fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

رفتن به کانال در Telegram
2 370
مشترکین
+1124 ساعت
+997 روز
+37430 روز
آرشیو پست ها
''ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ስር ለሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞችና አሰልጣኝ መምህራን መሰጠት ጀመረ፤ በአቅም ግንባታ ስልጠናው ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና የመንግስት ሰራተኛው የመንግስትን አቅጣጫ በመረዳትና መግባባትን በመፍጠር  የአስተዳደራችንን አልፎም የሀገራችንን ብልጽግና በማረጋገጥ ሂደት ላይ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል፤ የቢሮው አስተዳደር ሰራተኞች እና አሰልጣኝ መምህራን ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት 2 ተከታታይ ቀናት "ሀብት እና ብልፅግናን መፍጠር እና ማስተዳደር እንዲሁም አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስን መገንባት" በሚሉ ርዕሶች በቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ስልጠናው ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከየካቲት 6-7/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 6/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከሻሎም ኢንጂነሪንግ ድርጅት ጋር በመተባበር ላሰለጠናቸው ሰልጣኞች ተማሪዎች እውቅና ሰጠ:: ስልጠናው የተሰጠው በኮንስትራክሽን ዘርፍ በBasic General constraction በአጫጭር ስልጠና መርሃ-ግብር ሲሆን በዚህ ስልጠናም 16 የሚሆኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች ስልጠናቸውን በብቃት በማጠናቀቅ በራሳቸው በሰልጣኞች ተሰርቶ በተጠናቀቀው ግንባታ ውስጥ በኮሌጁ የእውቅናና ሰርተፊኬት ፕሮግራም ተደርጎላቸዋል:: ይህ ስልጠና ከግብ እንዲደርስም ሻሎም ኢንጂነሪንግ ድርጅት የስልጠና ግብዓቶችን ከማቅርብ ጀምሮ አስፈልጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ጉልህ ሚና የተወጣ ሲሆን የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በበኩሉ ለስልጠናው ብቁ የሆኑ ሰልጣኞችን ከመመደብ ጀምሮ ሰልጣኞቹ የሰለጠኑትን በተግባር የሚሰሩበት ሳይት በማመቻቸት ሰልጣኞች በሁሉም ረገድ ብቁና ተፈላጊ ሞያተኛ ሆነው እንዲወጡ ና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ትልቁን ድርሻ ተወጥቷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን የካቲት 4/2016 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ ዋና ስራ ሂደቶችና ክፍሎች የ2016 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛል:: የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩን እያደረገ የሚገኘው በኮሌጁ ዲን የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን ሲሆን በድጋፍና ክትትሉ ወቅትም ስራ ሂደቶችና ክፍሎች በበጀት አመቱ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማና ሪፖርት፣ በመረጃ እደረጃት፣ በQMS አተገባበር ያሉበት ደረጃ፣ በስራ አካባቢ ያላቸው የካይዘን አተገባበር እንዲሁም በግብአት አጠቃቀም ያሉበትን ቁመና የሚገመግም ሲሆን በተጨማሪም ስራ ሂደቶችና ክፍሎች እንደየስራ ባህርያቸው መፈፀም ከሚገባቸው ተግባራት ምን ያህሉን ተግባራዊ አድርገዋል ሚለው ላይም ያተኮረ የድጋፍና ክትትል መሆኑ ተገልጿል:: የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በድጋፍና ክትትሉ ወቅት ለስራ ሂደቶችና ክፍሎች በቃል ግብረ መልስ የሚሰጥ ሲሆን የድጋፍና ክትትሉ ማብቂያ ላይም ለሁሉም በፅሁፍ ግበረ መልስ የሚሰጥም ይሆናል:: የዚህ ድጋፍና ክትትል ዋና አላማ በተቋሙ የሚገኙ ስራ ሂደቶችና ክፍሎች በአፈፃፀም ጉድለት የሚታይባቸውን ተግባራቶች ለይቶ ትኩረት እንዲሰጣቸው የማድረግና የተሻለ አፈፃፀም ለታየባቸው ስራ ሂደቶችና ክፍሎች ደግሞ ለሌሎች ተሞክሮ እንዲሆኑ በማለም ሲሆን በቀጣይም ድጋፍና ክትትሉ በቀሩት ስራ ሂደቶችና ክፍሎችም የሚቀጥል ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን የካቲት 2/2016 ዓ.ም

አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በአጫጭር ስልጠና እያሰለጠናቸው ለሚገኙ ሰልጣኞች በተግባር የተደግፈ የስራ ላይ ልምምድ ስልጠና ሰጠ:: አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በSolar PV Instalation ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙትን 47 ሰልጣኞች በ > Apply Principles of renewable energy Operation. > Read and Interpret Plans and Specifications. > Install DC/AC Wiring Systems in conduit and Conneet Equipment. > Determine and sizing of PV system. > Perform Site Assessment. Unit of Competency ላይ ሰልጣኞቹን በኦሲስ ኦርፋን ቻሪቲ ለ 2 ቀን የቆይ በተግባር የተደግፈ የስራ ላይ ልምምድ ስልጠና ተሰጥቷል:: ሰልጣኞቹ በንድፈ ሀሳብ ሲከተታተሉ የቆዩትን ስልጠና ስራ ቦታው ላይ በአካል ተገኝተው በተግባር የሰለጠኑ ሲሆን ይህም ሰልጣኞቹ በቀጣይ ወደስራ አለም ሲገቡ በእጅጉ እንደሚያግዛቸው ተገልጿል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥር 30/2016 ዓ.ም

Witness of Christ Church ለኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ:: የስልጠና ድጋፉ የተሰጠው ለኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፖርትመንት አሰልጣኝ መምህራን ሲሆን የስልጠናው ይዘትም በResidential and Commercial Electrical Systems in USA Standard ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልፅጿል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥር 30/2016 ዓ.ም