1 330
مشترکین
+324 ساعت
+87 روز
+8330 روز
آرشیو پست ها
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
“ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል የአለም የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በፓናል ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ተከብሮ ዋለ፡፡
በአለም ለ37ኛ ግዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ36ኛ ግዜ “ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል የአለም የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በፓናል ውይይት ተከብሮ የዋለ ሲሆን በእለቱም በመገኘት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ በንግግራቸውም ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ጤናውን የጠበቀ መምህርና የአስተዳደር ሰራተኛ ያስፈልጋል ስለሆነም ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ ራሱን እና ቤተሰቡን ከHIV AIDS ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡
HIV AIDS ሀገር ወደ ፊት ለመሄድ ስትል ወጣቱን እና ለስራ ዝግጁ የሆነውን ትውልድ እያጠፋ እንዳትሄድ የሚያደርግና ለድህነት ምንጭ የሆነ አስከፊ በሽታ ነው ይህን በሽታ አመራሩና የኮሌጁ ሰራተኞች በጋራ በመሆን ማህበረሰቡ ንቃተ ህሊናው እንዲዳብር የተለያዩ ስራዎችን በጋራ መስራት እንደሚገባ አያይዘው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ ዘገባ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በኮሌጁ አዳራሽ ተከብሮ ውሏል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ክብረ በዓል ላይ የኮሌጁ ምክትል ዲኖችና አመራሮች እንዲሁም አጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰቦች ተገኝተዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 20/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
የቴክኖሎጂ እሴት ሰንሰለት ትንተና እና ሰነድ ዝግጅት ላይ ያኮረ ስልጠና ከየዘርፍ መስሪያ ቤቶች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖለጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከትኩረት ዘርፍ መ/ቤት ለተውጣጡ ባለሞያዎች፤ ለኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለተውጣጡ መምህራኖች የእሴት ሰንሰለት ትንተና ስልጠና ተሰጠ፡፡
ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ ተወዳዳሪነትን የሚያረጋግጥ አዋጭ ቴክኖሎጂ ለኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር መሆኑን ጠቅሰው የምርት ወይም የአገልግሎት የአመራት ሂደት በመተንተን ክፍተቶችን በመለየት እና ለክፍተቶቹም የቴክኖሎጂዎችን መፍትሄ ለማስቀመጥ የእሴት ሰንሰለት ትንተና ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የዚህ ስልጠና ዋና አላማ ከትኩረት መ/ቤት የተውጣጡ የተለያዩ ባለሞያዎች የዘርፋቸውን እሴት ሰንሰለት መስራት እንዲችሉና ዘርፉን ተወዳዳሪ በማድረግ የስራ ዕድል እንዲፈጥር ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ሲሆን በሚለዩት ቴክኖሎጂዎች የኢንተርፕራይዞችን፣ የተቋማትን እና የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት በመጨመር ለበርካታ ዜጎች የሥራ-ዕድል ለመፍጠርና እና የገቢ መጠን ለመጨመር እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት በተለያዩ አዋጆች ዙሪያ ለአስተዳደሩ ነዋሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
በመድረኩም ከሁሉም የወረዳ አስተዳደር ስር የተወጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና ለስራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀል አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ህጋዊ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 1246/2013 ላይ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል።
በዚህም አዋጆቹን በመረዳት በሰዎች የመነገድ፣ በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገወጥ መንገድ ለስራ ወደውጭ ሀገር መላክ ወንጀልን በመከላከል ረገድ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ዓላማው አድርጎ ከዚህ በተያያዘ ህጋዊው የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አካሄድ ላይ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 18/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+7
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ጉዳዮች ላይና በእቅድ አፈፃፀሙ ላይ ከአሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት እና የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።
በ2017 ዓ.ም በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ ክንውን ከትምህርትና ስልጠና፣በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት፣ ለኮሌጁ ተጨማሪ ገቢን ከማስገኘት አንጻር አንዲሁም በአጫጭር ስልጠና እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር መልካም ትስስርን ከመፍጠር አንጻር በዝግጅት ምእራፍ ውስጥ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን እንዲሁም በቀጣይ ሩብ አመት የተሸለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን ከኢንዱስትሪዎች ጋር መልካም ትስስርን በመፍጠር የኢንዱስትሪዎችን ችግር ለመፍታት የተሰራው ስራ ለሌሎች ኮሌጆጅ ጭምር አርአያ የሆነና የኢንዱስትሪዎችን ችግር ከመፍታት በዘለለ ለኮሌጁም ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ መንገድ መሆን እንደ ቻለ በእለቱ ተገልጿል ።
በእለቱም በዝግጅት ምእራፉ የተሰሩ እንዲሁም በአዲሱ ዕሳቤ መሠረት የተጀመሩ ስራዎችን በተመለከተና አፈፃፀማቸውን በዘየደ ተክሌ የቀረበ ሲሆን በአፈጻጸሙ ላይና በአዲሱ እሳቤ ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጓል ።
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 18/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
ለነፃ የንግድ ቀጠናው ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ።
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ስኬታማ ለማድረግ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በተቀናጀ አግባብ መወጣት እንዳለባቸው ተገልጿል ።
የነፃ የንግድ ቀጠና ምንነትና የባለድርሻ አካላት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በአንድ ማዕከል አገልግሎት ስር ውስጥ ያሉ ባለድርሻ አካላት እና ለነፃ የንግድ ቀጠናው አመራሮች ተሰጥቷል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አማካሪ አቶ ፍፁም ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የነፃ የንግድ ቀጠናውን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ በመግባቱ ለስኬታማነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚሰጡትን አገልግሎቶች በቅንጅት እንዲሰጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ፍፁም በተጨማሪም ስልጠናው የነፃ የንግድ ቀጠናው ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን የቤት ስራ ወስደው ከመስራት ባለፈ ስራዎችን ተቀናጅቶ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ግንዛቤ ወስደው እንዲሰሩና በነፃ የንግድ ቀጠናው የሚሰጡ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በጥራት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊና የከተማ አስተዳደሩ ተወካይ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው የነፃ የንግድ ቀጠናው ከመሰረቱ ጀምሮ ለስኬታማነቱ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው አሁን ላይም በተሟላ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጥ በሚያስፈልገው ድጋፍ ሁሉ ከተማ አስተዳደሩ ለመስራት ዝግጁ ነው ብለዋል።
የነፃ የንግድ ቀጠና ምንነትና የባለድርሻ አካላት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት አድርጎ በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፤ጉምሩክ ኮሚሽን ፤ ኢትዮ ቴሌኮም፤የኢትዮ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፤የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ፤ የተስማሚነት ምዘና፤ካይዘን፤ የከተማ አስተዳደሩ ተወካዮች ፤የፌዴራል የፀጥታ አካላት እና የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
#ምንጭ IPDC
ለገቢራ - ድሬዳዋ!!
በዛሬው እለት ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በተገኙበት በለገቢራ ገጠር ቀበሌ የደረሰ የማሽላ ማሳ ሰብሎች መሰብሰብ እና በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተመረቱ 26 ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ አስረክበናል።
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚሰጠው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዝርዝር።
ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ!
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 16፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
ድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በራስ አቅም ያስጠናው የምሩቃን እና የስራ ገበያና ፍላጎት የጥናት ውጤት ሪፖርት የቀረበበት መድረክ ተካሄደ፡፡
ይህ የዳሰሳ ጥናት እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ያለብንን ክፍተት የለየና በቀጣይ በምን የስልጠና መስኮች ላይ ትኩረት በማድረግ መስጠት እንደሚኖርብን ያመላከተ የዳሰሳ ጥናት ነው ያሉት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ ኃላፊዋ በንግግራቸው ወቅት ወጣቶችን አሰልጥኖ ማስመረቅ ብቻ ሳይሆን በሰለጠኑበት ሙያ ለሀገር እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ሰልጣኞችን ወደ ገበያው ማስገባትና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የድሬዳዋና የአካባቢውን ጸጋ ተጠቅመው ራሳቸውንና አካባቢያቸውን መለወጥ የሚችሉ ሰልጣኞችን ማፍራት ላይ ትኩረት አድርገው ኮሌጆች መንቀሳቀስ አለባቸው ያሉ ሲሆን ፡፡ ድሬዳዋ ከተማችን ነጻ የንግድ ቀጠና እንደመሆኗ መጠን ለ ነጻ የንግድ ቀጠናው ተፈላጊ የሆኑ ባለሙያዎችን ከማፍራት አንጻር ኮሌጆች በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋል ። በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስራዎችን እየሰራበት ያለው መንገድ የሚበረታታና ለሌሎች አቻ ኮሌጆች እንደ ተሞክሮ የሚቀርብ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል ፡፡
በተጨማሪም በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ዲን የሆኑት አቶ ሰልሃዲን አብዱልሃሚድ እንዳሉት ይህ የዳሰሳ ጥናት በተከታታይ ሁለት አመታት የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተመራቂዎች ገበያው ከሚፈልገው የሰው ሀይል ፍላጎት አንጻር ያሉበትን ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበረና የጥናቱ ውጤትም ኮሌጁ ከተቋቋመበት አላማ አንጻር ሲታይ አላማውን ለማሳካት ምን አይነት ስራዎችን በቀጣይ ምን መስራት እንዳለበት ለኮሌጆች ፣ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር የጠቆመ የዳሰሳ ጥናት ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይ በዳሳ ጥናቱ የተገኙ ግብአቶችን እቅድ ውስጥ በማካተት የሚሰራ ይሆናል ።በመጨረሻም ለዚህ ጥናት መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጥናቱን አስመልክቶ የEASTRIP ፕሮጀክት የM & E Specialist የሆኑት አቶ መሳይ ጥላሁን እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በICOS Consulting PLC እንዲሁም በኮሌጁ አቅም ተመሳሳይ ጥናት መደረጉን አስታውሰው አሁን የተጠናው ጥናት በራስ አቅም ማስጠናት መቻላችን በወጪ ረገድ ዋጋ ቆጣቢ የሆነና ከመረጃ ጥራት ጋር በትኩረት መስራት እንድንችል ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጃችን ከኢንዱስትሪው ጋር የማስተሳሰር ስራ እንዲሁም ቀሪ ጥናቶችን ደግሞ ሁሉን አሳታፊ አድርገን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይም የሥራና ክህሎት ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ዳይሬክትር ፤የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊዎችና ተወካዮች፤ የሁለቱም ኮሌጆች ዲኖችና ም/ዲኖች እንዲሁም የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት፤የኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርድ አባላቶች እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 14/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
#ስለ_ቢሯችን_ምን_ማወቅ_ይፈልጋሉ?
የድሬዳዋ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይን የሚመለከት ተጠሪነቱ ለቢሮው የሆነ ቦርድ ይገኛል ይህም ቦርድ የወል የስራ ክርክሮችን የሚያይ፣ የመወሰን እና የማስማማት ስልጣን የተሰጠው ሲሆን ከመንግስት እና ከአሠሪና ሠራተኛ ማህበር ውክልና ያላቸውን አባላት ይዟል፡፡
በዚህም ይህ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የአደረጃጀትን እና የወል የሥራ ክርክሮች ለመፍታት በቢሮው የሚከናወነውን የፍትህ ማስፈን ተግባር የሚመራበት ወጥ የሆነ ቀልጣፋና ውጤታማ የአሠራር ሥነ-ስርዓት በመዘርጋት የቢሮውን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም የማሳደግ ስራ ይሰራል፡፡
ቦርዱ ምን ይሰራል?
በዋናነት የወል የሥራ ክርክሮችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ይቀበላል፤
ችሎት ያካሂዳል፤
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መደበኛ ስልጠና አጠናቃቂ ለሆኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች የኢንተርፕሩንርሺፕ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል::
ስልጠናው በዋናነት ሰልጣኝ ተማሪዎች መደበኛ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲወጡ ስራ ፈጣሪነትን ተላብሰው እንዲወጡና በሚፈጥሩትም ስራ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከመጥቀም ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ እንዲተርፉ የሚያስችላቸው የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና እንደሆነም ተገልፇል::
የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናውን የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከEntrepreneurship Development Institute(EDI)ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ስልጠናው በቀጣዮቹ ቀናትም ቀጥሎ የሚሰጥ ይሆናል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ህዳር 14/2017 ዓ.ም
በአረብ አገራት ተቀጥረው ለመሥራት የሠለጠኑ ሥራ ፈላጊዎች የቅድመ ጉዞ ስልጠና ተሰጣቸው!!
በኢትዮጵያ እና በስድስት አረብ አገራት መንግሥታት ሥምምነት መሰረት ወደ አገራቱ ከሚሔዱ ሥራ ፈላጊ ዜጎች መካከል በኮሌጆች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ሰልጣኞች ጉዞ ከማድረጋቸው በፊት አስፈላጊ የሆነ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ የሚያስቸላቸው ገለጻ በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአሠሪና ሠራተኛ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባሙያዎች ተደርጎላቸዋል።
በዚህም ከአገር ውጭ ለስራ ጉዞ ሲያደርጉ ቅድመ ጉዞ መደረግ እና ማሟላት የሚገባቸውን እንዲሁም በጉዞ ላይ እና ለስራ በሚሄዱበት አገር ሊገጥማቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በተብራራ መልኩ ማግኘታቸው በቂ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ሰልጣኞች ተናግረዋል።
በተያያዘ ባሳለፍነው አመት እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ስልጠናቸውን አጠናቀው በህጋዊ መንገድ ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ስራ ፈላጊዎች ወደ አረብ አገር የተላኩ ሲሆን በያዝነው አመት በመጀመሪያው ሩብ አመት ብቻ ወደ ስልሳ የሚጠጉ ስራ ፈላጊዎችን መላክ ተችሏል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 14/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለጥንቃቄ!
ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጫት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ በመሆኑ መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን እየገለጽን ዜጎቻችን በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
የሁለትየሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ማግኘት ከፈለጉ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተከናወነው የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ዙሪያ
ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በፕሮጀክቱ ተወካይ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ስልጠና ላይ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ጭምር በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በዚህም በመጀመርያ ዙር የፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በቀጣይ ለሚሰጠው ስልጠና እንቅፋት እንዳይሆኑ ከወዲሁ ለማስተካከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር የመፍትሄ አቅጣጫዋችን ማስቀመጥ ተችሏል።
መድረኩ ቀጥሎም እንደ አገር አዲስ የሆነው የሶላር ቴክኒሺያን እና ኤክስፐርት የስራ መዘርዝር 'JOB BOX ' ሰነድ ከሲቪል ሰርቪስ በመጣ ባለሙያ የቀረበ ሲሆን ሰነዱንም የሚመለከታቸው ተቋማት ሁኔታውን በደንብ ገምግመው ግብረመልስ ተሰቶበታል።
በቀጣይም የተሰራው የJOB BOX ሰነድ እንዲፀድቅና የሶላር ፒቪ ተጠቃሚ ተቋማት የሶላር ኤክስፐርት/ ቴክኒሺያን በመቅጠር የሶላር ዘርፍ ላይ ያለውን ከፍተኛ ክፍተት መሙላት እንደሚጠበቅባቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም በADRA ፕሮጀክት የሰለጠኑ ባለሞያዎችም ከሚከፈትላቸው የስራ እድልም ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደላድል ይፈጥራልም ተብሏል።
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 13/2017 ዓ.ም
