ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر3 534
مشترکین
+24824 ساعت
+5847 روز
+97230 روز
آرشیو پست ها
⏰የክህደት ጽዋ፡ በጀነራል አሳምነው ስም የተፈጸመ የባንዳነት ውርደት!
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የብዙ ሺህ ጀግኖችን ደምና አጥንት የጠየቀ፣ አሁንም እየጠየቀ ያለ የመኖርና ያለመኖር ፈተና ነው። በዚህ መራራ የትግል ጉዞ ውስጥ፣ እንደ ብረት የጠነከሩ ጀግኖች ታሪካቸውን በደማቸው ሲጽፉ፤ ለጊዜያዊ ጥቅም፣ ለሆዳቸውና ለፍርሃታቸው ያደሩ ደግሞ በገዛ ሕዝባቸው ላይ ክህደት በመፈጸም የታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይወድቃሉ።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወሎ (ቤተ-አማራ) ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ አሳምነው (303ኛ) ኮር ዋና ሰብሳቢ የነበረው ፍቅሩ ሙልዬ የዚህ የታሪክ ዝቅጠትና የውርደት ማሳያ ሆኗል። ይህ ግለሰብ የሕዝቡን አደራ፣ የትግል ጓዶቹን ደምና የቆመበትን ህዝባዊ ዓላማ ወደ ጎን በመተው ለአገዛዙ እጅ መስጠቱ የክህደት ሁሉ ጥግ ነው።
ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነውና የሞራል ዝቅጠቱን አጉልቶ የሚያሳየው፣ ይህ ግለሰብ በትግል ሜዳ ቁሞ በታላቁ ሰማዕት በጄኔራል አሳምነው ጽጌ ስም ሲምልና ሲገዘት የነበረ መሆኑ ነው። በአሳምነው ስም መማል ማለት ለእውነት መቆም፣ ለሕዝብ ነጻነት እስከ መጨረሻዋ የደም ጠብታ መሰዋት ማለት እንጂ፣ ቃለ-መሐላን አረክሶ ገዳይ ሥርዓት ፊት መንበርከክ አልነበረም። የጀግናን ስም ለከንቱ ሽንገላና ለፖለቲካ ንግድ መጠቀሙ ትውልድ ይቅር የማይለው፣ የታሪክ ፍርድ የሚያስከትል ኃጢአት ነው። የሕዝቡን ስቃይ እያየ፣ በሕዝብ ላይ ሞት ለሚያዘንብ ኃይል እጅ መስጠቱ የጓዶቹን መስዋዕትነት የሚያቃልል ጥሬ የባንዳነት ተግባር ነው።
ሆኖም፣ ይህ ክህደት ማሳየት ያለበት አንድ ትልቅ እውነት አለ። የአማራ ሕዝብ ትግል በግለሰቦች ትከሻ ላይ የተንጠለጠለ ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ የሰረጸ ትልቅ የህልውና ማዕበል ነው። የአንድ ፍቅሩ ሙልዬ ክህደት የሚያሳየው የትግሉን መዳከም ሳይሆን፣ የትግሉን መጥራትና ጽዳት ነው። አብዮት ሁልጊዜም በጉዞው ላይ ገለባውን እያበጠረ፣ ፍሬውን እያጠነከረ ይጓዛል። እንዲህ ያሉ በውስጥ ተሰግስገው የነበሩ፣ ዓላማ ቢስና ፍርሃት ያሸነፋቸው ግለሰቦች ራሳቸውን አጋልጠው ከትግሉ መለየታቸው፣ ንቅናቄው በንጹሐንና በጽኑዓን ጀግኖች ብቻ ተከቦ ወደፊት እንዲራመድ ትልቅ አቅም ይፈጥርለታል።
ትግሉ ይቀጥላል! የነጻነት ጉዞው በአንድ ከዳተኛ ማፈንገጥ አይገታም። ታሪክ ለከዳተኞችና ለባንዳዎች የውርደት ሐውልት ሲያቆም፣ እስከ መጨረሻው ለጸኑት ግን ዘላቂ ክብርን ይለግሳል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህንንና መሰል የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን በጽናት እያለፈ፣ የሕዝቡን መከራ ወደሚያሳጥርበት የድል ማማ መውጣቱ አይቀሬ ነው!
እብናት ከተማን የተመኘ ጠላት ክፉኛ እየተመታ ነው!!
እብናት ከተማን ለመቆጣጠር አቅዶ የተጓዘው የጠላት ምስራቅ እዝ ሰራዊት በአፋብን በላይ እዝና አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ክፋኛ ምትን እያስተናገደ ይገኛል።
ዛሬ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም አፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር አፄ እያሱ ክ/ጦር ፣ ዞዝ አምባ ንጉሱ ክ/ጦር ፣ አሳምነው ብርጌድ ፣ መልዛ ንጉሱ ብርጌድ እና ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ጥምረት በመፍጠር ወደ እብነት ከተማ አሰፍስፎ የመጣውን የብልጽግና ግሬሳ ሰራዊት በፊት ለፊት ውጊያ እያደባዩት ይገኛል።
የዳግማዊ ቴዎድሮስ፭ኛ ኮር አካል የሆነው መብረቅ ክ/ጦር አዲስ ዘመን ቋላ ዮሐንስ ተብሎ ከሚጠራው ከፍተኛ ቦታና አርኖ ጋርኖ ከሚባለው ስትራቴጅካዊ ቦታ በመዝጋት ከእንፍራዝ አዲስዘመን እና ከአዲስ ዘመን እብናት ለድጋፍ ተጨማሪ የጠላት ኃይል እንዳይጓዝ ቆርጠው ዘግተዋል።
ህልውናችን በአርበኝነታችን!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ወሎ (ቤተ አማራ) ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር 19ኛ ክፍለ ጦር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ተጎናፀፈ።
ጠላት መነሻውን አይና ከተማ አድርጎ ቡግና ወረዳ 010 ቋሮ ቀበሌ ለመግባት እና ህዝብን ለማሰቃየት የተንቀሳቀሰው የጁል ሠራዊት ቡግና ወረዳ 08ደብረ ሮሃ ቀበሌ ልዬ ስሙ ሲቃን እየተባለ ከሚጠራው ቦታ የደፈጣ እና የቆረጣ ዉጊያ በመክፈት የአብይ አህመድ ዙፋን አሰጠባቂ ሰራዊት ከባድ ሸንፈትን ተከናንቧል።
አይበገሪዎቹን መቋቋም ያቃተው የጁላ ሰራዊት ገደል በመግባት እና ቀሪው ደግሞ ሲቃን ጎራ ተንጠልጥ
የድረሱልኝ ጥሪ እየተማፀነ ይገኛል።
ዉጊያዉም ከትላንት ማለትም ከቀን20/07/2018ዓ.ም ከቀኑ 8:00_ሌሊቱ 6:00 ድረስ የተካሄደ ሲሆን በረካታ ድሎችም ተመዝግበዋል ።
በዚህም 1ብሬን 10ክላሽእንኮፍ ከ2000በላይ የብሬን ተተኳሽ ፣ 4500የክላሽ ተተኳሽ እና በርካታ ቦምቦች ገቢ ተደርጓል።
የአበገሬዎቹ የአሳመነው ፅጌ ግልገሎች በብርኮ በኩል ሰርገው በመግባት አይና ከተማ ካድሪ ለመጠበቅ የተቀመጠውን የጁላ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት የተቀጣ ሲሆን አይና ገብሬል እና አይና ሸብራ አጠጌ የተከማቸውን የጁላ ሠራዊት በሞርተር ቅንቡላ እራት ሆነው አምሽተዋል ከሸብራ አጠጌ እና አይና ገብርኤል 28 የተደመሠሠ ሲሆን 2 አንቡላንስ እና 1 ኦራል ቁስለኛ ይዞ እደተመለሰ የውስጥ ምንጮቻችን አድርሰውናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ወሎ (ቤተ አማራ) ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ !!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠናምኒልክ ዕዝመጋቢት21/2018ዓ.ም
መሃመድ ተሰማ የተባለ የቀድሞ ምርኮኛ የአሁኑ ከበርቴ ጀኔራል በአዲዘመን ከተማ ለወረራ የተገኘ ቢሆንም በአፋብን በላይ ዕዝ 5ኛ ኮር መብረቅ ክ/ጦር ተከቦ ድረሱልኝ እያለ ነው።
ደቡባዊ እና ማዕከላዊ የጎንደር ቀጠና ለመውረር ተጨማሪ ሰራዊት ከተለያዩ አካቢዎች ለቃቅሞ የዘመተው መሃመድ ተሰማ በአዲዘመን ከተማ ማረሚያ ቤት ህይወቱን ለማትረፍ ዘሎ መግባቱ ታውቋል።
ይህ ነባር ምርኮኛ የእብናትና መሰል ከፍተኛ የደቡባዊ ጎንደር አካባቢዎችን ቀድሞ በመቆጣጠር ከከፍተኛ ገዥ መሬቶች እየተወረወረ የተነጠቃቸውን ወረዳዎች መልሶ ለመውረር በታቀደው የጠላት ዕቅድ መሰረት ነበር አዲዘመን ማዘዣ በማቋቋም እብናትን የከጀለው።
ቅሉ በአፋብን ጎንደር ጠ/ግ/ ዕዝና በላይ ዕዞች ጥምረት ዕቅዱ እየመከነ ይገኛል።
ህልውናችን በአርበኝነታቸን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
የአገዛዙ ሰራዊት የደቡብ ጎንደር ዞን ወረዳዎችን መልሶ ለመያዝ ያለ የሌለ ሀይሉን በማሰባሰብ በደራ ወረዳ ወረራ ለመፈጸም የሞከረ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር አህዶች ጋር ከከባድ መሳሪያ እስከ ድሮን ያሰለፈበት ከባድ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል።
ከጧት ጀምሮ እስካሁን በሚደረገው ውጊያ 5ጊዜ የድሮን ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ንጹሃንን ከመጨ*ፍጨፍ በዘለለ በወገን (በፋኖ) በኩል የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ግን ታውቋል።
ድል ለአማራ ፋኖ
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ይወዳጁ
👇
የጥንቃቄ መልዕክት !!
በ206ኛ ኮር ቀጠና በየቦቅላና ደባይ ጠላት ግን ወረዳ አካባቢ የድሮን ቅኝት ስላለ አስፈላጊው ጥንቃቄ ይደረግ።
+1
206ኛ ኮር በቁይ ከተማ በፈፀመው ጥቃት አቶ ታሪኩ ምኑዋጋው የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ብልፅግና ጽ/ቤት ወጣቶች ሊግ ኃላፊ እና የምርጫ አስፈፃሚ ካድሪ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ተገድሏል።
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
=======================================
የብልፅግና ታማኝ ካድሪ በመሆን የ7ኛውን ዙር ምርጫ ለማከናወን ወገቡን ታጥቆ የተሰለፈው የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ካድሪ የሆነው አቶ ታሪኩ ምኑዋጋው በ206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በቁይ ከተማ በተፈፀመ የቅጣት እርምጃ መገደሉ ተከትሎ የስንዴው ነዶው እንኩቶ ሁኖ አድሯል።
አቶ ታሪኩ ምኑዋጋው የብልፅግና ታማኝ አገልጋይ ከመሆኑም ባሻገር የአማራን ህዝብ አሳልፎ በመስጠት በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን በአረመኔው ሰራዊት ጋር አስሮ ሲያሰቃይ የነበረና የቁይ ከተማን ህዝብ በማስገደድ ቤት ለቤት ለምርጫ ሲመዘግብ ከተደረገበት ክትትል በኋላ በመጨረሻ ተወግዷል።
በተመሳሳይ ስዓት የወጀል ከተማ የብልፅግና ጽ/ቤት ወጣቶች ሊግ ኃላፊ የሆነው አቶ ጤናው ወንዴ በ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በተወሰደበት የቅጣት እርምጃ የተገደለ ሲሆን የአረመኔው ስርዓት አገልጋይ ካድሬዎችና የምርጫ መዝገብ ተሸካሚዎች ከፍተኛ ሽብር ውስጥ ገብተዋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በዓብይ የጨበራ ምርጫ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ መሳተፍ የአማራን ህዝብ የዘር እልቂት እንደመደገፍና የሀገራችን መከራ ለማራዘም እንደመደገፍ ይቆጠራል።
በግልም ሆነ በፓርቲ ውክልና ማንኛውም ተሳትፎ ማድረግ፣ያለህዝቡ ፈቃድና ይሁንታ ዓብይና ግብራበሮቹ የጦር ወንጀለኞች መሆናቸው እየታወቀ በምርጫ እንዳትሳተፉ አበክረን እናሳውቃለን።
✅ምርጫችን ህልውናችን ማረጋገጥ ነው!!
✅አቋማችን የእንቁ አርበኞቻችን የአደራ ቃል ኪዳን
መጠበቅና ማስጠበቅ ነው!!
✅ ምርጫችን የህዝባችን ደህንነት ማረጋገጥ ነው።
👉 በንፁሃን ጭፍጨፋ የሚደምቅ የጨበራ ምርጫ
አይኖርም!!
👉 ወንጀኛውን ዓብይ ለህግ እናቀርበዋለን እንጅ በምርጫ
ሽፋን አጅበን አንሞሸረውም!!
👉 የሚሞሽሩና የሚያጅቡ ቢኖሩ ወዮላችሁ!!!
ህልውናችን በአርበኝነታቸን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ንስሮች 74ኛ ክፍለ ጦር ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የባህረ ጊወርጊስ የምርጫ አስፈፃሚውን አፈፍ አድርገውታል።
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
አዝዘው አስቻለ ዳምጤ የምርጫ አስፈፃሚ አስተባባሪ በንስሮቹ 74ክፍለ ጦር በቁጥጥር ስር ውሏል።
የአማራን መከራ ለማራዘም ከገዳይ ጎን በመሰለፍ የአብይን ወንበር ለተጨማሪ አምስት አመት ለማራዘም የምትሯሯጡ ሁሉ በሁሉም ቀጠና ተመድባቹህ ያላቹህ ተላላኪወች በየተራ እየለቀምን እንደምናወጣቹህ በመገንዘብ
ከአሁኑ እራሳቹህን በማግለል ከህዝባችን ጎን መሰለፍ ይገባቹሀል እያልን በቀጣይም በተጠናከረ መልክ ስራችን የምንቀጥል ሲሆን በጊዜ ከድርጊታቹህ የማትቆጠቡ ከሆነ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን ።
{ ጀሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ልብ ይበል ተው ብለናል }
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ለምርጫ ጣቢያ ዘብነት በቆመ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር ድል ተቀዳጁ::
መጋቢት 20/2018 ዓ/ም ከፍላቂትና ከጋሸና ተሰባስቦ ወደ 22ኛ ክፍለ ጦር የተቀሳቀሰው የብልፅግና ሰራዊ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:30 ሰዓት ድረስ ከባድ ትንቅንቅ ሲደረግ ውሏል። በመሆኑም በክንዱ አሻግሬ ሻለቃ ፊትአውራሪነት ተለብልቦ ተመልሷል። አገዛዙ ለአንድ ወር ተጨቆና ተጠብቦ የሰራዉ ኦፕሬሽን በአንድ ሻለቃ ሲጨፈጨፍ ውሎ አዳሩንና የሀዘን እንጉሩጓሮውን ጋሸና ከተማ ላይ አድርጎ የሀዘን ድኳኑን ጥሏል።
106ኛ ኮር በዛሬው እለት በሶስት ወረዳዎች ላይ የጥላትን ሰራዊት ሲያመሽኩት የዋሉ ሲሆን ከመቄት እስከ ዳውንት ከዳውንት እስከ ጋዞ የሽመልስ አብደሳ አጀንዳ አስፈፃሚ ሎሌዎች ቅስማቸው እምሽክ ድቅቅ ብሏል። የዛሬው ብትር የአገኘሁ ተሻገርን የአረቂ ትቦ መስመር ያዘጋ ሆኖ ተመዝግቧል። ድልና ጀብድ ታሪክና ህዝብን እየሰራ የሚገኘው 106ኛ ኮር ጥላቶችን የእፍረትና ሽንፈት ሸማ እያለበሳቸው ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #106ኛ ኮር ህ/ግ መምሪያ ሀላፊ!
መጋቢት 20/2018 ዓ.ም
ፀሐይ ገና ከምስራቅ ሰንጥቃ ሳትወጣ፣ በዚህች የአማራ ፋኖ መናገሻ በሆነችው የድል ማማ ላይ ብርቱ ንፋስ ይነፍሳል። አየሩ የጀግንነትና የፅናት መዓዛ አለው። በአድማሱ ጫፍ ላይ አዲስ አበባ በጭጋግ ተከልላ ትታያለች፤ ያቺ የሥልጣንና የታሪክ ማዕከል የሆነችው ከተማ፣ ዛሬ በብርቱ ዓይኖች በብርቱ እይታ ትታያለች አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ከሚወዳቸው የትግል ጓዶቹ አርበኛ ኤፍሬም ባዩና አርበኛ አበበ ፀጋዬ ከተራራው ራስ ላይ እንደ ግርማ ሞገስ ያለው ቋጥኝ ቁመዋል። ዓይኖቻቸው ወደ ፊት አሻግረው አዲስ አበባን ይቃኛሉ፤ ነገር ግን የሚያዩት የአዲስ አበባን ሕንጻዎቹን ሳይሆን፣ የነገዋን የነፃነት መንገድ ነው። ከአርበኛው ኢሳያስ ደመቀ ከጎኑ ያሉት የትግል ጓዶቹም ቃላት አያስፈልጋቸውም፤ የሁላቸውም ልብ በአንድ ምት ይመታል ያ ምት ደግሞ "ድል" ይላል።
በዚያው ቅጽበት፣ ከመላው የአማራ ግዛቶች የሚተሙት የአሳምነው አናብስቶች (ፋኖዎች) ጉዟቸውን ወደዚህ መዳረሻ የሚያደርጉበት ቅፅበት ልብ ያሞቃል። በሸለቆና በገደላገዱ ውስጥ የሚታየው የአርበኞች ሰልፍ፣ ልክ እንደ ተቆጣ የዓባይ ወንዝ ይወርዳል። እነዚህ ጀግኖች በወኔና በታሪክ የታተሙ፣ ለቀጣዩ የትግል መስመር ራሳቸውን የሰጡ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።
ንጋቱ ሲቀደድ፣ በድል ማማው ላይ የቆሙት እነ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ፥አርበኛ ኤፍሬም ባዩና አርበኛ አበበ ፀጋዬ በፀሐይ ጮራ ተከበው ደምቀው ይታያሉ። ያ አዲስ አበባን አሻግሮ የሚመለከተው እይታቸው፣ የተስፋን ብርሃን የሰነቀና የማይታጠፍ የጽናት ማህተም ያረፈበት ነው። በዚያች ቅጽበት፣ የትግል መስመሩ ተውቦና ተቀናጅቶ፣ የታሪክ አዲስ ምዕራፍ ሊከፈት መሆኑን ለዓለም ያበስራል።Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር
እንበርታ ! አፋብን💪 ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከግንባር የቴሌግራም ገፃችንን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ፀሐይ ገና ከምስራቅ ሰንጥቃ ሳትወጣ፣ በዚህች የአማራ ፋኖ መናገሻ በሆነችው የድል ማማ ላይ ብርቱ ንፋስ ይነፍሳል። አየሩ የጀግንነትና የፅናት መዓዛ አለው። በአድማሱ ጫፍ ላይ አዲስ አበባ በጭጋግ ተከልላ ትታያለች፤ ያቺ የሥልጣንና የታሪክ ማዕከል የሆነችው ከተማ፣ ዛሬ በብርቱ ዓይኖች በብርቱ እይታ ትታያለች አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ከሚወዳቸው የትግል ጓዶቹ አርበኛ ኤፍሬም ባዩና አርበኛ አበበ ፀጋዬ ከተራራው ራስ ላይ እንደ ግርማ ሞገስ ያለው ቋጥኝ ቁመዋል። ዓይኖቻቸው ወደ ፊት አሻግረው አዲስ አበባን ይቃኛሉ፤ ነገር ግን የሚያዩት የአዲስ አበባን ሕንጻዎቹን ሳይሆን፣ የነገዋን የነፃነት መንገድ ነው። ከአርበኛው ኢሳያስ ደመቀ ከጎኑ ያሉት የትግል ጓዶቹም ቃላት አያስፈልጋቸውም፤ የሁላቸውም ልብ በአንድ ምት ይመታል ያ ምት ደግሞ "ድል" ይላል።
በዚያው ቅጽበት፣ ከመላው የአማራ ግዛቶች የሚተሙት የአሳምነው አናብስቶች (ፋኖዎች) ጉዟቸውን ወደዚህ መዳረሻ የሚያደርጉበት ቅፅበት ልብ ያሞቃል። በሸለቆና በገደላገዱ ውስጥ የሚታየው የአርበኞች ሰልፍ፣ ልክ እንደ ተቆጣ የዓባይ ወንዝ ይወርዳል። እነዚህ ጀግኖች በወኔና በታሪክ የታተሙ፣ ለቀጣዩ የትግል መስመር ራሳቸውን የሰጡ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።
ንጋቱ ሲቀደድ፣ በድል ማማው ላይ የቆሙት እነ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ፥አርበኛ ኤፍሬም ባዩና አርበኛ አበበ ፀጋዬ በፀሐይ ጮራ ተከበው ደምቀው ይታያሉ። ያ አዲስ አበባን አሻግሮ የሚመለከተው እይታቸው፣ የተስፋን ብርሃን የሰነቀና የማይታጠፍ የጽናት ማህተም ያረፈበት ነው። በዚያች ቅጽበት፣ የትግል መስመሩ ተውቦና ተቀናጅቶ፣ የታሪክ አዲስ ምዕራፍ ሊከፈት መሆኑን ለዓለም ያበስራል።Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር
ወንድም ከለላ ነው ይጠቅማል ለአንድ ቀን
የጨነቀ ለታ ያወጣል ክፍ ቀን
ብዙ ዘመቱበት ኮስታረውን ጀግና
አንደበተ ሙሉ አስተዋዩን ጀግና
ለስንት የሚበቀው ስንቱን ሴራ አረፈው
አርበኛ ጥላሁን እናቱ የወለደችው የሽፈራው ልጅ ነው
እኛም ተደናግጠን ሳውቀው ሴረውን እሱን ሳናግዘው
የሴራውን ጫፍ ግን በደንብ ስንረደው ከጎኑ ስንሆን
ስንቶች ተንጫጭተዋል አርፈው ቁጭ ብለዋል
እኛም ዝም ብለናል አትንኩት ብለናል
ድሮም የፈለግነው ዝምታ ብቻ ነው
አንደበተ ብረቱ ታላቁ አርበኛ ታጋይ
ልቡ እንደተራራ የማይገፈተረው ቆራጡ ታጋይ
ዝምተኛው ታጋይ አርበኛ ጥላሁን መህኑ ነወይ
ጥላ መከታ ነው ተንከባክበህ ያዘው
የሀገርህን ታጋይህን ጠበቅ አርገህ ያዘው
የክፍ ቀን ግዜ ወንድም ጠበቃ ነው
ጠበቅ አርገህ ያዘው ለክፍም ለደጉም
ወንድም ጠበቃ ነው ዝምተኛ ገዳኛ ይሄው ጥላሁን ነው ....
