AASTU-ECSF
رفتن به کانال در Telegram
Evangelical Christian Students' Fellowship at AASTU CBE: 1000656422959 Daniel Kebede and/or Samuel Tesfaye Telebirr: 0931106178 Daniel Kebede Stay tuned via: @galleryaastuecsfBot @souceoflifeBot @AASTU_Anony_Counseling_bot @i4u_contact_bot
نمایش بیشتر4 552
مشترکین
-324 ساعت
+147 روز
+5430 روز
آرشیو پست ها
4 552
#Last_message
³³ ንጉሡም እጅግ ዐዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” ይል ነበር። 2ኛ ሳሙ 18:33👉በዚህ ቁጥር ላይ ዳዊት ነፍሱን በእጅጉ ሲያስጨንቅ በነበረው እና ባሳደደው በልጁ አቤሴሎም ሞት ምክንያት የሀዘኑን ጥልቀት እናያለን። 👉ዳዊት " ምነው ሞቱን በወሰድኩለት " የሚልለትን የልጁን አቤሴሎም ማንነት ለወቀው ግን፤ የዳዊት በዚህ መጠን ማዘን በእጅጉ ግር የሚያሰኝ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም አቤሴሎም ማለት ንግስናን ለመውሰድ ሲል አባቱን በድፍረት ያሳደደ፤ ነፍሱን እስከሞት ያስጨነቀ፤ አባቱን ያከብር ዘንድ እግዚአብሄር ለእስራኤል የሰጠውን ህግ የተላለፈ፤ እናም ይህ እቅዱ ይሳካለት ዘንድ ደግሞ የተሻለውን ምክር ከሌላው ምክር እያስተያየ አባቱን ለመግደል የተቻለው በሙሉ ያደረገ ፀመፀኛ ልጅ ነበር። 👉ታድያ አባቱ ዳዊት እንዴት በዚህ ልክ ያዝንለታል? እንዲያው እፎይ ሊል አይገባውም ነበር ወይ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አንድ ይመስለኛል። ጥልቅ የሆነ የአባትነት ፍቅር እንዲሁም ርኅራሄ!! ይገርማል!! 👉 ይህ አስደናቂ ፍቅር ፣ በብዙ በደላችን ብዛት የማይሻርብንን ብርቱውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዳስብ አደረገኝ። በደልማ ከተባለ የሠማዩን አባታችንን አብልጠን የበደልን እኛ ነን፤ በፀመፅ ብዛት ከመንገድ የራቅን እኛን በፍቅሩ የመለሠ እግዚያብሄር ግን ጥልቅ የአባትነት ፍቅሩ ያስደንቃል። ክርስቶስ በእርግጥም ለኛ ለዓመፀች የተገባንን ሞት ወስዶ በምህረቱ ተቤዠን!! ታዲያ በክርስቶስ የተገለጠው ይህ ፍቅር አያስደንቅም?!! ለኛ ላልተገባን ስለገለጠው ፍቅር እግዚያብሄር ይመስገን!! 👉 ነገር ግን አቤሴሎም እንዲህ የሚወደውን የአባቱን ልብ የራሱን መንገድ ሲከተል አሳዝኖ አለፈ። እኛም ደግሞ የአቤሴሎምን መንገድ መከተል እንዳይሆንብን፤ የአፍቃሪያችንን ልብ የገዛ መንገዳችን በመምረጥ መስበር እንዳይሆንብን ፀጋው ይደግፈን!! ተባረኩ🙌 !! #እግዚአብሔርን_መፈለግ #በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
4 552
#ማስታወቅያ
📌 በቀጣይ ሳምንት ልዩ የበዓል ኦንላይን ፕሮግራም ስላለን፣ ከአሁኑ ጀምራችሁ ጓደኞቻችሁን በመጋበዝ አብራችሁን እንድትገኙ እናሳስባችኋለን!
📌 እንደምታወቀው ባለፈው ሳምንት 2ኛ ሳሙኤልን ከምዕራፍ 17 እስከ 23 አብበን የነበረ ሲሆን፤ በቀጣይ ሳምንት የቀረችውን ምዕራፍ 24 አንብበን የሳሙኤልን መፅሐፍ ንባብ ሙሉ በሙሉ ስለምንጨርስ፣ ሁላችሁም አዘጋጅታችሁ እንድትመጡ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።
📌 ክረምቱ ገብቶ በአካል ቢያራርቀንም ለsmall group ቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ መደወል፣ መጠያየቅ እና እርስ በእርስ መያያዛችሁን እንዳትተዉ አደራ እንላለን።😊
📌 በየሳምንቱ እንደምናደርገው ላልተደረሱ ህዝቦች መጸለያችሁን አትዘንጉ።
📌 በመጨረሻም የትኛውም ዓይነት የጸሎት ርዕስ ያላችሁ ሰዎች በሙሉ ከስር ባለው የFellowship Telegram Account መላክ ትችላላችሁ፦
👉🏼 @aastuecsfcontact 👈🏻
#እግዚአብሔርን_መፈለግ
#በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን
Follow AASTU ECSF On :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
4 552
4 552
#Book_Review
📕 The Case for Christ
✍️ Lee Strobel
ትንሣኤው የኢየሱስን አምላክነት እና ያስተማራቸውን እውነተኛነት የሚያስረግጥ ትልቅ ተአምር ነው።ለዚህ ክረምት የሚሆን ድንቅ መፅሐፍ ይዘንላችሁ መጥተናል። የቀድሞው መርማሪ ጋዜጠኛ ሊ ስትሮብል እውነቱን ለማወቅ ያደረገውን ጥናት እና ያገኘውን ሊካድ የማይችል እውነት በዚህ መጽሐፍ አስፍሮልናል።በዋናነትም በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት፣ አምላክነት፣ ሞት እና ትንሳኤ ላይ ያተኮረ ነው። ከላይ ካቀረብንላችሁ ፊልም ጋር አብሮ የሚሄድ በመሆኑ አሁኑኑ Download አድርገው ያንብቡት! ⬇️ #እግዚአብሔርን_መፈለግ #በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
4 552
#Movie_Recommendation
🎥 The Case for Christ (2017)
እውነቱን ለመፈለግ የወጣ ሰው ወዴት ይደርሳል?
የቀድሞው መርማሪ ጋዜጠኛ ሊ ስትሮብል፣ የክርስትናን እምነት መሰረት ለማፍረስ የታሪክ፣ የህክምና እና የህግ ማስረጃዎችን በመደርደር ያደረገው ጥናት ወዴት መራው?
ከመጽሐፉ ጥቆማችን ጋር አብሮ የሚሄደውን ይህን እውነተኛ ታሪክ መሰረት ያደረገ ድንቅ ፊልም እንድትመለከቱት እንጋብዛችኋለን!
🍿 የፊልሙን Trailer ከላይ ተመልከቱ!
🔗 ሙሉ ፊልሙን ለመመልከት፡
ከፕሮግራማችን ማብቂያ በኋላ ሙሉ ፊልሙን በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ፦ የፊልሙ ሊንክ
#እግዚአብሔርን_መፈለግ
#በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን
Follow AASTU ECSF On :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
4 552
4 552
4 552
#ጥያቄ
1.አኪጦፌል ራሱን በገዛ እጁ አንቆ የሞተበት ምክንያት ምንድነው?
ሀ. ዳዊት ያሴረበትን በማወቁና ሊገድለው በመነሳቱ
ለ. አቤሴሎም ከቤተ መንግስቱ አባሮት እንዲገደል በማሰቡ
ሐ. እግዚአብሔር በቁጣው አስደንገጦት በዳዊት እጅ አሳልፎ ስለሰጠው
መ. ምክሩ እንዳልተሳካለት ባየ ጊዜ
2.ዳዊት የልጁን የአቤሴሎምን መሞት ያወቀው በየትኛው መልእክተኛ ንግግር ነበር?
ሀ. በአኪማአስ
ለ. በኢዮአብ
ሐ. በኢትዮጵያዊው
መ. በአሜሌቃዊው
3.ዳዊት ከአቤሴሎም ሸሽቶ በሄደ ጊዜ ይረግመው የነበረውና ወደ እየሩሳሌም ሲመለስ በዳዊት እግር ስር ተደፍቶ ይቅርታ የጠየቀው ማን ነበር?
ሀ. ሜምፊቦስቴ
ለ. ሳሚ
ሐ. በልአም
መ. አቤሴሎም
4.ሳቤዕ ንጉስ ዳዊት ላይ በማመጹ የደረሰበት ቅጣት ምንድነው?
ሀ. አሜሳይ አሳዶ አንገቱን ቆርጦ ገደለው
ለ. ኢዮአብ ልቡን በጦር ወግቶ ገደለው
ሐ. የቤትመአካ ህዝብ አንገቱን ቆርጠው ለኢዮአብ ሰጡት
መ. ራሱ ዳዊት አሳዶ ይዞት ለሞት ዳረገው
5.ገባኦናውያን የእግዚአብሔርን ርስት ይባርኩ ዘንድ ለዳዊት ማስተሰሪያ ምን ይሁንልን አሉት?
ሀ. ከሳኦል ዘር ሰባት ወንዶች ይሰጡንና እንስቀላቸው አሉት
ለ. ከሳኦልና ከቤተሰቡ ወርቅና ብር እንዲሰጣቸው ጠየቁት
ሐ. ከእስራኤል አንድ ሺህ ወንዶችን ለመግደል ጠየቁ
መ. የሳኦልና የልጁ የዮናታንን ዐጽም እንዲሰጣቸው ጠየቁት
6.በሁለተኛ ሳሙኤል ምዕ23 መሰረት ከተጠቀሱት የዳዊት ሀያላን ሰይፉ እጁ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጤማውያንን የወጋው ማን ነው?
ሀ. አቢሳ
ለ. በናያስ
ሐ. ኤልኤዘር
መ. ሣማ
7. በሁለተኛ ሳሙኤል ምዕ19 መሰረት ዳዊት ወደ እየሩሳሌም ሲመለስ በኢዮአብ ምትክ የሰራዊቴ አዛዥ ባላደርግህ እግዚአብሔር ክፋ ያድርግብኝ ያለው ለማን ነበር?
ሀ. ለአሜሳይ
ለ. ለአበኔር
ሐ. ለኢዮአብ ወንድም አቢሳ
መ. ለሳቤዕ
8.በዳዊት ዘመነ መንግስት ለሶስት ተከታታይ አመታት ረሃብ በነበረበት ወቅት ዳዊት እግዚአብሔርን ሲጠይቅ እግዚአብሔር የሰጠው ምላሽ ምንድን ነው?
ሀ. ህዝቡ ለእግዚአብሔር ከእህላቸው ላይ አስራት መስጠት ስላቆሙ ነው
ለ. በእግዚአብሔር ፊት ዳዊትና ህዝቡ ስላደረጉት በደል ንስሀ ባለመግባታቸው
ሐ. እግዚአብሔር ምንም ምላሽ አልሰጠውም
መ. ሳኦል ገባኦናውያንን ስለገደለ እርሱና ቤተሰቡ የደም ዕዳ ስላለባቸው
9. ከዳዊት ሀያላን መካከል በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ የገደለው እንዲሁም በትር ይዞ በመውጣት አንድ ግዙፍ ግብፃዊ የገደለው ማን ነው?
ሀ. በናያስ
ለ. ዮዳሄ
ሐ. ሳማ
መ. አሣሄል
10.ከዛሬው ቃለ አግዚአብሔር የተማራችሁትን በአጭሩ ግልፁ?
#እግዚአብሔርን_መፈለግ
#በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን
Follow AASTU ECSF On :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
4 552
በመቀጠል ሁላችንም በጉጉት ወደምንጠብቀው እና ወደሚያሸልመው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ነው የምንሄደው 🤩
የጨዋታው ህጎች
1) መቼም ቢሆን የምትልኩትን መልስ Edit ማድረግ በፍጹም አይቻልም።🙅🏻
2)መልሳችሁን የምትልኩት @aastuecsfcontact ላይ ብቻ ሲሆን ከዚያ ውጪ Group ላይም ሆነ በሌላ ስፍራ መላክ ከጨዋታው ውጪ ያደርጋል።
3)Time Up ከተባለ በኋላ መልስ መላክ ዋጋ የለውም።
4) ተስፋ በመቁረጥ አለመሞከር አይቻልም።😁
5) ያላችሁ 15 ደቂቃ ብቻ ነው
መልካም እድል 🙌🏻
መስማማታቹን በReaction ካላሳወቃቹን ጥያቄውን አንለቀውም 😁
#እግዚአብሔርን_መፈለግ
#በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን
Follow AASTU ECSF On :
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
4 552
እሺ ቅዱሳን አሁን ደግሞ በኪሳችን... ማነው በመስጠት😁 የምናገለግልበት ጊዜ ነው... ስለዚህ በልግስና እንድትሰጡ ይሁን 🙏
ተባረኩልን
4 552
4 552
