Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school
رفتن به کانال در Telegram
1 942
مشترکین
-424 ساعت
-37 روز
-1430 روز
آرشیو پست ها
+4
“ለሰላማዊ መማር ማስተማር
የጋራ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ ከመምህራን እና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ።
(መስከረም 13/2019 ዓ.ም) እሸት ት/ቤት በ2019 ትምህርት ዘመን “ለሰላማዊ መማር ማስተማር የጋራ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ ከመምህራን እና ከድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጋር ምክክር አካሄደ።
✅ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለትውልድ ግንባታ በሚል ሰነድ ያቀረቡት የት/ቤቱ ም/ር/መ/ር ታምሬ አጎናፍር
በተማሪ ውጤትና ስነምግባር ላይ ለውጥ የሚያመጡ ስራዎች ለመስራት የተማሪዎችን ስነ-ምግባር መግራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ተግባር መሆኑን እና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በስነምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት በጋራ መስራት እንደሚገባ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ለሰላም እሴት ግንባታ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።
✅ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆነውን ትውልድ ሰላም መጠበቅና ብቁ ትውልድ ማፍራት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት በመሆኑ ለሰላም መጠበቅ አስፈላጊውን ሚና መወጣት ይገባል።
ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስፈን ችግሮችንና የችግር ምንጮችን በአግባቡ ለይቶ በመፍትሄዎቹ ላይ መስራትና በየጊዜው እየገመገሙ መሄድ እንደሚያስፈልግ ፣ ተማሪዎችም ሙሉ ጊዜያቸውን በትምህርት ላይ ብቻ እንዲያሳልፉ መምህራን ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም ለተነሱ ሀሳቦች ማብራሪያ እና ምላሽ በመስጠት የእለቱ ውይይት በመግባባት ተጠናቋል።
"ትውልድ በትምህርት ይቀረፃል"
"ሀገር በትውልድ ይገነባል"
የመማር ማስተማር ዘዴዎች ሦስት ዋና ዋና ምድቦች!
1. በአስተማሪ ላይ ያተኮሩ ዘዴዎች(Teacher-Centered Methods)
I. ንግግር (Lecture Method): አስተማሪው ለተማሪዎች በአፍ የሚያስተምርበት ባህላዊ ዘዴ ነው። ብዙ ሰዎችን በአንድ ጊዜ ማስተማር ቀላል ቢሆንም፣ የተማሪዎች ተሳትፎ አነስተኛ ሊሆን ይችላል።
II. ትዕዛዛዊ አመራር (Direct Instruction): አስተማሪው አንድን ችሎታ ወይም ፅንሰ-ሀሳብ በደረጃ በደረጃ በማብራራት፣ በማሳየት እና እየመራ ተማሪዎች እንዲለማመዱ የሚያደርግበት ዘዴ ነው።
III. ማሳያ (Demonstration): አስተማሪው አንድን ሂደት ወይም ሙከራ እያከናወነ ለተማሪዎች የሚያሳይበት ዘዴ ነው (ለምሳሌ፡ በሳይንስ ትምህርት ውስጥ ሙከራን ማሳየት)።
2. በተማሪ ላይ ያተኮሩ ዘዴዎች (Student-Centered Methods)
እነዚህ ዘዴዎች ተማሪዎችን በመማር ሂደታቸው ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ያደርጋቸዋል። ትኩረቱ ተማሪዎች በመሆን እራሳቸውን ችለው እንዲማሩ እና እውቀትን እንዲገነቡ ያበረታታል።
I. ውይይት (Discussion Method): ተማሪዎች በቡድን ወይም በጠቅላላ ተሰብስበው በአንድ ርዕስ ላይ ሃሳብ የሚለዋወጡበት፣ የሚከራከሩበት እና የሚደምድሙበት ዘዴ ነው።
II. ችግር ፈቺ (Problem-Based Learning - PBL): ተማሪዎች ከእውነተኛው ዓለም የተወሰደ ውስብስብ ችግር በመስጠት በቡድን ሆነው መፍትሄ እንዲያመጡ የሚደረግበት ዘዴ ነው።
III. ፕሮጀክት ላይ የተመሠረተ ትምህርት (Project-Based Learning): ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጋር በተያያዘ አንድን ፕሮጀክት (ለምሳሌ፡ ሞዴል መሥራት፣ ዘገባ ማዘጋጀት) በጥልቀት በመሥራት የሚማሩበት ዘዴ ነው።
IV. ጥያቄ ላይ የተመሠረተ ትምህርት (Inquiry-Based Learning): ተማሪዎች ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በመተንተን እውቀትን እራሳቸው የሚያገኙበት ዘዴ ነው።
V. ትብብራዊ ትምህርት (Cooperative Learning): ተማሪዎች በትናንሽ ቡድኖች ተከፋፍለው አንድ የጋራ ግብ ላይ ለመድረስ እየተባበሩ የሚማሩበት ዘዴ ነው።
3. በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘዴዎች(Technology-Based Methods)
I. መስመር ላይ ትምህርት (Online Learning / E-learning): ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጭ ሆነው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል በመጠቀም በይነመረብ ላይ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት ዘዴ ነው።
II. ድብልቅ ትምህርት (Blended Learning): ይህ ዘዴ የሁለቱም የፊት ለፊት (ክፍል ውስጥ) እና የመስመር ላይ ትምህርት ጥቅሞችን ያጣምራል።
III. የተገለበጠ ክፍል (Flipped Classroom): ተማሪዎች ትምህርቱን በቤት ውስጥ በቪዲዮ ወይም በሌላ የመስመር ላይ መረጃ ቀድመው ያጠናሉ፣ በክፍል ውስጥ ደግሞ በተግባር፣ በውይይት እና በፕሮጀክት ላይ ያሳልፋሉ።
የሀገራችን የትምህርት እጣፈንታን የሚወስነው የመምህራን ትጋትና አደራ ነው።
(መስከረም 7/2019 ዓ.ም) ትምህርት ከጥቁር ሰሌዳውና ከፊደል ገበታ አልፎ የፈጠራ፣ የመልካም ሥነ-ምግባርና የመልካም ጓደኝነት መገንቢያ ነው።
በሳይንስ፣ በሂሳብ፣ በአይሲቲና በሌሎችም የትምህርት ክፍለጊዜዎች ከሚመነጩ የፈጠራ ሀሳቦች የሚጎለብቱ ብሩህ አዕምሮዎች የነገዋን ሀገር የመገንባት ታላቅ አቅም አላቸው፤ በሥነ-ጽሑፍ የዳበረ ጥልቅ ዕውቀት ደግሞ የሀገራችንን ታሪክ፣ ባህልና የስልጣኔ እሴት ለዓለም የማስተዋወቅ ትልቅ ተስፋን ይሰንቃል።
በዚህ አገራዊ የትውልድ ግንባታ ሂደት ውስጥ ከወላጆች ሀላፊነት በተጨማሪ የትምህርት ቤት፣ የተማሪና የማህበረሰቡ ዋና ማዕከል የሆኑትን መምህራንን ነጥሎ ማየት ፈጽሞ አይቻልም።
መምህራን ዕውቀትን ከማስተላለፍ ባለፈ ማርፈድንና ኩረጃን የሚፀየፉ፣ የአነጋገር ዘይቤያቸው በስነ-ስርዓት የታነፀ፣ በፈጠራና በክህሎት የዳበሩ እንዲሁም አቅማቸውን የሚያወጡ መልካም ዜጎችን የሚያንፁ ዋና ተዋናይ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ወጣቱ ትውልድ የሀገራችን ትልቁ ሀብት በመሆኑ ብቁና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራን ትጋት የመሠረት ድንጋይ ነው ብለዋል።
መምህራን ተማሪዎችን ለነገው ተፎካካሪና ፈጣን ዓለም የሚያዘጋጅ ዘመናዊ ዕውቀት፣ ተግባራዊ ክህሎትና አገራዊ እሴቶችን የማስታጠቅ ታላቅ አደራ አለባቸው።
በዚህ ዘመን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ እያየለ በመሆኑ ተማሪዎች የአልባሌ ነገሮች ምርኮኛ ሳይሆኑ፣ ቴክኖሎጂ ያመጣቸውን በጎ ዕድሎችና የመረጃ ምንጮች ለጥናት፣ ለፈጠራና ለሀገራቸው ዕድገት እንዲጠቀሙ መምህራን የማስገንዘብና የመምራት ኃላፊነት አለባቸው።
ከዚህም ባለፈ እያንዳንዱ ተማሪ ውስጥ ያለውን ድብቅ ክህሎት በመፈለግና በማነቃቃት፣ በራሳቸው እንዲተማመኑና የሀገራቸውን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል ቁርጠኛ እንዲሆኑ ማነሳሳት ከመምህራን የሚጠበቅ ዋነኛ ተግባር ነው።
ዕውቀትን በትውልዱ ላይ ለማበልፀግ በትምህርት ሚኒስቴርና በመንግሥት ደረጃ በተሰሩ ስራዎች ተማሪዎች በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይሰናከሉና ትኩረታቸው እንዳይበታተን ሰፊ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ተዘርግቶ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ተችሏል።
የመንግሥት የልማትና የመሠረተ ልማት ስራዎች ከትምህርት ሚኒስቴር የአሰራር ማሻሻያዎች ጋር ተጣጥመው ሲቀጥሉ፣ የመምህራን ያልተቆጠበ ትጋትና የተማሪዎች ጽናት ተጨምሮበት ኢትዮጵያ በውጤታማና ብቁ ትውልድ እጅ ወደ ላቀ የስልጣኔ ማዕረግ ተሸጋግራ ትቀጥላለች።
+8
"በዕውቀት፣በመልካም ስነምግባር የታነፀ ትውልድ ግንባታ ለሀገር ብልፅግና ከፍታ"
(መስከረም 5/2019ዓ.ም) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት በእሸት ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የት/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ2019ዓ.ም የትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ።
✅ የትምህርት መዋለ ነዋይ ለሀገረ መንግስት መሠረት የሆነው የነገን ሀገር ተረካቢ ትውልድ በዕውቀት፣ በክህሎት፣በአመለካከት፣በመልካም ስነምግባር የማነፅ ሀገራዊ ትልም ለማላቅ በሚደረገው ርብርብ፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤታችን በድምቀት ተጀምሯል። ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት በትምህርት ዘርፋ የመጣው ለውጥ፣ የተማሪዎች ምገባ አቅርቦትና የትምህርት ግብአት አቅርቦቶች፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የወሰዳቸው ቁልፍ እርምጃዎች የመንግስታችንን እውነተኛ ልማታዊ አስተሳሰብና የታሪካዊ ዕድገት ራዕይ በተግባር ያሳዩ ስኬታማ ስራዎች ናቸው።
✅ የተማሪዎቻችንን ስነምግባር ከሀገራዊ እሴቶች ጋር በማጣጣም እና በትምህርት ውጤታቸው ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤታማ መሻሻል ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
ትውልድ አናፂ መምህራን፣የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች፣ተማሪዎቻችን በሙሉ፤ አዲሱ የትምህርት ዘመን የውጤታማነት የትጋት፣ የስኬት እና የከፍታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
'መልካም የትምህርት ዘመን'
Repost from Addis Ababa Education Bureau
+9
በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በስነምግባር ታንፀውና በእውቀት የዳበሩ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::
(መስከረም 5/2019 ዓ.ም) በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በይፋ ተጀምሯል፡፡
በተያዘው የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ተማሪዎች በስነምግባር ታንፀውና በእውቀት ዳብረው እንዲወጡ ማድረግ የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ በቅንጅት እየተሰራ ነው::
መንግሥት ለትምህርት ጥራትና ትውልድ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ብቁ ትውልድ ለመገንባት ለተማሪዎች ምቹና ዘመናዊ የመማሪያ አካባቢን በመፍጠር የትምህርት ቤቶች ማስፋፊያና አዳዲስ ግንባታ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመመገቢያ ክፍሎች መገንባት እንዲሁም ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-ሙከራዎችን ማስፋፋትና ማዘመን ስራዎች ተሰርተዋል::
በተጨማሪም የተማሪዎች የተመጣጠነ ምገባ ፕሮግራም እና የትምህርት ግብአት አቅርቦት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተማሪዎችም በደስታና በከፍተኛ ተነሳሽነት ትምህርታቸውን መጀመራቸውን ለመታዘብ ችለናል።
በእሸት ት/ቤት በተካሄደው የትምህርት ማስጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም የ2019 የትምህርት ዘመን የመመር ማስተማር ሂደት በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በጀመሩን ገልፀው ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ከዘርፉ ባለድርሻች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ለተከበራችሁ ውድ ተማሪዎቻችን እና የተማሪ ወላጆች በሙሉ
እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሠላም አደረሳችሁ!! አደረሰን እያልን የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ማስጀመሪያ ስነስርዓት በደማቅ ሁኔታ መስከረም 5/2019ዓ.ም ስለሚካሄድ ሁሉም የት/ቤታችን ተማሪዎች የደንብ ልብስ በመልበስ ጧት 2:00 በትምህርት ገበታችሁ ላይ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
"ትምህርት ቤቶች የብቁ ዜጎች መፍለቂያ እና በሁለንተናዊ ስብዕና የሚገነቡበት ማዕከል ናቸው"
ት/ቤቱ
ቀን 04/01/2019ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለተማሪዎቻችን በሙሉ
በቅድሚያ እንኳን ለ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን እያልን ነገ በቀን 05/01/2019ዓ.ም መደበኛው የመማር ማስተማር ስራ በይፋ የሚጀምር ስለሆነ ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ በት/ቤት ቅጥር ግቢ እንድትገኙ ይሁን።
ማሳሰቢያ ለተማሪ ወላጆች ፦ ከነገ ማክሰኞ (05/01/2019ዓ.ም) ጀምሮ ት/ት ስለሚጀመር ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ በማለት ለማሳወቅ እንወዳለን።
ት/ቤቱ
ለእሸት ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን፣ ሰራተኞች፣ ተማሪዎቻችን፣ ለወላጆች፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ እና ለአጋር አካላት እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።
🎉🌿 እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም ፣በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!🌿🌻🎉
🌻 አዲሱ ዓመት ትምህርት ቤታችንን የትኩረት መስኮች በተደራጀ፣ በተቀናጀና በትጋት በመፈፀም የበለጠ ስኬት የምናስመዘግብበት፤
🤝 ተቋማዊና ሀገራዊ ኃላፊነቶቻችንን በብቃት የምንወጣበት፤
🕊️ ሰላምና መረጋጋት የሚሰፍንበት፤
👌ፍቅር፣ መተሳሰብና መተባበር የሚጎለብትበት፤
🚀 ዕውቀትና የትምህርት ጥራት የሚያድጉበት የስኬትና የተስፋ ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን።
🌻አዲሱ ዓመት የሰላም፣የጤና፣የደስታ፣የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን እየተመኘሁ፤
✅ በ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመተሳሰብ፣በመከባበር፣በመደማመጥ ፣በትጋት ውጤታማ ስራ የምንሰራበት እና የተለመደውን የተቋማችንን ጠንካራ የስራ ባህል አጠናክረን በማስቀጠል የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል አልቀን በመስራት የተቋማችን ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት በአብሮነት፣በቅንጅትና በትጋት ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት ርብርብ እንድናደርግ አደራ ለማለት እወዳለሁ።
✅ የ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አጀማመርን በተመለከተ ሰኞ መስከረም 4/2019ዓ.ም የተማሪዎች ተግባርና ኃላፊነት በተመለከተ ፣የክፍል ድልድል፣ ትውውቅ የሚደረግበት ሲሆን ማክሰኞ ማለትም መስከረም 5/2019ዓ.ም የመጀመሪያ መደበኛ የትምህርት ክፍል (Day One Class One) የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን።
🇪🇹 አዲሱ ዓመት የሰላም፣የፍቅርና የመተሳሰብ ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ።
🌼 መልካም አዲስ ዓመት!🌻
ታምሬ አጎናፍር
የት/ቤቱ ም/ር/መ/ር
መስከረም/2019ዓ.ም
+6
ጳጉሜ 4 "በኅብር ቀን"
የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በወረዳ 09 ት/ጽ/ቤት ስር ያሉ ትምህርት ቤቶች በጋራ በመሆን በእሸት ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የንፅህና መጠበቂያ ለ80 ተማሪዎች በማበርከት ለ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንዲሆኑ እና በጎነትን እና እርስ በርስ የመደጋገፍ ባህልን ለተተኪው ትውልድ በማስረፅ ትውልድ አሻጋሪ እሴቶቻችንን በተግባር በመጠቀም አብሮነትን፣ መረዳዳትንና ሰው ተኮር ተግባራትን ባህል እያደረግን ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር የትምህርት ማህበረሰቡ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል።
"ህብረታችን ለአንድነታችን
አንድነታችን ለሁለንተናዊ ትብብራችንን"
ጳጉሜ 4 የህብር ቀን
(ጷግሜ 4/2018 ዓ.ም) ህብር ማለት የተለያዩ ሰዎች፣ ሀሳቦች፣ ባህሎችና አመለካከቶች ልዩነታቸውን እየጠበቁ በመከባበር፣ በመተባበርና በአንድ ዓላማ ዙሪያ ተሰባስበው አንድ የጋራ ኃይልና ውጤት መፍጠር ነው። ህብር ልዩነትን እንደ እንቅፋት ሳይሆን እንደ ጥንካሬ በመመልከት፣ የእያንዳንዱን አበርክቶ በማክበርና የጋራ ጥቅምን በማስቀደም የተሻለ ማህበረሰብና የተሻለ ነገን ለመገንባት የሚያስችል የአንድነት መርህ ነው።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በህብር የተለያዩ ሕዝቦች፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪኮችና አስተሳሰቦች በአንድ ሀገራዊ ማንነት የሚገናኙባትን ሀገር ናት። የኢትዮጵያ ልዩነቶቿን እንደ ጥንካሬና ሀብት በመቀበል በመከባበር፣ በመተሳሰብና በትብብር የጋራ እጣ ፈንታን መገንባት ችላለች፡፡
ኢትዮጵያ የብዝሃነቷን ቀለም አጥብቃ በመያዝ፣ የጋራ እሴቶቿን በማጎልበትና ሁሉም ዜጎቿ በእኩልነት የሚሳተፉበትን የጋራ ራዕይ በመገንባት ወደ ሰላም፣ አብሮነትና ዘላቂ ልማት የምትራመድ ሀገር ሆናለች።
በህብር ደምቀን የኢትዮጵያን አዲስ ከፍታ እናበስራለን!
የጽናት ቀን
(ጷግሜ 3/2018 ዓ.ም) ኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን የጀግኖቻችንን ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የምንዘክረው፡፡
ዛሬ ላይ ሀገራችን በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ዘመናዊ የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን፣ ከባድ መሣሪያዎችንና መድፎችን፣ እንዲሁም ተተኳሽ ጥይቶችን በራሷ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ማምረት ችላለች፡፡ ይህ በራስ የመቆም አቅም፣ የሕዝባችን ሰላምና የሁለንተናዊ ኢኮኖሚ እድገታችን ጽኑ መሠረት በመሆኑ፣ ሀገራዊ ጽናታችንን በተጨባጭ ልማትና በጠንካራ የመጠበቅና የመከላከል አቅም እያረጋገጥን የኢትዮጵያን ዘላቂ ብልጽግና እናጸናለን!!
+3
በትምህርት ቤታችን የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን መጋቢ እናቶች እያበረከቱት የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በተሳለጠ መልኩ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለመጋቢ እናቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
(ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትምህርት ዘርፋ ልዩ ትኩረት በመስጠት በትውልድ ግንባታ ሂደት ከፍተኛ በጀት በመመደብ ተግባራዊ ያደረገው የምገባ ፕሮግራም የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው።
ይህ ሰው ተኮር ተግባር በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል በትምህርት ቤታችን በማህበር የተደራጁ መጋቢ እናቶች እያበረከቱ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑን እነሱን ማበረታታት እና ማነቃቃት እጅግ ወሳኝ ነው።
የምገባ ፕሮግራሙ ይበልጥ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል የመጋቢ እናቶችን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ሂደቱን ለማሳለጥ ያለመ ሰነድ በማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት ስራ ፣ማህበሩ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለምገባ መርሀግብሩ ስኬታማነት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።
'በእውቀት የዳበረ ትውልድ ግንባታ
ለሀገር ብልፅግና ከፍታ'
+3
"የላቀ ስኬት በላቀ ትጋትና አመራር "
(ጳጉሜ 2/2018ዓ.ም) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት 33ኛውን የትምህርት ጉባኤ "ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች" በሚል መሪ ሀሳብ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና ሰጠ።
ለት/ቤታችን ውድ መ/ራን፣አስተዳደር ሠራተኞች ፣ተማሪዎቻችን ፣የወተመህ አባላት ፣ የተማሪ ወላጆች እንዲሁም አጋር ባለድርሻ አካላት በሙሉ
እንኳን ደስ አላችሁ !እንኳን ደስ አለን!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ2ኛው መንፈቅ ዓመት የትምህርት ቤቶች የቁልፍ ውጤት አመላካች (KPI) እና ሪፎርም ስራዎች አገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አፈፃፀምን መመዘኛ ውጤት በማዘጋጀት ምዘና አካሂዷል። እንዲሁም በ6ኛ ክፍል እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት አፈፃፀም።
በዚህ መሰረት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር ከሚገኙ 35 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል እንደወትሮው በውጤታማነቱና በስኬታማነቱ የሚታወቀው እሸት ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤታችን በከፍተኛ የላቀ አፈፃፀም በክፍለ ከተማ ደረጃ በተዘጋጀው የእውቅናና ሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ እውቅና ተበርክቶልናልና እንኳን ደስ አለን!! እንኳን ደስ አላችሁ!!
ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
👉 የ2018ዓ.ም የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የ8ኛ ክፍል የተማሪዎች ሰርተፍኬት ስለመጣ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ትምህርት ቤቱ
+1
ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበሩ 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶች ይፋ ሆኑ‼
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ተግባራዊ የሚደረጉ 11 የሥራና ተግባር የሙያ ዓይነቶችን ይፋ በማድረግ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የመምህራን ቅጥርን ጨምሮ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላለፈ።
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሙያ ትምህርትን ለማካተት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ በሁለተኛው ዙር ለሚተገበሩት በእነዚህ 11 የሙያ ዓይነቶች የመርሐ ትምህርት፣ የተማሪ ሞጁል እና የመምህራን መምሪያ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።
ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉት 11 የሙያ ዓይነቶች፦
📌ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ
📌አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
📌አልባሳት ቴክኖሎጂ
📌ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት
📌ቧንቧ ስራ
📌ሶፍትዌር ማበልጸግ
📌ሰብል አመራረት
📌ጤና ክብካቤ አገልግሎት
📌ሆቴል አገልግሎት
📌ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት
📌ምግብ ዝግጅት ናቸው።
Repost from Addis Ababa Education Bureau
Beeksisa!
Biiroon Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee Qulqullina Barnoota Bulchiinsa Magaalichaa Keessatti Kennamu Ol Guddisuuf Giddu-Gala Madaallii Saayinsii Moodeela Idil-Addunyaa Uumuudhaan Xiyyeeffannoodhaan Hojjachaa Jira. Haaluma Kanaan, Bara Barnootaa 2019tti Mana Barnoota Waliigalaa Sadarkaa Lammaffaa Misraq Goh Saayinsii Moodeela Idil-Addunyaa Keessatti Barattoota Kutaa 9ffaa Hanga 12ffaa Simatee Barsiisuuf Hojii Qophii Xumuree Jira. Salphaatti, Barattoonni Mana Barnootaa Kana Keessatti Barachuu Barbaaddan, Ulaagaalee Dorgommii Miidiyaalee Hawaasummaa Biiroo Barnootaa Irratti Ibsaman Bu'uura Godhachuun, Liinkii Ibsameen Hanga 8/12/2018 A.L.I.tti Galmaahuu Kan Dandeessan Ta'uu Isinii Beeksifna.
Liinkii Galmee:- https://bs.ministry.et
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
