💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot
نمایش بیشتر📈 تحلیل کانال تلگرام 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
کانال 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 13 807 مشترک است و جایگاه 6 304 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 576 را در منطقه أثيوبيا دارد.
📊 شاخصهای مخاطب و پویایی
از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 13 807 مشترک جذب کرده است.
بر اساس آخرین دادهها در تاریخ 31 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -203 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -8 بوده و همچنان دسترسی گستردهای حفظ شده است.
- وضعیت تأیید: تأیید نشده
- نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 26.55% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 6.00% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب میکند.
- دسترسی پستها: هر پست به طور میانگین 3 665 بازدید دریافت میکند. در اولین روز معمولاً 828 بازدید جمعآوری میشود.
- واکنشها و تعامل: مخاطبان بهطور فعال حمایت میکنند؛ میانگین واکنش به هر پست 0 است.
📝 توضیح و سیاست محتوایی
نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاههای شخصی توصیف میکند:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله
ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot”
به لطف بهروزرسانیهای پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 01 نوامبر, 2026)، کانال همواره بهروز و دارای دسترسی بالاست. تحلیلها نشان میدهد مخاطبان بهطور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کردهاند.
ስለ እራሳችን ስለ ዲናችን በጋራ በመመካከር የተሻለ ማንነት እንፍጠር !
=የእስልምና ሀይማኖት ትክክል መሆኑን ውስጥሽ ተቀብሎታል? ታምኚበታለሽ? ☛መልሷ አዎን! በትክክል ይሆናል። "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም" ማለቷ የዐቂዳዋ መስተካከልን ይጠቁማል። ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ማለቷ ኢስላማዊ ሸሪዓን መቀበሏን ያስገድዳል። ስለዚህ በነዚህ የምስክር ቃሎቿ መሰረት ኢስላምን የህይወት መስመሯ ማድረጓና የእምነቷ ብቸኛ ምንጭ መሆኑን ማፅደቋ ይታወቃል።
⎷ ሁለተኛው፦ ሒጃብ ከኢስላማዊ ድንጋጌዎችናግዴታዎች አይደለም ወይ? ብለን እንጠይቃታለን። ☛ይህች እህታችን አውነትን ለማወቅ እንደሚጥር ሰው ብትመራመርና ከልቧ ጉዳዩን ብታጤነው መልሷ "አዎን ሒጃብ ከኢስላም ግዴታዎች ውስጥ ነው!" የሚል ይሆን ነበር።
☛በአምላክነቱ ያመነችበት አላህ ሒጃብን በመፅሀፉ ውስጥ ግዴታ አድርጓል። በመልእክተኛታቸው ያመነችባቸው የአላህ መልእክተኛም በሱናቸው ውስጥ ሒጃብን ለሴት አማኞች በአጠቃላይ አዘዋል። እስልምና ትክክለኛ እምነት ነው ብሎ ተቀብሎ በውስጥ የሚገኙ ትእዛዛቶችን የማይተገብር ግለሰብን ምን ብለን እንሰይመው?
☞ይህ ግለሰብ በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን አላህ ካወደሳቸው ሰዎች ተርታ አይመደብም እነዚህ ትእዛዙን በመፈፀም ውዳሴ የተገባቸው እውነተኛ አማኞችን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ብሏል፦ "የምእመናን ቃል የነበረው ወደ አላህና ወደ መልእክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ግዜ ሰማንም ታዘዝንም ማለት ብቻ ነው። እነዚህም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው።" አን ኑር 51" ማጠቃለያ፦ ኢስላምን እምነቴ ነው ብላ ከተቀበለች እንዴት ትእዛዙን አትቀበልም?
🛑👉ሁለተኛው ምክንያት፦ ሁለተኛዋ እህት እንዲህ ትላለች ሸሪዓዊ ሂጃብ ግዴታ እንደሆነ አውቃለሁ ነገር ግን እናቴ ትከለክለኛለች እሷን ካልታዘዝኩ ደግሞ አላህ እሳት ያስገባኛል! " ለዚህች እህት የሚሰጠው መልስ የአላህ መልእክተኛ ጥበብ በተሞላው ንግግራቸው የተናገሩትን ነው እሱም "ፈጣሪን በማመፅ ላይ ፍጡርን መታዘዝ የለም" ማለታቸውን ነው። በኢስላም የወላጆች ደረጃ በተለይ የእናት ደረጃ በጣም የላቀ ነው። እንደውም አምላካችን አላህ የተለያዩ ቦታዎች ላይ እሱን በብቸኝነት ማምለክን ለፍጡር የሚያዝበት አንቀፆቹን በማስከተል የወላጆችን ሐቅ አደራ ይላል:- “አላህን ተገዙ በእርሱም ምንንም አታጋሩ በወላጆችም መልካምን ስሩ ... " አላህ በማመፅ ከመታዘዝ ውጪ ወላጆችን በሁሉም ነገር መታዘዝ ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦ "ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው።" ሉቅማን 15 እነሱን በወንጀል ላይ አለመታዘዝ ለእነሱ መልካም መዋልን የሚከለክል ጉዳይ አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል " በቅርቢቱ አለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው።" ማጠቃለያ፦ እናትሽንም አንቺንም የፈጠረውን አምላክ አምፀሽ እንዴት እናትሽን ትታዘዢያለሽ?
ይ
ቀ
ጥ
ላ
ል
=