fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

𝐀𝐛𝐝𝐢𝐬𝐚 𝐃𝐞𝐟𝐚𝐫

𝐀𝐛𝐝𝐢𝐬𝐚 𝐃𝐞𝐟𝐚𝐫

رفتن به کانال در Telegram

የውይይት ግሩፓችንን ይቀላቀሉ @AAbbddiissaa በግል ልትጽፉልኝ ለምትፈልጉ @AbdisaDefar የኃይለኞች ፈጣሪ ; በአብዲሳ ደፋር, ሙሉ ትረካ https://youtu.be/BkocwxjXMs4

نمایش بیشتر
7 186
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-237 روز
-2330 روز
آرشیو پست ها
ጁማአ ሙባረክ ያ ጀማአ👐

+2
የሚበር መኪና ተፈጠረ! 👏😳🔥 አረ ለElon እናጨብጭብ👏ወገን

ፍልስፍናን ሀ ብሎ የጀመራት ቀደምት ፈላስፋ ነዉ ሲሉ የተለያዩ ምንጮች ያወድሱታል፤በጊዜ ሂደት ወደ ሳይንስ ለተቀየረዉ የተፈጥሮ ፍልስፍናም ትልቅ መሰረት እንደጣለም ይታመንለታል ግለሰቡ ከኢዮኒያ 12 ዋና ዋና ከተሞች የአሳቢያን መፍለቂያ ከሆነቹ ባንዷ ሚሌጦስ የኖረዉ ታሌስ ነዉ። ታሌስ በ 585 ዓ.ዓ የተከሰተዉን የፀሀይ ግርዶሽ ተንብዮ ነበር ይባልለታል፤ የተለያዩ ንግርቶችም ታሌስ ከግብፅ በስነ ምድር ጥናት እራሱን አዳብሮ ወደ ሚሌጦስ እንደመጣ ይናገራሉ ይህን ከሚሉት ዉስጥም አኢትዮስ እና ኢዉዴሞስ ይገኙበታል።ሄሮዶተስም በበኩሉ ጂኦሜትሪን የፈለሰፈዉ የአባይ ወንዝ ጋር ሲደርስ መሬትን እንደገና ለመለካት በመሞከሩ መሆኑን ይናገራል። ፕሌቶ በቴዎቴቶስ ዉስጥ እንደሚተርከዉ ታሌስ ክዋክብትን እየተመለከተ ወደ ላይ እያየ ሲሄድ ወደ ጉድጓድ ወደቀ ይህን ያየች አንዲት ብልህና ቆንጆ የትራሺያ አገልጋይ ልጅም "ሰማይ ላይ ያለዉን ለማወቅ ትጓጓለህ፣ ከኋላህ እና ከእግርህ ስር ያለዉን ግን አታይም" ስትል እንደተሳለቀችበት አስፍሯል። ብዙ ፀሀፍት ታሌስ በጥላቸዉ ብቻ የፒራሚዶችን ቁመት እንደለካ ይናገሩለታል ይህ ትርክት ግን እዉነት ይሁን ወይ ደሞ ወደ ግብፅ መፍለሱን ለማስረገጥ የተነገረ ትረካ የሚለዉ አሁንም አወዛጋቢ ነዉ። ኢውዴሞስ በ "ጂኦሜትሪ ታሪክ" ውስጥ እንደሚለው አንድ ጎንና ከጎኑ ያሉት ማዕዘኖች እኩል የሆኑ ሦስት ማዕዘኖች እርስ በርሳቸው እኩል ናቸው የሚለውን ቲዎዮሪም ለታሌስ ይሰጣል፤ ምክንያቱም በባሕር ላይ ያሉ መርከቦችን ርቀት ለማሳየት ይህንን መጠቀም አስፈላጊ ነበር ይባላል። ይህ ስሌት ተመልካቹ ከባሕር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ ከታወቀ፣ በጥንታዊ ቴዎዶላይት (በችንካር ላይ የሚዞሩ ሁለት ዱላዎች፤ አንዱ የማየት መስመር፣ሌላው የደረጃ መስመር) ሊደረግ ይችላል። ኢውዴሞስ ለታሌስ የተመሳሳይ ሦስት ማዕዘኖች እውቀት የሰጠው ሌላ መንገድ ሊኖር አይችልም በሚል አስቀድሞ በተደረገ መላ ምት ነው። የታሌስ ቀጥተኛ ፅሁፎች እንዳለመትረፋቸዉ መጠን አብዛኛዎቹ ነገሮች ከሁለተኛ ወገን የመጡ ናቸዉ። ከታሌስ ዋና የፍልስፍና ሀሳቦች አንዱም የአፅናፈ አለም ከምን ተሰራ የሚለዉን ጥያቄ የሚመልስ ነዉ። አርስጣጢለስ በ "On the heavens" በተሰኘ ክታቡ እንዳሰፈረዉ ታሌስ ምድር እንደ እንጨት በዉሃ ላይ ትንሳፈፋለች የሚል ምልከታ ነበረዉ። ከዛም ባሻገር የሁሉ ነገር አርኬ(ይሄን ቃል አርስጣጢለስ የመጀመሪያ ዋና ቁስ፣እንደ መሰረት ሁኖ የሚያገለግል እና ነገሮች የሚጠፉበት ሲል ይተረጉመዋል) ዉሃ ነዉ የሚል ነበር። አርስጣጢለስ በ ሜታፊዚክሱ ውስጥ ደግሞ በጣም አጠቃላይ የሆነ ትንታኔ ሲሰጥ እንዲህ ይላል የመጀመሪያዎቹ ፈላስፎች አብዛኞቹ የቁስ ዓይነት መርሆች(አርኬዎች) ብቻ የነገሮች ሁሉ መርሆች እንደሆኑ ያስቡ ነበር፤ ማለትም ሁሉም ነገር የሚገኝበት፣መጀመሪያ የሚወለድበትና በመጨረሻ የሚጠፋበት፣ ቁስ እየቆየ ባሕርያቱ ብቻ የሚለዋወጡበት። በዚህ ምክንያት ፍጹም መወለድም ሆነ መጥፋት የለም ብለው ያምናሉ። የመርሁ ብዛትና ዓይነት ላይ ግን አይስማሙም፤ የዚህ ዓይነቱ ፍልስፍና መስራችም ታሌስ ውሃ ነው ይላል (ስለዚህም ምድር በውሃ ላይ እንደምትገኝ አሳወቀ)። ይህንን ግምት ያገኘው ምናልባት የነገሮች ሁሉ ምግብ እርጥብ መሆኑን፣ ሙቀት ራሱ ከእሱ እንደሚወለድና በእሱ እንደሚኖር በማየት፣ እንዲሁም የሁሉ ነገር ዘር እርጥብ ተፈጥሮ ስላለው ሊሆን እንደሚችል ያስቀምጣል፤ ውሃ ደግሞ ለእርጥብ ነገሮች የተፈጥሮ መርህ ነው። አርስጣጢለስ ታሌስ ለምን ዉሃን እንደመረጠ ምክንያት የሚሰጠዉ በመላምት ላይ ተመስርቶ መሆኑን ከዛዉ ላይ መረዳት ይቻላል፤ለምሳሌ የታሌስ መርህ (በአሪስጣጢለስ ትርጉም) "ዉሃ" ነዉ ሲል  የሄራክሊጦስ መርህ ደሞ "እሳት" ነው ይላል። ለታሌስና ለሄራክሊጦስ ግን እነዛ ነገሮች በግልጽ በጣም የተለያዩ ዓይነት ነገሮች ነበሩ። ስለ የታሌስ አፅናፈ አለም ከዉሃ መገኘት አስተሳሰብ (ምድር በላዩ ላይ ትንሳፈፋለች ከሚለው በስተቀር) የምናውቀው ሁሉ በወሬ መልክ፣ ምናልባትም በጣም አጭርና በመጠኑ የተዛባ፣ በአሪስጣጢለስ (ብዙም ጠንቃቃ ያልሆነ) አስተሳሰቡን ከራሱ የ "ቁሳዊ አርኬ" ሃሳብ ጋር የሚስማማ አርጎ ገልፆት ነዉ የምናገኘዉ። ሴኔካ (ምናልባት ከቴዎፍራስጦስ፣በፖሲዶኒዮስ ምንጭ በኩል) እንደሚለው ታሌስ ምድር በውሃ እንደተደገፈች፣ እንደ መርከብ እንደምትሄድና በውሃው እንቅስቃሴ እንደምትወዛወዝ ተናገረ፤ ምድር "ስትንቀጠቀጥ" የሚባለዉም ያኔ ነው። በሚል ይህ ታሌስ የምድር መንሳፈፍ ሃሳቡን የመሬት መንቀጥቀጥን ለማስረዳት እንደተጠቀመ ያሳያል። ከዚህ በተጨማሪ ታሌስ መግነጢሳዊ ድንጋይ ብረትን ማንቀሳቀስ ስለሚችል ነብስ አለዉ የሚል እሳቤ ነበረዉ።በሱ እይታም የነብስ እሳቤ አንቀሳቃሽ መሆኑን ልብ ይሏል።ስለዚህም በዛን ሰዓት መንቀሳቀስ እና ማንቀሳቀስ የሚችሉ ነገሮች ነብስ እንዳላቸዉ ይቆጠር ነበር በዚህም የተነሳ ወንዞች እና ዛፎች እንቅስቃሴን ስለሚያረጉ ነብሶች አሏቸዉ(ህያዉ ናቸዉ) የሚል እሳቤ ነበረዉ።ይህም ምልከታ ባንድም ሆነ በሌላ መንገድ ወደ ሃይሎዞይዝም ያመራል። ሃይሎዞይዝም ማለት ሁሉም ነገር፣ህይወት የሌላቸዉ ግዑዝ ነገሮች ሁላ ሳይቀሩ በሆነ መልኩ ህይወት አላቸዉ የሚል እሳቤ ነዉ። ምንጭ፤ ከላይ ከተያያዘዉ መፅሀፍ ገፅ 74 እስከ 99።

የዉይይት ጥሪ ለኦቦሌሳ ኪሪስቶስ ኬሳቲ ማነዉ በታሪክ ዉስጥ አለሌ ተሳዳቢ? ማነዉ የሰዎችን እምነት የማያከብረዉ? የክርስትና ሊቃዉንቶች ወይስ ኤቲስቶች። እዚህ ጋር ተራ ሰዎችን አዋቂ ናቸዉ ከሚባሉት
የዉይይት ጥሪ ለኦቦሌሳ ኪሪስቶስ ኬሳቲ ማነዉ በታሪክ ዉስጥ አለሌ ተሳዳቢ? ማነዉ የሰዎችን እምነት የማያከብረዉ? የክርስትና ሊቃዉንቶች ወይስ ኤቲስቶች። እዚህ ጋር ተራ ሰዎችን አዋቂ ናቸዉ ከሚባሉት በንፅፅር እያስተካከልኩ ነዉ። ወንድማችን በቀደመዉ ፅሁፉ ኤቲስቶች ተሳዳቢ ናቸዉ ሲል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል ስለዚህ እኛ ደሞ አይደለም ተራዉ ምዕመን የሱ ሊቃዉንቶች የስድብ ባለሞያ እንደሆኑ ልናሳየዉ እንወዳለን እና በክብር ለዉይይቱ ተጠርሃል።

W ኤቲስቶች! ነፃነታችሁን በሸነና በሉበት! ከሰሞኑ ኤቲስቶች እንደ አሸን እየበዙ መምጣታቸው እማይካድ ነው... ታዲያ የቀሩት አማኞች ኤቲስት እንዳይሆኑ ለማረግ ሲባል... ኤቲስቶችን ማጥላላት እና
W ኤቲስቶች! ነፃነታችሁን በሸነና በሉበት! ከሰሞኑ ኤቲስቶች እንደ አሸን እየበዙ መምጣታቸው እማይካድ ነው... ታዲያ የቀሩት አማኞች ኤቲስት እንዳይሆኑ ለማረግ ሲባል... ኤቲስቶችን ማጥላላት እና አቋማቸውንም ለማዋደቅ ሲሞከር እያየው ነው... ሃይማኖታቹ ይሄን ሁላ ገንዘብ እያፈሰሰ .. የአምልኮ ቤት እንደ አሸን እየገነባ.. በሺዎች እሚቆጠሩ ሰባኪዎች ኖረውትም... ኤቲስቶች ግን ባንክም ታንክም ሳይኖረን.. ፕሮፖጋንዳችሁን ከትውልዱ አእምሮ ውስጥ በቀላሉ መናድ መቻላችን... እምነታቹ የፀናው አሸዋ ላይ እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ሊሆናቹ ይገባ ነበር.. ግና አምናቹ እንጂ አይታቹ መች ታውቁና? ኢአማኝነት እንደእናንተ የሰውን ልጅ ሂወት ለመቆጣጠር የሚሰራ... መርዛማ ዶግማ እና ቀኖና ያለው አላዋቂነት ሳይሆን.. አለማወቃችሁን ተረድቶ መርዛችሁን ከመጋት መቆጠብ ነው... ነገር ግን እድሜልክህን እንደባሪያ እያስጎነበስክ.. ስታሰግደው እና እድሜውን ስታስማግደው የነበረ ባሪያህ... ካንተ ቁጥጥር ውጪ ሆኖ በራሱ እግር ቆሞ ስታየው.. ምን ያክል እንደሚያም ይገባኛል... የሰሞኑ ጩኸቶችም ከዚ.. ናርስሲስቲክ ማንነታቹ የወጣ ሲሆን... እንደ እግር እሳት እያንገበገባቹ ያለው ቁጭት ነው... አንተ ላይ ጥገኛ ሆኖ ሲያወድስህ የኖረው ምእመን... ከዚ በሁዋላ እንደ ድሮው.. 'መምህሬ ሆይ አስተምረኝ' (ሂወቴን በሪሞትህ ተቆጣጠርልኝ) እያለ ወዳንተ እንደማይመጣ ስታውቅ ... ብትችል እንደ ፈጣሪህ ሁሉ አንተም እሳት ካለኮስክበት ውስጥህ ያለው ንዳድ እንደማይበርድ ልቦናችን ያውቀዋል... ሰድበህ እና እውቀቱን አንቋሸህ ብቻ መተውክም ተመስገን ነው... ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል:: ኤቲስቶችዬ ማንንም እንዳትሰሙ! የነፃነት ዘመናችሁን በሸነና በሉበት.. ቁጭት ነው ያሳበዳቸው... ሂወታቹ ከነዚ ሳቃቸው እንደበረዶ ከሚቀዘቅዝ .. ለስላሳ ተኩላዎች ድናለች ደስ ይበላቹ! W ኤቲስቶች!

ከቅድመ ሶቅራጠስ የግሪክ ቱንቡ ፈላስፋዎች መካከል በዋነኝነት ሄራክሊተስ ይገኝበታል። ሄራክሊተስ ከዛሬ ወደ 2500 ዓመት በፊት (500 ዓ.ዓ. አካባቢ) በትንሿ እስያ በኤፌሶን ከተማ የኖረ ግሪካዊ ፈላስፋ ነው። አነጋገሩ አጭርና እንቆቅልሽ መሰል በመሆኑ <<ጨለማው>> የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶት ነበር። የጻፈው መጽሐፍም ዘመናትን ተሻግሮ ሙሉ በሙሉ ሊተርፍ አልቻለም፤ በመሆኑም ከተረፉ ቁርጥራጭ ክታቦቹ ላይ በመነሳት የፍልስፍና ምልከታዎቹን ለመዳሰስ እንሞክራለን። ሎጎስ : ሌላ በቅድመ ሶቅራጠስ ጊዜ የነበሩ ፈላስፋዎች አለም ከየትኛዉ ቁስ እንደተገኘች ሲያመሰጥሩ ሄራክሊተስ ግን <<ሎጎስ>> ወይንም ቃል የተሰኘዉን ምክንያትና የነገሮች መጠን ወይም የዓለም ሥርዓት ብሎ የወከለዉን ነገር አስተዋወቀ። ሄራክሊተስ እውነት ሁልጊዜ በፊታችን እንዳለ ይናገራል፤ ችግሩ እውነቱ መደበቁ ሳይሆን ሰዎች እንደ እንቅልፋም ሳያስተውሉ ማለፋቸው ነዉ። ስለዚህ ሲናገር እንዲህ ይላል
The Word proves those first hearing it as numb to understanding as the ones who have not heard. Yet all things follow from the Word.Some, blundering with what I set before you, try in vain with empty talk to separate the essences of things and say how each thing truly is. And all the rest make no attempt.  They no more see how they behave broad waking than remember clearly what they did asleep.
ይህ ሎጎስም(እዉነት) ለሁሉ የሚገኝ የጋራ ነገር እንደሆነ እና ሰዎች ግን በግል አስተሳሰባቸው ውስጥ ተዘግተው እንደሚኖሩ ይገልፃል። ሄራክሊተስ ማስተዋልን ከግል አመለካከት የሚለየውም በዚህ ነዉ። ፍሰት እና ለዉጥ : ሄራክሊተስ ሁሉም ነገር ተለዋዋጭ ነዉ የሚል እሳቤም ነበረዉ። ከሁሉ እሳቤዉም ታዋቂ የሆነዉ ይሄ ሲሆን የሌሎች ነገሮችን ሁሉ ተለዋዋጪነት እና የለዉጥን ቋሚነት አበክሮ ያሳያል። ስለዚህ ሲያወራም እንዲህ ይላል
The river where you set your foot just now  is gone those waters giving way to this, now this.
ከዚህ በተጨማሪ በየቀኑ የምትወጣዉ ፀሃይ ሳትቀር የትላንቷ እንዳልሆነች ያትታል ይህም እንደማይቀየር እርግጠኛ የሆንንባቸዉ ነገሮች እራሱ እየተቀየሩ እንደሆነ እና ልማድ ግን ይህንን ለዉጥ እንዳናይ እንደሚያዉረን ያሳዉቃል።በተጨማሪም በዚህ ለዉጥ ዉስጥ በነዉጥ ፋንታ ዕረፍት እንደሚገኝ ይናገራል። ሄራክሊተስ እሳትን እንደ የአለም መሠረታዊ ምልክት አርጎ ይወስደዋል፤ ምክንያቱም እሳት ተንቀሳቃሽ፣ተቅበዝባዥ እና ተለዋዋጭ በመሆኑ የነገሮችን መቆሚያ አልባ ፍሰት እና ለዉጥ ስለሚወክል ነዉ። ስለዚህም ሲናገር እንዲህ ይላል
That which always was, and is,and will be everliving fire,the same for all, the cosmos,made neither by god nor man
የተቃራኒዎች አንድነት : ልላ አእምሮን ከሚፈትኑ ምልከታዎቹ አንዱ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች በጥልቅ ስንመለከታቸዉ አንድ ናቸዉ የሚል ነዉ። ተራራን የሚያወጣዉም የሚያወርደዉም(ወደ ላይም ወደ ታችም) መንገድ አንድ ነዉ፤በክብ ዉስጥ መጀመሪያም መጨረሻም አንድ ነዉ፤ ስምምነትም የሚመጣዉ ከሰላማዊ ዕረፍት ሳይሆን ከተመጣጠነ ዉጥረት መሆኑን ሲያወሳ እንዲህ ይላል
The mind, to think of the accord that strains against itself,  needs strength, as does the arm to string the bow or lyre. From the strain of binding opposites comes harmony.
አንድ ነገር በአንድ ጊዜ አሉታዊም አዉንታዊም ሊሆን ይችላል፤ የባህር ዉሃ በጣም ንፁህ እና በጣም መጥፎም ነዉ፣ ለአሳዎች ይጠጣል ህይወትንም ይሰጣል ለሰዎች ግን አይጠጣም ይገድላልምን። ተቃራኒ ጥንዶች አንድ ላይ ተያይዘው ይታያሉ፤ ከእነሱም ዓለም አንድ ሆኖ ይወጣል። ብዙነትና አንድነት አይለያዩም ጥበብ ብዙ እዉነታዎችን መሰብሰብ ሳይሆን ሁሉንም የሚመራዉን አንድ ሥርዓት ማየት ነዉ ። ራስን ማወቅ : ለሄራክሊተስ ራስን ማወቅ ጥልቁን የነብስን ሎጎስ መረዳት ነዉ። ነብስ ካላስተዋልክ በቀር የማይደረስባት ጥልቅ ሎጎስ አላት የሚለዉን ሲገልጥ እንዲህ ይላል
The soul is undiscovered, though explored forever  to a depth beyond report.
ይህን የነብስ ሎጎስም ለመመርመር ዉስጣዊ ማስተዋልን ማካበት እንደሚገባ አብክሮ ይናገራል ከዛም ባሻገር ሟቾች የማይሞቱ ናቸው፣ የማይሞቱትም ሟቾች ናቸው፤ የእነዚህን ሞት ይኖራሉ፣ የእነዚህንም ሕይወት ይሞታሉ። ጥበብን መሻት : ለሄራክሊተስ ጥበብ መረጃን በማግበስበስ የምትገኝ የጅምላ ሸቀጥ አይደለችም፤ ይልቁንም ማስተዋል የሚገዛት ጥልቁን ሎጎስ በጥልቀት መረዳት ብቻ ወደ ጥበብ የሚያሻግር ድልድይም እንደሆነ ያሳዉቃል። በጊዜዉ የነበሩ ብዙ እናዉቃለን የሚሉ ግን አስተዉሎቱ የላቸዉም ብሎ ያሰባቸዉን ፈላስፋዎች ሲተች እንዲህ ይላል
Many who have learned from Hesiod the countless names of gods and monsters never understand that night and day are one.
ለእኔ አንድ ሰዉ ምርጥ ከሆነ አስር ሺህ ሰዎች ነዉ በማለትም የብዙ ሰዎች ድምፅ ከአንድ ጠቢብ አስተዉሎት እንደማይልቅ ያሳስባል። በመጨረሻም ሄራክሊተስ በዴልፊ ያለዉ ጌታ(በዛን ጊዜ በዚያ የታወቀ የአፖሎ ቤተመቅደስ ነበር ሰዎችም ወደዚያ በመሄድ ጥያቄን ለአማልክቱ ያቀርባሉ) አይደብቅምም አይናገርምም ይልቁንም ምልክት ይሰጣል ሲል ጥበብ ግልፅም ድብቅም እንዳልሆነች ግን ለሚፈልጋት እንደምትገኝ የሱ ፅሁፎችም እንዲያ እንደሆኑ ያወሳናል።

+2
ፈልስፍናን ከዜሮ ልንጀምራት ነዉ ተዘጋጁ ምዕመናት።

ይህ ቻናል ከተቋቋመ ጀምሮ ብዙ አይነት ፍልስፍናዊ ሀሳቦችን ሲዳስስ ቆይቷል። ሆኖም ግን አሁን ላይ እየቀረቡ ባሉ የታዳሚያን ጥያቄ መሰረት ፍልስፍና ሀ ተብሎ ከተጀመረበት የቅድመ ሶቅራጠስ ዘመን አሁን እስካለዉ የጊዜዉ contemporary ፍልስፍና ድረስ ለአንባቢዉ በሚሆን መልኩ የተደራጀ ዳሰሳ ለማቅረብ ወስነናል። በዚህም የተነሳ እዚህ ላይ በተያያዘዉ ፍኖተ ካርታ መሰረት ፍልስፍናን ከ ሀ እስከ ፖ ልናስዳስሳቹ ዝግጅታችንን መጨረሳችንን ስናበስራቹ በታላቅ የፍልስፍናዊ መነሳሳት ስሜት ነዉⓂ️

ህይወትን እንደ ሙከራ ስርጭት የማየት ጠንቆች በማህበረሰባችን እና በዙሪያችን ያሉ አካላት "ለዚች አጭር እና ጊዜያዊ ህይወት..." እያሉ ሲያወሩ ሁሌም እንሰማለን፤ በእዉነቱ አንድን ነገር ጊዜያዊ ለማለት ሌላ ቋሚ የሆነ ነገር በተነፃፃሪነት ሊኖር ይገባል እና በዚህም የተነሳ የዚችን ምድር ኑሮ ጊዜያዊ ስንል ሁሌም በምናባችን ከሱ ቡሃላ አለ ብለን እያሰብን ያለዉን ዘላለማዊ ህይወት በማማተር ነዉ። እንግዲህ የዚህን አስተሳሰብ መሰረት ለማወቅ ወደኋላ ሰርስረን ስንጓዝ ከሃይማኖቶች የአለም እይታ የመነጨ መሆኑ ወገግ ብሎ ይገለጣል። ሃይማኖቶች የእነሱን The so called "መንፈሳዊ እዉነት" ለማግዘፍ ምድራዊ እዉነትን እና ጊዜን ማሳነስ ግድ ይላቸዋል፤ ለዛም ነዉ ሁለቱን ነገሮች ሁሌም ቢሆን በተፃራሪ ሁኔታዎች የሚያስቀምጧቸዉ። መንፈስህን ለማጎልበት ስጋህን አድክም፤ ለስጋህ ቅድሚያ ስትሰጥ ደሞ መንፈሳዊ ህይወትህ ይበሰብሳል የሚሉ አስተምህሮቶችን ከሃይማኖታዊ ትርክቶች ዉስጥ ማግኘት ያን ያህል ከባድ አይደለም። ስለዚህ ሰዎች ስለዚኛዉ አለም ጊዜያዊነት ከተረዱ ይህኛዉን አለም የተሻለ ለማረግ ፍላጎት እና ተነሳሺነት ይኖራቸዋል ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል። አንድ መርከበኛ እየሰመጠ ያለ መርከብ ላይ ካለ እና ሌላ አዲስ ያማረ እና መቼም የማይሰምጥ መርከብ መጦ ወደዛ እንደሚሻገር ከተነገረዉ እየሰመጠች ያለችዋን መርከብ ለማትረፍ ሳይሆን የሚታገለዉ ያ ያማረዉ መርከብ እስኪመጣ የእራሱን ህይወት ለማቆየት ነዉ።በዚህም የተነሳ ሰዎች አሁን ያሉበት አለም ጊዜያዊ መሆኑ ተደጋግሞ ሲነገራቸዉ ትኩረታቸዉን ከዚህኛዉ አለም መሻሻል ላይ በማንሳት ወደ ቀጣዩ አለም ዝግጅት ላይ ያደርጋሉ። ምክንያቱም ready made የሆነ የተሟላ አለም ቃል የተገባለት አካል ስለምን ብሎ አሁን ያለበትን ጎዶሎ አለም ለሟሟላት ይጥራል? በዚህም የተነሳ ነዉ ምሁራን የጨለማዉ ዘመን የሚሉት የመካከለኛው ዘመን ጊዜ በደንቁርና እና በባዶ ተስፋ የታጨቁ፤ አዲስ ነገር ለመፍጠር ወኔ የሌላቸዉ፤ምድራዊ ህይወትን የጠሉ እና የተስፋይቱን መንግስት አንጋጠዉ በሚጠብቁ ሰዎች ተሞልቶ የነበረዉ። የሰዉ ልጅ በተፈጥሮዉ ተመራማሪ እና ጠያቂ ነዉ፤ ይህ ተፈጥሮዉም ከሌሎች የጫካ እንስሳት ተለይቶ አለምን እስከመግዛት እንዲደርስ አርጎታል። ሰዉን በቀላሉ ሰዉ ያረገዉ Curiosityዉ ነዉ። እና ይህን የሰዉን ልጅ ትልቁን ገፀ በረከት ስትቀማዉ ፀጉሩን እንዳጣዉ ሳምሶን ተራ 'እንስሳ ይሆናል። ሪቻንድ ዳዊኪንስ አንዴ "I am against religion because it teaches us to be satisfied with not understanding the world" ብሏል። ሃይማኖት ማህበረሰብን ወደ ኋላ ያስቀራል እና ይጎዳል የሚባለው የሆነን አካል ስለሚያስመልክ አይደለም ይልቁንም የሰዉ ልጅ አንስቶ ሊጠይቃቸዉ፣ሊመራመርባቸዉ፣ሊያፍተለትላቸዉ የሚገቡ ጥያቄዎችን ቀላል መልስ ሰጦ ስለሚያዘናጋ፣ስለሚያዳፍን እና አእምሮን ስለሚያቦዝን ነዉ። ይሄ እንዴት እንደዚህ ሊሆን ቻለ ተብሎ ሲጠየቅ "የእግዜር ስራ ረቂቅ ነዉ ይሁን አለ ሆነ" ተብሎ ሲመለስለት፤ ሀሴት እና ደስታ ብቻ ያለበት ከስቃይ የፀዳን አለም ለምን አንፈጥርም ብሎ ሲጠይቅ "በፀሎት እና በህጉ ኑር እና እሱን አለም ፈጣሪ ከሞትክ ቡሃላ ይሰጥሃል" ተብሎ ቃል ሲገባለት ፤ ይሄ ነገር ልክ አይደለም ለምን እንደዚህ ሆነ መቀየር አለበት ብሎ ሲጠይቅ "ይቺ አለም አንዴ ወድቃለች እና የመትረፍ ተስፋ የላትም መትረፍ የሚቻለዉ በመንፈሳዊ ህይወት ብቻ ነዉ" ተብሎ ሲነገረዉ ያለበትን ምድራዊ ሀላፊነት እርግፍ አርጎ በመተዉ የጥንት መድብሎችን እንደ ገደል ማሚቱ እየደጋገመ ሲጃጃል ኑሮ ሲጃጃል ይሞታል፤ ያንን ጅልነትም ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል። at the end of the day,It's all about ተስፋ የሚሉ ሰዎችም አሉ ግን እኔ እዉነት እዉነት እላቸዋለሁ መሰረተ ቢስ ከሆነ ተስፋ ምሬት የወለደዉ ተስፋቢስነት በብዙ እጅ ይሻላል። በባሪያ ንግድ ጊዜ ባሪያዎች ጌታዎቻቸዉን ድል አርገዉ ከሀገራቸዉ ያባረሩት የተሻለ ቀን ይመጣል የሚልን ባዶ ተስፋ አሽቀንጥረዉ ጥለዉ ምሬት የወለደዉ ተስፋቢስነት ባስነሳዉ ቁጣ ነዉ፤ቻይኖች እልል ካለ ድህነት አሁን ለደረሱበት የአምራችነት ማዕከል መለወጥ አስተዋፅኦ ያረገዉ ምሬት የወለደዉ ተስፋቢስነት ነዉ... ተስፋ ነገን ለማየት ጉጉት ይሰጣል ይባላል ይሄ ሀሰት ነዉ! ይልቁንም ባዶ ተስፋ የማይመጣዉን ነገ በማስጠበቅ ዛሬህን እንድታባክን ያረግሃል። ደስ የሚል ትርክት ስላላቸዉ ብቻ ነገሮች ላይ ተስፋ ከማረግ ይልቅ የማይመስሉ ነገሮች ላይ ተስፋን መቁረጥ እራስን የኋሊት ከታሰሩበት ገመድ ማላቀቅ ነዉ እና የመሆን እድሉ በጣም ላነሰ ነገ በቢሆንስ እርግጠኛ የሆንከዉን ዛሬህን መስዋት ልታረግ አይገባም።

እንዴት እንግደላት? ፍረዱባት እስቲ! "የ18 አመት ልጅ እያለች የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት ልጅ... የምትገደልበትን ቀን እየጠበቀች 30 አመታት በእስር ከቆየች በሁዋላ.. ባሳለፍነው ሳምንት
+2
እንዴት እንግደላት? ፍረዱባት እስቲ! "የ18 አመት ልጅ እያለች የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት ልጅ... የምትገደልበትን ቀን እየጠበቀች 30 አመታት በእስር ከቆየች በሁዋላ.. ባሳለፍነው ሳምንት ቀኑ ደርሶ... እምትገደልበትን መርፌ ወጏት.. መርፌው በአእምሮ ውስጥ እሚካሄድን እንቅስቃሴ አስቆሞ.. ቀጥታ ለሞት እሚዳርግ ሲሆን ማንም ሰው ከዚ መርፌ ተርፎ አያውቅም ነበር ... ነገር ግን የ50 አመቷ Christa Pike ይሄን መርፌ ከወጉአት በሁዋላም መተንፈስ አላቆመችም ነበር... ዶክተሮቹ ተደናግጠው... ሁለተኛ ዙር የግድያ ሙከራ ሊያረጉባት.. ሌላ መርፌን አምጥተው ወጉአት... ነገር ግን 2ተኛው መርፌም ሳይሰራ ቀርቶ ልትተርፍ ቻለች... አሁን ላይ መርፌው ከባድ የጤና ጉዳት አድርሶባት ኮማ ውስጥ የገባች ሲሆን.. ሃይለኛ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል ... (የወጉአትን መርዝ ከሰውነቱአ ውስጥ አውጥተው ካተረፉዋት በሁዋላ ድጋሚ ሊገድሎት ነው መሰል) ይሄም የሳይንሱን አለም እጅግ ግራ ያጋባ እና.. የህግ ሂደታችንንም ጥያቄ ውስጥ እየከተተ ይገኛል... እኔ እንደሆነ ይሄን የሞት ፍርድ እምትሉትን ጭካኔ ስቃወም እንደኖርኩ ይታወቃል... ነገር ግን እስቲ ሃይማኖታዊ አረመኔያዊነት ያስተማረንን ጨካኝነታችንን በዚ ታሪክ እንፈትነው.. አንድ ሰው ያደረሰውን ጥቃት ድጋሚ እንዳያደርስ አርገህ.. ማሰር ከቻልክ በሁዋላ ለምንድን ነው እምትገድለው? የፍትህ መዳረሻ መፍትሄን ማምጣት ነው ወይንስ የወንጀለኛውን ድርጊት መድገም?... አሁን የዚች ሴት ፍርድ ምን ይሁን ብትባሉ ፍርዳቹ ምን ይሆናል? .. ከ30 አመት በፊት የ18 አመት ልጅ ሆና ለሰራችው ወንጀል.. •2ቴ ልንገድላት ሞክረን ተርፋ ኮማ ውስጥ ገብታለችና... እዛው ኮማ ውስጥ እንዳለች እንድትሞት እንተዋት? •ወይስ አክመን እናትርፋትና ከኮማ እናስነሳት.. ከዛ ድጋሚ ስትነቃ ድጋሚ እንግደላት? (ሰማይ ቤት ላይ እንደሚደረገው ማለቴ ነው) ወይስ እንዴት እናርጋት? እስከየት ድረስ ስንጨክን ይሆን ፍፁም ፍትሃዊ እምንሆነው? ለምን እሳት ለኩሰንባት ለዘለአለም እንድትቃጠል አናረግም? ቅዱሱ እሩህሩሁ ፍትሃዊው መንፈሳቹ በዚ ልክ መልካም አደል? ፍሩዱባት እንጂ!

ይቺ ደሞ ለክርስትያን ዘመዶቼ👐

ይቺን ደሞ ለ humanist ዘመዶቼ ናት👐 Don't pray for us We don't need no Modern Jesus to roll with us The only rule we need is never givin' up The only faith we have is faith in us💯

ዛሬ ሰንበት እንደመሆኑ መጠን ለኤቲስት ዘመዶቼ መዝሙር ልጋብዛቹ ወደድኩ 👐

በነገራችን ላይ በዚህ ቪዲዮ ያልተደመምኩት እና ይሄ አቋም የብዙ ኢትዮጵያዊን አቋም እንደሆነ የማቀዉ እኔ ብቻ ነኝ ብዬ አላስብም። ግን ስለዚህ ጉዳይ ሳወራ ሳወራ ጠግቤም አላዉቅም እና የጠገብኩ ለታም ስለ ጉዳዩ ማዉራት መልሶ ይርበኛል። እሱም የእኛ ኢትዮጵያዊያን የማንነት ኩራት(National ego) ችግር ነዉ። ይሄ ፃዲቅ ህዝብ፣ይሄ የተባረከ ህዝብ፣ይሄ ያልተገዛ ህዝብ፣ይሄ የስልጣኔ ቀንዲል የሆነ ህዝብ፣ይሄ የሰዉ ልጅ መገኛ በኩር ህዝብ፣ይሄ በፈጣሪ የተመረጠ ህዝብ... በታሪክ ዉስጥ እራሳችንን የማናታልልባቸዉ እና ሀሰተኛ ባህሪያቶችን ለራሳችን የማናጎናፅፍባቸዉ ጊዜያት ኖረዉ አያቁም። እና ይቺ ልጅ ሀገሪቷ እራሷን የምትሰክስበትን ትርክት ይዛ ወጣች እና "ጥቁር አይደለዉም" አለች ምን አጠፋች? ምንም። ምክንያቱም አይደለም ከጥቁር ህዝቦች በስልጣኔ የኋሊት ከሚያዩን ምዕራባውያን እራሱ እንደምንበልጥ እና ልዩ ዘር እንደሆንን አርገን እራሳችንን ማየቱ የጥንት የጠዋቱ ልምምድ ነዉ። የሀገር ፍቅር እና በሀገራዊ ማንነት ከልክ በላይ መኩራት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ(ምንአልባት ለዚህ ህዝብ ላይለያዩም ይችላሉ) ነገር ግን ይህ ቅጥ ያጣ በተረቶች የዳበረ ኩራት ሀገርን እና ህዝብን እያጃጃለ ወደኋላ ከመጎተት ባሻገር አሁን እንደምታዩት አለም ላይ ያለንን ተቀባይነት በሚሸረሽር ሁኔታ አግጥጦ መገለጥ ይጀምራል። ኢትዮጵያ ላይ በታሪክ ዉስጥ ሲታይ የከረመዉን ዝንባሌን በማየት ኢትዮጵያዊያንን አቅም አልባዎቹ አርያኖች(ናዚዎች) ብለን ለመጥራት መድፈር እንችላለን። የሁል ጊዜ ዲስኩራችንም "ልዩ ነን" የሚል ነበር። አቅም ቢኖረን እና ሁኔታዉ ቢመቻችልን አለምን ለመዉረር ጎራዴ እና ጋሻ ቀስረን እንደምንወጣም ምንም ጥርጥር የለዉም። እባብ የልቡን አይቶ እግር ነሳዉ እንዲሉም የሆነ የማይታወቅ አካል ይህ ሀገራዊ ኩራታችንን አይቶ ጭንቅላት ነሳን እና በኢኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ አቅም ወደ ኋላ ቀረን እንጂ የአፍሪካን ግዛቶች የምናስጨንቅ የወገብ ቅማል መሆናችን አይቀሬ ነበር። እናም ወገኖቼ እናንተ ጥቁር ናቹ፤ድሃ ናቹ፤ምዕራባዉያኖች አሁንም ቢሆን በእጅ አዙር ስለሚገዟቹ ባርያ ናቹ፤ሰላም የማትወዱ እና እንግዳ ቀርቶ የሀገራቹን ሰዉ በሰላም ለማስተናገድ ይሁንታ የሌላቹ በዘር የምትባሉ እርኩሳንም ናቹ። ይህን እዉነታም አምናቹ እና ተቀብላቹ እራሳቹንም ሆነ ሀገራቹን ለማሻሻል ስሩ እንጂ በተፈጠሩ አፈ ታሪክ እና ተረቶች እራሳቹን እያሞኛቹ  በሚያሳፍረዉ ሀገራዊ ማንነታቹ አትመኩ።

Dear Mr. Abdisa Defar! First of all, congratulations on the first anniversary of የኃይለኞች ፈጣሪ መጽሐፍ! I read your book about 8 or 9 months ago, during a time when I was struggling with questions about God, religion, consciousness etc and the beliefs I grew up with. I had so many questions, but I was afraid of being a heretic or a sinner just for thinking about them. Actually, I first heard about your book from one of my friends. He told me about a religious person who became an atheist and wrote a book about it, however the way he described about the book was negative way. Somehow, instead of discouraging me, that made me even more fascinated, and I decided to read it myself. When I read your book and realized that I wasn't the only one thinking about those questions, something changed in me. I started thinking more freely and independently, without being so afraid of my own thoughts. Honestly, your book was one of the most mind-bending books I've ever read, and it marked the beginning of a great inner revolution in my life. For me, it wasn't just about atheism or religion. It changed the way I think, question things, and search for answers. I don't know if you realize how much your book can mean to someone who is silently struggling with these questions, but I wanted to share my experience with you as you celebrate its first anniversary. Thank you for writing it, and congratulations again! 🎊🎉🎉🎉🎊 17 years old reader whose inner world was profoundly changed by your book. @Ermi_prime

Elon Musk ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ተሸለመ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሳይንቲስቶች እና መሐንዲሶች የሚሰጠውን የአሜሪካ ከፍተኛው ክብር የሆነውን (National Medal of Science) ለኢሎን ማ
+2
Elon Musk ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ተሸለመ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሳይንቲስቶች እና መሐንዲሶች የሚሰጠውን የአሜሪካ ከፍተኛው ክብር የሆነውን (National Medal of Science) ለኢሎን ማስክ አበረከቱ። 'ኢሎን የዘመናችን ቶማስ ኤዲሰን ነው። ለኢሎን ነገሮች ሁልጊዜ በጥሩ ሁኔታ ይከናወናሉ፣ እንኮራብሃለን። በጣም እንኮራብሃለን። አንተ የሀገር ሀብት ነህ። ሳይንሳዊ ልብ-ወለድ ሀሳቦችን ወደ እውነት ቀይረዋቸዋል። በእውነት፣ እንደ እሱ ያለ ሌላ ሰው የለም" •••••••• የፕራምፕ ሙሉ ንግግር.. "በመጀመሪያ፣ አንድ ታላቅ የኢንዱስትሪ ሰው፣ ብሩህ አእምሮ ያለው መሐንዲስ እና ከታሪክ ታላላቅ የቴክኖሎጂ መስራቾች አንዱን እናከብራለን። ስሙ ኢሎን ማስክ (Elon Musk) ነው። በእውነት፣ እንደ እሱ ያለ ሌላ ሰው የለም። በታሪክ ውስጥ የአሜሪካን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከኢሎን የበለጠ አስተዋጽኦ ያደረጉ አሜሪካውያን ጥቂት ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች፣ የእሱ ብልህነት እና ቁርጠኝነት ሳይንሳዊ ልብ-ወለድ ሀሳቦችን ወደ እውነት ቀይረዋቸዋል። ይህ ደግሞ ፍጹም እውነት ነው። ኢሎን በ2002 ዓ.ም. የህይወት ዘመን ቁጠባውን በመጠቀም SpaceXን የመሰረተ ሲሆን፣ እጅግ አስቸጋሪ እና የማይቻል በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ወደ ምህዋር የደረሰ የመጀመሪያውን በግል ኩባንያ የተሰራ ፈሳሽ ነዳጅ የሚጠቀም ሮኬት ፈጥሯል። እሱ የሚያደርጋቸውን ነገሮች - በተለይም በብዙ የተለያዩ መንገዶች - ማድረግ ይቻላል ብሎ ያሰበ ማንም አልነበረም። SpaceX፣ የሀገራችንን ጠፈርተኞች ወደ ጠፈር ለመላክ በውጭ ሀገራት ላይ መታመንን ከናሳ (NASA) ትከሻ ላይ አስወግዷል። እንዲሁም ከጥቂት ሰዓታት በፊት 'Crew-12' ከተባለው ቡድን ጋር የተላከው የጠፈር መንኮራኩር ከአለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ በሰላም በመመለሱ ለSpaceX እንኳን ደስ አለዎት ማለት እፈልጋለሁ። እንኳን ደስ አላችሁ። ነገሮች በጥሩ ሁኔታ መከናወናቸውን ማረጋገጥ ፈልገን ነበር። ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ባይከናወኑ ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ትችላላችሁ? ያ በጣም አስደሳች ጊዜ አይሆንም ነበር። እሱ እዚህ ይገኝ ነበር ወይ ብዬ አስባለሁ፤ ምናልባት እዚህ ላይገኝ ይችል ነበር። ነገር ግን ለኢሎን ነገሮች ሁልጊዜ በጥሩ ሁኔታ ይከናወናሉ፣ አይደል? እንኮራብሃለን። በጣም እንኮራብሃለን። አንተ የሀገር ሀብት ነህ። በኢሎን አመራር ስር፣ SpaceX በታሪክ ትልቁ የሆነውን እና በፍጥነት እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል በአየር ላይ ተይዞ የሚመለሰውን 'Starship' የተባለውን ሮኬትም አዘጋጅቷል። ይህን የመሰለ ነገር ሲሰራ ማየትም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። እንዲሁም ትልቁን የመገናኛ ሳተላይት ኔትወርክ የሆነውን 'Starlink'ን ፈጥረዋል። እና በሰሜን ካሮላይና (North Carolina)፣ እኔም በሂደቱ ውስጥ ስለተሳተፍኩ በግሌ ልነግራችሁ እወዳለሁ፤ እዚያ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ አስከትሎ የነበረ ታላቅ አውሎ ንፋስ ተከስቶ ነበር። በታሪክ ከምናስታውሰው ጊዜ ሁሉ በበለጠ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ያዘነበ አውሎ ንፋስ ነበር። ኢሎንን ማነጋገር በመቻላችን በመቶዎች የሚቆጠሩ ህይወቶች ሊድኑ ችለዋል። ገዥው (Governor) እንዲህ ሲል እንደጠየቀኝ አስታውሳለሁ፡- "ጌታዬ፣ ኢሎን ማስክ የሚባል ሰው ታውቃለህ?" እኔም "አዎ፣ አውቀዋለሁ" አልኩት። "Starlink ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም ውሃው በጣም ጥልቅ ስለነበር ብዙ ደሴቶች ተፈጥረው ነበር፤ ሰዎችም ከዚያ ለመውጣት ምንም መንገድ አልነበራቸውም..." ...ደሴቶች ነበሩ፤ ምንም ዓይነት የመገናኛ ዘዴ አልነበራቸውም። ‘እኛን የሚረዳ ሰው ማግኘት አልቻልንም’ ብለውም ነበር። እኔም ኢሎንን (Elon) አነጋገርኩት፤ ያንን መሳሪያ ማግኘት ፈጽሞ የማይቻል ይመስል ነበር። ነገር ግን በጥቂት ሰዓታት ውስጥ መሳሪያውን እዚያ አደረሰው፤ በዚያም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት አዳነ። በሰሜን ካሮላይና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ታደገ። ስለዚህ፣ ያንን ክስተት ፈጽሞ አልረሳውም። እጅግ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር፤ እሱ የሠራው ስራም እንዲሁ። በጣም በፍጥነት ነበር እርምጃ የወሰደው። ሁሉም ሰው መሳሪያዎቹን ማግኘት አይቻልም ይሉ ነበር። ስለዚህ፣ ለዚያ ልዩ ወቅት እና ተግባር ኢሎን፣ አመሰግንሃለሁ። በተጨማሪም፣ ኢሎን ‘ቴስላ’ን (Tesla) መስርቷል፤ ይህም ከ75 ዓመታት በላይ በቆየ ጊዜ ውስጥ ስኬታማ የሆነ የመጀመሪያው አዲስ የመኪና አምራች ኩባንያ ነው። ለገበያ የሚሆኑ የመጀመሪያዎቹን የኤሌክትሪክ መኪኖች እና ለተጠቃሚዎች የሚሆን የመጀመሪያውን በራሱ የሚነዳ (self-driving) ቴክኖሎጂ አምርቷል። በኒውራሊንክ (Neuralink) አማካኝነት፣ ኢሎን ማየት፣ መናገር ወይም መንቀሳቀስ ለማይችሉ ሰዎች የማየት፣ የመናገር እና የመንቀሳቀስ ችሎታን እየመለሰላቸው ነው። እንዲሁም የSpaceXን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በሱፐር-ኢንተለጀንስ (superintelligence) ዘርፍ ከአለም መሪዎች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል። ኢሎን የዘመናችን ቶማስ ኤዲሰን ነው። እናም ኢሎን፣ እንኳን ደስ አለህ ልልህ እወዳለሁ። በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ጓደኛዬ ነህ፤ ነገር ግን አንተ በጣም ልዩ ሰው ነህ። በጣም አመሰግናለሁ፤ እንኳን ደስ አለህ ኢሎን።" @Abdisa_Defar

የኃይለኞች ፈጣሪ መፅሃፍ 1ኛ አመት ከ 10 ቀናት በሁዋላ መፅሃፋችን ከተለቀቅ 1አመት ይሞላዋል... የ2018 አነጋጋሪ መፅሃፍ የሆነውና.. በ1 አመት ውስጥ 100ሺዎች ያነበቡት.. የኃይለኞች ፈጣሪ
የኃይለኞች ፈጣሪ መፅሃፍ 1ኛ አመት ከ 10 ቀናት በሁዋላ መፅሃፋችን ከተለቀቅ 1አመት ይሞላዋል... የ2018 አነጋጋሪ መፅሃፍ የሆነውና.. በ1 አመት ውስጥ 100ሺዎች ያነበቡት.. የኃይለኞች ፈጣሪ.. አንደኛ አመቱን October 21/22 በTiktok Live ላይ በደማቅ እናከብረዋለን... ስለ ቀጣዩ መፅሃፋችንም እንወያያለን.. እናንተም ተገኝታቹ ሃሳብ አስተያየታችሁን ለመስጠት ተዘጋጁ .. ከዛ ቀድማችሁም ስለመፀሃፉ ማለት የምትፈልጉትን.. inbox ላይ @AbdisaDefar በፅሁፍ ብትልኩልኝ.. ቻናላችን ላይ እየለቀቅን ሞቅ ሞቅ እናረገዋለን:: W የኃይለኞች ፈጣሪ 🔥

ኢ-አማኒነት ምንድነዉ?
Anonymous voting

𝐀𝐛𝐝𝐢𝐬𝐚 𝐃𝐞𝐟𝐚𝐫 - آمار و تحلیل کانال تلگرام @abdisa_defar