቢያ ቦታ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በሚንቀሳቀስበት ሁሉም ቦታዎች 7. ፆታ ወንድ/ ሴት 8. የመመዝገቢያ ቀን ህዳር 22/03/2018 ዓ.ም በማንኛውም አካባቢ የምትገኙ ወጣቶች ትግላችንን በመቀላቀል መዋል ማደር ቅንጦት ሆኖበት በሰቆቃ ውስጥ ላለው የአማራ በጋራ እንቁም!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ድል ለአማራ ህዝብ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ስልጠናናክህሎት መምሪያ

‎እጅ መስጠት #ራስን ማጥፋት ነው። ‎ ‎ጦርነቱ የአረመኔው ስርዓት እና የአማራ ህዝብ ነው። ይሄን #ጨ*ካኝ ስርዓት ለማስቀጠል አብይ አህመድና አረጋ ከበደ ሰራዊታቸውን አሰልፈዋል። ‎ይሄ #ነው*ረኛ
+2
‎እጅ መስጠት #ራስን ማጥፋት ነው። ‎ ‎ጦርነቱ የአረመኔው ስርዓት እና የአማራ ህዝብ ነው። ይሄን #ጨ*ካኝ ስርዓት ለማስቀጠል አብይ አህመድና አረጋ ከበደ ሰራዊታቸውን አሰልፈዋል። ‎ይሄ #ነው*ረኛ ስርዓት እንዳይቀጥል የሚፈልገው የአማራ ህዝብ #ልጆቹን አሰልፏል። ‎ ‎ከዚህ ውጭ ያለ ታጣቂ ህዝባችንን እረፍት #ከመንሳትና ትግሉን #ከመጎተት ያለፈ #ፋይዳ የለውም። ‎ ‎የአማራ ህዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፍታት ባለመቻሉ ሁለት #አመት ከ6 ወር የተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተደርገዋል። ‎በዚህም ወንድሞችህን ገብረህ አንተም ማህበራዊ እረፍት ተነስተህ ቆይተሃል። ከዚህ በኃላ ወደጡት ብልት #ቆ*ራጩ ስርዓት #ስትመለስ ‎አንደኛ የሚታዘዝ ጦር አለማግኘት፤ ‎ሁለተኛ የተሻለ ምግብ ከተማ ያለ ስለመሰላህ እንጅ ለአማራ ህዝብ #ይበጃል የምትለው ሃሳብ እንደሌላችሁ ይሰማኛል። ‎እጅ ለሰጣችሁ፤ ለምትሰጡት የተዘጋጃችሁ ምልከታዬ ይሄው ነው። ‎ ‎እጅ መስጠት = ራስን ማጥፋት ነው። ‎ዝንታለም አማራ! ‎ኅዳር 22/2018 ዓ/ም ‎

የጠላት እንቅስቀሴ መረጃ ሸር ሸር ሸር የአብይ አህምድ ጡት ቆራጩ  ያለ የሌለ ሃይሉን አሟጦ ቢቸና ማንቆርቆይ ትምህርት ቤቱ አውሎ አሁን ከምሽቱ 2:307 መኪና መከላከያ ከደጀን ወደ ቢቸና እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ መረጃውን ለቴዎድሮስ አናብስቶች እንዲደርስ ሸር ሸር አድረጉ