fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

رفتن به کانال در Telegram

« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

کانال 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 13 938 مشترک است و جایگاه 6 200 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 504 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 13 938 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 11 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -136 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 0 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 22.70% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً N/A% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 168 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 0 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 0 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 12 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

13 938
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-377 روز
-13630 روز
آرشیو پست ها
ከምላስ ይልቅ ተግባር ማንነትን ይገልፃል እዉነተኛ ባልሆነ ማንነታችን ሰዎች ዘንድ መልካም መስሎ ለመታየት ከመጣር ይልቅ እዉነተኛ ማንነትን አዉቆ ለለዉጥ መንቀሳቀስ ነዉ ምንም ጊዜ ቢረዝም ዉጤቱ ግን ታላቅ ነዉ። = t.me/https_Asselefya1

~ጥቂት ክብር የሰጠሀቸው ሰዎች ሥርዓት ስላጡ እስከ መጨረሻው በሌሎች ክብር ሊገባቸው በሚገባ ሰዎች ላይ ድንበር አትለፍ። አንዲት ያወቅካት ሴት ሁሉንም ፍጥረታት አትወክልም። ዋጋቸውን ያላወቁት ስለረከሱ ክብር ትርጉም የለውም ማለት አይደለም። ንፍጣምን ቆንጆ ካልከው ንፍጡን ማምለክ ይጀምራል። እውነቱን ስትነግረው ለመረረው አትጨነቅ። ሁሉም ሰው የኋላውን የሚረዳበት ወደፊት አለው። ስህተቱን መቀበል ካልፈለገ ጋር አትሟገት። ልክ ላደረገው ስህተቱ ተወውና መኖርህን ቀጥል! 

ቲክ-ቶክና ዳዕዋ! ~ ዛሬ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የመረጃና የሃሳብ ልውውጥ ዋነኛ ስፍራ ሆነው ብቅ ብለዋል። ከእነዚህ መካከል ደግሞ ቲክቶክ (TikTok) በተለይ በወጣቶች ዘንድ ያለው ከፍተኛ ተደራሽነት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ነው። ይህ መድረክ ለዳዒዎችና ኡስታዞች ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል፤ ይህም ሱናን ለማሰራጨት፣ ቢድዓን ለማጥፋት፣ ተውሒድን ከፍ ለማድረግ፣ እንዲሁም የደረቁ ልቦችን  ለማርጠብ ትልቅ ዕድል ነው። እነዚህን ዘመናዊ መድረኮች ለአጥፊ ቡድኖችና የጥመት አንጃዎች ብቻ በመተው ዝም ማለት ተገቢ አይደለም። ይልቁንም፣ የእስልምናን ውብት የ ሰለፍያን ትምህርቶች ለሰው ልጆች ለማድረስ በንቃት መጠቀም ያስፈልጋል። ቲክቶክ ለዳዕዋ ያለው የላቀ ጥቅም፦ • ሰፊና ፈጣን ተደራሽነት: ቲክቶክ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያሉት ዓለም አቀፍ መድረክ ነው። በተለይ ወጣቶች ዘንድ ያለው ተመራጭነት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልእክትን ለብዙሃን የማድረስ ዕድል ይፈጥራል። ዛሬ ላይ ትኩረታቸው ለአጭር ጊዜ ብቻ በሚቆይበት ዓለም ውስጥ፣ ይህ እጅግ ጠቃሚ ነው። • አጭርና አሳታፊ ይዘቶች: የቲክቶክ ቪዲዮዎች አጭር በመሆናቸው በቀላሉ ትኩረትን ይስባሉ። መልእክቶችም ሳይሰለቹ በፍጥነት ይደርሳሉ። በዛሬው ፈጣን ዓለም ሰዎች ለረጅም ትምህርቶች ጊዜ ከሌላቸው አንፃር፣ ይህ ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ቲክቶክን ጨምሮ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች መልካምን ለማሰራጨት ከተጠቀሙበት መልካም ናቸው፤ ለጥፋት ከተጠቀሙበት ደግሞ ጥፋት ናቸው። ወደ አላህ መጣራት በአንድ ዘዴ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ ይልቁንም እንደ ጊዜው፣ ቦታውና ሰዎች ይለያያል። ስለዚህ ዳዒዎችና ኡስታዞች ከዘመኑ ጋር የሚሄዱና ለተለያዩ ሰዎች የሚመቹ አዳዲስ ዳዕዋ መንገዶችን መጠቀም ይኖርባቸዋል። ዛሬ ላይ በ አንድ ትልቅ መስጁድ ላይ የማታገኘውን ስብስብ አንድ ሚድያ መድረክ ላይ በ 2 ዲቃቃ ውስጥ ተሰብስቦ ታገኘዋለህ። የጥንቃቄ አስፈላጊነት! • ምንም እንኳን ቲክቶክ ለዳዕዋ ትልቅ አቅም ቢኖረውም፣ ሱስ የመሆንና ጊዜን የማባከን አዝማሚያው ሊታሰብበት ይገባል። ስለዚህ ለዳዕዋ የምንጠቀምበትን ጊዜ መገደብና ለሌሎች ጠቃሚ ተግባራት ጊዜ እንዳይቀንስ ጥንቃቄ ማድረግ ወሳኝ ነው። በመሆኑም፣ ዳዒዎችና ኡስታዞች የዛሬን ዓለም ሁኔታ ተረድተው፣ ያሉትን ዲጂታል መድረኮች በመጠቀም የእስልምናንና የሰለፍያን ውበትና ትምህርቶች ማኅበረሰቡ ዘንድ ማድረስ አለባቸው። ቲክቶክም ሆነ ሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ለጥፋት ቡድኖች ብቻ ተደርጎ መተው የለባቸውም! በጥበብ፣ በጥንቃቄና በታሰበበት መንገድ ጥቅም ላይ ከዋሉ፣ ሱናን ለማሰራጨትና የሰዎችን ልብ ወደ ኸይር ለመሳብ ታላቅ መሳሪያ ሊሆኑ ይችላሉ። ዋናው ቁም ነገር ጊዜያችንን በአግባቡ በመጠቀምና የአላህን ዲን ለማገልገል በመነየት እነዚህን መድረኮች መጠቀም ነው። አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ዲኑን ለመርዳት ለሚነሱ ሁሉ ብርታትን ይስጣቸው! -𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧- |•|t.me/AbuSufiyan_Albenan

መልካም ስነ ምግባር.mp39.40 KB

ኡስታዝ_ሳዳት_ከማል_ሃፊዘሁላህ (1).mp31.42 MB

~ ተግባቢ እና ተናጋሪሰዉ ለመሆን 5 መንገዶች 1" አድማጭ መሆን 2" የሰዉነት ቋንቋ መልመድ 3" የምትናገረዉ ነገር ይኑርህ 4" የምትናገረዉ ነገር ግልፀ እና ቀላል መሆን 5" ስለምንግባባዉ ሰዉ የተወሰነ ነገር ማወቅ = t.me/https_Asselefya1

=ሁሉም ነገር አላፊ ነው ግን አይረሳም የትላንትና ማንነታችን ከለለ ዛሬ ላይ ምንም ነን ካለፈ ህይወታችንጋ ሠላም ፈጥረን ተምረንበት ለማለፍ መሞከር እንጅ ለመርሳት በመታገል ውስጥ እያስታወሡ ሁል ጊ
=ሁሉም ነገር አላፊ ነው ግን አይረሳም የትላንትና ማንነታችን ከለለ ዛሬ ላይ ምንም ነን ካለፈ ህይወታችንጋ ሠላም ፈጥረን ተምረንበት ለማለፍ መሞከር እንጅ ለመርሳት በመታገል ውስጥ እያስታወሡ ሁል ጊዜ ህመምተኛ መሆን ራስን ይጎዳል ራሳችንን የመጎዳት መብት የለንም ሀቋን እንጠብቅላት https://t.me/Sahabaa1344

አላህ ስለሌላዉ ሰዉ ምን እንዳደረገ አይጠይቅህም ይልቁንስ አንተ ምን እንዳደረክ ነዉ የሚጠይቅህ ። =

أسباب_ضياع_صلاة_الفجر_الشيخ_عبدالرزاق_البدر_حفظه_اللهM4A_128K.m4a7.47 MB

እኔ አሁን ድረስ የሚቆጨኝ ፦  ከቤተሰብ ስንጣላ እነሱን የጎዳን እየመሰለን ምግብ አንበላም የምለዉ ነገር......    እኔጋ ብቻ ነዉ ግን ? = منقول

ጓደኛ እንደ መሰላል ነው ወይ ወደላይ ያወጣካል ወይ ወደታች ያስወርድካል ስለዚህ መሰላልክን ምረጥ!! || t.me/https_Asselefya1

ሀምሌ ነዉእኮ .... እንረስ 🖐 በሬዎቹ ግን ሲያሳዝኑ ዝናቡ ዘነበባቸዉ ህእ¡

ጁዝ አመ ለህትመት A4.pdf4.71 MB

በትኩረት በማንበብ ራሳችሁ ፈትሹ ያ ሸባብ ! ማግባት የእግር ኳስ ጨዋታ አይደለም። የጀግንነት መለኪያ አይደለም። በስሜት የሚወሰን ጊዜያዊ ፍላጎት አይደለም። ይልቁንም የቂያም ቀን አላህ ፊት የሚያስጠይቅ ከባድ አደራ ነዉ። 👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ሁለተኛ ማግባት…!? | ~ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ! በአሁኑ ጊዜ በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከአንድ በላይ ሚስቶችን ስለማግባት (ተዐዱድ) የሚፃፈውም የሚወራውም በዝቷል። ይህ ርዕስ በኢስላም የተፈቀደ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ጉዳዩን እጅግ ቀለል አድርገው ሲያቀርቡትና ሲያወሩት ይታያል። አላህ ከ አንድ በላይ ማግባትን በ ቁርኣን የፈቀደው ከአንድ በላይ ማግባትን ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕን አብሮ በመደንገግ ነው። «وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا» «በየቲሞችም (ፍትሕን) አለማድረጋችሁን ብትፈሩ (ከሌሎቹ) ለእናንተ የተዋበላችሁን (ሴቶች) ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ በመካከላቸውም አለማስተካከላችሁን(ፍትህን)ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ የጨበጧትን (ባሪያ) ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡» ይላል። ይህ አንቀጽ የንግግራችን ሁሉ መሰረት ነው። ፍቃዱ ከተሰጠ በኋላ ወዲያውኑ፦ "فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً" (አለማስተካከላችሁን(ፍትህን)ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ያዙ) የሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ ይመጣል። «ብትፈሩ» (خِفْتُمْ) የሚለው ቃል ጥርጣሬንም ይጨምራል። ፍትሕን ስለማስፈኔ እርግጠኛ ካልሆንኩ ወይም ከተጠራጠርኩ፣ መንገዱ አንድ ብቻ ነው።አንድ ብቻ! "فَوَاحِدَةً" 📌ፍትሕ እዚህ ላይ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦ ① የቁሳቁስ ፍትሕ፦ በሚስቶች መካከል በመኖሪያ ቤት፣ በቀለብ፣ በልብስ እና በሌሎችም ቁሳዊ ፍላጎቶች ላይ ፍጹም እኩልነትን ማሳየት። ② የጊዜ ፍትሕ፦ የማደሪያ ጊዜን በሚስቶች መካከል በእኩልነት መከፋፈል።ይህንን የፍትሕ ሚዛን መሳት የሚያስከትለው ቅጣት እጅግ ከባድ መሆኑን ነብያችን (ﷺ) አስጠንቅቀዋል፦ "مَنْ كَانَتْ لَهُ امْرَأَتَانِ فَمَالَ إِلَى إِحْدَاهُمَا جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَشِقُّهُ مَائِلٌ " «ሁለት ሚስቶች ኖረውት ወደ አንደኛዋ (በአያያዝ) ያደላ ሰው፣ የቂያማ ቀን አንደኛው የሰውነቱ ክፍል ሽባ ሆኖ (ተዘምሞ) ይመጣል።» 📚(አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ እና ሌሎችም በሰሂህ ሰነድ ዘግበውታል) እስቲ ለአፍታ ቆም ብለን እናስብ! በዚህ ከባድ ቅጣት ፊት እየቀለድን ነው? የአንዲትን ሀቅ በአግባቡ ሳንወጣ፣ ሁለተኛውን በደል ለመጨመር መሮጣችን ምን የሚሉት ነው። ቆም ብለን እናስብ! ጉዳዩን የስሜት ማብረጃ ሳይሆን፣ ከባድ የዲን አደራ እንደሆነ እንገንዘብ። 📚ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦    "والأفضل مع قيامه بحق الواحدة الاقتصار عليها، وإنما أبيح التعدد لمن احتاج إليه ولم ‏يجاوز العدل" «የተሻለውና በላጩ ሰውየው የአንዷን ሚስት መብት በአግባቡ የሚወጣ ከሆነ በአንዲት ላይ መብቃቃቱ ነው። ከአንድ በላይ ማግባት የተፈቀደው (አስገዳጅ)ፍላጎት ሲኖር እና ፍትሕን የማያጓድል ሲሆን ብቻ ነው።»   📚ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦    "إذا كان الإنسان لا يثق من نفسه بالعدل، أو يغلب على ظنه أنه لا يعدل، فإنه لا يجوز له أن يتزوج أكثر من واحدة، لقوله تعالى: (فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً)، فإذا كان يخاف ألا يعدل، فإن التعدد يكون بالنسبة له حراماً." «አንድ ሰው በራሱ ላይ ፍትሕን የማስፈን ብቃት እንደሌለው ካወቀ ወይም ከጠረጠረ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ለሱ ክልክል (ሀራም) ይሆንበታል። ምክንያቱም ጌታችን አላህ «አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ያዙ» ብሏል። ስለዚህ ፍትሕን መተግበር እንደሚፈራ ካወቀ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ለሱ ሀራም ይሆናል።» ንግግራቸው ግልጽ ነው፤ ፍትሕን የማስፈን ጥርጣሬ ካለ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ወደ ሀራምነት ይሸጋገራል። 📍ከአንድ በላይ ለማግባት ስታስብ ራስህን ልትጠይቃቸው የሚገቡ ወሳኝ ጥያቄዎች ይኖራሉ።ይህንን መንገድ ከማሰብህ በፊት፣ ልብህንና አቅምህን በእውነተኛነት ፈትሽ። የሰዎችን ግፊት ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ጫጫታወችን ወደጎን ትተህ፣ በእጅጉ ከባድ በሆነው የፍትሕ ሚዛን ራስህን መዝን። ① የመነሻ ዓላማዬ ምንድን ነው? • የምፈልገው ስሜቴን ለማርካት፣ በጓደኞቼ ፊት ለመፎከር…ወይንስ ከዚህ የጠለቀ፣ የቲሞችን ለመርዳት፣ ያላገቡ እህቶችን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ በፍትሕ ላይ የተመሰረተ ቤተሰብን ለማስፋት ያለኝ እውነተኛ የሸሪዓ ፍላጎት ነው? ② የመጀመሪያዋ ሚስቴ ሀቅ ሙሉ በሙሉ ተጠብቋል? • አሁን ላለችው ሚስቴ ሙሉ መብቷን—በቀለብ፣ በጤና፣ በመልካም አኑዋኑዋር፣ በስሜታዊ ድጋፍ…በአግባቡ እየሰጠሁ ነው? በሷ ላይ ያለብኝን ሃላፊነት ሳልወጣ፣ ሌላ ከባድ ሃላፊነት ለመጨመር መሞከሬ በደል ላይ በደል መጨመር አይደለምን? ③ ሁለት ቤቶችን በእኩልነት የማስተዳደር የገንዘብ አቅሜ ምን ይመስላል? • ሁለት እና ከዛ በላይ የሆኑ ቤተሰቦችን ያለ ምንም ችግር እና በእኩልነት ለማስተዳደር የሚያስችል የተረጋጋ ገቢ አለኝ? አንዷን እያብቃቃሁ ሌላኛዋን የማስርብ፣ ለአንዷ የተሻለ ቤት ሰጥቼ ሌላኛዋን በችግር የማኖር ከሆነ፣ የቂያማ ቀን ሽባ ሆኜ ከሚቀሰቀሱት እንደማልሆን ምን ዋስትና አለኝ? ④ ሁሉንም በእኩልነት የማስተናገድ የአካል፣ የጊዜ እና የስነ-ልቦና ዝግጁነት አለኝ? • በሁለት ቤቶች መካከል ያለውን ውጣ ውረድ፣ የሁለቱንም ሚስቶች ስሜትና ፍላጎት የማስተናገድ የአዕምሮ ብስለትና ጥንካሬ አለኝ? በሚስቶች እና በልጆች መካከል የሚፈጠሩ ቅናቶችን እና አለመግባባቶችን በፍትሕና በጥበብ የመፍታት ብቃቱስ? ⑤ስለ ፍትሕ ምን ያህል ተምሬአለሁ? • ቁርኣን እና ሐዲስ ስለ ፍትሕ የሚያስተምሩትን ትምህርት በጥልቀት አጥንቻለሁ? የዑለማዎችን ማብራሪያ አንብቤያለሁ? ፍትሕ ማለት በልብስና በምግብ እኩልነት ብቻ ሳይሆን፣ በመልካም ፊት፣ በንግግርና በአያያዝም ጭምር መሆኑን ተረድቻለሁ? እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች ቆም ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል። ምክኒያቱም ከአንድ በላይ ማግባት የእግር ኳስ ጨዋታ አይደለም፤ የጀግንነት መለኪያም አይደለም። በስሜት የሚወሰን ጊዜያዊ ፍላጎትም አይደለም። ይልቁንም፣ የቂያማ ቀን አላህ ፊት የሚያስጠይቅ ከባድ አደራ እና ሃላፊነት ነው። ስለዚህ፣ ጉዳዩን ቀለል አድርገው ከሚያወሩ ሰዎች ንግግር በመራቅ፣ የዲኑን ጥልቅ አስተምህሮ እንረዳ። አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይምራን። ሃላፊነታችንን በአግባቡ የምንወጣና እርሱን በሚያስደስት መልኩ የምንኖር ያድርገን። |•| t.me/AbuSufiyan_Albenan

🔖 ኪታቦች ሲፈልጉ ወደ "ሱቅ በደረቴ" ጎራ ይበሉ «ሁሉም አይነት ኪታብ» ከኛ ዘንድ ያገኛሉ። ╭┈──── ◖🇸🇦◗ ╰┈➢ t.me/suk_bederete123 ​ •┈┈•┈┈•⊰✿🇸🇦✿⊱•┈┈•┈┈•
+5
🔖 ኪታቦች ሲፈልጉ ወደ "ሱቅ በደረቴ" ጎራ ይበሉ «ሁሉም አይነት ኪታብ» ከኛ ዘንድ ያገኛሉ። ╭┈──── ◖🇸🇦◗ ╰┈➢ t.me/suk_bederete123 ​ •┈┈•┈┈•⊰✿🇸🇦✿⊱•┈┈•┈┈• ሳኡድ አረቢያ  ሁሉም ከተሞች እናቀርባለን ​