fa
Feedback
Hakim

Hakim

رفتن به کانال در Telegram

Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Hakim

کانال Hakim (@hakimethio) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 62 161 مشترک است و جایگاه 229 را در دسته پزشکی و رتبه 518 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 62 161 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 22 ژوئیه, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 1 036 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 27 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 10.20% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 7.47% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 6 338 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 4 642 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 49 است.
  • علایق موضوعی: محتوا بر موضوعات کلیدی مانند patient, ethiopia, disease, ነው።, medicine تمرکز دارد.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 23 ژوئیه, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

62 161
مشترکین
+2724 ساعت
+1867 روز
+1 03630 روز
آرشیو پست ها
Hakim
62 161
ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ | Gad bu’uu dhabuu cidhaanii | Undescended Testis ፍቺ፡- ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ ማለት አንድ ወይም ሁለቱም የወንድ የዘር ፍሬዎች ወደ
+2
ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ | Gad bu’uu dhabuu cidhaanii | Undescended Testis ፍቺ፡- ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ ማለት አንድ ወይም ሁለቱም የወንድ የዘር ፍሬዎች ወደ ከረጢቱ ውስጥ ሲወለዱ ወይም ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወደ ከረጢቱ አለመውረድ ነው። ምክንያት:- በእርግዝና ወቅት የወንድ የዘር ፍሬዎች በሆዱ የጀርባ ክፍል ውስጥ ይፈጠራሉ:: እርግዝና እየገፋ ሲሄድ ፍሬዎቹ ወደ ታች ይወርዳሉ። ይህ ሂደት ካልተሳካ, ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬን ያስከትላል:: እንዴት እንደሚታወቅ፡- ቤተሰቡ የጾታ ብልትን በመመርመር ብቻ ችግሩን ማወቅ ይቻላል። ከረጢቱ ውስጥ አንድ ወይም ሁለቱም የወንድ የዘር ፍሬዎች ከሌሉ ይህ ምናልባት ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ ነው እና የሃኪም ምክር ያስፈልገዋል። መፍትሄው ምንድን ነው:- በወሊድ ጊዜ ከታወቀ እስከ 6 ወር ድረስ ክትትል ሊደረግበት ይችላል. ከ 6 ወር በላይ የሚቆይ ከሆነ በቀዶ ህክምና ወደቦታው መመለስ ያስፈልጋል። ካልታከሙ ምን ያስከትለል:- ü መካንነት ሊያስክትል ይችላል፦ በተለይ ሁለቱም ፍሬ ያልቦታቸው ከሆኑ እና ሕክምናው ከዘገየ ü የዘር ፍሬ ካንስር የመያዝ እድሉ ከፍ ይላል ü የዘር ፍሬው ደም ስር ሊዞር ይችላል (testicular torsion) ü ለኣደጋ ይጋለጣል ü የዘር ፍሬ መጠን ይቀንሳል ü ለ ቡአ/ inguinal hernia የተጋለጡ ናቸው ü በልጁ ላይ እያደጉ ሲሄዱ የስነ-ልቦና ተፅእኖ ማምጣት ይችላል። Hiika: Gad bu’uu dhabuu cidhaanii jechuun cidhaan gara tokkoo yookaan lamaan isaayyuu korojoo cidhaanii (scrotum) keessatti kan hin argamne jechuudha. Akkamiin uuma? - Kunis kan uumamu yeroo daa’imni dhiiraa tokko garaa hadhasaa keessa jiru; Cidhaan kan uumamu garaa daa’immichaa keessatti. Ammuma umuriin ulfaa dabalaa adeemu micireen cidhaanii kun gad bu’uun korojoo isaa (scrotum) keessa buufata. Gaafa daa’imni dhiiraa dhalatu daa’imman baay’ee keessatti bakka saatti gad bu’ee argama. Daa’imman muraasa keessatti garuu erga dhalatanii yeroo muraasa keessatti gad bu’a. Kunis ji’oota jalqabaa jahan keessatti jechuudha. Akkamiin baramuu danda’ama? - Maatiin qaama ijoollee ilaalanii yoo cidhaan tokko yookaan lachuu hin jirre gara ogeessa fayyaa geessanii ilaalchisuu qabu. Yaalli isaahoo maali? - Cidhaan umurii ji’a ja’atti gad hin buune taanaan yaala baqaqsanii yaaluun sirreeffamuu barbaachisa. Yoo hin yaalamne rakkoo maalii geessisa? - Daa’imman cidhaan isaanii gad hin buune rakkoo garaa garaaf saaxilamu. Isaan keessaa murasni: ü Hammi dhala godhachuu isaanii ni hir’ata, keessattu gara lachuun yoo ta’ee. Akkasumas osoo hin yaalamiin yoo ture. ü Hangi (volume) cidhaanii hir’achaa adeema. ü Carraa kaansariin cidhaaniin qabamuu isaanii ni dabala ü Bu’a/inguinal hernia/ qabaachuu malu ü Ofirra miciiramuu cidhaaniif /Testicular torsion/ saaxilamoodha. ü Cidhaan korojoo isaan ala jiru balaa garaa garaan midhamuu danda’a ü Xiinsammuu daa’imaa irratti dhiibbaa qaqqabsiisuu mala v Kanaaf yaala yeroo isaa eeggate argachuun furmaata waalta’a ta’a. Dr. Tafese Gudissa: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም : Ispeshaalistii baqaqsanii yaaluu daa’immanii 📞 +251919399329 @HakimEthio

Hakim
62 161
በኦቲዝም ዙሪያ ለቀረበው ጽሑፍ እይታዬን ለማጋራት ወደድኩ የቀረበው ጽሑፍ በኦቲዝም ዙሪያ ያለውን ሳይንሳዊ እና ታሪካዊ እውነታ በተሳሳተ መንገድ ቀልቦ፣ ማህበረሰባዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጠቀሜታውን ችላ
+2
በኦቲዝም ዙሪያ ለቀረበው ጽሑፍ እይታዬን ለማጋራት ወደድኩ የቀረበው ጽሑፍ በኦቲዝም ዙሪያ ያለውን ሳይንሳዊ እና ታሪካዊ እውነታ በተሳሳተ መንገድ ቀልቦ፣ ማህበረሰባዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጠቀሜታውን ችላ በማለት የቀረበ ድምዳሜ ላይ የተመሠረተ ነው። የቀረበውን arguments በበሰለ ሳይንሳዊ፣ ማህበረሰባዊ እና ባህላዊ እይታ በዝርዝር እስኪ እንየው። የስሑት እይታዎች ትችት እና ሳይንሳዊ ሙግት የቀረበው ጽሑፍ «በታሪክ ውስጥ የነበሩ ታዋቂ ሰዎችን ከኦቲዝም ጋር ማያያዝ ሳይንሳዊ አይደለም» በሚል መነሻ የሚያቀርበው ሙግት የሕክምና ታሪክን፣ የስነ-አእምሮ እድገትን እና የወላጆችን ስነ-ልቦናዊ ተስፋ የመገንባት ተልዕኮን በውል ካለመረዳት የሚመጣ ነው። ፩. የዲያግኖሲስ ታሪካዊ አመጣጥ እና የቁሳዊ ምርመራ አለመኖር (Diagnostic History & Absence of Biomarkers) የጽሑፉ አቅራቢ «ኦቲዝም በሕክምና፣ በምርመራ፣ በሳይንሳዊ ሒደት የሚረጋገጥ ነው» በሚል ያስቀመጠው ድምዳሜ መሠረታዊ የስነ-አዕምሮ ሕክምናን (Psychiatry) መርህ ይቃረናል፡ ምንም ዓይነት የደም፣ የላቦራቶሪ ወይም የሬዲዮሎጂ ምርመራ የለውም፡ ኦቲዝም እንደ ደም ብዛት፣ ስኳር ወይም ካንሰር በላቦራቶሪ ምርመራ (Medical Biomarker) የሚረጋገጥ ሕመም አይደለም። የኦቲዝም ማረጋገጫ (Diagnosis) የሚሰጠው የባህሪ፣ የመግባባት እና የማህበራዊ ግንኙነት ምልከታዎችን (Behavioral Criteria) መሠረት በማድረግ ብቻ ነው። የታሪክ እና የስያሜ ዘግይቶ መምጣት፡ የኦቲዝም ስያሜ እና የምርመራ መስፈርት (Diagnostic Criteria) የተደራጀው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ (በተለይም ከ1980ዎቹ ወዲህ በDSM ስርዓት) ነው። ነገር ግን ስያሜው ከ1980ዎቹ በፊት አለመኖሩ፣ ከዚያ በፊት የነበሩ ሰዎች የኦቲዝም ባህሪያት አልነበራቸውም ማለት አይደለም። እንደ አልበርት አንስታይን፣ አይዛክ ኒውተን ወይም ሞዛርት ያሉ ከ200 እና 300 ዓመታት በፊት የነበሩ ሊቃውንት የኦቲዝም መገለጫ የሆኑትን ባህሪያት (Autistic Traits) በግልጽ ያሳይ እንደነበር የታሪክ ሰነዶች ያረጋግጣሉ። ፪. በታሪካዊ ግለሰቦች ላይ የሚታዩት የኦቲዝም ባህሪያት (Autistic Traits in Historical Figures) እንደ Behavioral Innovations ባሉ መሪ የበህሪ ምርመራ እና ድጋፍ ሰጪ ተቋማት የጥናት ሰነዶች ላይ እንደተጠቀሰው፣ ታሪካዊ ሰዎችን ከኦቲዝም ጋር ማያያዝ በዘፈቀደ ተረት ሳይሆን በታሪካዊ የባህሪ ማስረጃዎች ላይ የተመሠረተ ነው፦ አልበርት አንስታይን (Albert Einstein): እስከ 3 እና 4 ዓመቱ ድረስ አለመናገሩ (Delayed Speech)፣ አንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት የማድረግ (Repetitive and restrictive behavior) እና የማህበራዊ ግንኙነት (Social skill deficit) ፈተናዎች ነበሩበት። ሞዛርት (Mozart): የተወሰኑ ተደጋገሚ የእጅና የሰውነት እንቅስቃሴዎች (Stereotyped Movements)፣ ለድምፅ ያለው ከፍተኛ ስሜታዊነት (Sensory Sensitivity) እና ማህበራዊ የግንኙነት ድክመቶች ነበሩበት። ኤሚሊ ዲኪንሰን (Emily Dickinson): ከተለመደው ማህበራዊ ህይወት መገለል፣ ለስሜት ህዋሳት አነቃቂዎች (Sensory Stimuli) ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እና በብቸኝነት ስራ ላይ ብቻ ማተኮር። ሚካኤል አንጄሎ (Michelangelo) እና ሰር አይዛክ ኒውተን (Sir Isaac Newton): በሰራቸው ስራዎች ላይ ያለው አባዜ ያዘለ የዝርዝር ትኩረት (obsessive attention to detail in his work) እና ከሰዎች ጋር የመቀራረብ ከፍተኛ ፍርሃት/ችግር። እነዚህን ሰዎች በወቅቱ «ኦቲዝም» የሚል የህክምና ካርድ አልተሰጣቸውም በሚል ምክንያት የኦቲዝም ባህሪያቸውን መካድ ሳይንሳዊ ፍትሃዊነት አይደለም። ታዋቂ ሰዎችን መጥቀስ ያለው ማህበረሰባዊ እና ስነ-ልቦናዊ ፋይዳ በእኛ ባህልና ማህበረሰብ ውስጥ «አእምሮአዊ ወይም የዕድገት መዛባት» ያለባቸው ልጆች ሲወለዱ በብዙ ወላጆች ዘንድ የሚፈጠረው የመጀመሪያው ስሜት ተስፋ መቁረጥ፣ ብቸኝነት እና ጥልቅ የልብ ስብራት ነው። ያለው ጠቀሜታ እንመልከት፦ ፩. የተስፋ ጭላንጭል ማሳየት (Inspiring Hope and Resiliency): ወላጆች የልጆቻቸውን ፈተና እና የተግባቦት እክል በደንብ ያውቃሉ። ታዋቂ ሰዎችን መጥቀስ «ኦቲዝም ቀላል ነው» ለማለት ሳይሆን፣ «ልጆቻችን ተገቢውን ድጋፍ፣ ፍቅር እና የመማር እድል ካገኙ የትም መድረስ ይችላሉ» የሚል ተስፋን ለመስጠት ነው። ፪. የማህበረሰቡን የተዛባ አመለካከት/ስቲክማ መስበር (De-stigmatization): በባህላችን ውስጥ ያሉትን አሉታዊ አመለካከቶች ለመቀየር የልጆቹን ድክመት ብቻ ሳይሆን የሚደነቅ እምቅ አቅማቸውን (Strengths-based approach) ማሳየት ወሳኝ ተልዕኮ ነው። በዘመናዊ የኦቲዝም ባለቤቶች የተረጋገጠ እውነት፡ በአሁኑ ዘመን በህክምና የተረጋገጠላቸው እንደ ኤሎን መስክ (Elon Musk)፣ ሰር አንቶኒ ሆፕኪንስ (Sir Anthony Hopkins)፣ ዳን አክሮይድ (Dan Aykroyd) እና ቴምፕል ግራንዲን (Temple Grandin) ያሉ ሰዎች መኖራቸው፣ በታሪክ የነበሩትም (predecessors) እንደነበሩ በግልጽ ያሳያል። ማጠቃለያ በቀረበው ጽሑፍ ላይ «ሳይንሳዊ አይደለም» በሚል የቀረበው ክርክር የህክምና ታሪክን ክፍተት (Historical Diagnostic Void) ካለመረዳት የመጣ ነው። ኦቲዝም በሳይንስ የላቦራቶሪ ውጤት ሳይሆን በባህሪ የሚለይ በመሆኑ፣ ታሪካዊ ሰዎችን በባህሪያቸው መነሻነት መጥቀስ ሙሉ በሙሉ ምክንያታዊ እና አሳማኝ ነው። ከሁሉም በላይ ግን፣ እነዚህን ታዋቂ ሰዎች መጥቀስ ለወላጆችና ለቤተሰብ ጥንካሬን የሚሰጥ፣ የልጆቻቸውን አቅም በበጎ መንገድ እንድናይ የሚያስችል እና ወላጆች በፅናት ልጆቻቸውን እንዲደግፉ የሚያነሳሳ ማህበረሰባዊ ብርሃን ነው። አመሰግናለሁ። References 1. www https://academy.theibao.com/course/autism-spectrum-disorders 2. https://www.biermanautism.com/resources/blog/10-famous-people-with-autism-spectrum-disorder-asd/ 3. https://behavioral-innovations.com/blog/20-famous-people-with-autism-spectrum-disorder-asd/ George Yehish: Psychologist, International Behavior Analyst candidate @HakimEthio

Hakim
62 161
"እነዚህ ምስሎች ሰቆጣ ወረዳ 020 እና 023 ዋግ ኽምራ የተነሱ ናቸው:: በየመድረኩ "አንዲትም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም" በሚል አዳራሹ እስኪናጋ ሲደሰኮር ይዋላል። ለእናቶችና ህጻና
+3
"እነዚህ ምስሎች ሰቆጣ ወረዳ 020 እና 023 ዋግ ኽምራ የተነሱ ናቸው:: በየመድረኩ "አንዲትም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም" በሚል አዳራሹ እስኪናጋ ሲደሰኮር ይዋላል። ለእናቶችና ህጻናት ተብሎ የመጣ አንቡላንስ ለምንድን ነው በትክክል አገልግሎት የማይሰጠው? ለምንስ ለሌላ አገልግሎት ይውላል? እስከ መቼስ ነው የአንዲት እናት ሕይወት ከጥቂት ሊትር ናፍጣ በታች የሚገመተው? እስከ መቼ ነው በዋዛ ፈዛዛ እንዲህ አይነት ስህተቶች የሚቀጥሉት?" ‐ አስመላሽ ከሰቆጣ @HakimEthio

Hakim
62 161
Discussion In injuries characterized by severe deformity, such as complete spondyloptosis with anterior telescoping of the T7 vertebral body over T8, a combined anterior and posterior approach would traditionally be considered to restore anterior column support and facilitate reduction. However, combined approaches carry a substantially higher risk of complications, including pulmonary morbidity, persistent pleural effusion, hemothorax, chylothorax, dural-pleural fistula, major vascular injury, intercostal neuralgia, and chronic post-thoracotomy pain. Conversely, posterior reduction and stabilization without addressing the anterior defect may increase the risk of loss of reduction, hardware failure, and pseudoarthrosis. In patients with complete paraplegia, as in this case, a single-stage posterior vertebral column resection with spine shortening offers several important advantages. It avoids the morbidity associated with an anterior thoracic approach while allowing direct apposition of healthy vertebral endplates following vertebral shortening. Compression across these endplates promotes excellent anterior column reconstruction and interbody fusion without the need for structural grafts or cages. Combined with long-segment posterior fixation, this technique provides a stable construct, allowing immediate spinal stability and early mobilization. Because vertebral shortening eliminates the anterior defect, an additional anterior procedure is unnecessary. However, in patients with incomplete neurological injury, vertebral shortening exceeding the average segmental height of a thoracic vertebral body is generally discouraged, as excessive shortening may increase the risk of neurological deterioration. Conclusion This successful case demonstrates that complex spinal reconstruction using single-stage posterior vertebral column resection and spine shortening can be safely performed in carefully selected patients, even within a resource-limited setting. The procedure provided excellent deformity correction, stable fixation, and early mobilization while avoiding the additional morbidity associated with combined anterior-posterior surgery. This landmark achievement marks the beginning of yet another chapter in the advancement of neurosurgical care in Puntland, Somalia. Our sincere appreciation goes to the anesthesia team, operating room staff, intensive care team, and all healthcare professionals at Arafat International Hospital, whose dedication, professionalism, and teamwork made this milestone possible. Dr. Mohammed Omar (Dr. Rooble) Consultant Neurosurgeon at Arafat International Hospital, Puntland, Somalia @HakimEthio

Hakim
62 161
Ethiopian trained Neurosurgeon performs successful vertebral column resection and spine shortening in the nanagement of a rare case of severe thoracic fracture-dislocation in Puntland, Somalia Total vertebral column resection (VCR) with spine shortening through a single-stage posterior approach has been widely described in the management of congenital, infectious, tumoral, and other spinal deformities. It has also been utilized in patients with chronic progressive post-traumatic kyphosis presenting with pain or neurological deficits. However, only a limited number of cases have been reported in which acute thoracic fracture-dislocations were managed successfully using a single-stage posterior vertebral column resection and spine shortening procedure. At Arafat International Hospital in Puntland, Somalia, we successfully performed a single-stage posterior vertebral column resection and spine shortening for the reduction and stabilization of a severe T7–T8 fracture-dislocation. This achievement represents a significant milestone in expanding access to advanced neurosurgical care and the management of complex spinal disorders in this resource-limited region. It offers new hope to patients who previously had few or no treatment options. Case Presentation A 35-year-old man presented to our center five days after accidentally falling into a pit approximately six meters deep. Immediately following the injury, he developed complete loss of sensation below the abdomen and was unable to move either lower extremity. On arrival, the patient was in severe pain and cardiorespiratory distress. His vital signs were as follows: pulse rate 88 beats/min, blood pressure 75/50 mmHg, respiratory rate 29 breaths/min, and oxygen saturation 79% on room air. Physical examination revealed absent air entry over the posterior lower two-thirds of lung fields, marked mid-thoracic tenderness, and a visible step-off deformity. Neurological examination demonstrated complete paraplegia with motor power of 0/5 in both lower extremities. Sensory level was approximately at the xiphisternum. Anal tone was absent, and the bulbocavernosus reflex was absent, consistent with complete spinal cord injury associated with spinal shock. Computed tomography (CT) of the thoracic spine demonstrated complete T7–T8 fracture-dislocation with spondyloptosis. The T7 vertebral body had telescoped anterior to T8, with complete destruction of the posterior spinal elements at these levels. The patient also had bilateral hemopneumothorax. Initial Management During the first five days following admission, management focused on hemodynamic and respiratory stabilization. Bilateral chest tubes were inserted to treat the hemopneumothorax. The patient received blood and blood product transfusions and required vasopressor support, which was successfully weaned as his condition improved. Surgical Management On the fifth day after trauma, the surgical team led by Dr. Mohammed Omar (Dr. Rooble), Consultant Neurosurgeon at Arafat International Hospital, performed a T8 vertebral column resection with spine shortening through a single stage posterior approach. Excellent reduction of the deformity was achieved without the need for anterior column reconstruction. Endplate was prepared and morselized cancellous bone from resected T8 vertebra was packed in to T7/T9 space. Intraoperatively, the spinal cord was found to be completely transected with an associated cerebrospinal fluid (CSF) leak. The thecal sac was ligated, and the CSF leak was controlled. Long-segment posterior instrumentation extending four vertebral levels above and three levels below the injury (T4-T11) was performed to provide robust stabilization. The patient tolerated the procedure well. His chest tubes were subsequently removed, and wheelchair mobilization was initiated on the first postoperative day.

Hakim
62 161
photo content
+5

Hakim
62 161
Farewell Reflections After More Than Forty Years of Service Dear Colleagues, Alumni, Students, Friends, and College of Health
+3
Farewell Reflections After More Than Forty Years of Service Dear Colleagues, Alumni, Students, Friends, and College of Health Sciences Family, I write this letter with gratitude, humility, and hope as I conclude more than four decades of service in patient care, medical education, leadership, and research at our beloved institution. When I entered the School of Medicine as a young Ethiopian, I could not have imagined the remarkable journey that lay ahead. Medicine became more than my profession — it became my life's calling. Every patient I treated, every lecture, bedside seminar, and tutorial I took part in, every operation I performed, and every resident and fellow I mentored enriched my life far more than I could ever have anticipated. It has been one of the greatest privileges of my life to watch young learners become compassionate physicians, skilled surgeons, respected teachers, accomplished researchers, and visionary leaders. This has been the most enduring reward of my career. I believe I have contributed, even in a small way, to the success of those who now serve patients and lead academic work across Ethiopia and around the world. I consider my career richly blessed. Serving as a leader within my unit, department, and the Faculty of Medicine was both an honor and a profound responsibility. Together with dedicated colleagues and staff, we worked to strengthen tertiary health care, expand graduate training programs, foster research, and deliver a high standard of care to our patients. We also helped develop faculty for other medical schools in Ethiopia and beyond — the result of a shared vision, mutual respect, and unwavering commitment among the College's staff, even amid scarce resources. To my teachers, I am grateful for believing in me and shaping me into a professional, a scholar, and a servant leader. To my colleagues, thank you for your enduring friendship and shared commitment, including the memorable surgical outreach missions and society activities we undertook together. Your wisdom and partnership through moments of joy, challenge, and triumph have meant more than words can express. To the nurses, technicians, administrative staff, and every member of our health care team, thank you for the dedication and kindness that made our work possible through the years. To my students and trainees, you have been my greatest joy. I leave with immense pride, knowing that you now carry forward the noble tradition of our profession. Above all, I offer my deepest gratitude to our patients and their families for placing your trust in me during moments of fear, uncertainty, and hope. Caring for you has been the greatest privilege of my professional life, and it has reminded me daily that medicine is not only a science but also an act of compassion and humanity. Though I am stepping away from my formal responsibilities, my faith in the future of Ethiopian medicine has never been stronger. I see extraordinary promise in the next generation of physicians and surgeons. Continue to pursue excellence with integrity, lead with humility, embrace lifelong learning, and never lose sight of the human being behind every diagnosis. Our College of Health Sciences and Department of Surgery have been more than a workplace to me — they have been my academic home and an extended family. It has been an honor to be part of this community, and I believe our brightest days are still ahead. To my family, whose love, patience, and sacrifice sustained me through countless long days, sleepless nights, and emergency calls across the years — thank you, and God bless you. May God bless each of you, bless AAU College of Health Sciences, bless our patients, and bless Ethiopia. With profound gratitude and warm regards, Dr. Dereje Gullelat @HakimEthio

Hakim
62 161
Giant mandibular mass excision performed at Ciro General Hospital. This is a 25 years old male patient presented to our OPD w
+9
Giant mandibular mass excision performed at Ciro General Hospital. This is a 25 years old male patient presented to our OPD with the compliant of right lower face swelling of 5 years duration which was slow growing and painless. Recently, the patient had tried to cure it with traditional medication following which the swelling became infected and started to discharge pus with sinus tract formation. During our evalution the swelling extended to the condayl and coronoid with buccolingual expansion. CT scan showed a large right side manduibular mass which is radiolucent and multiple site perforation of the bucall cortex. With a diagnosis of an anurysmal bone cyst segmental, resection with disarticulation and reconstruction with recon-plate was performed, and the patient currently has a smooth post op course. Team members Surgeon: Dr. Yohannes H/mariam, Maxillofacial Surgeon Scrub: Sr. Alem Runer: Sr. Zufan Anesthesia: Abdulaziz Anastasia: Abel [Written consent obtained for use of pictures and history] @HakimEthio

Hakim
62 161
Case of the day Patient profile • 35-year-old G7P6 (gravida 7, para 6) presenting with unknown last normal menstrual period (
+5
Case of the day Patient profile • 35-year-old G7P6 (gravida 7, para 6) presenting with unknown last normal menstrual period (LNMP) and two months of amenorrhea Imaging • Transvaginal sonography (as seen in the video below) demonstrates Intrauterine findings • A gestational sac containing a yolk sac and a developing fetal pole with out cardiac activity, confirming an early intrauterine pregnancy Adnexal indings • A cystic structure approximately 5cmx5cm is visualized in the adnexa • This cyst contains low-level internal echoes and a distinct, irregular, highly echogenic (bright) focus and attached to the cyst wall. It has no flow on color doppler What are your top differentials and plan of action? Drop your expert opinions in the comments Dr. Rahmet Bedru: Assistant Professor of Obstetrics and Gynecology at Dilla University Teaching Hospital @HakimEthio

Hakim
62 161
ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት የሕክምና ዶክተሮች አሉ? ወደ 20,000 ገደማ። ይሄም 0.15 ሐኪም ለ1,000 ሰዎች ማለት ነው። የሚመከረው መጣኔ 2.3 ለአንድ ሺህ ሰዎች ነው። Ok, 2 ሐኪም ለ 1,000
ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት የሕክምና ዶክተሮች አሉ? ወደ 20,000 ገደማ። ይሄም 0.15 ሐኪም ለ1,000 ሰዎች ማለት ነው። የሚመከረው መጣኔ 2.3 ለአንድ ሺህ ሰዎች ነው። Ok, 2 ሐኪም ለ 1,000 ጥሩ ነው ብለን እናስብ። እዚህ ላይ ለመድረስ አሁን ያሉንን የሐኪሞች ቁጥር በ13.33 እጥፍ መጨመርና 266,000 ሐኪሞች መድረስ አለብን። ይህ ቁጥር ራሱ የሕዝብ ቁጥራችን ከ130 ሚሊየን በላይ አያድግም ብለን አስበን ነው። በብዙ ምክንያቶች በተለይ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ሕክምና ለማጥናት ፍላጎት የሚያሳየው ተማሪ ቁጥር እየቀነሰ ይመስለኛል። (በእርግጥ በጥናት የተደገፈ ነገር የለኝም)። ባልተለመደ ሁኔታ በሜዲካል ሳይንስ የተመረቁ ወጣቶች ሕክምናውን ትተው ወደ ሌላ ቢዝነስ መግባት የጀመሩም አሉ። አገር ጥለው ለመሔድ ልባቸው የተንጠለጠለውንም ጨምሩበት። እና የሐኪሞች ቁጥር እንዳይቀንስ አትሰጉም? Assume that ያሉት ሐኪሞች ሁሉ ደመወዝተኞች ናቸው እንበል። የሐኪሞች ደመወዝ ዝቅተኛው 60,000 ብር ከፍተኛው 80,000 ብር ቢሆን ቅር የሚለው አለ? የለም! በአማካይ 70,000 ብር ቢሆን X 12 ወራት X 20,000 ሐኪሞች = የዓመት ደመወዝ 16.8 ቢሊየን። በዚህ ዓመት በሙስና ያጣነው almost 100 ቢሊየን። እና 50 ፐርሰንት ሙስናዎችን በየዓመቱ ማስቀረት ብንችል ሌላ ተጨማሪ ወጪ ሳይጠይቅ የ3 ዓመት ከምናምን የሐኪሞችን ደመወዝ መሸፈን እንችል ነበር። ያለምንም የበጀት ጫና! ተጨማሪ በጀት ቢያስፈልግ እንኳን 16.8 ቢሊየን ምን አላት? Non-productive ለሆኑ ነገሮች ከምናወጣው ወጪ አንፃር? እ? ጤናው የተጠበቀ ዜጋ ያላት ሐገር በሁሉም ረገድ አትራፊ ናት። -------------------------- ማሳሰቢያ: - ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን አላካተትኩም። - ቁጥሮቹ በኔ assumption ብቻ የተሰሉ ናቸው። ጥናት ወሳኝ እንደሆነ እርረዳለሁ። - 'ሐኪሞች ብቻ ለምን? እኛስ' የሚሉትን ከግምት አላስገባሁም። ሁሉም ሙያ fair ክፍያ ቢገባውም ከሕክምና ጋር ማወዳደር ተገቢ ነው ብዬ አላስብም። Priority! በሐውለት አህመድ (ፒኤች ዲ) @HakimEthio

Hakim
62 161
The Surgical Society of Ethiopia, in collaboration with Fortis Healthcare, India, is pleased to invite you to an in-person CP
The Surgical Society of Ethiopia, in collaboration with Fortis Healthcare, India, is pleased to invite you to an in-person CPD session on *Latest Advances in Gastrointestinal and Oncology Surgery.* Learn from Dr. Neeraj Chaudhary, Senior Director & Head of GI, GI Oncology, Minimal Access & Bariatric Surgery at Fortis Hospital, Vasant Kunj, India, as he shares the latest evidence, innovations, and best practices shaping modern GI and oncology surgery. 📅 20 July 2026 🕔 5:00 PM EAT onwards 📍 Best Western Plus Addis Ababa (Next to Edna Mall) 🎓 2 CEU Points Take advantage of this opportunity to engage directly with an internationally renowned expert, network with fellow healthcare professionals, and earn CEU credits. *Register today and join us!* https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSduCtAYNyatVoVRnLHZ0KWixtutSHs6t_IvQPIkjuuez60dXw/viewform?usp=sharing&ouid=109728140181241474841 #SurgicalSocietyOfEthiopia #SSE #FortisHealthcare #CME #InPersonCME #GeneralSurgery #GIOncology #MedicalEducation

Hakim
62 161
Case of the day Patient profile • 35-year-old G7P6 (gravida 7, para 6) presenting with unknown last normal menstrual period (
+5
Case of the day Patient profile • 35-year-old G7P6 (gravida 7, para 6) presenting with unknown last normal menstrual period (LNMP) and two months of amenorrhea Imaging • Transvaginal sonography (as seen in the video below) demonstrates Intrauterine findings • A gestational sac containing a yolk sac and a developing fetal pole with out cardiac activity, confirming an early intrauterine pregnancy Adnexal indings • A cystic structure approximately 5cmx5cm is visualized in the adnexa • This cyst contains low-level internal echoes and a distinct, irregular, highly echogenic (bright) focus and attached to the cyst wall. It has no flow on color doppler What are your top differentials and plan of action? Drop your expert opinions in the comments Dr. Rahmet Bedru: Assistant Professor of Obstetrics and Gynecology at Dilla University Teaching Hospital @HakimEthio

Hakim
62 161
The power and health benefits of FORGIVNESS It is difficult to build a healthy society if we don't proceede with FORGIVNESS.
The power and health benefits of FORGIVNESS It is difficult to build a healthy society if we don't proceede with FORGIVNESS. FORGIVNESS is a sign of high emotional intelligence and high intellectual capacity to supress and control the instinctual urge and desire to attack back the wrong doer. FORGIVNESS has great power. It can liberate and heal two souls at the same time: The forgiver and the forgiven. As human beings we are all prone to making mistakes. Therefore, the door for FORGIVNESS should never be closed. Particularly, when the person admits his mistakes and desperately asking for FORGIVNESS. In addition to preventing unnecesary loses, FORGIVNESS also has a lot of other health benefits according to experts in the feild of psychology. References 1. Worthington EL Jr, Witvliet CVO, Pietrini P, Miller AJ. Forgiveness, health, and well-being: a review of evidence for emotional versus decisional forgiveness, dispositional forgivingness, and reduced unforgiveness. J Behav Med. 2007;30(4):291-302. doi:10.1007/s10865-007- 2. Worthington EL Jr, Witvliet CVO, Lerner AJ, Scherer M. Forgiveness in health research and medical practice. Explore (NY). 2005;1(3):169-176. doi:10.1016/j.explore.2005.02.012. Dr. Tegegn Molla, MD, Assistant professor of Neurology @HakimEthio

Hakim
62 161
We understand that being in the ICCU can be a stressful experience, and we strive to create a healing and supportive environm
We understand that being in the ICCU can be a stressful experience, and we strive to create a healing and supportive environment for our patients and their families. We provide comprehensive care for patients experiencing: ✅Acute Myocardial Infarction (Heart Attack) ✅Respiratory Failure ✅Shock ✅Life-Threatening Arrhythmia Our ICCU is staffed by a dedicated team of critical care physicians, cardiac nurses, and support staff who are committed to providing compassionate and personalized care to each patient. Contact Us 📲  0952 34 34 34 ☎️0116634740/41/20/ 📞9825      📌we are located around Bole ring road in front of cargo terminal At Addis Cardiac Center, we prioritize patient-centred care:) Join our social media communities!!!    ❇️ Facebook   ❇️Telegram

Hakim
62 161
Successful Separation of Heteropagus Twins at JJU Sheikh Hassan Yabare Referral Hospital A 6-day-old male neonate, born to an
+5
Successful Separation of Heteropagus Twins at JJU Sheikh Hassan Yabare Referral Hospital A 6-day-old male neonate, born to an 18-year-old primigravida mother, presented with a fully formed parasitic mass attached to his upper abdomen. He was born at full term via spontaneous vaginal delivery at home, weighing 3,575 g. Heteropagus twins are a rare type of conjoined twins in which an incomplete, smaller parasitic twin is attached to a normal (autosite) twin. This condition is extremely rare, occurring in approximately 1–2 million live births. The neonate is currently in stable condition following the successful surgical separation. Surgical team Dr. Solomon Webatu – Consultant Pediatric Surgeon Dr. Samuel Hunie – Consultant Anesthesiologist Dr. Yohannes Fekadu – GSR-4 Dr. Kalkidan Mesfin – GSR-4 Dr. Ayman Musa – GSR-3 Ahmed Abdi – Scrub Nurse Sr. Sacada Adan – Runner Nurse Anwar Wedaje – Anesthetist Shambel Mulatu – Anesthetist Source: JJU Sheikh Hassan Yabare Referral Hospital @HakimEthio

Hakim
62 161
የወር አበባ ህመም | Dysmenorrhea ✅የወር አበባ ህመም (Dysmenorrhea) ማለት የወር አበባ የሚመጣበት ወቅት የሚሰማ ህመም ነዉ። የህመሙ ደረጃ ብለያይም ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ከ
+3
የወር አበባ ህመም | Dysmenorrhea ✅የወር አበባ ህመም (Dysmenorrhea) ማለት የወር አበባ የሚመጣበት ወቅት የሚሰማ ህመም ነዉ። የህመሙ ደረጃ ብለያይም ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ከ1-2ቀን በየወሩ የዚህ ችግር ተጠቂ ናቸዉ። ለአንዳንዶች ትንሽ የወገብ አካባቢ ህመም ይሰማቸዋል፤ ለሌሎቹ ግን ከበድ ያለ የህመም ስሜት እና ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ራስ ምታትና መሰል ችግሮች ልኖሩ ይችላሉ። ✅የወር አበባ ህመም ዓይነቶች👇 👉1, የመጀመሪያ (primary dysmenorrhea): ይህ ዓይነቱ የመጀመሪያዉ ወር አበባ የሚታይበት እድመ ጀምሮ የሚከሰት ነዉ። ህመሙም ጊዜዉን ጠብቆ ከሚመረተዉ Prostaglandin ከሚባል ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር ጋር የተያያዘ ነዉ። ዕድሜ ገፋ ስል እና ስወልዱ ይህ ዓይነቱ የወር አበባ ህመም እየቀነሰ ይሄዳል። 👉2, ሁለተኛዉ ዓይነት የወር አበባ ህመም (Secondary dysmenorrhea) :ይህ ዓይነቱ የወር አበባ ህመም ከመኃል የሚጀምር እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ የሚሄድ ነዉ። ይህንን የሚያስከትሉ ሌላ ችግሮች ይኖሩታል። ለምሳሌ፦ የማህጸን ሞኝ እጢ (Myoma), Endometriosis, Adenomyosis... ያሉ ናቸዉ። ስለዚህም የትኛዉ ነዉ ምክኒያቱ የምለዉን ለማወቅና ለይቶ ለማከም በሐኪም መታየት እንዳለበት ይመከራል። ✅ህክምና 👉1, የህመም ማስታገሻ በተለይም NSIAD ቡድን የሚመደቡ እነ Ibuprofen ጠቃሚ ናቸዉ። 👉2, ለወሊድ መከላከያ የሚንጠቀማቸዉ በዉስጣቸዉ Estrogen እና progestin የተባሉ ንጥረ ነገሮችን የያዙ እንዲሁም Progestin ንጥረ ነገር ብቻ የያዙም ለወር አበባ ህመም ለማከም ይጠቅማሉ። ከመድኃኒት ህክምና ባሻገር የወር አበባ በሚመጣበት ወቅት ሙቅ ሻዉር መዉሰድ ፣ በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሰ ማድረግ ህመሙን ይቀንሳሉ። 👉ሚታየንን እሾህ እያነሳን ጉዟችን እንቀጥል! 👉ዶ/ር ጌታሁን ወዳሎ: የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪም @HakimEthio

Hakim
62 161
አልፎ አልፎ የሚፈትነኝ የሞያ አጋጣሚ! የካንሰር ስፔሻሊስት ዶክተር በመሆኔ አልፎ አልፎ የሚፈትነኝ የሞያ አጋጣሚ አለ። እሱም የታካሚው የቅርብ ሰዎች በተቻለ መጠን ሁሉንም የታካሚውን የህክምና መረጃ
+3
አልፎ አልፎ የሚፈትነኝ የሞያ አጋጣሚ! የካንሰር ስፔሻሊስት ዶክተር በመሆኔ አልፎ አልፎ የሚፈትነኝ የሞያ አጋጣሚ አለ። እሱም የታካሚው የቅርብ ሰዎች በተቻለ መጠን ሁሉንም የታካሚውን የህክምና መረጃ ከታካሚው እንድደብቅላቸው የሚጠይቁበት አካሄድ ነው። መነሻው ለታካሚው ከማሰብ እና በሀሳብ/በጭንቀት እንዳይጎዳባቸው ከመመኘት እንደሆነ እገምታለውኝ። ቢሆንም ይህንን ማድረግ ታካሚዎች ስለ ህክምናቸው የማወቅ መብታቸው እንደተጨፈለቀ እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። ይህም በህክምና ሂደቱ ላይ እምነት እንዲያጡ እንዲሁም ህክምናቸውንም እንዲያቋርጡ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በሀገራችን በዚህ ጉዳይ ላይ የተወሰኑ ጥሩ ምርምሮች የተደረጉ ሲሆን ሁለቱን በጥቂቱ እንድናያቸው ወደድኩኝ። የመጀመሪያው ጥናት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በካንሰር ታካሚዎች ላይ የተደረገ ሲሆን፥ ድምዳሜው ይህንን ይመስላል። "ታካሚዎች ቤተሰቦቻቸው ከሚጠብቁት (ከሚፈቅዱላቸው) በላይ ስለ ህክምናቸው በቂ መረጃ ማግኘት ይፈልጋሉ።" ሁለተኛው ጥናት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የተደረገ ነው። ይህ ጥናት ለየት ያለ እና የሚያስገርም ውጤት ነበር ያሳየው። ይህም - "84% የሚሆኑ የታካሚ ቤተሰቦች (ቢቻል) ለታካሚው ስለ ህመሙ ዓይነት ምንም ባይነገረው ይፈልጋሉ። ነገር ግን እነዚህ የታካሚው የቅርብ ሰዎች የካንሰር ህመም ቢገኝባቸው ግን ምንም ዓይነት መረጃ እንዲደበቅባቸው አይፈልጉም።" ከራሴ የህክምና ልምድ እና እነዚህን ምሰል ጥናቶችን ከግምት ውስጥ አስገብቼ አንድ ነገር በግልጽ መነገር እንዳለበት ነው የተረዳውት። እሱም - የታካሚዎች በህክምና ሂደት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መረጃ የማግኘት መብታቸውን ማክበር የሁላችንም ሀላፊነት ነው። ⁉️ እናንተስ ምን ትላላችሁ? Dr. Abraham Adamu: Assistant Professor of Clinical Oncology @HakimEthio

Hakim
62 161
የፅንስ ፆታ ማወቅ የሚያስደስት ወይስ የሚያስጨንቅ⁉️🤔 👉🏽 ጥንዶች የእርግዝና ጊዜ ከ18 ሳምንት እስከ 22 ሳምንት በደረሰ ጊዜ የልጃቸውን ፆታ ማወቅ ይችላሉ። በተሻለ አልትራሳውንድ ደግሞ ከ1
+3
የፅንስ ፆታ ማወቅ የሚያስደስት ወይስ የሚያስጨንቅ⁉️🤔 👉🏽 ጥንዶች የእርግዝና ጊዜ ከ18 ሳምንት እስከ 22 ሳምንት በደረሰ ጊዜ የልጃቸውን ፆታ ማወቅ ይችላሉ። በተሻለ አልትራሳውንድ ደግሞ ከ12 ሳምንት ጀምሮ የሚታወቅበት ጊዜ አለ። 👉🏽 ነገር ግን ረቀቅ ባሉ የዘረመል ምርመራዎች (genetic analysis) የፅንስ ፆታ ከ9 ሳምንት ጀምሮ ማወቅ ይቻላል። 👉🏽 በIVF (In Vitro Fertilization) እርዳታ የሚወልዱ ጥንዶች ደግሞ ገና ከመጀመሪያው ውጭ ላይ የተዳቀለው የወንድ ዘር (sperm cell) እና የሴት እንቁላል(egg) የፈጠረውን ፆታ ማህፀኗ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ማወቅ ይቻላል። 👉🏽 የፅንስን ፆታ ቀድሞ ማወቅ ይጠቅማል የሚሉ ጥንዶች እንዳሉ ሁላ፤ ማወቁ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላል የሚሉም በርካታ ናቸው። ⚡️⚡️ የፅንስን ፆታ ቀድሞ ማወቅ ብዙ ጥቅም አለው የሚሉ ጥንዶች የተወሰኑት ምክንያቶችይዘረዝራሉ:- ✍️ስሜታዊ ዝግጅት:- ይህም በርግዝና ወቅት ከልጃቸው ጋር እንዲቀራረቡ ይረዳል ይላሉ ✍️ተግባራዊ ዝግጅት :- ስም እንደማውጣት፣ የልጅን ክፍል እንደማስጌጥ፣ ልብስ መግዛትን እና የመጨረሻ ሰዓት ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ጭንቀቶችን ይቀንስልናል ይላሉ ✍️የመጓጓት ስሜትን መቀነስ :- ይህ ፆታን የማወቅ ጉጉት ጥርጣሬን ሊፈጥር ስለሚችል፤ ሌሎች እርግዝና ነክ የሆኑ ጉዳዬች ላይ ላያተኩሩ ስለሚችሉ ፥ ማወቃቸው ጉጉታቸውን ሊያረካ እንደሚችል እና እቅዶችን ማውጣት ላይ ጠንካራ እንደሚሆኑ ይናገራሉ ✍️ታላላቅ ወንድም ወይም እህት ካሉ ቀድመው ማወቃቸው የቅናት ስሜትን በተወሰነ መልኩ ሊቀንስላቸው እና እራሳቸውን በተወሰነ መልኩ እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል ተብሎ መታሰብ ✍️ከፆታ ጋር የተያያዙ የዘር ውርስ በሽታዎች ለምሳሌ እንደ ሄሞፊሊያ ለመሳሰሉት ወላጆች ለሚገጥሟቸው ችግሮች ቀድመው ዝግጅት እንዲያደርጉ መርዳት ⚡️⚡️ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እንዳሉ ሆነው ፥ በተቃራኒው ደግሞ ያሉ ጥንዶች ፆታን አስቀድሞ ማወቅ የተወሰኑ ችግሮች አሉት ብለው ያስባሉ:- እነኚህም ✍️አንዲት እናት ወይም አባት ሴት ልጅ እንዲኖራቸው "ቢመኙም" ነገር ግን ወንድ ልጅ ሊወልዱ እንደሆነ አስቀድመው ቢረዱ ይህ ለወሊድ የሚሰማቸውን ደስታ እና ጉጉት ሊቀንስ ይችላል። ባልና ሚስቱ በሕፃኑ ጾታ ቢደሰቱም፣ የቤተሰብ አባላት ወይም ጓደኞች ቅር መሰኘታቸውን ሊገልጹ ይችላሉ፣ ይህ ደግሞ በጣም አስጨናቂ እና በእውነት የሚያበሳጭ ሊሆን ይችላል! ✍️የመገረም ስሜት - ብዙ ጥንዶች ህፃናቸውን በሚጠብቁበት  የመጨረሻይቱ ደቂቃ ፆታውን ማወቅ የግርምት፣ ልዩ እና አስደሳች ተሞክሮ እንደሆነ ያምናሉ ✍️የፆታ አመለካከትን መቀነስ - ጾታውን አለማወቅ ወላጆች ስለ ልብስ፣ መጫወቻዎች ወይም የሕፃናት ክፍል ማስጌጫዎች አስቀድሞ ግምቶችን ከመፍጠር ወይም ባህላዊ የፆታ-ተኮር የሚጠበቁ ነገሮችን ከመግዛት እንዲቆጠቡ ሊረዳቸው ይችላል። ✍️ሁሉን ያካተተ ዝግጅት፡ ወላጆች በፆታ ላይ በተመሰረቱ የሚጠበቁ ነገሮች ከመገደብ ይልቅ የሕፃኑን መምጣት በአካታች እና በሚስማማ መንገድ ለማዘጋጀት ማተኮር ይችላሉ። ⚡️⚡️ በመጨረሻም ፆታን የማወቅ ሁኔታን ለጥንዶቹ ልተውና ፤ የሕፃኑን ጾታ ከመወለዱ በፊት ማወቅ ትክክል ወይም ስህተት የሚባል ነገር የለውም - ይህ ለባልና ሚስት ፍጹም የሆነ የግል እና ሚስጥራዊ ውሳኔ ይሆናል። ዋናው እና ጠቃሚው ነጥብ ፣ ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ጤናማ እርግዝና እና ጤናማ ህፃን መውለድ ስለሆነ። ለደረሳችሁ ነፍሰ ጡሮች - የአጥር ወፍ አትስማሽ እያልኩ መልካም ጊዜን ተመኘሁ። ዶ/ር ዳዊት መስፍን የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት https://t.me/DrDawitMOBGYN https://www.facebook.com/share/15QEEDkmoB/?mibextid=wwXIfr @HakimEthio

Hakim
62 161
የተስማማንባቸው ግን ስሑት የኾኑ ጉዳዮች በኦቲዝም ዙሪያ ወላጆች፣ ተቋማት፣ ባለሞያዎችና 'ይመለከተናል' የሚሉ ሁሉ የጥብቅና ወይም የመሟገት (Advocacy) ተልዕኮ ላይ፣ የግንዛቤ የማስጨበጥ እንቅ
+3
የተስማማንባቸው ግን ስሑት የኾኑ ጉዳዮች በኦቲዝም ዙሪያ ወላጆች፣ ተቋማት፣ ባለሞያዎችና 'ይመለከተናል' የሚሉ ሁሉ የጥብቅና ወይም የመሟገት (Advocacy) ተልዕኮ ላይ፣ የግንዛቤ የማስጨበጥ እንቅስቃሴ ላይ እና ሌሎች ማህበረሰቡን ለማንቃት፣ ለማስተማር ብሎም የተዛባ አመለካከትን ለመቀየር በሚደረገው ትግል ውስጥ የተስማማንባቸው ግን ስሑት የኾኑ ጉዳዮች አሉ። በተሳሳተ መንገድ ከሚተላለፉ መረጃዎች መካከል በሕክምና/በሳይንስ ከኦቲዝም ጋር መኖራቸው ያልተረጋገጡ ሰዎችን መጥቀስ ይገኝበታል። ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሰዎች (A Person living with Autism) ማህበረሰቡ እነሱን የሳለበት/የሚረዳበት መንገድን ለመቀየር በመፈለግ የኛ ልጆች ድክመት ብቻ እንደሌለባቸው፣ ያጋጠማቸውን የአዕምሮ ዕድገት መዛባት ብቻ ላይ እንዳናተኩር በአጠቃላይ ኦቲዝም ጨለማ ጎን ብቻ እንደሌለው ለማሳወቅ ኦቲዝም የሌለባቸውን ሰዎች አለአግባብ እንጠቅሳለን። ለምሳሌም፦ ፩ | አልበርት አንስታይን (Albert Einstein) ፪ | ሊዮኔል ሜሲ (Lionel Messi) ፫ | አይዛክ ኒውተን (Isaac Newton) ፬ | ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ (Leonardo da Vinci) ፭ | ኒኮላ ቴስላ (Nikola Tesla) ፮ | ቶማስ ኤዲሰን (Thomas Edison) ፮ | አሌክሳንደር ግራሃም ቤል (Alexander Graham Bell) ፯ | ሞዛርት (Mozart) ፰ | ቻርልስ ዳርዊን (Charles Darwin) ከላይ የተዘረዘሩት እና ሌሎች ያልተጠቀሱት ታዋቂ ሰዎች ከኦቲዝም ጋር ስለመኖራቸው የተረጋገጠ ሳይንስ የለም። ምንም እንኳን መጠቀሳቸው ጉዳት ባይኖረውም ትክክለኛውን እና ስህተቱን አጥርቶ ማወቅ ተገቢ ግን ነው። ሆኖም በትክክል በሳይንስ/በምርመራ የተረጋገጡ ዝነኛ፣ ታዋቂ እና የዓለምን ታሪክ የቀየሩ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሰዎች በጥቂቱ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል፦ ፩ | ቴምፕል ግራንዲን (Temple Grandin) ፪ | ዳሪል ሃና (Daryl Hannah) ፫ | ሄሊ ሞስ (Haley Moss) ፬ | ጄኮብ ቬላዝኬዝ (Jacob Velazquez) ፭ | ካርሊ ፍላይሽማን (Carly Fleischmann) ፮ | ናኦኪ ሂጋሺዳ (Naoki Higashida) ፯ | ኮዲ ሊ (Kodi Lee) ፰ | ቶም ስቶልትስመን (Tom Stoltsmon) ፱ | ጄሰን አርዳይ (jason arday) ኦቲዝም በሕክምና፣ በምርመራ፣ በሳይንሳዊ ሒደት የሚረጋገጥ እንጂ በግለሰቦች የሕይወት ታሪክ ላይ ተመሥርቶ የሚሠጥ ስያሜ አይደለም። Paradigm shift ! Reference: American Psychiatric Association. (2022). Diagnostic and Statistical Manual of Mental Disorders (5th ed., text rev.; DSM-5-TR). Pellicano, E., & den Houting, J. (2022). Annual Research Review: Shifting from "normal science" to neurodiversity in autism science. Journal of Child Psychology and Psychiatry, 63(4), 381–396. ዋኖስ መስፍን: Special/Inclusive education Professional, Autism and other developmental disabilities Advocate/Trainer/ Practitioner @HakimEthio

Hakim
62 161
Question to the page @HakimEthio
Question to the page @HakimEthio