Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Ethiopian Construction Vacancy & Tender Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK 📩 @Philemona7
نمایش بیشتر📈 تحلیل کانال تلگرام Ethiopian Construction Vacancy & Tender
کانال Ethiopian Construction Vacancy & Tender (@etconpwork) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 16 996 مشترک است و جایگاه 2 249 را در دسته حرفه و رتبه 1 963 را در منطقه أثيوبيا دارد.
📊 شاخصهای مخاطب و پویایی
از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 16 996 مشترک جذب کرده است.
بر اساس آخرین دادهها در تاریخ 29 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 427 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 5 بوده و همچنان دسترسی گستردهای حفظ شده است.
- وضعیت تأیید: تأیید نشده
- نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 15.86% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 10.34% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب میکند.
- دسترسی پستها: هر پست به طور میانگین 2 693 بازدید دریافت میکند. در اولین روز معمولاً 1 755 بازدید جمعآوری میشود.
- واکنشها و تعامل: مخاطبان بهطور فعال حمایت میکنند؛ میانگین واکنش به هر پست 7 است.
📝 توضیح و سیاست محتوایی
نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاههای شخصی توصیف میکند:
“Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World
Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK
📩 @Philemona7”
به لطف بهروزرسانیهای پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 30 ژوئن, 2026)، کانال همواره بهروز و دارای دسترسی بالاست. تحلیلها نشان میدهد مخاطبان بهطور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته حرفه تبدیل کردهاند.
የሰማይ ጠቀሱ ግድብ ምረቃየቅዳሜን እረፍት በምናጣጥምበት በዚህ ወቅት፣ በደቡብ ምዕራብ ቻይና ሲቹዋን ግዛት የሚገኘው የሹዋንግጂያንግኩ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ማመንጫ ክፍል ትናንት አርብ ዕለት ከዋናው የኃይል አውታር ጋር ተገናኝቷል፤
ይህ ክስተት በዓለማችን ላይ እጅግ ረጅሙ የሆነውን ግድብ የኃይል ማመንጨት ጉዞ በይፋ ያስጀመረ ሲሆን፣ በሰው ልጅ ምህንድስና ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፤ይህ ግዙፍ ግድብ 315 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የከፍታውን ዘውድ ጭነው የነበሩትን የጂንፒንግ-1 (Jinping-I) እና ሊያንግሄኩ (Lianghekou) የውሃ ማጠራቀሚያዎችን በመብለጥ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። ከአፈርና ከዓለት የተገነባው ይህ ግዙፍ መዋቅር፣ የሰው ልጅ በትጋትና በዕውቀት ተራራዎችን ማፍረስ ብቻ ሳይሆን አዲስ ተራራዎችንም መገንባት እንደሚችል ያሳየበት ህያው ምስክር ነው፤ ግድቡ 2 ሚሊዮን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ በዓመት በአማካይ 7.7 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት (kWh) ንጹህ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። የሚገርመው ነገር፣ ይህንን ግድብ ለመገንባት የፈሰሰው የአፈርና የዓለት ድምር መጠን ከ46 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ሲሆን፣ ይህንን ቁስ አንድ ሜትር ከፍታና አንድ ሜትር ስፋት ባለው ግንብ ብንደረድረው፣ የምድርን ወገብ አንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መዞር ይችላል!
ከዚህ አስደናቂ ስኬት ጀርባ ለአሥርተ ዓመታት የዘለቀ የጽናት ታሪክ አለ። የፕሮጀክቱ ዲዛይነር የሆነው POWERCHINA Chengdu የውሃ ሀብት ጥናቱን የጀመረው ገና በ1950ዎቹ (እ.ኤ.አ.) የነበረ ሲሆን፣ በዳዱ ወንዝ ላይ ያለውን የሃይድሮሊክ ፕላን ያረቀቀው ደግሞ በ1977 ነበር። ትውልዶች አልፈው እቅዱ ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ ለዓለም ድንቅ ስራ ለመሆን በቅቷል፤የጉዞው መንገድ አልጋ በአልጋ አልነበረም፤ እ.ኤ.አ. በ2003 በነበረው የአከላለል ማሻሻያ ወቅት፣ መጀመሪያ ታስቦ የነበረው “ዱሶንግ” የተባለው ፕሮጀክት ከመጠን በላይ መሬትን በውሃ ስለሚያጥለቀልቅ እንዲሰረዝ ተደርጎ ነበር። ሆኖም መሃንዲሶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ፣ ጥናታቸውን ወደ ላይኛው የወንዙ ክፍል በማሻገር የዙሙዙ እና የቹኦሲጂያ ወንዞች በሚገናኙበት ስፍራ ላይ የአሁኑን “ሹዋንግጂያንግኩ” (ትርጉሙም የሁለት ወንዞች መገናኛ) ግድብን መሰረቱ፤ የ315 ሜትር ከፍታውን ግድብ በዚያ አስቸጋሪ ስፍራ ላይ መገንባት ከባድ የተፈጥሮ ፈተናዎችን የጋበዘ ነበር። አካባቢው በከፍተኛ ከፍታ ላይ የሚገኝ፣ ብርድ የሚበረታበት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ያለበት እና የወንዙ ወለል የአፈር ንብርብር እጅግ ጥልቅ (እስከ 68 ሜትር) የሆነበት ቦታ ነው። ከዚህ ቀደም በዓለም ላይ በ250 ሜትር ጥልቀት ላይ እንዲህ ዓይነት ግዙፍ የአፈርና ድንጋይ ግድብ ተገንብቶ አያውቅም ነበር፤
በክረምት ወቅት ከ2,200 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ ስራን ለማቀላጠፍ የምህንድስና ቡድኑ በአይነቱ ልዩ የሆነ ትልቅ የአየር ድጋፍ ያለው ሽፋን (membrane structures) እና የፀሐይ ብርሃንን የሚያንጸባርቁ የማሞቂያ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሟል። ይህ ዘዴ የግንባታ ቁሳቁሱን ሙቀት በ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በመጨመር ስራው ያለ መቆራረጥ እንዲቀጥል ከማድረጉም በላይ፣ በዓለም የመጀመሪያውን ዘመናዊና ሙሉ ሰንሰለቱን የጠበቀ “የስማርት ቁጥጥር” ስርዓት ተግባራዊ አድርጓል፤ይህ ፕሮጀክት በከፍታው ብቻ ሳይሆን በበርካታ የምህንድስና ዘርፎች የዓለምን ክብረ ወሰን ሰባብሯል። በውስጡ የያዘው ከመሬት በታች የተገነባው የሃይል ማመንጫ ዋሻ (underground powerhouse)፣ እጅግ ረጅሙ የቁሳቁስ ማጓጓዣ ስርዓት፣ የዓለማችን ትልቁ የውሃ መሳቢያ ክሬን (hydraulic hoist) እና ግዙፉ የጎርፍ መልቀቂያ ዋሻ ፕሮጀክቱን የቴክኖሎጂ ቁንጮ ያደርጉታል፤ ከመሬት በታች ያሉትን ውስብስብ የጂኦሎጂካል ፈተናዎች ለመቋቋም ቡድኑ የአካባቢውን ሁኔታ መሰረት ያደረገ አዲስ “የዓለት ፍንዳታ (rockburst) ምደባ ስርዓት” ዘርግቷል። ይህ የፈጠራ ስራ የድንገተኛ ዓለት ፍንዳታ አደጋን በ40 በመቶ የቀነሰው ሲሆን፣ በቁፋሮ ወቅት ሊፈጠር የሚችለውን ከፍተኛ መዛባት ወደ 30 ሚሊ ሜትር ብቻ በመቀነስ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ደህንነት አረጋግጧል፤
ይህ ግዙፍ የውሃ ማጠራቀሚያ በዓመት 2.9 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም አለው። ሙሉ በሙሉ ስራ ሲጀምር፣ በወንዙ ግርጌ የሚገኙትን ሌሎች የሃይል ማመንጫዎች አቅም በ6.6 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ያሳድጋል፤ የሲቹዋንን የኃይል አቅርቦት ያረጋጋል፤ እንዲሁም በያንግትዜ ወንዝ ላይ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ በመከላከል ረገድ እንደ ታላቅ ጋሻ ሆኖ ያገለግላል። መልካም ቅዳሜ@etconp
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
