fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

رفتن به کانال در Telegram
1 328
مشترکین
+224 ساعت
+87 روز
+9730 روز
آرشیو پست ها
የአምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ባለሙያዎችን ማፍራት እንደሚገባ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ከሚገኙ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ጋር በኢንዱስትሪ ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ:: የምክክር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ ባስተላለፉት መልዕክትም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ወደ ኢንዱስትሪ የሚገቡትን ብቻ ሳይሆን ኢንዱስትሪው ላይ እየሰሩ የሚገኙትን ባለሙያዎችን ጭምር የሚፈለገው ደረጃ ላይ እንዲደርሱ አሰልጥኖ ማብቃት እንዱ ተግባሩ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም እንዲረዳ በየትኛው ዘርፍ ላይ ትኩረት ተደርጎ ቢሰራ የሚስተዋለውን ችግር መቅረፍ ይቻላል የሚሉትን ጉዳዮች በቀጥታ ከእናንተ ከጉዳዩ ባለቤቶቹ ጋር ለመወያይትና መረጃዎችን ለመሰብሰብ ይህ የምክክር መድረክ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም በሚኖረን የምክክር መድረክ ላይ ብዙ ግብዓቶች ከተሳታፊዎች እንደሚጠብቁ ገልፀው በኢንዱስትሪው ውስጥ ምርታማነትን ከማስፋፋት አንፃር እንዲሁም በትክክል የኢንዱስትሪውን እድገት እየጎተቱ ያሉ ጉዳዮችን ከቴክኒክና ሙያ ዘርፉ አኳያ ሊፈቱ የሚችሉትን በዝርዝር መረጃ እዲሰጡም ጠይቀዋል:: የዳሰሳ ጥናት ሰነዱን ለተሳታፊዎች ሰፋ ባለ ማብራሪያ ያቀረቡት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ በንግግራቸውም በዚህ ጉዳይ እስካሁን በነበረው የተናጠል እንቅስቃሴ የሚጠበቅውን ውጤት ማስመዝገብ እንዳልተቻለ አስታውሰው ከጅምሩ በቅንጅት ሲሰራ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር እንደሚቻልና ለሚስተዋሉ ችግሮችም የመፍትሄ አካል መሆን ስለሚቻል ሁላችንም በንቃት ልንሳተፍ ይገባልም ብለዋል:: ከመድረኩ በተደረገው ገለፃ መሰረትም አምራችና አገልግሎት ሰጪ እንዱስትሪዎች እንደየዘርፋቸው በቡድን ተከፋፍለው የምክክር መድረኩ የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎች በየድርጅቶቻቸው የተለዩ ፍላጎቶችን እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቡ ይሆናሉ ያሏቸውን ለመድረኩ አወያዮች በማቅረብ ለፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ ግብዓት ማግኘትም ተችሏል:: በተጨማሪም በመድረኩ የዳሰሳ ጥናት ፎርም አጠቃቅም በተመለከት በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አስተባባሪ አሰልጣኝ መ/ር አቤል ዘገየ አማካኝነት ለተሳታፊዎች ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ለዚህ ተግባር በተመደቡ ባለሙያዎች አማካኝነት በየኢንዱስትሪዎቹ በመሄድ ለዳሰሳ ጥናቱ የሚያስፈልገውን መረጃ የሚያደረራጁ መሆኑም በመድረኩ ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን የካቲት 27/2017 ዓ.ም

ለቅድመ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ፡፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም ከተለዩት ቅድመ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች መካከል ስራቸውን በመመልከት ለሞዴልነት እጩ የሆኑ 47 ኢንተርፕራይዞችን በመምረጥ በሞዴል መመሪያውና በቀጣይ ሞዴል ሆነው የሚያበቃቸው ሃሳቦች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የኢንተርፕራይዞችን አቅም ለማሳደግና የፋይናንስ ፍላጎታቸውን ለመደገፍ የተቋቋመው የሲድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ በሚሆኑበት አግባብ ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 25/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በአጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች እንቅስቃሴን አስመልክቶ ለከወረዳ ምክትል ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የአንድ ማዕከል እና የቢሮው ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ። በዚህም መድረክ ለተሳታፊዎች ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ጌታቸው በአስተዳደሩ የተፈጠሩ ዕድሎችን በተለይም የኢንደስትሪዎች መስፋፋት የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተከትሎ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን የአስተዳደሩ ሥራ ፈላጊዎች እንዲጠቀሙ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት እንዲሁም የሥራ ፈላጊዎችና የኢንተርፕራይዞች ምዝገባ፤ በየመንደሩ የቤተሰብ ቢዝነሶች እንዲፈሩ ከማድረግ አኳያ በየጊዜው መሰል ውይይቶች እንደሚደረጉ አብራርተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ https://lmis.gov.et የሚከናወነው ምዝገባ በተለያዩ ህብረተሰቡ በስፋት በሚገኝባቸው ቦታዎች ድረስ በመሄድ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች እንደሚሰሩ የገለጹ ሲሆን በመጨረሻም "ብቃት" የወጣቶች ሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሶስተኛ ዙር ትግበራ መጀመሩን አስመልክቶ ሁሉም አካላት በቅንጅት በመስራት ከዚህ በፊት በሁለቱ ዙሮች የተገኘውን ውጤት በማሻሻል መድገም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 25/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና የተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በሁለቱ የመንግስት እና የግል ኮሌጆች ላይ የኢንስፔክሽን ምልከታ ማካሄድ ጀመረ፤ በዚህም ኢንስፔክሽን ኮሌጆቹ የሚሰጡትን ትምህርትና ስልጠና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተሰጡ ስለመሆኑ በአካል በመመልከትና በማረጋገጥ የሚታዩ ክፍተቶችና ችግሮች ቢኖሩ በአጭር ጊዜ ለማስተካከል እዲያስችል ግብረመልስ የሚሰጣቸው ይሆናል። የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ስለ ኢንስፔክሽኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን ጥራትን ማረጋገጥ ዋና አላማው አድርጎ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው  ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሴክተሮችን ባሳተፈ መልኩ እንደሚካሄድና በሁሉም ኮሌጆች በተመሳሳይ የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 25/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለውን ምቹ አጋጣሚ በመረዳትና ዘርፉንም በመቀላቀል በወርቃማ ጊዜያቸው አምራችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ዜጋ የሚያደርጏቸው አማራጮች ላይ በንቃት ሊስተፉ እንደሚገባ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሰራውን ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በማጠናከር በሳብያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚገኙ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘርፉን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄዷል:: በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማደረግ አኳያና እንደ ሀገር ከተያዘው የትኩረት አቅጣጫም አንፃር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለወጣቱ በተለይም ከዚህ በኃላ ወደዘርፉ ለሚቀላቀሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ብዙ መልካም እድሎችን የያዘ ዘርፍ መሆኑን በዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት በሰፊው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መስራት ተችሏል:: በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ለተማሪዎች መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚያስመዘግቡትን ውጤት ተከትሎ ዩኒቨርሲቲ በመግባትና ባለመግባት አቅማቸው እንደማይለካ በመናገር የቴክኒክና ሙያም ሌላኛው የተሻለው አማራጭ መሆኑንም ከወዲሁ መረዳት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ባለው ነባራዊ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ከሚገቡትም ይልቅ በቴክኒክና ሙያ ውስጥ የሚያልፉ ዜጎች በየትኛው መመዘኛ የተሻለ እድል ያላቸው መሆኑንም አፅዕኖት ሰተው ተናግረዋል:: አክለውም በተሻሻለው ፖሊሲ መሰረት የትኛውም በቴክኒክና ሙያ የሚያልፍ ሰልጣኝ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊያሳካ የሚችለውን የመጨረሻውን የPHD (Level 8) ድረስ እራሱን እያሻሻለ መድረስ የሚያስችለው አሰራርም መዘርጋቱን የገለፁ ሲሆን ተማሪዎችም የወደፊት እጣፈንታቸውን የሚወስኑበት ምርጫቸውን በጥንቃቄና ብስለት በተሞላበት መንገድ እንዲወስኑ ምክር ለግሰዋል:: የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎቶችን በማስገንዘብ የፈጠራ ሃሳባቸውን በኮሌጃችን ውስጥ እንዲያዳብሩ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን የገለፁት በኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም በት/ቤቱ ውስጥ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶችን በማቀናጀት የቴክኒክና ሙያ ክበብ እንደሚቋቋም ጠቅሰው ኮሌጁም ከዚህ ጋር ተያይዞ አስፈላጊው ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን የካቲት 25/2017 ዓ.ም

ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!
ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!

በአዲስ የተዘጋጁና የተከለሱ የሙያ ደረጃዎች፤ የስርዓተ-ስልጠና እና የማሰልጠኛ መሳሪያዎች የማስተዋወቂያ መድረክ ተዘጋጀ፤    በዚህም መድረኩም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲን መሰረት ተደርገው በ8(ስምንት ዘርፍ) የአገሪቱ የትኩረት ዘርፎችን መሰረት ተደርገው የተከለሱና የተዘጋጁ 192 ሙያ ደረጃዎች፤ የስርዓተ ስልጠና እና የስልጠና መርጃ መሳሪያዎችን በመንግስት እና የግል ኮሌጆች የዲፓርትመንት ተጠሪዎች፤ ስልጠናውን ለሚመሩ የስልጠና አስተባባሪዎችና ስልጠናውን ለሚደግፉ የቢሮው ባለሙያዎች በነባሩና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዝርዝር ሙያዎችን በማስተዋወቅ፤በማሰራጨትና አተገባበር ላይ የታዩ እና ያጋጠሙ አውንታዊና አሉታዊ ነገሮች ላይ በጋራ በመመክርና በመወያት ለመተግበርና በስራ ላይ ለማዋል መግባባት ተፈጥሯል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 21/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም ወር በሰላም አደረሳችሁ። ረመዳን ከሪም !!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም ወር በሰላም አደረሳችሁ። ረመዳን ከሪም !!

#ዜና| ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከመደበኛው ስልጠና በተጨማሪ ትምህርትና ስልጠናው ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በገጠር ክላስተር የሚገኙ ወጣቶችን እና ሴቶችን በአጫጭር ስልጠናዎች በማሰልጠን የእድገቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተባለ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ22 በላይ ከተለያዩ ገጠር ክላስተር ወረዳዎች የተውጣጡ ሰልጣኞችን የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዲሁም የቢሮው ም/ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በተገኙበት በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች በዛሬው እለት አስመረቀ ፡፡ ትምህርት እና ስልጠና ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ እድገት ቁልፍ መሳሪያ ነው።ይህንን መሳሪያ ደግሞ የከተማው ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ በገጠር ክላስተር የሚገኙ ወጣቶችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሊሰራ ይገባል ያሉት በምርቃቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው ሲሆኑ ፡፡ ኃላፊው አያይዘውም ይህ ስልጠና ከዚህ በፊት በገጠር ክላስተር የሚገኙ ሴቶች በስልጠና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን የመለሰ ነው ፡፡ በቀጣይም በዚህ ስልጠና የተሳተፉ ሴቶችን በማደራጀት እንዲሁም ከኮሌጁ ጋር በመተባበር የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ እንዲሰሩ እንደሚደረግ ገልጸዋል ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞ በሙያዊ ክህሎት እና በስነምግባር የታነፀ ተነሳሽነት የተላበሰ አምራች ዜጋን በጥራት እና በብዛት በመፍጠር ረገድ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ እድገት በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለጹትየስራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጣፋ ሲሆኑ አያይዘውም የሃገራችን ብልጽግና እንዲረጋገጥ በገጠር ክላስተር የሚገኙ ወጣቶችን ያማከለ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል ። በመጨረሻም ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ ኮሌጁ በመደበኛ ከሚሰጣቸው ትምህርትና ስልጠናዎች በተጨማሪ ብዛት ያላቸውን የአጫጭር ስልጠናዎች አዘጋጅቶ ለከተማው ወጣቶች ብሎም ለገጠሩ ክላስተር ወጣቶች እየሰጠ ይጋኛል ያሉ ሲሆን አያይዘውም በዛሬው እለት የተመረቃችሁ ለኮሌጁ አበንባሳደሮች ናችሁ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ወጣቶች በኮሌጁ በመገኘት ትምህርትና ስልጠናዎችን እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው እለት ያስመረቃቸው 10 በምግብ ስራ፣6 በጸጉር ስራ እንዲሁም 6 በልብስ ስፌት ሲሆን በአጠቃላይ 240 ሰአታትን በስልጠና አሳልፈዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን የካቲት 21/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አዘጋጅነት ለሚካሄደው 4ኛው ዙር የ2017 ዓ.ም የክህሎት ውድድር በአስተዳደር ደረጃ ለማካሄድ ተወዳዳሪዎች በውድድር  መስፈርቱ ላይ የግንዛቤ  ማስጨበጫ  ስልጠና ተሰጠ። በቀጣይም በተለያዩ ሙያዎች ላይ በአስተዳደር ደረጃ ውድድር የሚያካሂዱ ሲሆን ውድድሩን በበላይነት የሚያጠናቅቁ ተወዳዳሪዎች አስተዳደሩን በመወከል በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የክህሎት ውድድር አልፎም እስከ አለም  አቀፍ  ድረስ የሚዘልቅ  በዋናነት የስልጠና  ጥራትንም ከማሳደግ አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ የሚኖረው ይሆናል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 20/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ለግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችና ለአገልግሎት ተጠቃሚ ድርጅቶች አዲስ ተሸሽሎ የወጣውን አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና አዋጁን መሰረት በማድረግ በወጣው መመሪያ ቁጥር 45/2013 ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ አካሄደ፤ በዋናነት ስልጠናው እንዲዘጋጅ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሕግና አሠራርን በመከተል ፍትሃዊ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የሥራ ስምሪት አገልግሎት በሀገር ውስጥ የሚሰጡበትን ሁኔታ መወሰን በማስፈለጉ፤ በኤጀንሲ አማካኝነት ለሥራ የተሰማራውን ሠራተኛ መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ኤጀንሲው እና የአገልግሎት ተጠቃሚው ድርጅት ሊኖራቸው የሚገባውን የጋራና የተናጠል ኃላፊነት ለይቶ የማመልከቱ ተገቢነት ስለታመነበት ነው፤ በዚህም የስልጠና መድረክ ይህንን መመሪያ ኤጀንሲዎቹ እንዲረዱ ከማድረጉ ጎንለጎን እንደከዚህ ቀደሙ ህገወጥ የሆኑትን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ህጋዊነትን የሚያበረታታ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 20/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ