1 331
مشترکین
+124 ساعت
+97 روز
+8030 روز
آرشیو پست ها
ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
****
የድሬዳዋ አስተዳደር
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም "ብቃት" የወጣቶች ሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የ2016 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡
መድረኩም በአዲሱ አገራዊ እሳቤ መሰረት አድርጎ ለዜጎች የስራ እድልን በመፍጠር አሁን ያለውን የሥራ አጥ ቁጥር ለመቀነስና የሥራ ባህልን በማጎልበት የሚያስፈልጓቸውን የሙያና የክህሎት ስልጠናዎች ወስደው ወደ ስራ እንዲሰማሩ በማመቻቸትና ራሳቸውን ከስራ አጥነት እንዲያላቅቁ በማድረግና በመተግበር ረገድ እንደ አስተዳደር በከተማና በገጠር የተሰሩ ስራዎች ተገምግመዋል፡፡
በዚህም የሚመለከታቸው የቢሮው አመራርና ባለሙያዎች፣ የወረዳ ሥራ ክህሎት ማስተባበሪያዎች እንዲሁም የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ አስተባባሪዎች በተገኙበት በ2016 በጀት አመት በዘጠኝ ወራት የተሰሩ አጠቃላይ የስራ ዕድል ፈጠራ በተለይም በብቃት ፕሮግራም የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ላይ ሁሉም የወረዳ አንድ ማዕከላት አፈጻጸማቸው ቀርቦ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ በአጭር እና በረጅም መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ላይ መወያየትና መግባባት መፍጠር ተችሏል፡፡
በመድረኩም ላይ የቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ በቢሮ እና በአንድ ማዕከላቱ መናበብ የተሰሩ መልካም ስራዎችን አበረታተው በቀጣይ በተለይ በአዲሱ ዕሳቤ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ዘለቄታቸውን እና አስተማማኝነታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ ድጋፍ እና ክትትሎችን አጠናክሮ መቀጠል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 23/2016 ዓ.ም
ሐረር
በኢትዮጵያ ለ49ኛ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ135ኛ ጊዜ እየተከበረ ላለው የአለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን እንኳን አደረሳችሁ!
ቀኑን ስናከብር የሠራተኞችን ጥቅምና መብቶች የማስከበር እንዲሁም ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኝነታችንን የምናሳይበት ይሆናል።
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
ድሬዳዋ
የ2016 ዓ.ም የላብአደሮች ቀን በድሬዳዋ ናሺናል ሲሚንቶ አ.ማ ቅጥር ግቢ ቡስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
ቀኑን በማስመልከት የቻይና ቲም ሰራተኞችና ኢትዮጵያዉያን ሠራተኞች የተሳተፉበት የተለያዩ አዝናኝ ስፖርታዊ ጫወታዎች ተካሄደዋል::
ሚስተር ዣንግ ለሰራተኞች ኢለቱን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሰተላልፈዋል
ዕለቱን በማስመልከት በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ መሀመድ ኢብራሂም የዘንድሮ በዓል በአዲሱ እሳቤ ምርትና ምርታማነትን ማዕከል ያደረገ መርህ የሚከበር መሆኑን ገልፀዉ አሰሪና ሰራተኛዉ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ግንኙት ማደበር እንደሚጠበቅባቸዉ መልዕክታቸዉን አሰተላልፈዋል
በዕለቱ በተካሄዱ ስፖርታዊ ዉድድሮች በግልና በቡድን አሸናፊ ለሆኑ በድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ Mr.ዣንግ ሚንሂንጉኣ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ከድሬዳዋ እና ከኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ጋር በመሆን ክህሎትን መሰረት ያደረገ ሃገር ወዳድነት እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ለማላበስ በሙያ ደረጃ ውስጥ የተካተቱ ብቃት አሃዶች እና ኮርሶችን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኝ መምህራንን ለማፍራት የሚያስችል ስልጠና ለአሰልጣኝ መምህራን ለተከታታይ ቀናት ተሰጠ፤፤
በዚህም የተሰጠውን ስልጠና አስመልክቶ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ያለ አሰልጣኝ መምህራን ልማት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ የሚታሰብ ስላልሆነ ትኩረት ተሰጥቶት በሁለቱም ኮሌጆች ላይ የውስጥ አቅምን በመጠቀምም ሆነ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በትብብር በኮሌጆቹ በተለዩ የእውቀት እና የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ ስራዎች መሠራታቸውን አውስተዋል።
ይህም ስልጠና አእምሮን፤ ልብን እና እጅን በተግባር ማገናኘት የሚችሉ፤ ሁለንተናዊ ብቃትን የተላበሱ፤ የአስተሳብ፤ የአመለካከት እና የስነ- ምግባር ባህሪ ለውጥ የሚያመጡ ስልጠና አጠናቃቂ ሰልጣኞችን ለማፍራት የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+3
ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆየው የኢትዮጵያ ታምርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር በድሬዳዋ ከተማ በይፋ ተከፍቷል።
ኤግዚቢሽን እና ባዛሩን የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ የአስተዳደሩ አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፈትህያ አደን መርቀው ከፍተዋል።
በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ ላይም የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተሳታፊ የሆነ ሲሆን በኮሌጁ የተሰሩ እና ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ያመረታቸው ችግር የፈታባቸው የተለያዩ የማሽነሪ መለዋወጫዎች ፣ በኮሌጁ የተሠሩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም የፋሽን አልባሳትና የቆዳ ውጤቶችን ለጎብኚዎች ይዞ ቀርቧል::
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from N/a
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በጎ አድራጎት ክበብ መጪው የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረገ::
የበጎ አድራጎት ክበቡ ያዘጋጀውን የአስቤዛ እና የገንዘብ ድጋፍ የኮሌጁ ዲኖች ተገኝተው ለአቅመ ደካሞች ያስረከቡ ሲሆን አያይዘውም ለመጪው የትንሳዔ በዓል መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል::
በዚህ ክበቡ ባደረገው የአስቤዛ እና የገንዘብ ድጋፍ ተጠቃሚ የሆኑት አካላት በኮሌጁ ማህበረሰብ ጥቆማ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ለተለዩ 20 እቅመ ደካሞች የአስቤዛና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው "ፅዱ ኢትዮጵያን እንፍጠር" ንቅናቄን ተቀላቀሉ!
ኢትዮያውያን ከዳር እስከ ዳር አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አሕመድን የ #ጽዱኢትዮጵያ የዲጅታል ቴሌቶን ንቅናቄን ተቀላቅለው የድርሻቸውን እያበረከቱ ይገኛሉ!
ንቅናቄውን ያልተቀላቀላችሁ አመራሮች፣ ባለሞያዎች እና ሁሉም ሰው ያገባኛል በሚል በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የ“ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ንቅናቄን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል::
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ላይ ያተኮረ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ተካሄደ፤
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በዘርፉ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን እና ባለሙያዎች እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡
በዚህም በዘርፉ ላይ በተለይም በኮሌጆች ላይ በአሰልጣኝ መምህሩ የሚነሱ ጥያቄዎች እና በሰልጣኝ ተማሪዎች ላይ የሚስተዋሉ መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮች ማለትም ውጤት ተኮር የትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ ስርዓት፣ የሰልጣኝ ተማሪዎች ቅበላና መጠነ ማቋረጥ፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አተገባበር ጋር የተያያዙ በዋናነት መሠረታዊ የዘርፉን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ጥናቶች ቀርበው ውድድር የተካሄደ ሲሆን ከተወዳዳሪዎችም አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ድሬዳዋን ወክሎ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡
ይህም ውድድር በዋነኛነት ለዘርፉ ችግር ፈቺ የሆኑ ሃሳቦች በማፍለቅ አሰራሮችን ለማሻሻል እና ለመከለስ በግብዓት የሚየገለግሉ እንደሚሆኑና ተወዳዳሪዎች በኮሌጆቻቸው በተግባር ፈትነው ያቀረቧቸው እነዚህ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮች ለዘርፉ መሻሻልና ማደግ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን በዳይሬክቶሬቱ የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ቡድን መሪ ወ/ሮ አለምፀሀይ ጌታቸው ተናግረዋል።
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+7
የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 በጀት አመት መደበኛና የEASTRIP እና SIFA ፕሮጀክት የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ የኮሌጁ ማህበረሰብ በተገኙበት በዛሬው እለት አካሄደ።
የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩን የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን የመሩት ሲሆን በተቋሙ የሚገኙ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲኖች እንዲሁም የስራ ሂደቶች የዘጠኝ ወር ተቋማዊ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን በኮሌጁ ፕላንና ፕሮግራም እንዲሁም የፕሮጀክቶችን ደግሞ በፕሮጀክቱ M&E specialist በኩል ለኮሌጁ ማህበረሰብ አቅርበዋል በተጨማሪም skills-based volunteerism በተቋሙ ውስጥ ለማስጀመር አጠቃላይ ገለጻ በአቶ ሳምሶን ተክሉ አማካኝነት ቀርቧል::
በእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩ በመደበኛና በፕሮጀክት ዋና ዋና ቁልፍ ተግባራት ፣ በተቋሙ የማስፈፀም አቅም ፣በሀብት አጠቃቅም እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ የሪፖርት ግምገማ የተደረገ ሲሆን የቀጣይ ሦስት ወር የሚሠሩ ቀሪ ስራዎች ላይ የስራ አቅጣጫን በማስቀመጥ መድረኩ ፍፃሜውን አግኝቷል።
የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ ከሚገኙ የወረዳ አመራሮችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ አካሄደ።
የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በመድረኩ ለተገኙ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተልዕኮና ስትራቴጂ እንዲሁም በተቋማት ጥራት ቁጥጥር ላይ ኤጀንሲው እያከናወናቸው ስለሚገኙ ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፤
በመድረኩ ከአመራሮቹና ከሚመለከታቸው ለተወጣጡ አካላት የዘርፉን ተልዕኮ ለማሳካትና ጥራትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉና በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በተለይም በአጫጭር ስልጠና እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ውጤታማነትን ከማሳደግ አንጻር መግባባት ተፈጥሯል፡፡
ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ስራዎች ያመላከቱት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ መሰል መድረኮች በስፋት እንደሚዘጋጁ በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታሪኩ ለገሰ ተናግረዋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ለቀበሌ አንድ ማዕከላት ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ፡፡
በዚህም ቅድመ ሞዴል፣ ሞዴል፣ እድገት ሽግግርና ከምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ጋር በተያያዘ ኢንተርፕራይዞችን የመለየትና ለሞዴልነት የበቁ ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍና ክትትል በሰፊው ለማካሄድና በኢንተርፕራይዞች መረጃ ምዝገባ (LMIS) ዙሪያ የተሰሩትን ስራዎች የገመገመ ሆኗል፤
ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ሽግግራቸው እንዲሰራላቸው፣ በሞዴል መመዘኛ መሰረት እንዲመዘኑ ከዛ ውስጥ የተሻለ የሚባሉትን በምርጥ ተሞክሮ በተጨማሪ ታዳጊ መካከለኛ በየአመቱ የሚሸጋገሩትን በመስፈርቱ መሰረት የመለየት ስራ በቀጣይ ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ተወካይ ወ/ሮ መቅደስ ከፈለኝ ተናግረዋል።
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
