2 214
مشترکین
-324 ساعت
-127 روز
-5230 روز
آرشیو پست ها
2 213
አላህ ያሳዉቀን
በመጨረሻም፣ ለመወደድ ስንል ብቻ ምንም ዓይነት ጥረት ማድረግ እንደማያስፈልገን አምናለሁ። ሕይወታችንን ይበልጥ ውብ ወይም ብልህ ለመምሰል በመጣር እንጨርሰዋለን። እኔ ግን ሁለት እውነታዎችን ተገነዘብኩ፤ የሚወዱን ሰዎች የሚያዩን በልባቸው ስለሆነ፣ እኛ ካሉን በላይ የሆኑ ማራኪ ባሕርያትን ያላብሱናል። ሊወዱን የማይፈልጉት ደግሞ ምንም ያህል ብንጥር መቼም አይረኩም። አዎ፣ እንከኖቻችንን እንዳሉ መተዋቸው ትልቅ ዋጋ እንዳለው በእውነት አምናለሁ። ምክንያቱም እነዚያ እንከኖቻችን እኛን በልባቸው ለሚረዱን ሰዎች እውነተኛ ማንነታችንን የሚያሳዩ ውድ ስጦታዎች ናቸውና።
2 213
ዶይስቶይቭስኪ አንድ እውነት ልንገራችሁ ብሎ ይጀምራል፦
‹‹ዓለም እንደ እናታችሁ አይደለችም ንዴታችሁን የመታገስ አመል የላትም፤ ቢርባችሁ ደርቃችሁ ትቀራላችሁ እንጂ ማንም ግድ አይሰጠውም!። እናት ግን ቀን ላይ ተናዳችሁ ትጮኹባታላችሁ፤ እናም ማታ በቀኑ መጨረሻ ሁሉንም እረስታ እራት ታቀርብላችኋለች..›› ❤🩹
2 213
https://t.me/miracle_semir_amiiiii
ሀ ብለን አዲስ ስም አዲስ ምእራፍ ጀምረናል ስታዩት እንዳትደናገሩ ብዬ ነዉ ፎሎ እያረጋቹ አበረታቱን semir ami ነኝ
ስለ አዲስ ስሙ ማብራሪያ ቻናሌ ላይ አለ እየገባቹ አለን በሉኝ
ሰላም ለልባችሁ😊
2 213
መንገድ
ለአንድ አኞ ልቦለድ ወይም ግጥም፣ አጨራረሱን አይታችሁ ይቅርታ ልታደርጉለት ትችላላችሁ። አድክሟችሁ አድክሟችሁ በመጨረሻ ‘አሪፍ!’ ትሉ ይሆናል። ግን ህይወታችሁን እንደዚህ መታገስ አትችሉም። አጨራረሳችንን ሰዎች እንጂ እኛ አናውቅም። ዋናውን ነገር፣ መንገዳችንን ከባድ ባናደርግ እላለሁ።
Semir ami
2 213
“ልብ የልብን ጠረን ያሸታል” ይላሉ ኢብነል ቀይዪም። አንዳንዴ መውደድ የልብ ትውውቅ ነው። ብዙ ያላወራኸውን፣ ብዙም የማታውቀውንና ምንም ያላደረገልህን ሰው እንዲሁ ትወደዋለህ። "ለምን ወደድከኝ?” ብለህ ምክንያት ብትጠይቅ ምክንያት የማይነግርህ ብዙ ወዳጅ አለ።
Semir ami
2 213
"አንድ ሰው ሲናፍቃችሁ ረጅም መልዕክት ፃፉለትና ተኙ እንጂ አትላኩት፤ ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ ደግማችሁ ስታነቡት በጣም የዋህ ሰው መሆናችሁን ትረዳላችሁ።🥰🤝
Semir ami ezel
2 213
ትንሽ ሲከፋው በድንገት ፊቱ ጭው እና ግርጥት የሚል ሰው ውስጡ ያጠራቀመው ብዙ ችግር እና ያልተናገረው ህመም አለው ማለት ነው
ጥፍሩን የሚበላ ሰው የወደፊት ህይወቱ በጣም የሚያስጨንቀው እና "ምን ይሉኛል" ብሎ ይሉኝታ የሚያጠቃው ሰው ነው
አንድ ሰው መተኛት የሚያበዛ እና ከአልጋው መውጣት የማይፈልግ ከሆነ ሀዘን ላይ ነው ማለት ነው -አዋራው
በሆነውም ባልሆነውም ቁጣ የሚቀናው ሰው እንክብካቤ: ፍቅር እና ትኩረት የሚፈልግ ሰው ነው
ዝም ብሎ የሚስቅ ሰው ገጥሟችሁ ያውቃል? ምናልባት የሆነ የሚሸፍነው ሃዘን እና ችግር ውስጡ አለ
👇🏾
አጠገባችሁ ያለውን ሰው እያያችሁ
ቆሞ ስለሄደ: ስለሳቀ: ስለተኛ እና ስለበላ ደስተኛ ነው ማለት አይደለም
"ደህና ነህ?" : "ደህና ነሽ?" እንባባል❤️🙌🏼
Semir ami ezel
2 213
ጨዋን የሚያውቁት ሲጣሉት ነው! ክፉ አያወራ፣ ገመናን አይናገር፣ ለምን ብሎ አይሞግት
ዝም እንዳለ ከነ ትዝታው ትቶህ ይሄዳል🤍
Silence is so beautifulness 🥰
Semir ami ezel
2 213
ከተረዳሁት
አብዝቶ ውሸት መናገር አላህ ዘንድ ስምህ "ውሸታም" ተብሎ ከመፃፉ በተጨማሪ ምን እንደሚደብር ታውቃለህ? ብዙ ውሸት ስለምታወራ የሆነ ጉዳይ ላይ ምን ብለህ እንደዋሸህ ትረሳዋለህ.. እንደኔ የነገሩትን ሁሉ ባላወቀ ሃዬ ብሎ ከሚያልፍ ሰው ጋር ብቻ ምትገናኝ ከሆነ ፒስ ነው.. ካልሆነ ግን "ያኔኮ እንዲህ ብለህ ነበር..." ሲሉህ ምን ብለህ እንደዋሸህ ግራ ትጋባለህ..🙂
«ውሸት ብዙ ነው፤ እውነት ግን አንድ ናት» አይደለ ያሉት ሰዎቹ😃
2 213
አንተ ለሚስትህ "እወድሻለው"ነዋ ያልካት ...
አሊይ ረዲየሏሁ አንሁ ግን ለ ፋጢማ እንዲ ነበር ያሉት ..
"ሀዘንሽ ሰውነቴ ላይ ካሉ ቁስሎች በላይ ያሳምመኛል "💗
2 213
አሁን አጠገቤ እያለፍክ "አታካብድ ባክህ ከመንገዴ ዞር በልልኝ" ያልከኝ እብድ፣
አንተ ራስህ አታካብድ ባክህ። ምን? በደህና ጊዜ ስለተገላገልክ ራስህን እንዴት ነዉ ምታየዉ ባክህ🙂፡)
😏
2 213
"10 ሺህ ብር አበድረኝ" አለኝ
"7 ሺ ነዉ ያለኝ" ስለዉ፦
"እሱን አምጣና 3ሺ ይቀርብሃል" ብሎኝ እርፍ🤔
ምንድነህ አንተ ሰዉ ነህ ወይስ🤔😭
እህይት ያለ አህያ😏
2 213
ለዚህ ፈራሽ በስባሽ ሥጋ
ወዳጄ ሆይ ተው አትስጋ
መሞትህን አትዘንጋ
ቀኑ ሲመሽ አንተ ንጋ!
፨
በዚህ ተፅናና ኑሮ ሲጎዳህ
አንተም ታልፋለህ እንኳንስ ፍዳህ!
፨
አይዞህ!
የኃዘን ወጀብ አይሂድ ይዞህ
አትሁን ለጋ!
ከቤት አትውጣ ሞትን ፍለጋ
ደስታህን ያዘው!
መግነዝህንም ቀድመህ ገንዘው!
ኑሮህን ወጥን!
ቀድመህ ቅበረው ባዶውን ሳጥን!
፨
ፍፁም አትርሳ
ይሄ ሁሉ ዕዳ፣ ፍዳና ችጋር
ማለፉ አይቀርም ከአንተ ማለፍ ጋር!
Semir ami ezel
