Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 406
مشترکین
+924 ساعت
+527 روز
+35430 روز
آرشیو پست ها
የድሬዳዋ አስተዳደር በስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኘው የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአይሲቲ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ለአስተዳደሩ አልፎም ለአገር አርአያ የሚሆን በዛሬው ዕለት በተዘጋጀ ፕሮግራም የስልጠና ክፍሉ ለአሰልጣኝ መምህራን ኦፊስ የሚገለገልበትን ስፍራ በካይዘን በማደራጀት ጽዱ እና ውብ አድርጎ የኮሌጁ ማኔጅመንትና የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት በተገኙበት አስመርቋል፡፡
በዚህም ፕሮግራም ላይ የትምህርትና ስልጠና ክፍሉ ኃላፊ አቶ አቤል ፋንታሁን ስለተሰራው ስራ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በዋናነት በትምህርትና ስልጠና ክፍሉ በሚገኙ አሰልጠኝ መምህራን መካከል በተፈጠረው መቀባበልና መልካም ተግባቦት ይህ ስራ ተሰርቶ እንዲህ ባለ ሁኔታ እዲጠናቀቅ እንዳደረገውና ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የአሰልጣኝ መምህራኑን እውቀትና ጉልበት እንዲሁም በኮሌጁ የሚገኙ ሌሎች ትምህርት ክፍሎችና በአጠቃላይ የኮሌጁን የውስጥ አቅም በመጠቀም መሰራቱን እና በቀጣይም በዋናነት በዲጂታላይዜሽን አቅጣጫ በኮሌጁ ውስጥ ያለውን ተሞክሮ በማስፋት እንደ አስተዳደር ተጨባጭ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ኮሌጁ ለሪፎርም ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታውሰው በተለየ መልኩ የትምህርት ክፍሎች የካይዘን ትግበራ ላይ መሆናቸውንና ጥሩ አፈጻጸም እየስመዘገቡ ከሚገኙትም የአይሲቲ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠቃሽ መሆኑን አንስተው ይህን አርአያ የሚሆን ስራ ሌሎችም ትምህርትና ስልጠና ክፍሎች እንዲከተሉ በማሳሰብ ኮሌጁ ለውጥን የሚያስቡና የሚሰሩ እጆችን እንደሚያበረታ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥቅምት 28/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ጋር በጋራ በመስራት የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማደረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
ከመቶ ሀያ አምስት አመት በላይ እድሜ ያለዉ የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት በውስጡ በርካታ እምቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ማሽነሪ ዎችና ወርክ ሾፖች የያዘ ነው:: ይህን የድርጅቱን አቅም ለመጠቀም እና በካይዘን ትግበራ ዙሪያ ድርጅቱ ያለበትን ክፍተት ለመሙላት የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በጋራ ለመስራት በማለም ከድርጅቱ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል::
በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ የኮሌጁ ኃላፊ አቶ ታደለ አሰፋ እንዳሉት ስምምነቱ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን የካበተ እውቀት ለመጠቀም እና የእውቀት ሽግግር ለማደረግ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል። በተጨማሪም ኮሌጅ በካይዘን ትግበራ ላይ ያለዉን ተሞክሮ ለድርጅቱ በሚጠቅም መልኩ እንደሚያሰለጥን ገልፀዋል። ግንኙነቱን ለማስጀመር ኤሌክትሪካል ዲፓርትመት መመረጡን የገለጹት አቶ ታደለ በቀጣይ ወደ ሌሎች ዲፓርትመንቶች እንደሚሰፋ አስረድተዋል::
የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ወ/ዮሐንስ ተቋሙ ከ1911 ጀምሮ የተገነቡ በርካታ ወርክ ሾፖች እንዳሉት ተናግረዋል። እነዚህን እምቅ አቅሞች ድርጅቱ ለወጣቶች የማስተላለፍ አላማ እንዳለው ተናግረዋል። የተፈረመውን ስምምነት ተግባዊ ለማድረግ በርብርብ እንደሚሰራም አቶ አየለ ገልፀዋል። በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህርት ህይወት እሸቱ በበኩላቸው ኮሌጁ የካይዘን እቅዶችን በማውጣት ወደ ስራ መግባቱን ገልፀው ድርጅቱም ለኮሌጁ መምህራን እና ተማሪዎች የተግባር እውቀት ከፍተኛ እንገዛ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም የበጀት አመት እቅድ ላይ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ተወያየ።
በእለቱ በነበረው መድረክ በቅድሚ የስራ ሂደቶች እንዲሁም የዋና ስራ ሂደቶች የ2014 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ለተቋሙ ሰራተኞች ያቀረቡ ሲሆን በመቀጠልም የሁሉም የስራ ሂደቶች በቅደም ተከተል የ2015 ዓ.ም እቅዶቻቸውን ለመድረኩ አቅርበዋል።
መድረኩ ቀጥሎም የቀረቡት እቅዶች ላይ ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ ሀሳብና አስተያየት ተሰቶባቸው ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመጨረሻም የዋና ስራ ሂደቶችና የክፍል ተጠሪዎች ከኮሌጁ ዲን ጋር የ2015 ዓ.ም እቅዳቸውን በፊርማ ርክክብ አድርገዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን።
ጥቅምት 25 2015 ዓ.ም
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ02 ቀበሌ የሚገኘውን የወ/ሮ ይመኙሻል ዳኜ የፈራረሰ ቤት በ1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ባማረ መልኩ በአዲስ በመገንባት አስረከበ።
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንደገለፁት እንደዚህ አይነት በጎ ተግባራት ላይ መሳተፍና ከአቅመ ደካሞች ጎን መቆም በምንም የማይተካ የህሊና እርካታ የሚያስገኝ መሆኑን ገልፀው ይህ የተቸገሩትን የመደገፍ ስራ ጅምር መሆኑንና በቀጣይ ለምንሰራቸው በጎ ተግባራት ጥሩ ተሞክሮ የወሰድንበት ነው ሲሉም አክለዋል።
አያይዘውም ኮሌጁ ቤቱን ሰርቶ ከማስረከብ በተጨማሪ የተለያዩ የቤት እቃዎችን(ቁም ሳጥን፣ ቲቪ) ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው እዚህ በጎ ስራ ላይ የተሳተፉት የኮሌጁ ሰራተኞችና ተባባሪ አካላትንም አመስግነዋል።
የ02 ቀበሌ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አቤል ምስራቅ በበኩላቸው ስራዎችን መጀመር ቀላል እንደሆነና በዚህ መልኩ ስራዎችን አጠናቆ ፍፃሜውን ማየት ትልቅ ብርታት የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን በመግለፅ ይህም የፓርቲያችን ዋና መገለጫውም ነው ብለዋል።
በመጨረሻም የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው እንደዚህ ያሉ በጎ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ቢሯቸው ሁሌም የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለፅ በአዲስ መልክ ተገንቡቶ የተጠናቀቀውን የቤት ቁልፍ ለወ/ሮ ይመኙሻል ዳኜ ያስረከቡ ሲሆን በኢትዮ-ጣሊያን ኮሌጅ በኩል የተገኘ የአስቤዛ ድጋፍም በእለቱ ድጋፍ ተደርጓል።
ከርክክብ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተሰማቸውን የገለፁት ወ/ሮ ይመኙሻል ዳኜ በበኩላቸው በፊት የነበሩበት ቤት በጣም ከማርጀቱ በተጨማሪ ዝናብ በዘነበ ቁጥር ቤት ውስጥ ውሃ ገብቶ እየተኛ እንቅልፍ ይነሳቸው እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ ያን ሁሉ ስቃይ ያለፍኩት በእናንተ ነው በማለት ሁሉንም በማመስገን የማይጠገብ ምርቃታቸውን መርቀዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኬሽን
ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ውጤትን መሰረት ያደረገ ውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና አተገባበርን አስመልክቶ ከ ኮሌጁ መምህራን ጋር ተወያየ።
በመድረኩ የ2014 ዓ.ም ውጤትን መሰረት ያደረገ ትምርህትና ስልጠና አተገባበር የነበረበትን ክፍተት እንዲሁም ጠንካራ ጎኖቹ የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይም የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍና የተገኙ መልካም ውጤቶች በማጠናከር በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሚፈለገው ጥራት ትምህርትና ስልጠናውን ለማከናወን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከመምህራን ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
ጥቅምት 15 2015 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ በሚል መሪ ቃል በተደረገ ሀገራዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ድምጻቸውን አሰሙ።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 12/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
