fa
Feedback
Anu Parenting Solutions 🇪🇹 with Tigist G.

Anu Parenting Solutions 🇪🇹 with Tigist G.

رفتن به کانال در Telegram

I am Tigist, Mom, Developmental Psychologist ✨ Certified Parenting Coach ✨ Helping 🇪🇹 parents discipline without shouting/yelling 📩 1:1 Coaching @Anuparenting

نمایش بیشتر
1 416
مشترکین
-124 ساعت
-37 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
Who taught you about sex education?
Anonymous voting

At what age did you first learn about sex education?
Anonymous voting

When do you think children should start learning sex education?
Anonymous voting

ስለወሲብ/relationship መቼ እና ከስንት አመት ጀምሮ ነው ማስተማር ያለብን? Comment ላይ ፃፉ 👇👇👇👇
ስለወሲብ/relationship መቼ እና ከስንት አመት ጀምሮ ነው ማስተማር ያለብን? Comment ላይ ፃፉ 👇👇👇👇

የወላጅ ጥያቄ መች ይመስላቸዋል???
የወላጅ ጥያቄ መች ይመስላቸዋል???

My dear! ስለወሲብ መቼ እና ከስንት አመት ጀምሮ ነው ማስተማር ያለብን?

ቀን 6፡ ስሜትህ ትእዛዝ አይሰጥህም (Your Feelings Don't Have to Control Your Actions) ብዙ ጊዜ እንዲህ እንላለን፦ "በጣም ተናድጄ ነበር፣ ስለዚህ ጮህኩ።" ግን ቁጣ ስ
ቀን 6፡ ስሜትህ ትእዛዝ አይሰጥህም (Your Feelings Don't Have to Control Your Actions) ብዙ ጊዜ እንዲህ እንላለን፦ "በጣም ተናድጄ ነበር፣ ስለዚህ ጮህኩ።" ግን ቁጣ ስሜት ነው፤ ጩኸት ደግሞ ምርጫ ነው። ቁጣ መሰማት ስህተት አይደለም። ነገር ግን ቁጣችንን እንዴት እንገልጻለን የሚለው የእኛ ምርጫ ነው። ሁሉም ወላጆች ይናደዳሉ። ነገር ግን የተረጋጉ ወላጆች አንድ ነገር ይማራሉ፦ "ስሜቴን ማስተዋል እችላለሁ፣ ግን ስሜቴ እንዲመራኝ አልፈቅድም።" Today's Challenge ዛሬ ቁጣ ሲሰማችሁ... ከመናገራችሁ በፊት ስሜታችሁን በስም ጥሩት። ለምሳሌ፦ "አሁን ተናድጃለሁ።" "አሁን ተጨንቄያለሁ።" "አሁን ደክሞኛል።" ከዚያ ለራሳችሁ እንዲህ በሉ፦ "ስሜቴን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ምላሼን እኔ እመርጣለሁ።" የዛሬ ማሰላሰል ✔ ዛሬ ምን ስሜት በጣም ተሰማኝ? ✔ ስሜቴን በስም ስጠራው ምን ተለወጠ? ✔ ዛሬ ቢያንስ አንድ ጊዜ ስሜቴ እንዳይመራኝ መምረጥ ቻልኩ? **ኮሜንት ላይ ይፃፉ፦ "ቀን 6 ጨርሻለሁ!"

ዛሬ በሰፈሬ walk እያደረኩ አንድ ነገር አየሁ... 14 ዓመት የምትመስል አንዲት ልጅ ከእድሜዋ እኩያ ወይም ትንሽ ከሚበልጣት ወንድ ጋር በተደበቀ ቦታ ቆመው ሲሳሳሙ አየሁ። ሳላውቃት ብዙ ጥያቄዎች
ዛሬ በሰፈሬ walk እያደረኩ አንድ ነገር አየሁ... 14 ዓመት የምትመስል አንዲት ልጅ ከእድሜዋ እኩያ ወይም ትንሽ ከሚበልጣት ወንድ ጋር በተደበቀ ቦታ ቆመው ሲሳሳሙ አየሁ። ሳላውቃት ብዙ ጥያቄዎች በአእምሮዬ መጡ። እናቷ "የት ነሽ?" የት ነገርሽ ብላ ብትጠይቃት ምን ትላለች? አልፈልግም ማለት እንደምትችል ተምራ ይሆን? ከወላጆቿ ጋር ስለ ፍቅር፣ ግንኙነት እና ወሲብ በግልፅ አዉርታ ይሆን? ከዚያም ራሴን ጠየቅኩ፦ "እኔ እናቷ ብሆን ዛሬ ብቻ ምን አደርግ ነበር?" ከ15 ዓመት በፊት ምን አስተምሬያታለሁ? ስለ ሰውነቷ? ራስዋን ማክበር? ስለ ድንበር (Boundaries)? ስለ ፍቃድ (Consent)? ስለ "አይ" ማለት? ስለ ግፊትን መቋቋም? የወሲብ ትምህርት?? ራሳቸውን እንዲያከብሩ፣ ጤናማ ውሳኔ እንዲወስኑ እና አደጋን እንዲያውቁ ማስተማር ነው። አንዳንድ ውይይቶች ዛሬ ቢያስቸግሩንም፣ ነገ ልጆቻችንን ሊጠብቁ ይችላሉ። https://t.me/anuparentingsolutions

ሰላም ወላጆች ይህ challenge መጀመርያ የነበራችሁ ተነሳሳሽነት የት ጠፋ? እኔም እንድቀጥል እኮ እናንተ እየተከታተላችሁ መሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ። ምን ተቸገራችሁ? ፃፉልኝ

ቀን 5፡ ሀሳባችንን እንቀይር (Change Your Thoughts, Change Your Response) ስለ ሁኔታው የምናስበው ሀሳብ ነው ምላሻችንን የሚወስነው። ለምሳሌ... ልጃችሁ ሳይሰማችሁ ሲቀር፣
ቀን 5፡ ሀሳባችንን እንቀይር (Change Your Thoughts, Change Your Response) ስለ ሁኔታው የምናስበው ሀሳብ ነው ምላሻችንን የሚወስነው። ለምሳሌ... ልጃችሁ ሳይሰማችሁ ሲቀር፣ "ሆን ብሎ እያናደደኝ ነው።" "አያከብረኝም።" "ልጆቼ ከቁጥጥሬ ዉጪ ሆኑ።" እነዚህ ሀሳቦች ቁጣችንን እንዲጨምር ያደርጋል። ነገር ግን እንዲህ ብናስብ... "ልጆቼ ገና ልጆች ናቸዉ እየተማሩ ነው።" "እኔ አሁን ማስተማር አለብኝ፣ ማስፈራራት አይደለም።" "ልጄ አስቸጋሪ አይደለም፤ አስቸጋሪ ጊዜ እያለፈ ሊሆን ይችላል።" የምንሰጠው ምላሽ ይቀየራል። ሀሳባችንን ስንቀይር፣ ባህሪያችንም ይቀየራል። የዛሬ Challenge ዛሬ መቆጣት መጮህ ስሜት ሲሰማችሁ... 👉 በራሳችሁ የሚመጣውን የመጀመሪያ ሀሳብ አስተውሉ። ከዚያ በኋላ በዚህ ሀሳብ ይቀይሩት፦ "ልጄ ገና እየተማረ ነው። የእኔ ሥራ ማስተማር ነው፣ መጮህ አይደለም።" Reflection ✔ ዛሬ ምን አይነት አሉታዊ ሀሳብ ወደ አእምሮዬ መጣ? ✔ በምን አዎንታዊ ሀሳብ ቀየርኩት? ✔ ይህ ምላሼን እንዴት ቀየረው? ኮሜንት ላይ ይፃፉ፦ "ቀን 5 ጨርሻለሁ!"

Challenge እንዴት ነበር ዛሬ??

ስልጠና እየጠያቃችሁኝ ያላችሁ ወላጆች Private coaching/1 to 1 እንጂ የግሩፕ ስልጠና ለአሁን የለም። private ከፈለጋችሁ በዉስጥ አዉሩኝ @anuparenting

እንዴት በ30 ቀን ፈተናው ላይ መቀጠል ይችላሉ? 1. ከተሳሳታችሁ ተስፋ አትቁረጡ። ይህ ፈተና ፍጹም ወላጅ ለመሆን አይደለም፤ እየተማሩ ለመሻሻል ነው። ጠዋት ብትጮሁ እንኳን፣ ከሰዓት ወይም ማታ እን
እንዴት በ30 ቀን ፈተናው ላይ መቀጠል ይችላሉ? 1. ከተሳሳታችሁ ተስፋ አትቁረጡ። ይህ ፈተና ፍጹም ወላጅ ለመሆን አይደለም፤ እየተማሩ ለመሻሻል ነው። ጠዋት ብትጮሁ እንኳን፣ ከሰዓት ወይም ማታ እንደገና ይሞክሩ። አለመሳካት የፈተናው አካል ነው፤ መተው ግን አይደለም። 2. በየቀኑ የተማራችሁትን ሁሉ ተግብሩ። አዲሱን challenge ብቻ ሳይሆን የቀደሙትንም ይቀጥሉ። ለምሳሌ፦ 5 ሰከንድ ቆም ማለት፤ 3 ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ፤ Trigger ን ማስተዋል አስፈላጊ ከሆነ ለጥቂት ጊዜ ከቦታው ራቅ ማለት (walk away) ለራሳችሁ የሚረጋጋ ንግግር (self-talk) ማድረግ እነዚህ ሁሉ አንድ ላይ ሲሠሩ ነው ለውጥ የሚመጣው። 3. እዚህ ግሩፕ ላይ ተሳታፊ ይሁኑ። በትክክል ብታደርጉትም ወይም ብትሞክሩም ብትጮሁም comment ላይ ፃፉ። No one is perfect we just try 4. በየቀኑ 5 ደቂቃ ለራሳችሁ ይስጡ። የዛሬውን ትምህርት ያንብቡ፣ የዛሬውን Challenge ያድርጉ፣ ከዚያም ራሳችሁን ይጠይቁ፦ "ዛሬ ምን ተማርኩ?" "ምን በደንብ አደረግሁ?" "ነገ ምንን ማሻሻል እችላለሁ?" ትንሽ እርምጃ በየቀኑ ሲደጋገም ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

ቀን 4፡ ሰውነታችንን ማረጋጋት ትላንት በቀስቃሽ እና ምላሽ መካከል ያለውን Space እንዳለ ተማርን። ዛሬ ደግሞ በዚያ Space ውስጥ ሰውነታችንን እንዴት ማረጋጋት እንዳለብን እንማራለን ከዛ cha
ቀን 4፡ ሰውነታችንን ማረጋጋት ትላንት በቀስቃሽ እና ምላሽ መካከል ያለውን Space እንዳለ ተማርን። ዛሬ ደግሞ በዚያ Space ውስጥ ሰውነታችንን እንዴት ማረጋጋት እንዳለብን እንማራለን ከዛ challenge እናደርጋለን። ከመጮሃችን በፊት ሰውነታችን ሁልጊዜ ምልክት ይሰጠናል። ለምሳሌ፦ 🔸 ልባችን በፍጥነት ይመታል። 🔸 ትንፋሳችን ይፈጥናል ወይም ይቆራረጣል። 🔸 ሰውነታችን ይወጠራል። እነዚህ ምልክቶች "ቆም!" የሚሉ የሰውነታችን መልዕክቶች ናቸው። እነሱን በጊዜ ካስተዋልን፣ ጩኸትን ከመጀመሩ በፊት ማቆም እንችላለን። ✅ Today's Challenge ዛሬ የሚያስጮህ ነገር ሲመጣ... 1️⃣ በመጀመሪያ የሰውነታችሁን ምልክቶች አስተውሉ። 2️⃣ 3 ጥልቅ ትንፋሽ ውሰዱ። በእያንዳንዱ ትንፋሽ ውስጥ በልባችሁ እንዲህ በሉ፦ "ሀሳቤን እቆጣጠራለሁ..." "ሰውነቴን አረጋጋለሁ..." "በእርጋታ እመልሳለሁ..." ከዚያ በኋላ ብቻ ለልጃችሁ ምላሽ ይስጡ። ማታ ይህን ፃፉልኝ። ✔ ጩኸት ከመጀመሩ በፊት በሰውነቴ ምን ምልክቶች ተሰሙኝ? ✔ 3 deep ጥልቅ ትንፋሽ ከወሰድኩ በኋላ ሰውነቴ እንዴት ተለወጠ? ✔ ዛሬ ቢያንስ አንድ ጊዜ ከመጮሄ በፊት ራሴን ማረጋጋት ቻልኩ? "ቀን 4 ጨርሻለሁ!"

3ኛ ቀን Challenge እንዴት ነዉ??

Youtube ላይ ብቅ ብለሽ ከዛ ጠፋሽ ያላችሁኝ ዘመዶቼ ይሀዉ እንደገና ብቅ ብያለሁ። 👆👆👆👆 Subscribe share Comment....ወዘተ አድርጋችሁ ካበረታታችሁኝ በሌላ video እመለሳለሁ። ''የልጆች እርስበርስ መጣላት ለምን እና መፍትሔ'' በሚል። https://t.me/anuparentingsolutions

ሰላም ወላጆች የለመድነዉ ነገር ለመስበር ከባድ ነዉ ነገር ግን ምንም ቢሆን መቀጠል አለብን። እየሞከራችሁ ስለሆነ ነዉ የምትሳሳቱት። ስለዚ እንሞክር አሁንም።

ቀን 3፡ በ በቀስቃሽ እና በምላሻችን መካከል ያለውን ክፍተት (The Space) ማወቅ ትላንት የ ABC Model ተማርን። A (Antecedent) – Trigger ወይም ሁኔታ B (Behavior) –
ቀን 3፡ በ በቀስቃሽ እና በምላሻችን መካከል ያለውን ክፍተት (The Space) ማወቅ ትላንት የ ABC Model ተማርን። A (Antecedent) – Trigger ወይም ሁኔታ B (Behavior) – የእኛ ምላሽ ብዙ ጊዜ እኛ እንዲህ ይመስለን ይሆን ቀስቃሽ➜ ጩኸት ግን እንዲህ ነዉ Trigger ➜  Space ➜ Behavior ይህ ትንሽ Space በጣም ኃይለኛ ነው። በዚያ ቅጽበት ምርጫ አለን። ጩኸትን መምረጥ እንችላለን... ወይም በተረጋጋ መንገድ ምላሽ መስጠት እንችላለን። በዚያ ጊዜ ለራሳችሁ እንዲህ በሉ፦ "ቆይ... እየተቆጣሁ ነው። ይህ ስሜት ያልፋል። አሁን ምን ዓይነት ወላጅ መሆን እፈልጋለሁ? ይህንን የራስ ዉይይት ማድረግ አእምሯችንን ከራስ-ሰር ምላሽ (automatic reaction) ወደ ተመረጠ ምላሽ (intentional response) ይወስደናል። ✅ የዛሬ ተግባር (Today's Challenge) ዛሬ ጩኸት የሚመጣበትን ጊዜ ሲያስተውሉ... Trigger/ ቀስቃሽ አስተውሉ። Space መኖሩን አስተውሉ። ለራሳችሁ እንዲህ በሉ፦ "ቆይ... ምርጫ አለኝ።" ከዚያ በኋላ ብቻ ምላሽ ይስጡ። ማታ ላይ እነዚህን ጥያቄዎች መልሱ፦ ዛሬ ይህንን Space ስንት ጊዜ አስተዋልኩ? በዚያ ጊዜ በሰውነቴ ምን ተሰማኝ? (ልቤ ፈጠነ? ሰውነቴ ተወጠረ? ድምፄ ከፍ ሊል ጀመረ?) ምላሽ ከመስጠቴ በፊት ቆም ማለቴ እንዴት ተሰማኝ? ኮሜንት ላይ ይፃፉ፦ "ቀን 3 ጨርሻለሁ!"

Youtube ላይ ብቅ ብለሽ ከዛ ጠፋሽ ያላችሁኝ ዘመዶቼ ይሀዉ እንደገና ብቅ ብያለሁ። 👆👆👆👆 Subscribe share Comment....ወዘተ አድርጋችሁ ካበረታታችሁኝ በሌላ video እመለሳለሁ። ''የልጆች እርስበርስ መጣላት ለምን እና መፍትሔ'' በሚል።