ስለ - ህግ - አገልግሎት ⚖
رفتن به کانال در Telegram
ስለቤተሰብ ሕግ ፣ስለንግድ ሕግ፣ስለወንጀል ሕግ፣ስለውርስ ሕግ፣ስለውል ሕግ ፣የሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሚያገኙበት ቻናል ነው። ለጥያቄ እና አስተያየት በቴሌግራም አካውንታችን @DesiignerA 📞 0916455355 ☎️
نمایش بیشتر1 488
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+107 روز
+1030 روز
در حال بارگذاری دادهها
کانالهای مشابه
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26اکتبر '26
اکتبر '26
+546
در 0 کانالها
سپتامبر '260
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '260
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '260
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '260
در 0 کانالها
Get PRO
مه '260
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '260
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '260
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '260
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '260
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '250
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '25
+21
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '25
+45
در 0 کانالها
Get PRO
مه '25
+47
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '25
+34
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '25
+43
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '25
+52
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '25
+32
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '24
+52
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '24
+63
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+75
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '24
+96
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '24
+503
در 0 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 18 اکتبر | +1 | |||
| 17 اکتبر | +1 | |||
| 16 اکتبر | +3 | |||
| 15 اکتبر | +1 | |||
| 14 اکتبر | +3 | |||
| 13 اکتبر | 0 | |||
| 12 اکتبر | +4 |
پستهای کانال
በወንጀል ጉዳይ አንድ ተከሳሽ ክስ ደርሶት ወይም ከተነበበለት በኋላ ፍ/ቤቱ መቃወሚያ አለሕ ወይ ብሎ ይጠይቀዋል !! መቃወሚያ ሲባል ምን ማለት ነው?
✅የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ተከሳሹ ስለ ክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም በክስ ማመልከቻ የተገለፀውን ነገር የሚቃወምበት ስርዓት ነው፡፡
✅ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አላማ ፍርድ ቤት እና ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክሩ ፍሬ ነገር ሳይገቡ መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ በመስጠት ጊዜ መቆጠብ ነው፡፡
✅ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊነሳባቸው የሚችሉ ነጥቦች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
✅ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የክሱን ይዘት በተመለከተ ሊቀርብ ይችላል፡፡
🔺 ማንኛውም የክስ ማመልከቻ ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበት እና የተፈረመበት ፤ ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል እንዲሁም የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር እና ሁኔታዎች፤ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ስፍራ ተገቢ በሆነ ጊዜም በደል የደረሰበት ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት፣ተከሳሽ ድርጊቱን በመፈፀም የተላለፈው የህግ አንቀጽ
መያዝ አለበት፡፡ክሱ ግልፅ እና የተከሳሽን የመከላከል መብት የማያጣብብ መሆን አለበት፡፡
🔺 በመሆኑም እነዚህ ነገሮች ግልፅ ባልሆኑ እና ባልተሟሉ ጊዜ ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማንሳት ይችላል፡፡
•🔺በተጨማሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 130/2 ስር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚያስነሱ ነገሮች ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡
➨ተከሳሽ በዚሁ ነገር ክስ በሌላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ያለ መሆኑ
➨በዚሁ ክስ ከዚህ በፊት ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ
➨ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ህግ የታገደ ወይም ምህረት ወይም ይቅርታ የተደረገለት መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡
➨ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር በተከሰሰ ጊዜ እና ለብቻው ተነጥሎ ክሱ ባይታይለት የሚጎደው መሆኑን፣
➨ክሱን ለማቅረብ በህጉ መሰረት ፈቃድ ያልተሰጠ መሆኑ ለምሳሌ ተከሳሽ በአለም አቀፍ ህግ ዲፕሎማቲክ ኢሙኒቲ የማይከሰስ እንደሆነ፣
➨በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም በዚህ የወንጀል ክስ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ፣
➨ለፈፀማቸው ተግባሮች ኀላፊ አለመሆን ፤ለምሳሌ የተከሳሽ አድሜ ከዘጠኝ አመት በታች ከሆነ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 48 ላይ እንደተመለከተው ማንም ሰው በእድሜ ፣ በህመም ፣ባልታሰበ የእድገት መዘግየት ወይም ጥልቅ በሆነ የአዕምሮ የመገንዘብ ችሎታ መቃወስ ወይም የወንጀል ድርጊት በሚፈፅምበት ጊዜ የድርጊቱን አይነት ወይም ውጤት ለመገንዘብ ወይም በዚህ ግንዛቤ መሰረት ራሱን ለመቆጣጠር በፍፁም ያልቻለ ሲሆን ኢ-ኃላፊ ስለሚሆን አይቀጣም፡፡
✅ ከላይ የተዘረሩት ነጥቦች ባጋጠሙ ጊዜ ተከሳሽ እራሱ ወይም በጠበቃው አማካኝነት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊያነሳ ይችላል፡፡
✅ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወዲያውኑ ካልተቃወመ በቀር ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ
ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው ፍርድ ቤቱን የሚፀና ፍርድ ለመስጠት የሚያግደው ከሆነ ብቻ ነው (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.130/3)፡፡
✅ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
✅ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
✅ሰበር ሰሚ ችሎቱም ተከታዩን ትንታኔ ሰጥቶበታል፡-
. አንድ ሰው በወንጀል ህግ እና ስነ ስርዓት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም ነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 130 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 131 ተደንግጓል፡፡
.ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሜ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊ እና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ መሆኑ በውሳኔው አስፍሯል፡፡
✅ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ሊምታታ የማይገባው መቃወሚያ በማለት ተከራካሪ ወገኖች እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤ ሕግም ይሁን ተከሳሽ በክርክር ወይም ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ጣልቃ የሚገቡበት ስነ ሥርዓት ነው፡፡
ለምሳሌ ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ለምስክሩ በዋና ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄ ቢቀርብ ወይም ምስክሩ ከተመለከተው ወይም ከሚያውቀው ነገር ባሻገር ግላዊ አስተያየቱን ወይም ግምቱን እንዲሰጥ ቢጠየቅ ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ቢጠየቅ ተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ አለኝ ብለው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ ምስክሩ መልስ እንዳይመልስ ማድረግ ይችላሉ፡፡
| 2 | የገጠር መሬትን በተመለከተ የሰበር ውሳኔዎች!***
1. የገጠር መሬትን በተመለከተ ሁለት ዳኝነቶች በአንድ ላይ ተጣምረው ሲቀርቡ የፍርድ ቤት ስልጣን፣ በተመለከተ በመሬት አዋጁ፣ በስነ-ስርዓት ህጉ እና የክልል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መካከል ግጭት ካለ የመሬት አዋጁ ልዩ ህግ በመሆኑ በቀዳሚነት ሊተገበር ይገባል (Special prevails over the geberal)። የሰበር መ/ቁ. 191968
2. ወራሽነትን ቀድሞ በማረጋገጥ የገጠር መሬትን ቀድሞ መያዝ ልዩ የወራሽነት መብትን የማያጎናፅፍ በመሆኑ ሌሎች ወራሾችን ድርሻቸውን ከመጠየቅ አይገድብም።
የሰበር መ/ቁ. 181643
3. የገጠር መሬት አዋጁ ላይ የገጠር መሬትን በሽያጭ ዉል ማስተላለፍ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ መሬቱ ላይ ቤት ቢኖርበትም ባይኖርበትም ዉሉ ህግን ያለተከተለ ሰለሆነ አይፀናም። የሰበር መ/ቁ. 186431
4. የገጠር መሬት ስጦታ ተደርጎል ተብሎ የሚመዘነው በጊዜው በነበረው የገጠር መሬት ህግ እንጅ ከስጦታው በኋላ ተሻሽሎ በወጣው ህግ አይደለም። (Principle of non-retroactivity) የሰበር መ/ቁ. 185848
5. የገጠር መሬት ስጦታን በተመለከተ የመሬት አዋጆቹ ስራ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ ወይም ደግሞ በህጎቹ ባልተሸፈኑ ጉዳዪች ላይ የፍ/ህጉ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ስለሚተላለፍበት ሁኔታ የተዘረዘሩት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሊሆኑ ይገባል። (Common approach of the Cassation using the 1960 Civil Code provisions as a gap feeling to rural land matters) የሰበር መ/ቁ. 188853
6. ከሚመለከተው የመንግስት አካል በስተቀር አንድ ግለሰብ የያዘውን መሬት አያያዙ በህገ-ወጥ መንገድ በሚል አስለቅቆ መያዝ አይችልም። (No one can take justice by his own hand) የሰበር መ/ቁ. 187618
7. የገጠር መሬት ኪራይ ይርጋ ጋር በተያያዘ የመሬት አዋጁ በግልፅ ካላስቀመጠ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ የፍ/ህ/ቁ. 1845 ነው። የሰበር መ/ቁ. 187484
8. ትዳር በሞት ምክንያት ከፈረሰ በሌላኛው ተገቢ የተያዘ የገጠር መሬት እንዲመለስ በወራሾች የሚቀርብ ጥያቄ በጋብቸ የተፈራ የንብረት ክፍፍል ጥየቄ ስለሆነ ሰበር ቀደም ብሎ በቅፅ 4 የመ/ቁ. 17937 በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል። የሰበር መ/ቁ. 186461
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 537 |
| 3 | 📍8 መሠረታዊ ህግ ነክ ነጥቦች:
1. አንድ ሰው ተከሰሰ ማለት ጥፋተኛ ነው ወይም ተጠያቂነቱ ተረጋግጧል ማለት አይደለም። ጥፋተኛነት ወይም ተጠያቂነት በሕግ አግባብ ተመስርቶ በሂደት የሚወሰን ጉዳይ ነው።
2. ሕግ ሁሉም ውሎች በጽሑፍ እንዲደረጉ አያስገድድም። ተዋዋዮች ውላቸውን በቃል ወይም በጽሑፍ መልክ ለማድረግ በመርህ ደረጃ ነፃነት አላቸው። ውል በጽሑፍ መደረግ የግድ የሚሆነው ተፈጻሚው ሕግ ይህንን እንደ ግዴታ ሲያስቀምጥ ነው።
3. ክስ መመስረት በራሱ ባለመብትነትን አያረጋግጥም። ክስ መመስረት አንድ ጥያቄን በሕግ አግባብ ለተገቢው አካል ለማቅረብ የሚያስችል ሂደት ነው። የተጠየቀው መብት መኖሩና የሚገባው ሕጋዊ መፍትሔ ግን በቀረበው ማስረጃና ተፈጻሚ በሚሆነው ሕግ መሠረት በዳኝነት አካሉ ይወሰናል።
4. ሕጋዊነትና ሞራላዊነት አንድ አይደሉም። አንድ ድርጊት ሕጋዊ መሆኑ በራሱ በሞራል ትክክል ነው ማለት አይደለም። በተመሳሳይም ሞራላዊ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ሁልጊዜ ሕገወጥ ነው ማለት አይቻልም። ሕጋዊነት በሕግ የሚወሰን ሲሆን፣ ሞራላዊነት ደግሞ ከሥነ-ምግባርና ከማኅበራዊ እሴቶች ጋር ይያያዛል።
5. አንድ ሰው ለጥያቄ ወይም ለምርመራ በፖሊስ መጠራቱ በራሱ ተከሷል ወይም ጥፋተኛ ነው ማለት አይደለም። የፖሊስ ጥሪ፣ የምርመራ ሂደት፣ ክስ መቅረብ እና ጥፋተኛነት የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
6. የምስክር መኖር ብቻ ጉዳዩን አያረጋግጥም። የምስክሩ ተዓማኒነት፣ የሰጠው ምስክርነት፣ ተገቢነቱ እና ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ያለው ተያያዥነት በሕግ አግባብ ይመዘናል። በመሆኑም “ምስክር አለ” የሚለው ብቻ የጉዳዩን ውጤት አይወስንም።
7. አንድ ውል በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት መደረጉ ወይም መረጋገጡ ብቻ ውሉ በሁሉም መልኩ ሕጋዊና ተፈጻሚ ነው ማለት አይደለም። የሰነድ ማረጋገጥ ከውሉ ይዘት፣ ከተዋዋዮች ሕጋዊ አቅም እና ከሌሎች የሕግ መስፈርቶች ጋር የሚመረመር የተለየ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ውሉ በሰነዶች ጽ/ቤት መረጋገጡ በሌላ የሕግ ምክንያት እንዳይፈርስ ወይም እንዳይሰረዝ ፍጹም ዋስትና አይሰጥም።
8. አንድ ሰው ባለዕዳ በመሆኑ ብቻ አበዳሪው በራስ ፈቃድ የባለዕዳውን ንብረት ወይም ገንዘብ መውሰድ ይችላል ማለት አይደለም። አበዳሪው ያለውን መብት ለማስፈጸም ሕጉ የደነገገውን ሥርዓት መከተል ይገባዋል።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 778 |
| 4 | የጥብቅና ፈቃድ ማረጋገጫ ፈተናዎች
1.የህገ መንግስቱን መሰረታዊ መርሆዎችን ዘርዝር።
2.በአጭር ሥነ-ሥርአት እና በተፋጠነ ሥነ-ሥርአት የሚቀርቡ ጉዳዮችን ዘርዝር።
3.ፍርድ ቤት የራሱን ውሳኔ የሚያይባቸው ሁኔታዎች ምንምን ናቸው።
4.ይቅርታና ምህረት ልዩነቱ ምንድነው።
5.በአስገዳጅ ሁኔታ እና በህጋዊ መከላከል መሀከል ያለው አንድነት እና ልዩነት ምንድነው።
6.ቀብድ የተቀበለ ሰው ውሉን ለማቋረጥ ቢፈልግ ምን ማድረግ አለበት።
7.ሰራተኛ በራሱ ያለ ማስጠንቀቂያ ስራ ሊያቋርጥ የሚችልባቸው ሁኔታዎች መንድናቸው።
8.ሁለቱ አይነት የቅጣት ገደቦች አንድነት እና ልዮነት።የሚፈቀድባቸው እና የሚከለከልባቸው መንገዶችን አስቀምጥ።
9.በአስቸኳይጊዜ አዋጁ የማይታገዱ የህገ መንግስቱ አንቀጾች የትኞቹ ናቸው።
10.የውል መሰረዝ እና መፍረስ አንድነት እና ልዩነት።
11.ለመሰየም የሚፈቀድበት እና የሚከለከልበት መስፈርት።
12.አስቦ እንድ ሰው ወንጀል አድርጎ የማይቀጣው መቼ ነው።
13.ፍርድ ቤት ቅጣትን በመሰለው የሚያቀልባቸው የወንጀል ህግ አንቀጾች የትኞቹ ናቸው።
14.ተደራራቢ ወንጀሎችን አይነት ዘርዝር።አንድነት እና ልዩነታቸውስ።
15.ልዩ የቅጣት ማክጃ እና ማቅለያ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው።
• በወንጀል ስነስርአት ይግባኝ የማይባልባቸው ጉዳዮችን ዘርዝር
17.የአስተዳደር ውል እና መደበኛ ውል ልዩነት።
18.እዳ ሚከፈልበት ጊዜ ቅደም ተከተሉ…..ማለት ለሰራተኛ የሚከፈል፣ለግብር የሚከፈል፣ለቀለብ የሚከፈል የቱ ይቅደም።
19.ለውርስ ያልተገባ መሆን እና ከውርስ መነቀልን አብራራ።
20.የቅጣት ይርጋ እና የክስ የርጋን በወንጀል አብራራ።
21.ከውል መፈጸም ጋር በተያያዘ ተዋዋዮች በተናጠል ውል መሰረዝ(unilateral cancelations) የሚችሉባቸው ሁኔታዎች ምድናቸው።
22.በስውር የተደረገ ይዞታ እና በማያሻማ አይነት የተደረገ ይዞታ ልዩነት እና አንድነት።
23.የመልካም ጸባይ ዋስትናን መርህን አብራራ።
24.የወንጀል ህግ ግብ እና አላማ አስቀምጥ።
25.ክስ ወደሌላ ስፍራ የሚዛወርባቸው ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው።
26.በጋብቻ እና እንደ ባልና ሚስት መኖር ያላቸው አንድነት እና ልዮነት።
27.በፍርድ መከልከል እና ህግ መከልከል ልዩነት እና አንድነት።
28.ጋብቻ ከፈረሰ በኃላ አንዲት ሴት 180 ቀን ሳይሞላት ማግባት የምትችለው መቼ ነው።
29.ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ዘርዝር።
30.ጋብቻ የሚፈርስባቸው 4ቱ ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው።
ጋብቻ በተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነት ላይ የሚኖረውን ውጤት ዘርዝር።
31.ለውርስ ያልተገባ ሰው ሟችን ሊወርስ የሚችልበት exceptions ምድን ናቸው።
32.አንድ ግዴታ እንዲፈጸምለት የሚጠይቅ ሰው ለግዴታው መኖር ማስረዳት አለበት(one who alleged the fact has to proof it)ለሚለው የህግ መርህ በወንጀልም ይሁን ፍትሐብሆር ያሉ exception ኖችን ዘርዝር።…..ለምሳሌ የውርስ ህግ 896፣ የወንጀል ህግ 35።
33.ፍርድ ቤት አንድን ሰው ጥፋተኛ ካለ በሓላ ከቅጣት በፊት ወንጀሉ በይርጋ የቀረ መሆኑን ቢያውቅ መዝገቡን በይርጋ መዝጋት አለበት ወይስ በይግባኝ ነው ሊታረም የሚገባው የወንጀል ህግ 216(2)።
34.ውልን በግዴታ እንዲፈጸም ለማዘዝ የሚቻለው መቼ ነው። የፍ/ህ 1776።
35.የወንጀል አፈጻጸም ደረጃዎችን ዘርዝር።አንቀጽ 26 እና ተከታዩ
36.የህግ ሰውነት የተሰጣቸው ድርጅቶች የሚቀጡባቸውን የወንጀል ህግ ልዩ ክፍሎች ዘርዝር።
37.ከአድማ እና አምባጎሮ ውጭ ህብረት የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዴትያሉ ናቸው።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 921 |
| 5 | ወንጀል ሕጋችን፦ ስርቆት፣ ከባድ ስርቆት፣ ውንብድና፣ ዝርፊያ እና መሸሸግ ልዩነታቸው ምንድን ነው?
ብዙዎቻችን እነዚህን የንብረት ወንጀሎች በማደባለቅ እንጠቀማቸዋለን። ነገር ግን በኢትዮጵያ ወንጀል ሕግ መሠረት እያንዳንዳቸው የተለያየ የድርጊት ዓይነት፣ የቅጣት መጠን እና ሕጋዊ መለኪያ አላቸው።
ልዩነታቸውን በጥቅሉና በግልጽ እንደሚከተለው እንመልከት፦
1️⃣ ስርቆት (Simple Theft)
የሌላውን ሰው የሚንቀሳቀስ ንብረት ባለቤቱ ሳይያውቅ ወይም ሳይፈቅድ፣ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማድረግ በማሰብ በደባ ወይም በስርቆት መውሰድ ነው።
ምንም ዓይነት ኃይል/ዛቻ (Violence) የሌለበት፣ በስውርና በደባ የሚፈጸም ነው።
2️⃣ ከባድ ስርቆት (Aggravated Theft)
ሕጋዊ ትርጉም፦ ስርቆቱ የተፈጸመበት ሁኔታ፣ ቦታ፣ ወይም መንገድ ወንጀሉን ከባድ የሚያደርገው ሲሆን ነው።
ዋና መለያዎች፦
# በሌሊት፣ በቡድን፣ ወይም መሣሪያ/መሳሪያ መሰል ነገሮችን በመያዝ ከተፈጸመ፤
# መቆለፊያ በመስበር፣ በር/መስኮት በመስበር ወይም የመግቢያ ቁልፍ አስመስሎ በመስራት ከተፈጸመ፤
# በእምነት ማጉደል ወይም በሥራ አጋጣሚ (ለምሳሌ፦ ዘበኛ፣ አጋዥ) ከተፈጸመ።
3️⃣ ዝርፊያ (Robbery)
የሌላውን ሰው ንብረት ለመውሰድ ሲባል ኃይልን (Force) መጠቀም ወይም በሕይወትና አካል ላይ አደጋ ለማድረስ ማስፈራራት/መዛተት ነው።
ከስርቆት የሚለየው ቀጥተኛ ኃይል፣ ጥቃት ወይም የዛቻ ድርጊት (Violence or Threat) የሚታከልበት በመሆኑ ነው።
4️⃣ ውንብድና (Brigandage / Banditry)
በቡድን በመደራጀት ወይም መሣሪያ በመታጠቅ መንገድ በመዝጋት፣ በሕዝብ ወይም በግል ንብረት ላይ ጥቃት በማድረስ የሚፈጸም እጅግ ከባድ የዝርፊያና የሽብር ድርጊት ነው።
በታጠቀ ቡድን የሚፈጸም፣ የህዝብን ሰላምና ጸጥታ በከፍተኛ ደረጃ የሚያናጋ እና ከግል ንብረት አልፎ የማኅበረሰብ ደህንነት ላይ አደጋ የሚደቅን ነው።
5️⃣ የስርቆት ዕቃ መሸሸግ (Receiving or Storing Stolen Property)
አንድ ንብረት በስርቆት፣ በዝርፊያ ወይም በወንጀል የተገኘ መሆኑን እያወቁ ወይም መጠራጠር ሲገባው ንብረቱን መግዛት፣ መረከብ፣ ማስቀመጥ ወይም መሸሸግ ነው።
ግለሰቡ በስርቆቱ ድርጊት ላይ ቀጥታ ባይሳተፍም፣ በወንጀል የተገኘውን ንብረት በስውር በመያዙ ወይም በመግዛቱ ተጠያቂ ይሆናል።
6️⃣ ከባድ መሸሸግ (Aggravated Storing/Concealment)
የሌላውን ሰው ወንጀል መሸሸግ ወይም የተሰረቀ ንብረት መረከብ በከባድ ሁኔታ ሲፈጸም ነው።
ዋና መለያዎች፦
#ድርጊቱን የተለመደ ሙያ ወይም ንግድ (Habitual Business) አድርጎ ሲይዘው፤
# በከባድ ወንጀል (ለምሳሌ፦ በዝርፊያ ወይም በውንብድና) የተገኘ ንብረት መሆኑን እያወቁ ሲሸሽጉ፤
# በስፋትና በከፍተኛ ደረጃ የተደራጀ የመሸሸግ ድርጊት ሲሆን።
“ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!”
የወንጀል ሕጋችን የንብረት መብትን ለማስከበርና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ለእያንዳንዱ ድርጊት እንደ ከባድነቱ መጠን የተለያየ የሕግ ተጠያቂነትና የቅጣት እርከን አስቀምጧል።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 782 |
| 6 | የሰነድ አለመኖር የካሳ መብትን ያሳጣል?
=========================
ለመሆኑ አንድ ግለሰብ ለአሥርተ ዓመታት የቆየ ይዞታ እያለው፣ ይዞታውን የሚያረጋግጥ "የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ወይም ደብተር" ስለሌለው ብቻ ያለ ካሳ ከመሬቱ እንዲፈናቀል ሕጉ ይፈቅዳል?
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 198400 (ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም) በሰጠው ውሳኔ ለዚህ ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ሰጥቷል።
የክርክሩ መነሻ
አመልካች በጅማ ከተማ ውስጥ ለረጅም ዘመን የቆየ ይዞታ ያላቸው ሲሆን፣ የከተማው አስተዳደር "ይዞታው ለሕዝብ ጥቅም ይፈለጋል" በሚል ለልማት ሲነሳ አመልካች "የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ (ካርታ) የላችሁም" በሚል ካሳ ሳይከፈል እንዲነሱ መወሰኑ ክርክሩን አስነስቶታል።
የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ
መደበኛ ፍርድ ቤቶች "አመልካች በቅድሚያ የይዞታ ማረጋገጫ ማውጣት ነበረባቸው" በሚል የሰጡትን ውሳኔ የሰበር ሰሚ ችሎቱ በመሻር የሚከተሉትን መሠረታዊ የሕግ ነጥቦች አስፍሯል፦
የሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ፦ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(1) እና (7) መሠረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በሠራው ንብረት ላይ ሙሉ መብት አለው። መንግሥት ለሕዝብ ጥቅም ሲል ንብረቱን በሚወስድበት ጊዜም ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት።
የሰነድ አለመኖር እና የይዞታ መብት፦ አንድ ግለሰብ ይዞታው ላይ ለረጅም ዘመን መቆየቱ እየታወቀ፣ አስተዳደራዊ በሆኑ ምክንያቶች ወይም በወቅቱ የነበሩ አሠራሮች ባለመኖራቸው ምክንያት የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ባይኖረውም፣ ይዞታው ለሕዝብ ጥቅም ሲፈለግ "ሰነድ የለህም" በሚል ብቻ ያለምንም ካሳ እንዲነሳ ማድረግ የሕግ መሠረት የለውም።
የአስተዳደሩ ግዴታ፦ ይዞታው ለሕዝብ ጥቅም ሲፈለግ፣ አስተዳደሩ በቅድሚያ ይዞታው የአመልካች መሆኑንና ለምን ያህል ጊዜ እንደቆዩ አጣርቶ ተገቢውን ካሳ ሊከፍል ይገባል እንጂ፣ ካሳ ላለመክፈል የሰነድ አለመኖርን እንደ መከላከያ ሊጠቀምበት አይችልም።
ይህ ውሳኔ በተለይ በከተማም ሆነ በገጠር በይዞታቸው ላይ ለረጅም ዘመን የቆዩ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ (ካርታ) ያልወጣላቸው ዜጎች፣ ለልማት ሲነሱ የመካስ መብታቸውን የሚያስከብር ነው።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 918 |
| 7 | 👉በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር እንደተደነገገዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ የሽያጭ ዉል በጽሁፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት መደረግ እንዳለበት ሕጉ አስገዳጅ
ልዩ የሆነ አጻጻፍ(ፎርም) ደንግጓል፡፡ 👉የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 አተረጓጎምና ተፈጻሚነት በሚመለከት ይህ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 36887 ላይ እና በሌሎች መዝገቦች ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ በተመለከተዉ አስገዳጅ ትርጉም መሰረት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስርየተደነገገዉ የዉል አጻጻፍ(ፎርም) ዋና ዓላማ በተዋዋይ ወገኖች የቤት ሽያጭ ዉል ለመኖሩ በማስረጃነት እንዲያገለግል
በመሆኑ በመካከላቸዉ የቤት ሽያጭ ዉል እንደነበርና ገንዘብምተቀባብለዉ እንደነበር አምነዉ ዉሉ
በዉል አዋዋይ ፊት አለመደረጉንና አለመመዝገቡን(authenticate አለመደረጉን) ብቻ ምክንያት
በማድረግ ዉል የለም ብለዉ የሚቃወሙ ተከራካሪዎችን የሚያጠቃልል እንዳልሆነ ትርጉም
ሰጥቷል፡፡
👉በመሆኑም የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ተፈጻሚነት ተዋዋዮች የቤት ሽያጭ ዉል በዉል አዋዋይ ፊት በማድረግ አላስመዘገብንም ብለዉ ቢከራከሩም መዋዋላቸዉንና የሽያጭ ገንዘብ መቀባበላቸዉን እስካመኑ ድረስ ዉሉ ዉጤት እንዳይኖረዉ የሚያደርግ አይደለም፡፡
👉በአንጻሩ
ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛዉ በተለይም ሻጭ ዉሉን አልተዋዋልኩም ብሎ በተከራከረ ጊዜ ሕጉ በዚህ
ድንጋጌ ላይ በተቀመጠዉ የአጻጻፍ ስርዓት መሰረት እንዲፈጸም የፈለገዉ ዉሉ መኖሩን ለማረጋገጥ በመሆኑ ዉሉ በዉል አዋዋይ ፊት ካልተደረገና ተዋዋይ ነዉ በተባለዉ ወገን ከተካደ ሊፈጸም የሚችል ዉል የለም ወደሚል ድምዳሜ የሚያደርስ ነዉ ፡፡
👉በተያዘዉ ጉዳይ ተጠሪ ለክሱ መነሻ የሆነዉን የቤት ሽያጭ ዉል አልፈጸምኩም፤አልፈረምኩም የቤት
ሽያጭ ገንዘብ ነዉ ተብሎ በዉሉ የተገለጸዉን በብር 650,000.00 አልተቀበልኩም በማለት በግልጽ
ክደዉ መከራከራቸዉን ከሥር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔዎች ግልባጭ ተመልክተናል፡፡
👉ይህም የሚያሳየዉ የተጠሪ ክርክር የቤት ሽያጭ ዉሉ ፊት አልተደረገም እንዲሁም ተረጋግጦ አልተመዘገበም የሚል ብቻ ሳይሆን ዉሉ ስለመደረጉ ክደዉ መከራከራቸዉን ነዉ፡፡
👉በመሆኑም ለክሱ መነሻ የተደረገዉ ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት በጸና አኳኋን የተደረገና በሕግ ፊት
ዉጤት የሚኖረዉ አይደለም ተብሎ በይግባኝ ሰሚዉ ችሎትና በስር ፍርድ ቤት የተደረሰዉ ድምዳሜ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡
👉 ሆኖም ግን በጸና አኳኋን የአጻጻፍ ስርዓቱን ተከትሎ ባለመደረጉ በሕግ ፊት ዉጤት አይኖረዉም የተባለ ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1808/2 ስር በተደነገገዉ መሰረት ፈርሶ ዉለታዉን ለመፈጸም የተደረገ ነገር ቀሪ ሆኖ ተዋዋዮች ዉሉ ከመደረጉ በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባ ፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1815 ስር በመደንገጉ ዉሉ ዉጤት የለዉም የሚባል ከሆነ አመልካች ከፈልኩኝ ያሉትን ገንዘብ ተጠሪ ሊመልሱ የሚገባ መሆን አለመሆኑ መወሰን ስላለበት ነዉ፡፡ 👉ስለሆነም በዉሉ ላይ ተጠሪ
መፈረማቸዉ በፎረንሲክ ምርመራ መረጋገጡ ግራ ቀኙን ወደነበሩበት ሁኔታ ለመመለስ ጥቅም ላይ
የሚዉል ማስረጃ ሆኖ ከሚቀር በስተቀር ተጠሪ ዉሉን አልተዋዋልኩም ብለዉ በግለጽ ክደዉ ያቀረቡትን ክርክር እና ዉሉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት በጸና አኳኋን
አልተደረገም በማለት ያሰሙትን ክርክር ዋጋ የሚያሳጣ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችልአይደለም።
የሰ/መ/ቁ... 185708
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 196 |
| 8 | *25 የሙስና ወንጀሎች**
(አዋጅ ቁጥር 881/2007 )
1. በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል (አንቀፅ 9)
2. ጉቦ መቀበል (አንቀፅ 10)
3. የማይገባ ጥቅም መቀበል (አንቀፅ 11)
4. አስታራቂ ሽማግሌዎችና ሌሎች ሰዎች የሚፈፅሙት ጉቦ የመቀበል ወንጀል (አንቀጽ 12)
5. የመንግስት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት (አንቀጽ 13)
6. አደራ በተሠጠው ዕቃ ያለአግባብ ማዘዝ (አንቀፅ 14)
7. በሥራ ተግባር የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል (አንቀፅ 15)
8. በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ (አንቀፅ 16)
9. በህገወጥ መንገድ መሰብሳብ ወይም ማስረከብ (አንቀፅ 17)
10. ያለአግባብ ጉዳይን ማጓተት (አንቀፅ 18)
11. ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት (አንቀፅ 19)
12. ያለአግባብ ፍቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ (አንቀፅ 20)
13. ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ (አንቀፅ 21)
14. የሥራ ሚስጥርን መግለፅ (አንቀፅ 22)
15. መንግሥታዊ ወይም የህዝባዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት፣ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል (አንቀፅ 23)
16. መንግስታዊ ወይም የህዝባዊ ድርጅት ስነዶችን ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ (አንቀ8 24)
17. ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት (አንቀፅ 25)
18. ዋጋ ያለዉን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ መስጠት (አንቀፅ 26)
19. ማቀባበል (አንቀፅ 27)
20. በሌለው ሥልጣን መጠቀም (አንቀፅ 28)
21. በግል ተሰሚነት መነገድ (አንቀፅ 29)
22. በምርጫ ላይ የሚሰጥ መደለያ (አንቀጽ 30)
23. ከባድ የእምነት ማጉደል (አንቀፅ 31)
24.ከባድ አታላይነት (አንቀፅ 32)
25. በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ ስለመርዳት (አንቀጽ 33
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 339 |
| 9 | 👉ቼክ ተላላፊ የገንዘብ ሠነድ በመሆኑና በዋስትናነት አይሰጥም በሚል በሕግ የተደነገገ ክልከላ ባለመኖሩ በመርህ ደረጃ ቼክ ለዋስትና ሊሰጥ ይችላል፡፡ ሆኖም በሰበር መዝገብ ቁጥር 166392 ላይ በቀን 26/08/2012 ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ ላይ በመርህ ደረጃ አግባብነት ያለዉ የፍ/ብ/ህጉና የንግድ ህጉ ለቼክ የሰጡት ዋና ዓላማ ለመያዣነት እንዲያገለግል ነዉ ባይባልም እንደማንኛዉም ሊተላለፉ እንደሚችሉ ሰነዶች በመያዣነት ወይም በዋስትና ሊሰጥ እንደሚችልና ይህ በሚሆንበት ጊዜ ግን በንግድ ህጉና በፍ/ብ/ህጉ ላይ በተቀመጡት ግልፅ ድንጋጌዎች መመራት ይኖርበታል (የን/ህ/ቁ 950 ና ፍ/ብ/ህ/ቁ. 2866)።
👉በተለይ የመያዣ ዉል ስምምነት በሚደረግ ጊዜ ዉሉ መከተል ስላለበት ፎርም በተመለከተም በግልፅ የተደነገገ ስለመሆኑ ከን/ህጉ ቁ. 952 እና የፍ/ብ/ህጉ ቁ. 2828 መመልከት ይቻላል።
👉 የመያዣ ወይም የዋስትና ዉል
ህጉ በፅሑፍ በሰነድ ካልተደረጉ በህግ ፊት ዋጋ የላቸዉም (ፈራሽ ናቸዉ) በማለት ከደነገጋቸዉ ጥቂት የዉል ዓይነተች ዉስጥ አንዱ ስለመሆኑ ግልፅ ነዉ (የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1725(ሀ)፤ 1922(1-3)፣ 2828(1-2))። ሌላዉ ደግሞ የመያዣዉ ስምምነት ለምን ግዴታ እንደተደረገ፣ የግዴታዉ መጠን (ከፍተኛ የገንዘብ ወሰን) በጥንቃቄ ግልፅ መደረግ እንዳለበትናስምምነቱ የተደረገበት ቀን በግልፅ ልቀመጥ እንደሚገባ ህጉ የግድ ይላል (የፍ/ብ/ህ/አንቀጽ 2828 (1-2)፣ 2864-2866ና የን/ህ/ቁ. 952)። እነዚህ የህጉ አስገዳጅ ድንጋጌዎች
ካልተሟሉ የመያዣ ስምምነት ዉል አለ ማለት አይቻልም።
👉 ስለሆነም ቼኩ የተሰጠዉ ለዋስትና ዓላማ እንደሆነ ተገልጾ በጽሁፍ የዋስትና ዉል ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር ቼክ ለዋስትና አላማ ተሰጥቷል በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት እንደሌለዉ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡
👉ተጠሪ ቼኩን የሠጡት የዕቁብ ዕጣ ሲወጣላቸው ለዋስትና ዓላማ ከሆነ ይሕ ስለመሆኑ በጸሁፍ የተደረገ የመያዣ ውል (pledge) በማቅረብ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡
👉የሰ/መ/ቁ. 201980
ቀን ፡- ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ/ም
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 433 |
| 10 | በመሬት ድንበር መገፋት ጉዳይ ፍርድ ቤት ከተጠየቀው ዳኝነት በላይ ሊወስን ይችላልን?
መግቢያ
በከተማም ሆነ በገጠር መሬት ድንበር መገፋት ምክንያት የሚነሱ ክርክሮች በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች በብዛት ከሚታዩ ጉዳዮች መካከል ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች ከሳሽ ወገን በክሱ ውስጥ የተገፋበትን መሬት መጠን በግልጽ ሁኔታ ጠቅሶ ዳኝነት ይጠይቃል። ከዚያም ፍርድ ቤቱ በምስክሮች፣ በካርታ ባለሙያዎች ወይም በአስተዳደር አካላት አጣርቶ እውነተኛውን የተያዘ መሬት መጠን ያረጋግጣል።
ጥያቄው የሚሆነው ግን በምርመራው የተገኘው መጠን ከከሳሽ በክሱ ውስጥ ከጠየቀው መጠን በላይ ቢሆን ፍርድ ቤቱ በሙሉ የተገኘውን መጠን ሊወስን ይችላልን? የሚለው ነው።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ. 165593 ቅጽ 28 በሰጠው አስገዳጅ ትርጓሜ መሠረት ፍርድ ቤቱ ከተጠየቀው ዳኝነት በላይ ሊወስን አይችልም።
1. የፍርድ ቤት ውሳኔ ወሰን በተጠየቀው ዳኝነት የሚወሰን መሆኑ
በፍትሐብሔር ክርክር ውስጥ የክርክሩን ወሰን የሚያስቀምጠው ከሳሽ በክሱ ውስጥ ያቀረበው ዳኝነት ነው።
ፍርድ ቤት የሚመለከተውም የቀረበውን ጥያቄ እንጂ ያልተጠየቀ ጉዳይ አይደለም።የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 182(1)
ይህ ድንጋጌ ፍርድ ቤቱ በክሱና በመከላከያው ውስጥ በቀረቡ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲወስን ያስገድዳል።
ምሳሌ፦አቶ አበበ ጎረቤቱ 50 ካሬ ሜትር መሬት ገፍቶብኛል ብሎ ክስ ቢያቀርብ፣ፍርድ ቤቱ የሚያየው 50 ካሬ ሜትሩን እንጂ ከዚያ ውጭ ያልተጠየቀ ጉዳይ አይደለም።
2. ከተጠየቀው በላይ መጠን በምርመራ ቢገኝ ምን ይሆናል?
በባለሙያ ምርመራ፣ በካርታ መለኪያ ወይም በአስተዳደር አካል ማጣራት 60 ወይም 70 ካሬ ሜትር መሬት መያዙ ቢረጋገጥም ፍርድ ቤቱ በቀጥታ ከተጠየቀው በላይ ሊወስን አይችልም።
ምክንያቱም ያልተጠየቀን መብት ማስፈጸም የፍርድ ቤቱ ሥልጣን አይደለም።ምን አልባት ቀሪውን በሌላ መዝገብ መጠየቅ እንደሚችሉ መጠቆም ይቻላል።
ምሳሌ፦ አቶ አበበ 50 ካሬ ሜትር እንደተያዘበት ጠየቀ።በመሬት ምርመራ 80 ካሬ ሜትር መያዙ ተረጋገጠ።ፍርድ ቤቱ 80 ካሬ ሜትር ተመልሶ ይሰጥ ብሎ ሊወስን አይችልም።በክሱ ውስጥ የተጠየቀው 50 ካሬ ሜትር ብቻ ላይ ይወስናል።
3. የፍርድ ቤት ግዴታ በተጠየቀው ዳኝነት መጠን ብቻ መወሰን መሆኑ
የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 224(1) ፍርድ ቤት በክርክሩ ውስጥ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ ብቻ መወሰን እንዳለበት ያስገድዳል።ይህም ከተጠየቀው በላይ አይፈረድም የሚለውን የሥነ-ሥርዓት መርህ ያንፀባርቃል።
ምሳሌ፦ ከሳሽ 100,000 ብር ካሳ ከጠየቀ፣ማስረጃው 150,000 ብር ጉዳት መኖሩን ቢያሳይም፣ፍርድ ቤቱ 150,000 ብር ሊፈርድ አይችልም።ከፍተኛው የሚፈርደው 100,000 ብር ብቻ ነው።
4. የሰበር ችሎት ውሳኔ ቁጥር 165593 ያስቀመጠው መርህ
ሰበር ችሎቱ እንዲህ ብሎ አስገዳጅ ትርጓሜ ሰጥቷል።በመሬት ድንበር መገፋት ጉዳይ ከሳሽ የጠየቀው ዳኝነት መጠን ከአስተዳደር አካል በተደረገ ማጣራት ከተገኘው መጠን ያነሰ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ በተጠየቀው ዳኝነት ልክ ብቻ መወሰን አለበት።ይህ ማለት የፍርድ ቤቱ ሥልጣን በከሳሽ ጥያቄ ወሰን ውስጥ ብቻ እንደሚንቀሳቀስ ያሳያል።
5. ከሳሽ ከተጠየቀው በላይ መጠን ካረጋገጠ ምን ማድረግ ይችላል?
ከሳሽ በምርመራው ከተጠየቀው በላይ መሬት መያዙን ካረጋገጠ፣
ክሱን ለማሻሻል ሊጠይቅ ይችላል፤ወይም በተገቢው ሂደት ተጨማሪ ዳኝነት ሊጠይቅ ይችላል።ነገር ግን ፍርድ ቤቱ በራሱ ተነስቶ ከተጠየቀው በላይ ሊፈርድ አይችልም።
የዚህ መርህ አስፈላጊነት
ሀ. የተከሳሽን የመከላከል መብት ይጠብቃል
ተከሳሹ የሚከላከለው በቀረበበት ጥያቄ መጠን ነው።
ለ. የፍርድ ሂደትን ፍትሐዊ ያደርገዋል
ያልተጠየቀ ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንዳይሰጥ ያደርጋል።
ሐ. የፍርድ ቤትን ገለልተኝነት ያረጋግጣል
ፍርድ ቤቱ የአንዱን ወገን ጥያቄ ከፍ አድርጎ አይተካም።
ማጠቃለያ
በመሬት ድንበር መገፋት ጉዳዮች የፍርድ ቤት ውሳኔ ወሰን የሚወሰነው በከሳሽ በቀረበው የዳኝነት ጥያቄ ነው። የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 182(1) እና 224(1) እንዲሁም በሰበር መዝገብ ቁጥር 165593 ቅጽ 28 በተሰጠው አስገዳጅ ትርጓሜ መሠረት፣ በምስክር ወይም በአስተዳደር አካል ማጣራት የተገኘው የተያዘ መሬት መጠን ከተጠየቀው በላይ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በተጠየቀው ዳኝነት ልክ ብቻ መወሰን አለበት።
ይህ መርህ የፍርድ ሂደቱን ፍትሐዊነት፣ የተከሳሽን የመከላከል መብት እና የፍርድ ቤትን ገለልተኝነት ለማስጠበቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 350 |
| 11 | የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ሊከናወን የሚችለው ጋብቻው ሲፈርስ ብቻ ነው።ፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 27/2018
➤መዝገብ ቁጥር 143/2017
ከድንጋጌዎች ማየት የሚቻለው ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ የሚኖራቸው የንብረት ግንኙነት ለጋራ ንብረት የተሻለ ቦታ መስጠቱን ነው። በመሆኑም ፍርድ ቤቶች በትዳርኛዎች መካከል የሚደረገውን የንብረት ክርክር በሚመለከቱት፣ በሚመረምሩና ሲወስኑ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ የሕግን ግልጽ ድንጋጌዎች፤ ሕገ መንግሥቱ ለቤተሰብና ለጋብቻ የሰጠውን ልዩ ጥበቃና በጋብቻ ውስጥ ሊያሳካ ያሰበውን ማኅበራዊ ዓላማ መሰረት ያደረገ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ ወይም በተቃራኒ የሚሰጥ ውሳኔ ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግሥትና በሕግ ከተሰጣቸው ሥልጣን ውጪ እንዲሄዱና የሕግ የበላይነት መርህ እንዲሸረሸር የሚያደርግ ነው። በተለይም ይህ አይነቱ ጥበቃ ሴቶችን የማብቃት እና በፍቺ ወቅት ለሴቶች መብት መከበር ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በጥንቃቄ ሊተረጎም የሚገባው ነው።
የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክርክር ሊቀርብ እና በፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊሰጥበት የሚችለው በባልና ሚስት መካከል ያለው ጋብቻ ሲፈርስ ብቻ ነው። የባልና ሚስት ጋብቻ ጸንቶ ባለበት ሁኔታ ፍርድ ቤቶች በባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ላይ የሚያደርጉት ክርክር እና የሚሰጡት ውሳኔ የሕገ መንግሥቱን አንቀፅ 34 የሚጥስ ነው።
ባልና ሚስት ወይም ከሁለቱ አንዱ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት መብትን ለማስከበር ከሌሎች 3ኛ ወገን ጋር የሚያደርጉት ክርክር ንብረቱ የባልና ሚስት ወይም የ3ኛ ወገን መሆን አለመሆኑን ብቻ በመወሰን ክርክሩን መቋጨት አለባቸው እንጂ አልፈው የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር በማድረግ የሚሰጡት ውሳኔ ከሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 34 ጋር የሚቃረን ነው።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 540 |
| 12 | ⚖️ በፍርድ ቤት ክስ ከመመስረትዎ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ የሕግ ነጥቦች! ⚖️
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በተለያዩ መዝገቦች ላይ የሰጣቸውን የሕግ ትርጓሜዎች አጠናቅረን አቅርበንልዎታል፡፡
እነዚህ ነጥቦች፣ አንድ ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ዓይነት መሠረታዊ ነገሮችን ማሟላት እንዳለበት፣ እንዲሁም ክሱ ተቀባይነት ሊያጣ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ያሳያሉ፡፡
1. የክስ ምክንያት እጦት (Lack of Cause of Action)
አንድ ክስ ከሕግ አንጻር ተቀባይነት ያለው መሠረት ከሌለው፣ ፍርድ ቤቱ ከመጀመሪያው ውድቅ ሊያደርገው ይችላል፡፡
🚫 ሕገወጥ የገጠር መሬት ውል: የገጠር መሬትን ለረጅም ዓመታት (ለምሳሌ ለ80 ዓመት) በውል መስጠት የሽያጭ ውጤት ስላለው ሕገወጥ ነው፡፡ በዚህ ሕገወጥ ውል መሠረት ይዞታ የያዘ ወገን እንዲለቅ ይገደዳል፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 199452)
🚫 የማይንቀሳቀስ ንብረት ውል ማስረጃ: የቤት ሽያጭ ውል መኖሩን ለማስረዳት፣ በሕግ ሥልጣን ባለው አካል ፊት በጽሑፍ የተደረገ ውል መቅረብ አለበት፡፡ (ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723(1)) (ሰ/መ/ቁ. 199400)
🚫 "ውል ይፈረምልኝ" ጥያቄ: "የሽያጭ ውል ይጸናልኝ" ወይም "ተከሳሽ ቀርቦ ይፈርምልኝ" የሚል የዳኝነት ጥያቄ፣ ውል በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ በሕግ ተቀባይነት የሌለውና ሊቀርብ የማይችል ጉዳይ ነው፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 225310)
🚫 በውል ያልተገደበ አካል: ውልን መሠረት በማድረግ፣ በውሉ ተዋዋይ ባልሆነ 3ኛ ወገን (ለምሳሌ በንብረት አስተዳዳሪ) ላይ የክስ መሠረት የለውም፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 190775)
🚫 የስጦታ ውል መፍረስ: በስጦታ ውል ላይ ያልተመዘገበ ቅድመ ሁኔታን (ለምሳሌ "ሊጦረኝ" በሚል) በማንሳት ውሉ እንዲፈርስ መጠየቅ የክስ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 197354)
2. ክስ የማቅረብ መብትና ጥቅም (Locus Standi - ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 33)
ክስ ማቅረብ የሚችለው በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ መብት ወይም ጥቅም ያለው ወገን ብቻ ነው፡፡
📌 የሕጋዊ ጥቅም መኖር: ማንኛውም ሰው ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑን ካላረጋገጠ በቀር ክስ ማቅረብ አይችልም፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 180756)
📌 የሕጋዊ ሰውነት መኖር: የንግድ ማኅበራትና ድርጅቶች ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉት ሕጋዊ ሰውነት (በአግባቡ የተመዘገቡ) ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 199173)
📌 የበሰለ ክስ መሆን: አንድ ባለአክሲዮን "ወደፊት ተጠያቂ ልሆን እችላለሁ" በሚል ስጋት ብቻ ግብር እንዲከፈል ክስ ማቅረቡ፣ እዳው ገና "ያልበሰለ" (not mature) በመሆኑ ሕጋዊ ጥቅም የለውም፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 206807)
📌 የሁከት ክስ አቅራቢ: "ሁከት ይወገድልኝ" ክስ ለማቅረብ၊ አመልካች በሕጋዊ መንገድ ይዞታውን በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ የያዘ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 197775)
3. በይርጋ (Prescription) የመክሰስ መብት መገደብ
ሕግ፣ መብትን ለመጠየቅ የተወሰነ የጊዜ ገደብ ያስቀምጣል፡፡ ይህ ጊዜ ካለፈ መብቱ በይርጋ ይታገዳል፡፡
⏳ የጋራ ንብረት ገቢ: በጋራ ሀብት የተገኘ ገቢ (ፍሬ) እንዲካፈል የሚቀርብ ክስ፣ ያላግባብ መበልጸግን መሠረት ያላደረገ በመሆኑ በ2 ዓመት ይርጋ አይታገድም፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 197753)
⏳ የውርስ ይርጋ መቋረጥ: ወራሾች የውርስ ይዞታውን በጋራ ሲጠቀሙበት ከቆዩ፣ የ3 ዓመቱ የውርስ ጥያቄ ይርጋ (ፍ/ሕ/ቁ 1000) ይቋረጣል፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 197567)
⏳ የሕፃናት ውርስ መብት: የወላጅ ውርስ ድርሻ የሚጠየቅበት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው፣ ወራሹ (ሕፃኑ) አካለ መጠን ከደረሰ በኋላ ነው፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 197567)
⏳ ሥልጣን በሌለው ፍ/ቤት መክሰስ: ክስን ሥልጣን ለሌለው ፍ/ቤት አቅርቦ መከራከር፣ ይርጋውን የሚያቋርጥ በቂ ምክንያት ሆኖ ይወሰዳል፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 199323)
4. ሥነ ሥርዓታዊ ገደቦች (Procedural Bars)
📜 Res Judicata (በፍርድ ያለቀ ጉዳይ): አንድ መሠረታዊ ጭብጥ (ለምሳሌ የውል መቋረጥ ጥፋት) ቀደም ሲል በሌላ መዝገብ ተወስኖ የጸና ከሆነ፣ በድጋሚ ሊመረመር አይገባም፡፡ (ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5) (ሰ/መ/ቁ. 197790)
📜 ከተጠየቀው ዳኝነት ውጪ መወሰን: ፍርድ ቤት በክሱና በመከላከያው ላይ በተነሱት ጭብጦች ላይ ብቻ መወሰን ሲገባው፣ ከተጠየቀው ዳኝነት ውጪ ሊወስን አይችልም፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 197942)
📜 የሁከት ክስ vs. ባለቤትነት: በባለይዞታነት (ሁከት) ክርክር ላይ፣ ፍርድ ቤቱ አድማሱን አልፎ በባለሀብትነት (የመፋለም) ጉዳይ ላይ መወሰኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 198594)
📜 በፍርድ አፈጻጸም ላይ አዲስ ዳኝነት: የአፈጻጸም ችሎት፣ በዋናው ክርክር ያልተጠየቀን ነገር (ለምሳሌ ቤት የማፍረስ ትዕዛዝ) በአፈጻጸም መዝገብ ላይ ሊሰጥ አይገባም፡፡ (ሰ/መ/ቁ. 199518)
እነዚህ ነጥቦች የፍትሐብሔር ክርክሮች ውስብስብነትና የሥነ ሥርዓት ሕጎችን በአግባቡ መረዳት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ያሳያሉ።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 425 |
| 13 | በአደራ የተሰጠ ገንዘብ መኖሩን ለማስረዳት ተቀባይነት የሚኖረው ማስረጃ በጽሑፍ የተደረገ የአደራ ውል እንጂ ሌላ የቃል ወይም የሰነድ ማስረጃ ስላለመሆኑ
የፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 2782 እና 2472(1)
የሰ/መ/ቁ፦ 149861 ቅፅ 23
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 557 |
| 14 | new criminal procedure and evidence code Draft .docx | 2 662 |
| 15 | ምክር ቤቱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አፀደቀ
(ዜና ፓርላማ) መጋቢት 24፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
ረቂቅ ሕጉ በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት የወንጀል ፍርድ ሂደት የተጠርጣሪን እና የተከሳሽን እንዲሁም በወንጀል ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ሰብአዊ መብቶች ለማክበርና ለማስከበር የሕግ የበላይነት በማስፈን የአሰራር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል፡፡
የተቀላጠፈ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እና ልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴን እንዲሁም ለተጎጂዎች ካሣ የሚከፈልበትን አግባብ ያካተተ ዓለም አቀፍ መርህን የተከተለ ረቂቅ ሕግ እንደሆነ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ አያይዘው አስረድተዋል፡፡
ረቂቅ ሕጉ ከኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እና ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ መርሆች እና እሴቶች እንዲሁም ከወንጀል ህጉ ጋር የተጣጣመና ዘመናዊ በመሆኑ ጠቀሚ እንደሆነ ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል፡፡
ረቂቅ ህጉ በህገ መንግስቱ፣ በወንጀል ሕጉ፣ ዓለም አቀፍ ህጎች እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች የተረጋገጡ ልዩ ትኩረት ለሚያሻቸው ለሴቶች፣ ህፃናት እና አካል ጉዳተኞች የተሰጣቸውን መብቶች ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነም የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ረጅም ጊዜ የቆየና የዘገየ ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ወቅቱን የሚመጥን አዋጅ በመሆኑ የህዝብን የፍትህ ሥርዓቱን ለማስፈን እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡
የዜጎችን ሰብአዊ እና ዲሞክራሲአዊ መብቶችን ለማስከበር እና የፍትህ ሥርዓቱን በማዘመን ወቅቱን ያዋጅ አግልግሎት ለመስጠት ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን የምክር ቤት አባላት አመላክተዋል፡፡፡
በሌላ በኩል የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ በአተገባበር ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ከፍትህ አካላት ጋር መወያየት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
ከምርመራ ሂደት እና ከዲጂታል አሰራሮች ጋር በተያያዘ ዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብትን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት የምክር ቤት አባላቱ አስገንዝበው፤ በማረሚያ ቤት ቆይተው ፍርድ ቤት ነፃ የሚላቸው ዜጎች የካሳ ክፍያ ሥርዓትን ለመዘርጋት በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማስቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ምክር ቤቱ፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ፤ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 አድረጎ በሁለት ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 2 605 |
| 16 | 👉በፍርድ ቤት በክርክር ላይ ባለ ጉዳይ ተከራካሪ ወገኖች ነገሩን በእርቅ ለመጨረስ ተስማምተው፣ እርቁም በጽሁፍ ተደርጎ ለፍርድ ቤት ቀርቦ፣ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተረጋግጦ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ከተደረገ፦
👉የእርቁ ስምምነት እንደ ፍርድ ተቆጥሮ የአፈጻጸም ክስ ሊቀርብበት የሚችል መሆኑ፤
👉ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በተከራካሪ ወገኖች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር፣ እንደ መደበኛ ውል "ውል ይፍረስ" ተብሎ አዲስ ክስ ማቅረብ አይቻልም።
👉አንዴ በፍርድ ቤት የጸደቀ የዕርቅ ስምምነት እንደ ማንኛውም ተራ ውል ተቆጥሮ "ውሉ ይፍረስልኝ" ተብሎ አዲስ ክስ እንደማይመሰረትበት ነው። 👉ይልቁንም ስምምነቱ እንደ ፍርድ ስለሚቆጠር፣ አንዱ ወገን ባይፈጽም በቀጥታ ወደ አፈጻጸም (Execution) ነው ።
👉የሕግ መሠረት፦ የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 274(2)፣ 386፣ 3...
👉የመዝገብ ቁጥር፦ 143086 ቅጽ 28
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 2 275 |
| 17 | 7 መሰረታዊ የፍርድ አፈጻጸም መርሆች
***
በዳንኤል ፍቃዱ / ጠበቃና የህግ አማካሪ/
1. የአስፈጻሚው ፍርድ ቤት ሥልጣን እና ተግባር
የውሳኔው ተገዢነት፦ የአስፈጻሚው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የፍርድ ውሳኔ የማስፈጸም ጠባብ ሚና ብቻ ነው ያለው። በፍርዱ ላይ አዳዲስ መብቶችን የመጨመር ወይም ግዴታዎችን የመቀነስ ሥልጣን የለውም (As is principle)።
ትርጓሜ፦ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በድጋሚ የመስማት ሥልጣን ባይኖረውም፣ በፍርዱ አጻጻፍ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦች ካሉ ውሳኔው ሊፈጸም በሚችልበት ሁኔታ ላይ ጠባብ የትርጓሜ ሥራ ሊሠራ ይችላል።
2. ሐራጅ እንደ የመጨረሻ አማራጭ
ቅድሚያ የሚሰጣቸው አማራጮች፦ የንብረት ሽያጭ የመጨረሻው አማራጭ ነው። ሕጉ ከሐራጅ በፊት በስምምነት፣ በግል ሽያጭ ወይም ንብረቱን በዓይነት በማካፈል ዕዳው የሚከፈልበትን መንገድ ያበረታታል።
ሐራጅን የማስቆም መብት (አንቀጽ 427)፦ አንድ የፍርድ ባለዕዳ ሐራጁ ከመጠናቀቁ በፊት ሙሉ ዕዳውን፣ ወለዱን እና የአፈጻጸም ወጪውን ከከፈለ ሐራጁን የማስቆም መብት አለው። ከፊል ክፍያ ግን ሽያጩን አያስቆምም።
3. የሥነ-ሥርዓት መስፈርቶች (የሐራጅ ማስታወቂያ)
የሐራጅ ማስታወቂያ፦ ሕጋዊ ሐራጅ ለማካሄድ ስለ ንብረቱ ትክክለኛ መግለጫ እና ወቅታዊ የገበያ ዋጋ የያዘ ማስታወቂያ (በአንቀጽ 423 መሠረት) መውጣት አለበት።
ጥብቅ ተገዢነት፦ ተጫራቾች በማስታወቂያው ላይ በተጠቀሰው መግለጫ ይገደዳሉ። ለምሳሌ ማስታወቂያው ላይ የተጠቀሰው የቦታ ስፋት ካለው ትክክለኛ ስፋት ያነሰ ቢሆንም፣ ገዢው የሚያገኘው በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሰውን ስፋት ብቻ ነው።
4. የሁለተኛ ሐራጅ ሥርዓት (አንቀጽ 428)
የመጀመሪያ ሐራጅ፦ የቀረበው ከፍተኛ ዋጋ ፍርድ ቤቱ ካስቀመጠው ግምት ጋር እኩል ካልሆነ ወይም ካልበለጠ ንብረቱ አይሸጥም።
ሁለተኛ ሐራጅ፦ የመጀመሪያው ሐራጅ ካልተሳካ፣ በሁለተኛው ሐራጅ ወቅት ንብረቱ ለቀረበው ከፍተኛ ዋጋ ይሸጣል። በዚህ ደረጃ ዕዳው እንዲከፈል ለማድረግ ሲባል መጀመሪያ የተቀመጠው ግምት ዋጋ አይኖረውም።
5. የሦስተኛ ወገኖች ጥበቃ (አንቀጽ 418)
ተቃውሞ የማቅረብ መብት፦ በፍርዱ ሂደት ውስጥ ተከራካሪ ያልነበሩ ሦስተኛ ወገኖች፣ ንብረቱ ከመታገዱ በፊት በንብረቱ ላይ ሕጋዊ መብት ወይም ይዞታ ካላቸው አፈጻጸሙን የመቃወም መብት አላቸው።
የውል ቅድሚያ፦ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ እንደሚያሳየው፣ ንብረቱ ከመታገዱ በፊት የተደረገ ሕጋዊና የተመዘገበ የሽያጭ ውል፣ ምንም እንኳ የባለቤትነት ካርታው ዝውውር ባያልቅም፣ ከእገዳው በላይ ቅድሚያ ይሰጠዋል።
6. የሕገ-መንግሥት ገደቦች (የገጠር መሬት ሽያጭ ክልከላ)
የመሬት ባለቤትነት፦ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(3) መሠረት መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ነው።
የገጠር መሬት ሽያጭ፦ የገጠር መሬትን ለዕዳ መክፈያነት በሐራጅ መሸጥ በፍጹም የተከለከለ ነው። በገጠር መሬት ላይ ያሉ እንደ መጋዘን ያሉ ግንባታዎችንም ለመሸጥ የሚደረግ ጥረት በሕግ ፊት ዋጋ የለውም።
7. የክፍያ ክፍፍል (አንቀጽ 403)
በተመጣጣኝ የማካፈል መርህ፦ አንድ አበዳሪ ንብረቱን ቀድሞ ስላሳገደ ብቻ ቅድሚያ አያገኝም። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ፣ ንብረቱ ሳይሸጥ በፊት የአፈጻጸም ጥያቄ ላቀረቡ ሁሉም የፍርድ ባለመብቶች እንደ ዕዳቸው መጠን በተመጣጣኝ (Pro-rata) ይከፋፈላል
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 2 170 |
| 18 | የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 28
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 1 868 |
| 19 | አቤቱታን ስለማሻሻል የተሰጡ 5 የሰበር ውሳኔዎች
✍🏿 ከሳሽ በመጀመሪያ ቀጠሮ ያላቀረበው ማስረጃ በሂደት እንዲያቀርብ ከተፈቀደ ተከሳሽም የቀረበውን ማስረጃ አግባብነት እና ተአማኒነት ለመቃወም እንዲችል የመከላከያ መልሱ እንዲያሻሽል ሊፈቀድለተ ይገባል፡፡ ተከሳሽ በማስረጃው ላይ አስተያየት ብቻ እንዲሰጥ መገደብ የመከላከል መብቱን ያጣብባል፡፡ ሰ.መ.ቁ 160314 ቅጽ 24።
✍🏿 ክስ እንዲሻሻል ሲፈቀድ ከሳሽ ቀድሞ ያቀረበውን የክስ ምክንያት መቀየር አይችልም፡፡ ስለሆነም ብድር ለማስመለስ የቀረበ ክስ እንዲሻሻል ከተፈቀደ በኋላ የክሱን ምክንያት ወደ ያላአግባብ መበልፀግ በመቀየር የተሻሻለ ክስ ከቀረበ ፍርድ ቤቱ ሊቀበለው አይገባም፡፡ ያለመቀበሉ ውጤት ክርክሩን በቀድሞው የክስ ምክንያት እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ ሆኖም ከሳሽ በቀድሞው የክስ ምክንያት መቀጠል ካልፈለገ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ይዘጋዋል ሰ.መ.ቁ 161736 3 ለ 2 በሆነ በአብላጫ ድምጽ የተሰጠ።
✍🏿 የመከላከያ መልስ እንዲሻሻል ሲፈቀድ ተከሳሽ በመጀመሪያ መልሱ ላይ ያላቀረበውን አዲስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማንሳት አይችልም፡፡ ሰ.መ.ቁ 55973 ቅጽ 12።
✍🏿 አቤቱታ ሊሻሻል የሚችለው በጉዳዩ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነም በጉዳዩ ላይ ፍርድ ተሰጥቶ መዘገብ ከተዘጋ በኋላ አቤቱታ ለማሻሻል የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሰ.መ.ቁ 89641 ቅጽ 15።
✍🏿 ከሳሽ ክሱን እንዲያሻሽል ተፈቅዶለት ካሻሻለ ምንም እንኳን በተሻሻለው ክስ ላይ የተጨመረው ነገር መሰረታዊ የይዘት ለውጥ የማያመጣ መስሎ ቢታይም ፍርድ ቤት ተከሳሹ ለተሻሻለው ክስ አዲስ የመከላከያ መልስ እንዲያቀርብ ዕድል ሊሰጠው ይገባል፡፡ በመሆኑም “በተሻሻለው ክስ መልስ እንዲሰጥበት ማድረጉ የሚያመጣ ለውጥ አይኖረውም” በሚል ምክንያት ተከሳሽ ለተሻሻለው ክስ የመከላከያ መልሱን ሳያቀርብ ፍርድ ሊሰጥ አይችልም፡፡ ሰ.መ.ቁ 95620 ቅጽ 16
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 2 546 |
| 20 | የወራሽነት የምስክር ወረቀት መያዝና የውርስ ሀብት እየተጠቀሙ መቆየት በተመለከተ ሕጉ ምን ይላል?
የውርስ ሀብት እየተጠቀመ ያለ ሰው በማንኛውም ጊዜ የውርስ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል።
ነገር ግን አውራሽ ከሞተበት ጊዜ አንስቶ በሦስት ዓመት ውስጥ የውርስ ጥያቄ ያላቀረበ ሰው ውርስ ንብረት እየተጠቀመ ካልሆነ በስተቀር በእጁ የወራሽነት ምስክር ወረቀት ይዞ ቢገኝም የውርስ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም ፤ በይርጋ ተገድቧልና።
የሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 205248 (መ/ቁ. 44237፣38533 ወዘተ) የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው በማንኛውም ጊዜ የውርስ ንብረት ጥያቄ ማንሳት ይችላል በማለት የሰጠው ትርጉም ተለውጧል በማለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሰ/መ/ቁ.243973 ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss
https://t.me/aboutlawsss | 2 496 |
