fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

رفتن به کانال در Telegram
1 331
مشترکین
+124 ساعت
+97 روز
+8030 روز
آرشیو پست ها
በድሬዳዋ አስተዳደር የተዘጋጀው፥ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ዛሬም ቀጥሎ ተካሄደ። ይህ ውድድር በስራ፥ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እንዲሁም በሳ
+4
በድሬዳዋ አስተዳደር የተዘጋጀው፥ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ዛሬም ቀጥሎ ተካሄደ። ይህ ውድድር በስራ፥ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እንዲሁም በሳይንስ፥ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ነው። በቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድሩ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል፥ የማርያም ሰፈር 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ያብስራ ከበደ አንዱ ነው፡፡ በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ጄኔሬተር በመስራት ለውድድር የቀረበው ተማሪ ያብስራ ከበደ፥ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራው ችግር ፈቺ ሆኖ ስላገኘው ለውድድይዞ መቅረቡን ተናግሯል፡፡ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማበልፀግ በአስተዳደሩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ፥ ይህ የፈጠራ ስራዎች ውድድር ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ተገልጿል። የድሬዳዋ ስራ፥ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የዘርፍ ሽግግር ባለሞያ አቶ ሸመልስ ፍሰሃ በበኩላቸው፥ በየአመቱ የሚካሄደው ይህ ውድድር ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት የሚደረገውን ጥረትም ያግዛል ብለዋል፡፡ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተጀመረው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ላይ ከአስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች፥ መምህራን እና ኢንተርፕራይዞች እየተካፈሉ ይገኛሉ። ©️ DireTVአማርኛ | ግንቦት 2016 ዓ.ም

ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራትና የሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚብሽን (Job fair) በማዘጋጀት ሥራ አጥ ዜጎችን ከሥራ ጋር ማስተሳሰር ተቻለ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ይህን ሥራና ሠራተኛ የሚገናኙበት መድረክ ሲያዘጋጅ የሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚብሽኖች አሰሪውና ሥራ ፈላጊው በአንድ ቦታ የሚገናኙበትና ሥራ ፈላጊዎች አሰሪው ላቀረበው ክፍት የሥራ ቦታ ያመለከቱበትና ቀጣሪው ቃለመጠይቅ ያደረገበት መድረክ ሆኗል፡፡ በዚህም መድረክ ላይ ተሳታፊ የሆኑ በአጠቃላይ ሥራ ፈላጊውና (job seekers) እና ቀጣሪዎች (Employers) በቀላሉ መገናኘት እንዲችሉ መንግሥት ከሚሰጣቸው የስራ ስምሪት አገልግሎቶች መካከል ሥራና ሰራተኛ ማገናኘት ኤግዚብሽን (Job fair) በተለይም ከኢንደስትሪዎች ጋር በማስተሳሰሩ ረገድ የላቀ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ተናግረዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ግንቦት 12/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

በአስተዳደር ደረጃ የ2016 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የሥራ ፈጠራ ውድድር መካሄድ ጀመረ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምርና ስልጠና ኤጀንሲና የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና  ኢኖቬሽን ኤጀንሲ በጋራ ባዘጋጁት የ2016 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የሥራ ፈጠራ ውድድር በአስተዳደሩ በሚገኙት የመንግስትና የግል ኮሌጆች በቴክኒክና ሙያ  ስልጠና ተዋናዮች (በሰልጣኝ፣ አሰልጣኝ እና አንቀሳቃሾች እንዲሁም ተቋማት) በተጨማሪም የአጠቃላይ ት/ቤት ተማሪዎችና መምህራን የሚያሳትፍ ይሆናል፤ የውድድሩ ዋናው አላማም በአስተዳደሩ የሚገኙ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ችሎታ ያላቸውን ወጣቶችና የሙያ ባለቤቶች መካከል  ከፍተኛ የውድድር ተነሳሽነትን መንፈስ በመፍጠር በመሰረታዊ  የስራ ፈጠራ፤ ተግባራዊ ምርምር እና ቴክኖሎጂዎችን የመቅዳት፣ የማሻሻል፣ የመፍጠር የማለማመድ እና የማሸጋገር ስራዎቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥራት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ይታሰባል፤ በውድድሩ ማስጀመሪያ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት በአዲሱ የዘርፉ ፖሊሲ በተመላከተው መሰረት የክህሎትና የቴክኖሎጂ አቅምን ሊያሳዩና ሊያሳድጉ የሚችሉ ውድድሮችን ማድረጉ በዘርፉ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን ከማነቃቃት በዘለለ ከኢንደስትሪው ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ሲሆን አስተዳደሩም የተለየ ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ግንቦት 9/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+1

የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከልና ቅድመ ምርመራ በማድረግ ከበሽታው ራስን ብሎም ማህበረሰብን ማዳን በሚቻልበት እንዲሁም በስራ ቦታ የኤች አይቪ ኤድስን የመከላከልና መቆጣጠር ፅንሰ ሀሳብ ላይ ለድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ፡፡ በቢሮው የሴቶች ወጣቶችና ኤች አይ ቪ ኤድስ ማስተባበሪያ አዘጋጅነት ከአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በተጋበዙ የጤና ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን አመራሩና ሰራተኛው ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እና ትኩረት በተሰጣቸው ሴቶችን፣ አምራችና ሰራተኛ ሀይሉን ተጠቂ የሚያደርጉ በሽታዎችን በመረዳት እራሱን በምርመራ በማወቅና በመጠበቅ የነቃ እንዲሆን የሚያስችለው ይሆናል፡፡ በመድረኩ ላይ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ተገኝተው በተለይ የኤች አይ ቪ ጉዳይ በማህበረሰባችን ዘንድ የሚታየው መዘናጋትና በበሽታው የሚከሰተውን ችግሮች መቅረፍ እንዲቻል መሰል መድረኮችን ማመቻቸት የሚገባ ሲሆን ለዚህም ሁሉም የቢሮው ማህበረሰብ የድርሻውን በትብብርና በኃላፊነት መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ የማህፀን በር ካንሰርን መከላከልና ቅድመ ምርመራ በማድረግ ስርጭቱንና ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት መቀነስ አሁን ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው መሆኑንና የሴቶች ጉዳይ ብቻ አድርጎ መመልከት ሳይገባ ወንዶችም ከሴቶች ጎን በመሆን መከላከሉን እና ቅድመ ምርመራውን ሴቶች እንዲያደርጉ ሊያበረታቱ እንደሚገባ ተሳታፊዎች አንስተዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ግንቦት 7/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+6

ከፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በመጣ ከፍተኛ ባለሙያ በ E-LMIS (Ethiopian Labor market information system) አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለኮሌጁ ማህበረ
+5
ከፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በመጣ ከፍተኛ ባለሙያ በ E-LMIS (Ethiopian Labor market information system) አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለኮሌጁ ማህበረሰብ በዛሬው እለት ተሰጠ:: የE-LMIS በስራና ክህሎት ሚንስቴር መስሪያ ቤት የበለጸገና የስራና ሰራተኛ ፍላጎትን ለማቀራረብ ታስቦ የተሰራ ሲስተም ሲሆን በተለይ በቴክኒክና ሙያ በኩል ስልጠናቸውን ለሚያጠናቅቁና ለምናሠለጥናቸው ሠልጣኞች የሥራ ትስስር ለመፈጸም የሚያግዝ ሲስተም ሲሆን የሀገራችንን የስራ አጥ ቅነሳው ስራ ላይ የራሱን ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችል ተደርጎ የበለጸገ ሲስተም እንደሆነ በግንዛቤ ማስጨበጫ ወቅት ተብራርቷል፡፡ በተጨማሪም ይህ ሲስተም ሲበለጽግ ተጨማሪ ከሌሎች ሲስተሞች የሚለይበትን ጉዳይ በባለሞያው ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የውጪ ሃገር ስራ ስምሪት እንዲሁም ከቅጥር ጋር የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ ታስቦ እንደተሰራም በእለቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን፣ የኮሌጁ ኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲን ወይዘሮ ትግስት በዙ እንዲሁም የዲፖርትመንት ተጠሪዎችና የማኔጅመንት አባላቶች መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡ የኮሌጅ ኮምኒኬሽን ግንቦት 07/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

አስተዳደሩን ፀጋ መሰረት ያደረገ ክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል፥ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ግንቦት 6/2016 ዓ/ም የክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ገበያ ተኮር አጫጫር ስልጠናዎች አፈጻጸም  ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚመክር መድረክ ተካሄደ። በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው መድረክ ላይ የአስተዳደሩ የከተማ ወረዳዎችና የገጠር ክላስተር አመራሮች፤ የአንድ ማዕከላት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጀማል አደም እንደተናገሩት ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በሁሉም ወረዳዎች ፀጋን መሰረት ያደረገና ክህሎት መር በሆነ መንገድ ማህበራትን በማደራጀት በተለይ ኮሌጆች በሚሰጧቸው ስልጠናዎች ተጠቃሚ ለመሆን በቅንጅት ሁሉም አካላት በመናበብ የሚሰሩበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ብለዋል። በመጨረሻም ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በአስተዳደሩ እስከ አሁን ስልጠና እየተሰጠ ካለባቸው የተወሰኑ ዘርፎች በተጨማሪ በሌሎች ዘርፎችም የሥራ ዕድል በመፍጠር በየአካባቢው ወደ ስራ ያልገቡ ወጣቶችን በመለየት ወደ ስራ እንዲገቡ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባው በመግለጽ ቀጣይ ሥራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ማጠቀለያ ሰጥተዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት

በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር እየተገነባ የሚገኘው የEASTRIP ፕጀክት የ Railway ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ህንጻ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የድሬዳዋ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤ
+3
በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር እየተገነባ የሚገኘው የEASTRIP ፕጀክት የ Railway ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ህንጻ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የድሬዳዋ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በተገኙበት የአንድ ወር የግንባታ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው እለት ተከናወነ፡፡ በግምገማው ላይ የልህቀት ማእከሉ አሁን ያለበትን ደረጃ በአማካሪ ድርጅቱ ተወካይ እንዲሁም ግንባታውን ለመገንባት ውል የገባው የአተም ኮንስትራክሽ ድርጅት ተወካይ በኩል ቀርቧል፡፡ በሪፖርቱ መሰረትም የተለያዩ ውይይቶች የተደረገ ሲሆን  በመጨረሻም ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዳሉት ይህ ህንጻ እንደ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ከሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው ስለዚህ የህንጻው ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለታለመለት አላማ እንዲውል ሁሉም አካላት በጋራ እና በርብርብ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ግንቦት 2/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

‹‹ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን ለመስራትና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የወረዳ እንዲሁም የክላስተር ማእከላት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል›› አቶ ሳሊም ኡስማን የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ******************************* በድሬዳዋ ከተማ ያሉ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስልጠና ፍላጎትን በመለየት በፍላጎታቸው መሰረት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ከወረዳ እና ከክላስተር ከተውጣጡ አመራሮች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተዘጋጀ፡፡ ውይይቱን የመሩትና የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን ሲሆኑ በንግግራቸውም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጃችን በላባቸው አምርተው በእጃቸው ሰርተው እራሳቸውን መጥቀም የሚችሉ ከዛም አልፎ ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጎች የሚፈሩበት ትልቅ ተቋም ነው፡፡ ስልዚህም በዚህ ተቋም እና በወረዳዎች እንዲሁም በክላስተር ማእከላት ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን ለመስራትና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የወረዳ እንዲሁም የክላስተር ማእከላት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ም/ዲንና የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ አቶ ሰልሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም በከተማም እንዲሁም በገጠር ያሉ ወጣቶችን የክህሎት ፍላጎት ለማሟላት ይቻል ዘንድ Mobile TVET ለማቋቋም እቅድ ይዘን እየተንቀሳቀስ እንገኛለን ይህም የወጣቶቻችንን የስራ በሃል እንዲሻሻል እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለሚፈጠረው የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ በኢንተርፕራይዝ ልማት እንዲሁም ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አንጻር በከተማም እንዲሁም በገጠር የሚገኙ ወጣቶች በኮሌጃችን ያለውን እምቅ አቅም እንዲጠቀሙ በጋራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ግንቦት 2/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የግብርናውን ዘርፍ ሊያዘምኑ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻልና ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በማዘመን የአስተዳደሩን የገጠር ነዋሪ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን መስራት እንዲያስችለው ከአስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ጋር ከዚህ በፊት የተደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ ወደ ተግባር መቀየር ባለባቸው ጉዳዮች ላይ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እንዲሁም የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች አመራርና ቴክኖሎጂ የሚሰሩ አሰልጣኝ መምህራን በተገኙበት ውይይት በማድረግ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ተፈጥሯል፡፡ በዚህ የሁለትዮሽ የውይይት መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተሰሩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተግባር ለማስገባት በቅንጅት መስራትና በተለይ የተጠቃሚውን ማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡ አቶ መሀመድ አሚን የአስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ም/ኃላፊ በበኩላቸው ፍላጎትን የመለየት ስራ በጋራ የሚሰራበትን ሁኔታ በማመቻቸትና የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ኃላቀር የአስተራረስ አካሄድን ለመቀየር በቁጭት መነሳት ይገባናል ያሉ ሲሆን በቀጣይ አመራሩ በበላይነት የሚመራው ከሁለቱም ቢሮዎችና ኮሌጆች የተወጣጡ ቴክኒካል ኮሚቴዎችን በማዋቀር ወደ ስራ ለመግባት ከስምምነት ተደርሷል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የግብርናውን ዘርፍ ሊያዘምኑ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻልና ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በማዘመን የአስተዳደሩን የገጠር ነዋሪ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን መስራት እንዲያስችለው ከአስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ጋር ከዚህ በፊት የተደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ ወደ ተግባር መቀየር ባለባቸው ጉዳዮች ላይ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እንዲሁም የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች አመራርና ቴክኖሎጂ የሚሰሩ አሰልጣኝ መምህራን በተገኙበት ውይይት በማድረግ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ተፈጥሯል፡፡ በዚህ የሁለትዮሽ የውይይት መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተሰሩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተግባር ለማስገባት በቅንጅት መስራትና በተለይ የተጠቃሚውን ማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡ አቶ መሀመድ አሚን የአስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ም/ኃላፊ በበኩላቸው ፍላጎትን የመለየት ስራ በጋራ የሚሰራበትን ሁኔታ በማመቻቸትና የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ኃላቀር የአስተራረስ አካሄድን ለመቀየር በቁጭት መነሳት ይገባናል ያሉ ሲሆን በቀጣይ አመራሩ በበላይነት የሚመራው ከሁለቱም ቢሮዎችና ኮሌጆች የተወጣጡ ቴክኒካል ኮሚቴዎችን በማዋቀር ወደ ስራ ለመግባት ከስምምነት ተደርሷል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

ከፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች በ E-LMIS ሲስተም አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ:: በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት ሀላፊና ምክትል ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ እንዲሁም የዲፖርትመንት ተጠሪዎችና በሂደቱ ስር የሚገኙ ባለሙያዎች በተገኙበት ስለ ሲስተሙ አሠራር፣ ፋይዳ እና ዉጤት ከዉጭ ሃገር ሥራ ስምሪትና የውስጥ ሥራ እድሎችን በማመቻቸት ላይ እንዲሁም የተለያዩ  ብልሹ አሠራሮችን ለማስቀረት የስርዓቱ ሚና የጎላ መሆኑንና ለዜጎች በE-LMIS ሲስተም ምን  ጥቅሞች እና እንዴት በቀረበላቸው ሲስተም መጠቀም እንደሚችሉ ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ ተሰጥቷል። እንዲሁም የE-LMIS ሲስተም ተጠቃሚ ለመሆን እንዴት በራስ መመዝገብ እንደሚቻል እና በቀረቡት ብዙ አማራጮች ተጠቃሚ መሆን ኢንደሚችሉም በቂ የሆኔ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

Repost from N/a
photo content
+9

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፡፡ በዓሉ የደስታ፣ የሰላም፣ የጤና እንዲሁም የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን፡፡ መልካም በዓል
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፡፡ በዓሉ የደስታ፣ የሰላም፣ የጤና እንዲሁም የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን፡፡ መልካም በዓል!                     አቶ ሮቤል ጌታቸው     የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ