Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 370
مشترکین
+324 ساعت
+937 روز
+36430 روز
آرشیو پست ها
የድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረፊያና ማረሚያ ቤት ጋር ለታራሚዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዙሪያ ከስልጠና እስከ ስልጠና ማዕከል አቅም ግንባታ መፍጠር የሚያስችል የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ።
የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ከማረሚያ ቤቱ ጋር የተደረገው ስምምነት ኮሌጁ ያለበትን ያለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት ያለፈ በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ታራሚዎች የበቁ ሞያተኞችን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት ሁሉአቀፍ በሆነ ድጋፍና በጥምረት የመስራት የሁለትዮሽ መግባባት የፈጠረው ነው ብለዋል።
በስምምነት ፊርማው ላይ የማረሚያ ቤቱ ሀላፊ ረ/ኮሚሽነር ወንድሙ ደበላ እንደተናገሩት ስምምነቱ ማረሚያ ቤቱ ለታራሚዎች የሚሠጠዉን ስልጠና ከማጠናከር ባለፈ ታራሚዎች ታንፀዉ እንዲወጡ የአንድ አካል ሚና ብቻውን ውጤት ስለማያመጣ ኮከሌጁ ጋር የተደረገው ስምምነትና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጨረሻም በማረሚያ ቤቱ እየተሰጠ የሚገኘውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ያግዝ ዘንድ አጠቃላይ የገንዘብ ግምታቸው ስድስት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ሶስት መቶ ብር የሚያወጡ ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለአውቶሞቲቭ እና ለፈርኒቸር ስልጠናዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ የስልጠና ማቴሪያሎችና ማሽኖችን ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥር 28/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
የአሰልጣኝ ልማት እና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የአሰልጣኝ ልማት ቡድን ለኢትዮ-ጣልያን እና ድሬዳዋ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የ ELECTRICAL ELECTRONICS አሰልጣኝ መምህራን ለ15ቀናት በ POER SYSTEMS SYMULATION AND ANALISIS, PSIM, MATLAB, ETAB, MULTYSYSTEM and MOTOR XP የሶፍትዌር እና የተግባር ስልጠናዎችን ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በተጋበዙ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና አስጀምረዋል፤፤
ስልጠናው አሰልጣኞች ካላቸው እውቀት በተጨማሪ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካሉ አሰልጣኞች በሙያው እውቀትን እና ልምዶች ለመካፈል እንዲሁም የቴሙትስ አሰልጣኞች ያላቸውን የካበተ የተግባር እውቀት እና ልምዶችን ለዩኒቨርስቲ አሰልጣኞች የሚያካፍሉበት የሁለትዮሽ እውቀት ሽግግር የሚደረግበት አጋጣሚ መሆኑን ተጋባዥ አሰልጣኙ ብርሃኑ ደገፋ (ዶ/ር) ገልፀዋል፤፤
ቴክኒክና ሙያ በየወቅቱ የዘመነውን የቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት አድርጎ በየጊዜው ስልጠናውን የሚያዘምን እንደመሆኑ አሰልጣኞችም ብቁ እና ተወዳዳሪ ስልጠና አጠናቃቂዎችን ለማፍራት እንዲችሉ ወቅታዊ ስልጠናዎችን የሚያገኙበት ዕድሎችን እንደሚመቻችም የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ተናግረዋል፤፤
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 18/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ ብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ ይላል::
👉ኢትዮ-ጣሊያን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለዳዊት አረጋውያን መርጃ የሙያ ድጋፍ አደረገ
የኮሌጁ ውድ-ወርክ ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ዳዊት አረጋውያን መርጃ ከለጋሾች ያገኛቸውንና አገልግሎት መስጠት የማይችሉ አልጋዎችና ወንበሮችን የሚያስፈልጉ ግብአቶችን አሟልቶ በመጠገን አስረክቧል።
የጥገና ስራውን በመስራት በቅን መንፈስ ሙያዊ ድጋፍ ላደረጉት ለኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና ምክትል ዲን አቶ ኤልያስ አህመድ እና የዲፓርትመንቱ ተጠሪ ለሆኑት አቶ ዮሴፍ እንዳልካቸው የአረጋውያን መርጃ ድርጅቱ ሀላፊ አቶ ዳዊት በቀለ በአረጋውያኑ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Dawit Aregawiyan Merja
ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
አድራ ኢትዮጵያ በሶላር ፒቪ የመንገድ መብራት ዝርጋታ እና ጥገና የእሴት ሰንሰለት ዙሪያ ተዘጋጅቶ በቀረበ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ::
አድራ ኢትዮጵያ ከአድራ ጀርመኒ ጋር በመተባበር በጀርመን መንግስት ድጋፍ ለሶላር ፒቪ ዝርጋታ እና ጥገና የሚሆን የማሰልጠኛ ወርክሾፕ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በማዘጋጀት ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በዘርፉ ያሉትን ማነቆዎች ለመቀነስ እና አዲሱን የGreen TVET Approach ለማሳወቅ ከፍተኛ ስራ እየሰራም ይገኛል።
በዚህም መሰረት ከድሬደዋ TVET ኤጀንሲ ቢሮ ጋር በመተባበር በተሰራው የሶላር ፒቪ የመንገድ መብራት ዝርጋታ እና ጥገና የእሴት ሰንሰለት በድሬደዋ ከተማ (Value Chain Analysis On Solar PV Street Light Installation & Maintenance in DD city)በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በቀረበው ሰነድ ላይ ዘርፉን የሚያነቃቃ ጠቃሚ እና ሰፊ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር በማድረግ ዘርፉ ላይ ያሉትን ክፍተቶች ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ለሰልጣኞች ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር እንደሚቻልም በመድረኩ ተመላክቷል።
በዚህም ትልቁን ድርሻ ከሚወስደው የድሬደዋ መንገዶች ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታዋችም መፈጠራቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ስራውን በማስፋትና ወደ ገጠሩ አካባቢ በመውረድ ገጠሩን አካታች የሆነ የእሴት ሰንሰለት በመስራት አብሮ ችግሩን መቅረፍ የሚያስችል ሁኔታ እንዲፈጠርም አቅጣጫ ተይዟል።
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 22/2016 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስራ ሂደት በዳይመንድ ሚስማር ፋብሪካ የመስክ ምልከታ አካሄደ::
በፋብሪካው በነበረው ጉብኝት በቅድሚያ ከድርጅቱ ሀላፊና ባለቤቶች ጋር በስራ ላይ ስለሚገጥሟቸው ችግሮች እንዲሁም ከተቋሙ በሚደረግላቸው የድጋፍ አይነቶች ዙሪያ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን የሚስማር ማምረቻ ወርክ ሾፖችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል::
በምልከታው ወቅትም ድርጅቱ በማሽን ጥገና ወቅት የመለዋወጫ እጥረት እንዳለበትና ለረጅም ጊዜ በብልሽት ምክንያት ያለ ስራ የቆሙ ትልልቅ ማሽነሪዎችም እንዳሉ መታዘብ ተችለዋል::
ተቋሙ በቀጣይ በድርጅቱ የተለዩ ችግሮች ላይ በኮሌጁ ሊፈቱ የሚችሉትን በዝርዝር በመለየትና ከድርጅቱ ጋር የጋራ ስምምነት በመፈፀም የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፍ እንደሚይደርግም ተገልጿል::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ህዳር 28/2016 ዓ.ም
